Friday, January 7, 2011

ምክንያተ ጡመራ Why Blogging?

ለትምህርትም ለኑሮም አገሬን ለቅቄ ከመውጣቴ በፊት፣ አዲስ አበባ ላይ፣ ከጓደኞቼ ጋር የምናስበውንም የምንጭረውንም ነገር የምናስቀምጥበት አንዳንድ ደብተር (Journal) ነበረን። ግጥምም፣ መጣጥፍም፣ ፖለቲካም፣ መዝናኛም … የሆነውን ሁሉ የምንጭርበት ነበር። ነገር ግን ልጫረው እንጂ ለጋዜጣም፣ ለመጽሔትም፣ ለሬዲዮም ሆኖ አያውቅም ነበር። በየወሩ ግድም ባለን የጓደኞች የሥነ ጽሑፍ ጉባዔ እዛው እቤታችን የምናነባቸውን ነገሮች የምናዘጋጅበትም ነበረን። አንድ ቀን ሰብስበን መድበል እናደርጋቸዋለን የሚል ሐሳብ ነበረ። እንዲያውም ኃላፊነቱን ለእህታችን ለጽላት (የዳንኤል ምሽት ይላል የገጠር ሰው) የሰጠናት ይመስለኛል። ከዚያ ኑሮ ሲበታትነን - እኔም አውሮፓዬ ሔድኹ። ዳንኤል ክብረትም፣ አሥራት ከበደም፣ መስፍን ነጋሽም፣ ተስፋዬ ሽብሩም፣ መርሻ አለኸኝም፣ አሉላ ጥላሁንም፣ ያሬድ ገ/መድኅንም ግርማ ወ/ሩፋኤልም፣   ሸዋደግ ሞላም፣ ታምሩ ለጋም፣ ትዕግስት ዳኜም፣ ጽላት ጌታቸውም፣ ምስራቅ ግዛው ሁሉም ሁሉም በኑሮ ጣጣ ሲጠመድ መድበላችንን ውሃ በላው ወይም መድበላችን ውሃ ጠጣ። 

ሲጀመር፦ ወደ ጡመራው ለመዞር ሐሳብ አልነበረኝም። ሥራዬ አብዛኛው ከጽሑፍ ጋር የሚገናኝ እንደመሆኑ ሌላ የጽሑፍ ነገር በመዝናኛነትም ቢሆን መጀመሩ ቀላል ሸክም አይሆንም ብዬ ፈራኹ። የምጽፋቸውንና የምሞነጫጭራቸውን አንዳንድ መጣጥፎች የሚያውቁ ወዳጆቼ “ግዴለም፣ ግዴለም፤ እኮ በል፣ እኮ በል” ብለው ብዙ ጊዜ ሲገፋፉኝ ቆዩ። እሺ፣ በጄ” አላልኳቸውም።

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ወዳጄ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት አዲስ አበባ ከሚታተመው ከ“ሮዝ” መጽሔት ጋር አስተዋወቀኝና “ካልጻፍክ” ሲል ግድ አለኝ። “እንዳልክ” አልኩና መጫጫር ጀመርኩ። ከዳንኤል ጋር ብዙ ዘመን አብረንም ከመኖር፣ አብረንም ከመሥራት ውጥር አርገው ካልያዙኝ እንደማልሠራ ጠባዬን አውቆታል። “ሮዝ መጽሔትም” በየ 15 ቀኑ “ውጥር አድርጎ ሲይዘኝ” በወር ሁለት ነገር መወርወር ያዝኩ። ያንንም እያሰለስኩ በፌስቡክ ላይ ጫንኩት። ዳንኤልን የዛሬ ዓመት አካባቢ “ብሎግ ጀምር፣ ጦምር” ብዬ ግድ ልኩት እኔ ነበርኩ አሁን ደግሞ በተራው ዳንኤል ሰሞኑን ወደ ሀገረ አሜሪካ ሲመጣ “መጻፍህ ካልቀረ ብትጦምረው” አለኝ። እኔም “መጻፌ ካልቀረ፣ እስከዛሬስ በየወረቀቱ ላይ ጫጭሬ ያስቀመኳቸውንም የምጨምርበት አንዲት “የሕዋው ደብተር ብትኖረኝ ምን ይጎዳኛል” ብዬ "ቁሳቁስ መስጠት ብቻ ሳይሆን መልካም ሐሳብም ማካፈል ጥሩ ነው" በሚል መነሻ ለመጦመር ተነሣኹ።

ዕድሜ ለቴክኖሎጂ፣ ሰው የሚያስበውንና የሚያልመውን፣ የሚፈልገውንና የሚፈቅደውን የሚያስነብብበት፣ የሚያስደምጥበት፣ የሚያሳይበት ሰፊ “አደባባይ” ተፈጥሯል። በፊደል ከሽኖ በጽሑፍ፣ በድምጽ ቀምሮ በምጥን ሬዲዮ (ኦዲዮ) መልክ፣ በቪዲዮ አሳምሮ በዩ-ቲዩብ እና በመሳሰሉት ነገሮች ሐሳቡን ማቅረብ ይችላል። ከሁሉ ከሁሉ ለጊዜው ልቤን የገዛው “ብሎጊንግ” ወይም ጡመራ ነው።

Blogging / ብሎጊንግን ጡመራ (መ ሲነበብ ይጠብቃል) ያለው “ደጀ ሰላም” ነው። በሥነ ጽሑፋዊ የመፍጠር ፈቃዱ  (“poetic license” እንደሚባለው) “ደጀ ሰላም” የመፍጠር መብቱን ተከትሎ አዲስ ቃል አስተዋውቆናል። “ጦማር” (መ አይጠብቅም) የሚለውን ቃል ወስዶ ግስ አድርጎ፣ ገሰሰውና “መጦመር” የሚል ቃል ፈጥሮ በዚያው አረባው፣ እናም “መጦመሪያ መድረክ”፣ “ጦማሪ” እያለ አስፋፋው። ሌሎቹም ጦማርያን በዚሁ ቃል መጠቀሙን ቀጠሉበት። እኔም በዚሁ እከተላለኹ። እንግዲህ ከማጀቱ ወደ “አደባባይ” ብቅ እንበል። መልካም ንባብ።


25 comments:

መብሩድ said...

ሰናይ!እና ምን ይለናል፡፡እንኳን ለዚህ አበቃህ እኛንም እንኳን አደረሰን፡፡
እንግዲህ እናንተ ወንድሞቻችን/አባቶቻችን ጦማር እንደቅኔ መነጣጠቅ ከያዛችሁ እኛም እንደ TVchannel እየቀያየርን መኮምኮም አያቅተንም፡፡
ጦማሪ ይኑር እንጂ ለማንበብ እንተጋለን፡፡እድሜና ጸጋ ያድለን፡፡
እንከሰ ምንተ ንብል፡፡
ጥበብ መንፈሳዊ ወዘመናዊ ይሀብክሙ፣ወለንህነሰ አዕይንተ ንባብ ወአእምሮ ይጸግወነ፡፡
ወደጄዋለሁ እወደዋለሁም።

Melaku Y. said...

" መድበላችንን ውሃ በላው ወይም መድበላችን ውሃ ጠጣ"። This is funny man! Deacon Ephrem i wish u the best and may God bless your work, time and days ahead

zemichael said...

Welcome ababa. Hope u ll teach us a lot.

jupiter said...

Really Ephrem,i am happy to read this!! God be with you!!

Mikiyas said...

that is really wonderfull,,,,, keep it up,,,,,, may God give u the strength in all your efforts,,,,

Aster said...

አማን በአማን ሠናይ ውዕቱ! ይበል ብለናል ዲን.ኤፍሬም ለረዥም ጊዜ ስንጠብቀው የነበረው ብሎግህ ገናን አስታኮ እንደ ሥጦታ በማግኘታችን የሚያስመሰግን ነው፡፡ የቅዱሳን አምላክ እስከ መጨረሻው ያስፈፅምህ፤ እድሜ ከጤና ያድልህ!

Anonymous said...

ዲ/ን በጣም በጣም ደሥሥሥሥሥሥሥ ብሎኛል::
ከላይ ወንድም መብሩድ ያለው ተስማምቶኛል::

"እንግዲህ እናንተ ወንድሞቻችን/አባቶቻችን ጦማር እንደቅኔ መነጣጠቅ ከያዛችሁ እኛም እንደ TVchannel እየቀያየርን መኮምኮም አያቅተንም፡፡"

Anonymous said...

d/n ephrem bel eganem woha atetan enge

Anonymous said...

ሁሌ የማስበው ነገር ነበር እንካን ለዚህ አበቃህ መጨረሻው ያሳምርልህ

Anonymous said...

Good Job Dn Ephrem,
When I read other blogs, I always think about you. I wish you could make it a blog of any issues like Dn. Daniel's. I mean don't only focus on relgious issues.

God Bless your work.

Selam SJ said...

This is my 2011 gift from you to me. May God bless you and your work. I thank you for letting me join you(read in to) your creative mind. I also look forward to leaning many many things from "Adebabye"

Desalew said...

Good job!! berta wondimae.

Anonymous said...

እጅግ በጣም ደስ ይላል። እንደዚህ ሁሉም በአለበት ምልከታዎችንና እወነትን ማካፈል መቻል። እኛም በስውር ከሚመስል ውስጥ ተደብቀን አስተያየት ከመስጠት እንዲሁ በአደባባይ የአመለካከት ፍጭት እንድናደርግ ይርዳን
ቴዎድሮስ

Anonymous said...

wed wendemocha

egziabher yasfetsemachu

and as u begin with different categories ,keep it up and i preffer even if u give more infessis to spritual issues.

Abiot k oldenburg germany

please keep ur swares to church as mk member and keep also ur contribution to mk.

may God bless u

Anonymous said...

ስብሃት ለእግዚአብሄር በሰማያት ወሰላም በምድር ለሰብዕ በእውነት በጣም ደስ ብሎኛል ወንድማች ትልቅ ስራ ነው የድንግል ልጅ ስራህንና ቤተሰብህን ይባርከ በዚህ አጋጣሚ ሚስትህ ሳላመሰግን አላልፍም ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራት

Anonymous said...

Ephriye,

I have been expecting this. I am so happy it has now come to my screen.

Bertalin wendimachin, Amlak yaberitah.

Mihret/Mitty KeHagerBet

Anonymous said...

“When I stand before God at the end of my life, I would hope that I would not have a single bit of talent left, and could say, "I used everything you gave me.”
Erma Bombeck.

John said...

እድሜ ለንስሃ ዘመን ለፍስሐ የምትሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ወደ ልቡናችን ትመልሰን ዘንድ አንድ የመማርያ ዕድል ስለጨመርክልን እናመሰግንሃለን፡፡ የሚጽፉና የሚያስተምሩ ወንድሞቻችንንም በጸጋ እና በጤና ጠብቅልን! ተ መ ስ ገ ን !

Anonymous said...

I know Efrem Eshet starting from 1984 E.C at KCTE. specially, He likes very much discussion at day and night.I know that you have a good potential,please continue i am very happy.
MY GOD BLESS YOU!!

Anonymous said...

ይበል ብለናል፡፡ ይሁንና በፊት በፊት አንተንም ሆነ ከላይ የዘርዝርካቸውን ጓደኞችህን ሳውቅ የእግዚያብሄርን ቃል በቃልም በመጻፍም ስታደርሱን ነበር፡፡ ምነው ታዲያ በዚህ ዘመን ወደ አለማዊ ጽሁፎች አተኮራችሁሳ ? አለማዊ ነገሩን ተዉት ማለቴ ሳይሆን ገና ድሮ የተነሳችሁለት የአገልግሎት ነገር ባይረሳ የሚል ወንድማዊ ምክሬን በትህትና ለመለገስ ነው፡፡

ኤፍሬም እሸቴ said...

ስለ ወንድማዊ ምክሮ አመሰግናለኹ። ይህንን እዚህ መጻፋችን ሌላውን ከመጻፍ የሚያግደን አይመስለኝም። "የተነሣንለት አገልግሎት" እንዳይተጓጎል እርስዎም በጸሎትዎ አይርሱን።

Anonymous said...

ከአሳሪው አስተሳሰብ መውጣት ይኖርብናል፡፡
ደ/ን እፍሬም በአካል አላውቅህም፡፡ነገር ግን
የጥናት ወረቀቶችህን ፣ መጽሐፍህን፣መጣጥፎችህን
አንብቤያለሁ ብዙ ወዳጆቼ ስላንተ ብዙ ስለነገሩኝ
የማውቅህ የቅርብ ወዳጄ ያክል ነው ላንተ ያለኝ ስሜት፡፡
አንተ ያለፍክባቸውን ፍኖት ከሚከተሉት ወገን ነኝ፡፡
የእናንተ ትውልድ አካል ሆኖ ያወቀውን ጎርሶ የሚኖር
ስንት አለ መሰለህ፡፡ ከዚህ የመውጫው ጊዜ አሁን ነው፡፡
በርታ ወንድማችን፡፡ዓለማዊ መንፈሳዊ የሚለው የአገልግሎት
ፍልስፍና ገና በቅጡ መታየት ይኖርበታል፡፡ዓለምን በሁሉም ነግር
ማብቃት ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡

Anonymous said...

Dn Ephrem,

You are known for creating some new amahric words, can you post them all together please? I saw some of them...

Anonymous said...

Which ones did you see? Share here.

abenete Temeheret said...

may God Bless you and your hand we need additional spiritual thing on your blog
wondwosen

Blog Archive