Friday, January 7, 2011

ምን ዓይነት “ኦርቶዶክስ” ነን?

A picture I took from St.Emmanuel Church
in Berlin Germany
“ፌስቡክ”ን መጠቀም ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ሰዎች “ሃይማኖት” የሚለው ቦታ ላይ የሚያስቀምጡትን ስመለከት እንዲሁም አንዳንድ የማላውቃቸው ሰዎች ወይም “የፌስቡክ ጓደኝነት” የሚጠይቁኝ ወዳጆቼ እነማን መሆናቸውን ለማወቅ የግል ማኅደራቸውን እና ማንነታቸውን ወደሚያሳየው ቦታ ስገባ እና ስለ ሃይማኖታቸው ሳነብ የሚገርም ነገር አይቻለኹ። ይህንን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሣሣኝ ደግሞ ተደጋጋሚነቱ ነው። እና እነዚህ ወዳጆቼ ሃይማኖት የሚለው ሥፍራ ላይ ሲጽፉ “ግሪክ ኦርቶዶክስ” ይላሉ። ሰዎቹ ግሪካውያን እንነዳልሆኑ ይታወቃል።
ምክንያቱም ግሪካዊነት በትውልድ የሚመጣ ዜግነት ነው። ማለት የፈለጉት ደግሞ ስለዜግነታቸው እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ነገሩ “ምን ዓይነት ኦርዶክስ እንደሆንን ያለመረዳት” ወይም “ኦርቶዶክስነታቸውን ለሌሎች ዜጎች የማስረዳት ችግር” መሆኑን ገመትኩኝ። ስለዚህም ነው “ምን ዓይነት ኦርቶዶክስ ነን?” ለማለት የፈለግኹት። የሚገርመው ይህንን የሚመስል አንድ ድንቅ ጉዳይ በማስታወስ ልጀምር። ታሪኩ የታላቁ ኢትዮጵያዊ የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ነው። እንዲህ ይላል፦
   "ይህችን መጽሐፍ ለመጻፍ ያነሣሣኝ ዋናው ምክንያት የሚከተለው ነው። በ1962 ዓ.ም ለትምህርት ወደ ውጭ አገር በሔድኩበት ጊዜ ብዙ ፈረንጆች እኔንም ሆነ ጓደኛዬን  የሚጠይቁን “የቅብጥ” ‘የኮፕት ቤተ ክርስቲያን መነኮሳት ናችሁ ወይ?’ እያሉ ነበር። በትምህርት ገበታችንም ላይ እንዳለን የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን “የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን” እያሉ ሲጠሯት በማስማቴ ኅዘን አደረብኝ። በመሠረቱ “ኮፕት/ ቅብጥ” ግብጽ ወይም ምስር ማለት ሲሆን “”ሂኩፕታህ” በጥንት የግብጽ ቋንቋ “ቤት” ማለት ነው። ከሱ የወጣ ነው። ግሪኮች ግን “ሀ” ፊደል ስለሌላቸው “ኤጊፕቶስ” ወይም ኮፕት ይሉታል። እንግዲህ “ኮፕት” የሀገር ወይም የነገድ ስም ነው ማለት ነው። ስለዚህ የግብጽ ክርስቲያኖች በሀገራቸው በነገዳቸው የኮፕት ወይም የቅብጥ ክርስቲያኖችም ይባላሉ።  ዐረቦችም እል አቅባጥ ይሏቸዋል። የቃሉ ፍች ይህ (ሆኖ) ሳለ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን የቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ብሎ መሠየም ሀገረ ትውልድን የሚያቃውስ ዜግነትን የሚደመስስ መስሎ ይታያል። … እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት በዶግማና በቀኖና አንድ ይሁኑ እንጂ በሀገረ ስብከት የየራሳቸው ድርሻ ስላላቸው፣ ባንዱ ስም ሌላው አይጠራበትም። ስለዚህ በስማችን ሌላ እንዲጠራበት አንፈልግም፤ እኛም በሌላ ስም መጠራት አንሻም።” (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ 3ኛ እትም፤ 1991 ዓ.ም፤ ገጽ 8-9)"

His Grace Archbishop Zekarias and Melake Tsion Belachew Worku,
at Columbus Ohio St.Gabriel Church
.
እንግዲህ አሁን ሃይማኖታቸው የ“ግሪክ ኦርቶዶክስ” የሚመስላቸውም ቢሆኑ የተሳሳቱት ብፁዕነታቸው እንዳሉት የራስን እምነትና ታሪክ ካለማወቅ የተነሣ ነው። እርሳቸው “የቅብጥ ኦርቶዶክስ” እንዳልሆንን ያስረዱበት መልስ አሁንም ላነሣነው ጥያቄ መልስ ይሆናል።

በእንግሊዝኛ ወይም በሌላ የውጭ ቋንቋ ራሳችንን መግልጽ ቢያስፈልግም “ኦርየንታል ኦርቶዶክስ Oriental Orthodox” (ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ሶርያ፣ ሕንድ-ማላንካራ፣ አርመን እና ኤርትራ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት) መሆናችንን፤ ከዚያም ውስጥ ደግሞ ልክ እንደ አርመን ኦርቶዶክስ ክርስትናን በመቀበል የሚቀድማት የሌለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች መሆናችንን መናገር ትክክለኛ መልስ ነው።

ግሪኮችን ጨምሮ የራሺያ እና የሌሎች የምሥራቅ አውሮፓ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት እንደ እኛው “ኦርቶዶክስ” ቢባሉም “ኦርቶዶክስ ተዋሕዶዎች” አይደሉምና በዶግማም ሆነ በቀኖና አንድነት የለንም። ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንንም አብረን አንካፈልም። እነርሱ ጋር አንጠመቅም፣ አናስጠምቅም። ቁርባናቸውንም አንቆርብም። እነርሱም “የምሥራቅ ኦርቶዶክሶች Eastern Orthodox” ይባላሉ። ስለዚህ ራሳችንን “የግሪክ ኦርቶዶክስ” ማለት ራሳችንን “ካቶሊክ” ወይም “ፕሮቴስታንት” እንደማለት ይሆናልና ትርጉሙ ትክክል አይሆንም።

በተጨማሪም ሃይማኖታችን “ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነው Ethiopian Orthodox Tewahedo” ማለት በራሱ ትልቅ ምስክርነት ነውና እምነታችንን በትክክል ለመግለጥ እንሞክር። ከዚህ በተረፈ ግን የብፁዕነታቸውን መጽሐፍ (የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ) ማንበብ “የተዋሕዶ ልጅ” መሆን ማለት ምን ማለት መሆኑን በትክክል ስለሚያስረዳን ያላነበባችሁ ታነቡ ዘንድ እጋብዛለኹ። መልካም ንባብ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር22 comments:

Anonymous said...

ግሪክ ኦርቶዶክስ ke Oriental Orthodox gare lemesmamate
eyetnegageru new yebalale
dn ephrame selezehe yemtawekew alehe

Anonymous said...

ወንድማችን ጥሩ ተመልክተሃል እኔም ይገርመኝ ነበር፡፡ ግን ግሪክንም ከአምስቱ እመድባቸው ስለነበር ይሄን ስላስረዳህን እግዚአብሄር ረጅም እድሜ ይስጥልን፡፡

Anonymous said...

ክቡር ዲያቆን በጣም እናመሰግንህ ኣለን።

Anonymous said...

Dn Ephrem Egziabher yistilin
Is it true that Ethiopia is the second oldest christian nation in the world? I thought we were the first. Atlanta

Anonymous said...

First, I would like to thank you for this great massage. My comment is about the following statment:
"ግሪኮችን ጨምሮ የራሺያ እና የሌሎች የምሥራቅ አውሮፓ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት እንደ እኛው “ኦርቶዶክስ” ቢባሉም “ኦርቶዶክስ ተዋሕዶዎች” አይደሉምና በዶግማም ሆነ በቀኖና አንድነት የለንም።"

Of course, I do believe Greece and Rassian orthodox are the part of Eastern Orthodox. But, the list of the Oriential Orthodox that you mentioned above are not "Orthodox Tewahedo". They are only "Orenthiel Orthodox". The word "Tewahedo" is given specifical for Ethiopian Orthodox just like Coptic Orthodox (Egyptian) and Malankal Orthodox (Indian).

In addition, the six oriential orthodoxes have a common belife (Dogma) only. Most of them do not have same Cannon (Sereat). For example, Ethiopian and Ertrean orthodox are the only countries that they have the ark of the covenant (Tabot).

Welet Mariam

Anonymous said...

Dear, Ephrem

I was not surprise that you hide my comment. But, what surprised me is that you let Getinet post wrong information. Even if you said that you do not know about Abune Paulos, I am sure you know bout Egyptians belief about original sin.

At this generation, we do not have martyrs. The only martyrs who can come at this generation are those who are speaking the truth. The only thing I can say is that let God help you to speak the truth.

Welet Mariam

zee said...

thank you!

Anonymous said...

Belibe betam sasibew ena sabselesilew yenebere neger new.yihin neger kezih befit gubae lay temire neber.ye'ahunu degmo betam gilts silehonelign dn. betam ameseginalew beteley degmo ye ABUNE GORGORIOS mels betam yigermal.

Anonymous said...

While I understand that you do not want to be associated with a religion that is not really your own, I want to point something out. The individual names and divisions between the various denominations came after the Apostolic Age. During the Apostolic age itself, there was never a denominational division among the Churches even though there were diverse practices among them. What Paul and the other apostles saw as a solution to this problem was not to divide the Churches among denominational lines but rather to address the particular problems ailing them. In fact, in his letter to the Philippians, Paul says that if there is any thing that the people in Philippi do not understand, God will make it clear to them(Phil 3:15). What Paul is saying here is that as long as they were the same on the core issue of Who Jesus was and what he did for us, that all else would be made clear by God over time. Therefor I feel that rather than be divided across the particular histories of the Churches, it is more important to focus on the differences in actual beliefs and try to address those differences in a way that God's true Gospel will stand.

abiyu said...

Thank you very much efi

Anonymous said...

በአለም ባሉ ክርስቲያኖች መካከል ያሉ መለያየቶች በእኔ እምነት መሰረታዊ ልዩነት ያላቸው ድህነትን በማሳጣት ወይም በመስጠት ወደገሀነብ እና መንግስተሰማያት የሚያስገቡ አይመስለኝም። ከዚያ ይልቅ የአምላክን ረድኤትና በረከት ሊያጎሉብን እንደሚችሉ አስባለሁ። ብዙ የሐይማኖት አስተማሪዎች ግን ልዩነቶችን በማጉላት በአለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖች ይባስ ብሎ ኦርቶዶክሱን ከኦርቶዶክስ፣ ፕሮቴስታንቱን ከፕሮቴስታንት፣ የካቶሊኮችን ብዙ ባላደምጥም በመለያየት በአለም ላይ ክርስቲያኖች በመተባበር ሊኖራቸው የሚችለውን መንፈሳዊ፣ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተፅዕኖ በማሳነስ ከዚያ ይልቅ "ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ግዙአትም" የሚለውን በዚህች አለም ላይ ሊኖረን የሚገባውን ሀላፊነትና ተግባር እየዘነጋን እርስበርስ እየተነካከስን በመጠፋፋት ላይ እንገኛለን። ይህ ደግሞ ለጊዜውም ቢሆን በአገልግሎት ውስጥ ያሉትን ግለሰቦች ከመጥቀም ያለፈ አላማ ያለው አይመስለኝም። ስለዚህ ክርስቲያኖች በስላሴ የምናምን ሁሉ ዶግማና ቀኖናዎቻችን እንደተጠበቁ ሆነው ህብረታችንን ብናጠናክረው፣ ለተከታዮቻችን ብቻ ልዩነቶችን ብናስጨብጣቸው በቂ ይመስለኛል። በመቀራረባችን እርስበርስ የመማማር እድላችንና ልዩነቶቻችንን የማጥበብ ዕድልም ሊኖር እንደሚችል ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል። ዓለም ግን ፍቅራችንንና አንድነታችንን ማየት ቢችል በእርግጥም የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮች እንደሆንን ይታወቃል የሚል ሀሳብ አለኝ። በቁማችን ሊወርሰን እና ሁሉንም ነገር ከእጃችን ሊነጥቅ እየገሰገሰ ያለውን አለማቀፋዊነትም መቋቋም እንችላለን ብየ አስባለሁ።
ትሁቱ ከአዲስአበባ

Anonymous said...

thanks efri, but may be there is no choice from the bar when ppl wants to post their faith !

Anonymous said...

ehhhh who cares

Anonymous said...

thanks wendem yalwekenewn selasweken kale hiywet yasemalen

Anonymous said...

አንድ ደግሞ ያልተነሳ ነገር አለ። ኦርቶዶክስ የሚለው ቃል ኢትዮጵያዊ አይደለም። ወደ ጥንታዊው ኢትዮጵያዊነታችን ተመልሰን ማንነታችንን እንደገና ብናስተካክል መልካም ነው፤ የማንነታችን መለያ ነውና!!

Wolde Kirkos said...

My understanding is that the Oreantal and Eastern Orthodox Churches are not in communion as my brother Efrem stated. This is primarily due to differences in dogma when it comes to the nature of Christ. However, threr are also many similarites between the two and in fact the Coptic Orthodox Church recognizes baptism and marriage if conductked at the Greek Orthodox Church. I am not sure if threre is official stand on this by Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.

elias gebeyehu said...

kale hiwot yasemalin

elias gebeyehu said...

kale hiwot yasemalin wendemie

elias gebeyehu said...

kale hiwot yasemalin

Adane Fekadu said...

D/n Ephrem, thanks for passing this lesson out. Most of us make this mistake not only on our profile of social networks (such as Facebook) but also in our daily conversation with "foreign" (better to say, non-Ethiopian) people we face oftentimes. Thanks again.

Anonymous said...

in the name of father,in the name of son and in the name of holysprit,amen!!!
dear brother God bless you and your family too.God can raise his servants from any where,for any time,for the sake of his holy name to bless his people.Please go ahead this spiritual works are the most useful for us.The book of abune Gorgorios is, a book that shows the identity of Ethiopian Orthodox Tewahido Church,the history(different challenges) has been expressed.Please people who do not read this book can get their identity God bless Ethiopia and Ethiopian orthodox Tewahido Church and followers and the land too,Amen!!!

Melaku Tamrat said...

ስለዚህ ራሳችንን “የግሪክ ኦርቶዶክስ” ማለት ራሳችንን “ካቶሊክ” ወይም “ፕሮቴስታንት” እንደማለት ይሆናልና ትርጉሙ ትክክል አይሆንም።
I don't think this is true becoz catholic and protestant has their own dogma and far from orthodox dogma. forexample Catholic's dogma is not orthodoxy it has its own dogma which is different from the orthodox.it is will be easy to compare other orthodox church with the greek orthodox rather than with catholic or protestant.

Blog Archive