Wednesday, February 2, 2011

የአንባብያን አስተያየት

ወንድማችን ዲያቆን ኤፍሬም በቅድሚያ የከበረ ሠላምታዬ ይድረስህ። የተነሳው ርዕስ አዲስ ለመጡትም ሆነ ገና ወደ አሜሪካ ለመምጣት ላሰቡ ወገኖቻችን በጣም ጠቃሚ እንደሚሆን አምናለሁ። ምንም እንኳ ብዙዎች ወገኖቻችን የውጭ ሀገር ኑሮ እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነ ቢገለጽላቸውም፣ ያለ መታደል ሆኖ እውነታውን ላለመቀበል "እሱ ሀብታም እየሆነ እያየሁት እሱን እንዳልጋፋው፣ እሱን እንዳላስቸግረው፣ ሊረዳኝ ስላልፈለገ ብቻ ክፉ ክፉውን ያወራልኛል" በማለት ራሳቸውን ስለሚደልሉ ወይም ስለሚያሞኙ ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ ለአደጋ ሲጋለጡ ይስተዋላል። አንተም ወንድሜ በተለያዩ ምሣሌዎች ችግሮቹን ለማሳየት የበኩልህን ጥረት አድርገሃል። 


እንደ እኔ፣ እንደ እኔ የሚታየኝ፣ ማንም ሰው አገር፣ ግዛት ወይም አካባቢ ሲቀይር ኑሮ ከመጀመሩ ወይም ሥራ ከመያዙ አስቀድሞ ስለዚያ አገር ወይም አካባቢ ሕግና ደንብ፣ ህብረተሰቡ ቦታ (value) ስለሚሰጣቸው ጉዳዮች፣ በህብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያላቸው ጠባያት (በኛ ባህልና እምነት ያልለመድናቸው ሊኖሩ እንደሚችሉ በመገመት)፣ የአየሩ ሁኔታ፣ አመጋገባቸው፣ አለባበሳቸው፣...ወዘተ መጠየቅ ወይም ማንበብ ይኖርበታል። ይህንንም ማድረግ የሚችለው ደግሞ ወይ ጥሩ ዘመድ ሲኖረው (ለዛውም እሱን ቁጭ ብሎ የሚያስረዳ ሲገኝ) ወይም እንግሊዝኛ አንብቦ መረዳት የሚችል ሲሆን ብቻ ነው። አለበለዚያ ግን "ጨረቃ ላይ ወደቀ" ማለት ነው። ወንድሜ ዲያቆን ኤፍሬም! እንደምገምተው ለሀገሩ ባዳ ባለመሆንህ የኛ ከሙኒቲ ቢሮ ውስጥ አዲስ ለመጡ ወገኖች በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተዘጋጀ በራሪ ወረቀት ካለ አይተህ፣ የራስህን ሀሳብ ጨምረህ ከቤተሰብህና ከሥራህ ጊዜ ትንሽ ቀንሰህ ብታዘጋጅ ምን ይመስልሃል? እኔ ብዙ ባላውቅም በዚህ ጉዳይ ሊተባበሩህ የሚችሉ ወገኖችንም ድጋፍ ብትጠይቅ የሚያስከፋ አይመስለኝም። ከዚያ በተረፈ ተጨማሪ መረጃ ለሚፈልግ የሚከተለውን ድረ ገጽ መመልከት ይችላል። www.welcometousa.gov ወይም ደግሞ ይህንን ፒ..ኤፍ. ዶኩመንት download ማድረግ ይችላል። http://www.uscis.gov/files/nativedocuments/M-618.pdf 

በተረፈ ዲያቆን ኤፍሬም አገልግሎትህን እግዚአብሔር ይባርክልህ!
(አምሐ)

+++++++++++++++++++++++++
Adebabay - needs to be a different one - a true fair and free Adebabay 

Ephre,
I like Adebabay... it becomes adebabay where different issues raised badebabay. Great! but from the comments forwarded and the nature of the issues you are pointing out, etc., i suggest you make it Adebabay that is not only where you can forward ideas/issues but also people who are joining you in adebabay can reflect and discuss issues freely. Not only interms of forwarding thier comments and ayzoh, berta, :):) belabla but also enrich the issues and to come up with a tangible action points which can be easily taken up by the readers and done in thier daily life. In this cas you will be creating a fair and free playground where everybody can be participating well - adebabay.

With Love and appreciation,

Z. E

3 comments:

Anonymous said...

Hello Dn.Ephrame I saw some commentes about our dream of america so it was so interesting and nice view. I have one experience in my life regarding to the title which is i gradute back home in one university and i get bacheliour degre when i came to usa my dream and my hope was too much the reason was i work differently from other pepole but the tru was not complitly diffferent. so i decide to go college but my result was law lable but i didn't accept that and work hard in small lable at last after 4 yaers later I staretd low lable now i will gradut after 1year later .

Anonymous said...

ወንድማችን ኤፍሬም እውነት እግዛብሄር ይባርክህ

Anonymous said...

Dikin Epharme sele America yesafkewu betam tiru ena ewunetega newu sewu hulu limarebet yegebal Tesfayem betem tiru beeha tekebaye binorm bayenorm menageru tiru new beyegizewu yemimtu selalu wededum telum erasachwun emazegaget yetekmachewalna bertu. Betam bezu neger eyayenina eyeseman newun sewu ketegoda behuala kemazen hasab mekafelu tiru newu Egzeabher yebarkachu.

Blog Archive