Sunday, January 30, 2011

ድብርት

ምንድር ነው?
ደርሶ ልቤን ያከበደው፣
ጠይም ፊቴን ያከሰለው፣
ጥርሴን ከሣቅ የከለለው።

የዕንባ እናቴን ጠርቶ፣
ዓይኔን ደም ቀብቶ፣
ጉሮሮዬን በሳግ ሞልቶ፣
አንጀቴን በእጥፋት ቀንቶ፣
ደስታዬን በሐዘን የወጋው፣
ቀኔን ከጎዳና የጣለው፣
ምንድር ነው?
(ታኅሣሥ 17/93 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ) 

6 comments:

Anonymous said...

Mekefat new efi!
Degmo lemen yekfagn!
Alekefam.


(arif gitim new)

Anonymous said...

dbrt new

Anonymous said...

+++
ያልከው ትክክል ነው
ፀበል ፍቱን መድኅኒቱ ነው::

Tadesse said...

ለናት ነዋ ለተዋህዶ!!!
---------------

ይሆናል የናት ነገር ያባት ነገር
ሆኖብህ ለሰው ማይነገር
አትታማ አባት ነው እናት ናት
ለወሮ በላ፤ለመናፍቅ አሳልፈህ አትሰጣት
እንደካም ላለ መሆን ፈልገህ
እሳት ሆኖ ገረፈህ ለበለበህ
ጠይም ፊትህን አከሰለው
አንጀትህን በላው ጨረሰው ገደለው::

ይሁን ታዲያ ምን አለበት
ፊት ቢከስል፤ እንጀት ቢያርር፤ ጨጋራም ቢቃጠል
ዞሮ ዞሮ ነገ ጥዋት የትል አይደል?

ወንድሜ ሆይ እኔ የምልህ አባባ
ዛሪ እንዲህ ብትቃጠል ብታነባ
ነውና የሚገባ

ለተዋህዶ ለናትህ
እንካን መጥቆር መክሰም ፊትህ
ትሰጥ የለም ወይ ውድ ሕይወትህ!!!


ታደሰ ከበደ
Jan 31, 2011 9:02 PM, Alexandria, VA
ለዲ ኤፍሪም እና ለተዋህዶ ልጆች በሙሉ

Anonymous said...

አዞህ ወንድሜ አትደበር
መቆዘሙም ያልፋል በእግዚአብሄር
እኔ እምልህ በርታና
ድብርትን አጥፋ ከአንተና ከእማማ
ቆም ብለህ አስተዉል የአምላክህን ቃል ለአፍታ
የሚያስጨንቃችሁን ለእኔ ተዉት ብሎን የለ እንደ የእኛ ጌታ፡፡

ሙሉግታ መልኩ(ክ/ኪሩቤል) ከጎንደር

Anonymous said...

ድብርት ምንድን ነዉ? ላልከው
እኔ እንዳየሁት እንደዚህ ነው።
ፍቅር ሰጥቶ ምላሽ ማጣት
ፊትን ሰጥቶ ፊት መነሳት
ጠዋት ማታ ሰላም አጥተህ
ራስህ ዞሮ በዝቶ ደምህ
መፍትሄ የሌለው መቃተት
ትርጉም አልባ ሰውነት
የራስህ የሆነው ነገር
ለራስህ ሲሆንብህ ምስጢር
ግራህ የሚሰራዉን ግብር
ቀኝህ ሳያውቀዉ ሲቀር
ደሞ በዚያ ላይ ሰውን ማጣት
የምትተነፍስለት የምትተነፍስበት
ኧረ ጌታዬ ምን ነዉ ዝም አልክ
ሁልዬ ስትጮህ ወደ አምላክ
በቃህ! የሚልበት ቀኑ
ሳይታወቅ ዳር ወሰኑ
ለእኔ እንዲህ ነው ድብርት ማለት
ወጥቼ ወርጄ እንዳየሁት።


በሥላሴ ታደሰ

Blog Archive