Saturday, January 29, 2011

“ጭንቅ አንችልም”

በዚህ ባለፈው ሰሞን በፍጥነት የጣለ የበረዶ መዓት የምኖርበትን አካባቢ አሽመድምዶት ነበር። ለነገሩ ይኼንን ያህል ብዙ ጫማ በረዶ ጥሎ ሳይሆን ከሜትሮሎጂው ግምት ውጪ  እና ከጠበቁት ፍጥነት በላይ ለአንድ ሙሉ ቀን በመጣሉ፣ በረዶ በመጥረግ እና በተመሳሳይ ሥራ ላይ ሊሠማሩ የሚገባቸው ሰዎች በመዘናጋታቸው ነው ተብሏል።  የመጀመሪያውን ቀን የምኖርበት አፓርታማ መብራት ሳይቋረጥበት ለመቆየት የበቃ ቢሆንም በሁለተኛው ቀን ግን መብራት ማግኘት አልቻልንም። እናም መብራት ሲጠፋ ቀስ በቀስ እያለ ቤታችን መቀዝቀዝ ጀመረ። ሻይ እንዳናፈላ ምድጃው አይሠራም። ወደ ውጪ እንዳንወጣ በረዶው እና የአየሩ ጠባይ በጣም አስቸጋሪ ነው።
(Watch the short Video I recorded herehttp://www.youtube.com/watch?v=_SUo1akK8UY)በተለይም ሕጻናት ላሉበት ቤተሰብ ደግሞ ችግሩን የበለጠ ያወሳስበዋል። የመገኛኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ከሆነ በየመንገዱ ላይ በረዶውን መሸከም ያቃታቸው ዛፎች በመገንደሳቸው መንገዶች እየተዘጋጉ ከሥራው ወደ ቤቱ ለመሔድ የወጣው ብዙ ሠራተኛ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ወድቆ ነበር። በአምስት እና አስር ደቂቃ የሚሸፈኑ ርቀቶችን ለማቋረጥ እስከ ሁለት እና ሦስት ሰዓት በመኪና ውስጥ መቀመጥ ግድ ብሏል። ብዙ ሠራተኞች መኪናቸውን ባገኙት ቦታ እያቆሙ ወደሚቀርባቸው ሆቴል መግባትን መርጠዋል። በዚህም ምክንያት ሆቴሎች የመጨናነቅ ችግር ገጥሟቸዋል።

በአፓርታማ ውስጥ ሳይሆን በግል ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ነዋሪዎች የመብራት አቅርቦት ሲቋረጥ ብርዱን ሽሽት ወደ ሆቴሎች መሄድን መርጠዋል። ነገር ግን ከሆቴሉም ለመድረስ መንገዱ ለመኪና ሲያመች አይደል? እናም ይህንን ነገር ሲመለከቱት “ለካስ ይኼ አሜሪካ የሚባል አገር ጭንቅ አይችልም?” አስብሎኛል። አሁን አፍሪካ ቢሆን ምን እናደርጋለን? መብራት ቢጠፋ እንጨት ለቅመን እናበስላለን፣ ወይም እንሞቃለን። ገበያ ባይኖር ሰዉ ከየጓሮው ከተከለው ለመግደርደሪያ ላያጣ ይችላል። ነዳጅ ድራሹን ቢጠፋ ግማሹን መንገድ በእግሩ፣ ግማሹን በጋሪው፣ ግማሹን በከብት ጀርባ ይወጣዋል። ደግሞስ ባይሄድስ ምን ይቀርበታል?


ሆስፒታሉ ሁሉስ ቢዘጋ? ታዲያ ምን አዲስ ነገር አለው። መጀመሪያዉኑ ለስንቱ ሰው ሲደርስ ነው? በደማከሴው፣ በጸበሉ፣ በወጌሻው በምኑም በምኑም ራሱን ይፈውሳል። የምትወልደውም በመንደር አዋላጅ፣ የሚሰበረውም በአገር ወጌሻ፣ የሚያብደውም በታወቀ ጸበል ይፈወሳል።

አሁን እዚህ አሜሪካን አገር 911 ባይኖር፣ ፖሊስ እና እሳት አደጋ እንዲሁም አምቡላንስ አገልግሎት ባይኖር ሰዉ ምን ይሆናል? አያድርስ ነው። እዚያ ወደ አፍሪካስ? ፖሊሱ እና ወታደሩ ቢጠፋ በአገር ሽማግሌ ይዳኛል። 911 የሚባለውን የድንገተኛ አደጋ መደወያ ቁጥር መጀመሪያውም አያውቀውም። አምቡላንሱ የጎረቤት ሰዎች ትከሻ ስለሆነ አያስፈልገውም። ስለዚህ ለችግር ጊዜ ከዚህ ከአሜሪካው አፍሪካ ይመረጥ ይሆን? 

9 comments:

Anonymous said...

definitely
my professor game me an assignment and but i had finished it with in a week, one week before the due date. They are not working after working hours & at weekends. He think that it is also the same to me.That is why he gave me two weeks. But we, Ethiopian students, took every time for study(day and night) and can stand sufferings.

A student abroad

ሲሎንዲስ ዘአውሮፓ said...

About the snow,my friends and I have been discussing z issue earlier when the Britons couldn't manage their unexpected snow.It looks that the Nordics would benefit if they start a new dept named snow management for the 'not snowy' westerns.I wont post my pics or videos of this winter, coz u may argue that its done wiz Photoshop:)

On z other matters its true, zey r more flesh-comforted but vulnerable and we r more challenged but resistant.

Rebkka ke frankfurt said...

Selam D, Ephrem Enqan adrshe lembetatin bale Egzabher Yemsgen Ekekin yest amlak tefrin aynsam yelal yagerswe. hulnem endakme nwen yemstwe (Afrika)akmaten bfeked ylwes tiger meht talnwena, ynanten berdo yamtabein.lenantem Egzabher yedrslathu.Endalkwe tegrun betta sayhon destwenm bihon yemymerbin bebtahtin(ETHIOPIA) nwe! beylenbet selamuin yestin

Anonymous said...

lol ababa i like this, It is good theory of relativity. Hiw

ዘክርስቶስ said...

እኔም በአጠግብህ፦ አንተ ካለህበት ክላይሜት የባሰ በረዶ ቦታ ነው ያለሁበት። እንዳልከው የሚገርመው አፍሪካዊያን ችግር ቢደርስብን መዋጠጫ አፈላልገን ግባችን ሳንመታ አንቀርም። ሰmoኑን ሪሰርች ሰርተን እንድናቀርብ ፕሮፌሰራችን አዘዘንና ወንድሜ! ከብርዱ ዝለት የተነሳ ማነው ሰርቶ የሚያቀርብ? ኢትዮጵያዊው ወንድምህን ግን እንደምን ብዬ እጄን ከአፌን እንፋሎት እየዘገንኹ በማሟሟቅ ታይፕ አድርጌ ያለምክንያት ፕረዘንት ሳደርግ ፕሮፌሶሩ የደስታም አትለው የሀዘን ፊት ሰጠኝ።

Anonymous said...

እዚያ ወደ አፍሪካስ? ፖሊሱ እና ወታደሩ ቢጠፋ በአገር ሽማግሌ ይዳኛል። ብለህ ነው!?
እንጃ። ምናልባት የጥንት ያአባቶቻችንን እያሰብን ካልሆነ በተቀር። የዘመናችንን አስታራቂ ሽማግሌዎችማ አየናችው። ኧረ ወንድሜ ያንን 911 አያሳጣችው።

Anonymous said...

right you are...

raguel said...

መዝሙር 147:16 አመዳዩን እንደ ባዘቶ ይሰጣል፤ ጉሙን እንደ አመድ ይበትነዋል፤

17 በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፤ በበረዶውስ ፊት ማን ይቆማል?

18 ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።

netsi said...

u made me think of ይሄ የነሱ ጭንቅ አለመቻል ተጋብቶብን ይሆን እንዴ ያገሬ ሰው ቤተክርስቲያናችንን የከፋፈሉዋት? We believe that there is a huge problem in our church but please tell them these so called chicken Christians that they should face it instead of running away. They don't know the consequences of their action, they are ruining generation and the country.

*sigh*!

Blog Archive