Monday, February 28, 2011

የኢንተርኔቱ ዓለም እና ጣጣው

የዚህን እትም የሮዝ፣ ይቅርታ የ“አዲስ ጉዳይ”፣ ጽሑፌን በሌላ ርዕስ ላይ እያዘጋጀኹ ነበር። በመካከሉ የአሜሪካ ድምጽ ለመስማት ከፍቼ መስማት ጀምሬ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የአንድ ወዳጄ  ስልክ አንቃጨለ። ሳነሳው የአሜሪካ ድምጽን ለመስማት ሞክሮ እንዳልተከፈተለት ነገረኝ። “ኧረ እየሰማኹ ነው፤ እስቲ ድጋሚ ሞክረው” አልኩት። ሞከረው። አይሰራም። እኔም እሰማው የነበረውን ትቼ ድጋሚ ሌላ ስከፍት እውነትም ሌላ ሆኗል። ድረ ገፁ ግን ራሱ የአሜሪካ ድምጽ ነው። የሚታየው ግን የተለመደው የቪ.ኦ.ኤ ዓርማ ሳይሆን በአረብኛ ያሸበረቀ “እኛም እንደምንችል አሳየናችሁ” የሚል ፉከራ ቢጤ ነው።ቀጥሎም “ወ/ሮ ክሊንተን፤ አሜሪካ ውስጥ ያሉ የተጨቆኑ ‘አገሮችን’ ድምጽ መስማት ይፈልጋሉ? የሙስሊሙ ዓለም የዩ.ኤስ.ኤን ማታለል አያምንም። በሙስሊም አገሮች ጉዳይ ጣልቃ መግባትዎን እንዲያቆሙ እንጠይቆታለን” ይላል። ከዚያም “List Of Hacked WebSites” ብሎ የ98 ድረ ገጾችን ስም ይዘረዝራል። ጉዳቸውን ልይ ብዬ የተወሰኑትን ከፈትኩ። እውነትም ከጥቅም ውጪ አድርገዋቸዋል። ይህንን ጽሑፍ እስከፈጸምኩበት ሰዓት ድረስ ድረ ገጾቹ አይሰሩም፣ ጉዳዩ በዜና ማሰራጫዎችም ሲነገር አልሰማኹም። ምናልባት ዘግየት ብሎ ይናገሩት ይሆናል።


የእንዲህ ዓይነቱ የሳይበር (የኢንተርኔት ጥቃት) ሰለባ የሚሆኑት ድርጅቶችና መንግሥታት ብቻ ሳይሆን ግለሰቦችም ጭምር ናቸው። ከዚህ በፊት ብዙ ወዳጆቼ “ኢ-ሜይሎቻቸው” እየተመነዘበሩ (Hacked እየሆኑ) በስማቸው ለሌሎች ሰዎች የርዳታ ጥያቄዎች ሲላኩ አጋጥሞኛል። በ2009 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ አንድ ዶ/ር (ስላላስፈቀድኳቸው ስማቸውን መጥቀስ አልፈለኩም) የግል ኢ-ሜይላቸው ተሰርቆ ኖሮ በእርሳቸው ስም የገንዘብ እርዱኝ ጥያቄ ተልኮ ነበር። በቅርቡም እንዲሁ ዓይነት ተመሳሳይ ጉዳይ በአሜሪካ ባሉ በአንዲት ታዋቂ ኢትዮጵያዊት ስም ተልኮ አይቻለኹ። አንዲት ጣሊያን የምትገኝ ወዳጄ ኢ-ሜይሏ “Hack” ከተደረገ በኋላ የተላከውን ባካፍላችሁ የምለው የበለጠ ግልጽ ይሆናል።


How are you? How is everything with you? I want to inform you that I came for a program here in London; I have been doing bad financially and in Health wise. At this time I'm out of cash and very sick. I was not successful in transferring money on line to my external account before leaving, my attention was urgently needed. Please, I need to pay my bills at the Hotel and also get some drugs for my health. I have contacted my bank for money transfer, but they said nothing can be done because I need to sign some papers before funds can be transferred to me here.
Please, I need you to kindly send me £2300.00 or any amount you can afford for my upkeep, I suggest you send the money today via Western Union Money Transfer with this Information's.
Name: XXXXXXXXX (ስሟን ጠቅሰውታል)
Address: - 39, Marylebone Road. London, NW1 6JQ. United Kingdom.
I promise to refund the money back as soon as I return. I will be waiting to hear from you as soon as possible with the transfer information's including the MTCN number on the receipt so that I can take necessary actions. Am sorry for any inconvenience this may cause you. With Best Regards, ….. 
ይላል።


በአጭሩ ለማቅረብ፣ ይህቺ ወዳጄ ካለችበት አገር ወደ ሎንዶን እንደሄደች፣ በዚያም “የሆነ ችግር እንዳጋጠማት”፣ በዚህም ምክንያት መጥፎ ሁኔታ ላይ እንደወደቀች፣ ከዚህ ችግሯ በፍጥነት እታደጋት ዘንድ £2300 ፓውንድ ወይም ያለኝን ገንዘብ በፍጥነት እንድልክላት፣ አገሯ ስትመለስ እንደምትከፍለኝ የሚናገር ነው።


ቅድም ያልኳችሁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር በ2009 ኢሜይላቸው “ሃክ ሲደረግ” በስማቸው የተጠየቀው £1400 ፓውንድ ሲሆን ባለፈው ሳምንት ይኸው ዕጣ የገጠማቸው የዲሲዋ ኢትዮጵያዊት ደግሞ £1500 ፓውንድ ነበር። እንዲህ ዓይነቱ አስደንጋጭ መልእክት የሚደርሳቸው ወዳጅ ዘመዶች፣ በተለይ በርቀት ያሉ፣ ወገናቸውን ለመታደግ በፍጥነት ያላቸውን ይልካሉ። ለዚህ ደግሞ አንድ ገጠመኝ ልጨምር።


የዛሬ ዓመት አካባቢ ዳላስ ከተማ ከሚገኝ ወዳጄ ጋር በስልክ ስናወራ ሁለታችንም የምናውቀው አንድ ጓደኛችን እንግሊዝ አገር ሄዶ ንብረቱ እንደተዘረፈ፣ ስለዚህም ለእርሱ ገንዘብ ልኮ እየተመለሰ መሆኑን አጫወተኝ። “በምን አወቅህ?” ስለው ኢ-ሜይል እንደጻፈለት ነገረኝ። ነገሩ ውሸት መሆኑን፣ ቶሎ ሄዴ ገንዘቡን ማስመለስ እንዳለበት ስነግረው ወደ ቤቱ መንዳቱን ትቶ ወደ “ዌስተርን ዩኒየን/ Western Union” ቢሮ ተመለሰ። ጉዳዩን ጨርሶ እንደነገረኝ የላከውን $1000 ዶላር አስመልሶ ለተፈጠረው ስሕተት ወደ $80 አካባቢ ዶላር ተቀጥቶ የተረፈውን ብር ሊያገኝ ችሏል። ያ ችግር ገጠመው የተባለው ሰው ግን አዲስ አበባ በሰላም ተቀምጦ ነበር።


የሚገርመው እነዚህ የኢንተርኔት ሌቦች የሰዉን ሁሉ ኢ-ሜይል እየጠለፉ የሚዘርፉት አብዛኛው ከእንግሊዝ ናቸው። ምንም ዓይነት የጥናት መረጃ ወይም ማስረጃ ማቅረቡ ስለሚከለብድ ነው እንጂ በዚህ የሌብነት መስክ የተሰማሩት ናይጄሪያዎች ናቸው እየተባሉ ይታማሉ። ዋናው ቁምነገር “እነማን ናቸው?” ሳይሆን “እንዴት ራስን መከላከል ይቻላል?” የሚለው ነው። ችግሩ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ የተረዳኹት የሚከተሉትን ዓይነት ዜናዎች ሳነብ እና ስሰማ ነው። እነሆ።


የእንግሊዝ መንግሥት በዚህ ወር እንዳስታወቀው (http://www.bbc.co.uk/news/uk-politics-12492309) እነዚህ የኢንተርኔት ወንጀለኞች በአንድ ዓመት ብቻ የ27 ቢሊዮን ፓውንድ ኪሳራ አድርሰዋል። ከዚህ 27 ቢሊዮን ፓውንድ መካከል 21 ቢሊዮኑ ከንግዱ ሕብረተሰብ፣ 2.2 ቢሊዮኑ ከመንግሥት፣ 1.3 ቢሊዮኑ ደግሞ ከዜጎች የተወሰደ መሆኑን ይኸው ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የተደረገው መረጃ ያሳያል። 


እንደ ኢትዮጵያ ባለው ኢንተርኔት ተጠቃሚው ሕዝብ እና ድርጅት እጅግ በጣም አናሣ በሆነበት አገር ጉዳቱም ያንኑ ያህል አናሳ ስለሚሆን ለጊዜው ብዙም የሚያሳስብ አይደለም። ነገር ግን በኢ-ሜይላችን እና በስማችን የማይሆን ነገር ሲላክ የሚፈጥረውን ስሜት ግን ለመቀነስ፣ ብዙ ነገር የተጻጻፍንበትን እና ብዙ መረጃዎች የያዝንበትን ኢ-ሜይል በቀላሉ ላለማጣትም ቢሆን ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ ይሆናል። ከዚህም በተጨማሪ የአገራችን የንግድ መስመር ዞሮ ዞሮ ወደ ኢንተርኔት እየገባ እንጂ እየወጣ ስለማይሄድ ከወዲሁ ዝግጅት እና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። በተለይ ባንኮች፣ አየር መንገዶች፣ ሆቴሎች፣ መብራት ኃይል እና ቴሌኮሚዩኒኬሽንን የመሳሰሉ መንግሥታዊ ድርጅቶች እና የአገሪቱ ምስጢሮች ያሉባቸው ቁልፍ ቁልፍ ተቋማት የጥቃት ሰለባ የመሆን ዕድላቸው ሰፊ ነው። የዘመኑ ጦርነት መሣሪያ በመተኮስ ብቻ አይደለም። ከዚያ ባልተናነሰ መልኩ በኢንተርኔቱ የሚደረገውና በይፋ የማይታየው ጦርነት እጅግ የጦፈ ነው።


በ2007 የራሺያ መንግስት በዚሁ ዓይነት ጥቃት ኢስቶኒያ/ Estonia የተባለችውን አገር ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ አድርጎት ነበር (http://www.guardian.co.uk/world/2007/may/17/topstories3.russia)። የአሜሪካ መንግሥት እንደሚናገረው ከሆነ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር የኢንተርኔት ጥቃት ይደረግበታል። የንግድ ተቋማቱ እና መከላከያው በተለይም “ፔንታጎን” የመጀመሪያ ዒላማዎች ናቸው። 


የዚህ ጥቃት የቅርብ ጊዜ ሰለባ ሆኖ በመገናኛ ብዙሃን የሰማኹት የካናዳ መንግሥት ሲሆን “ሌቦቹ” የአገሪቱን ኢንተርኔት አጥር ሰብረው መግባት ችለዋል (http://www.nytimes.com/2011/02/18/world/americas/18canada.html)። ያገኙትን እነርሱ ያውቃሉ። ካናዳዎቹ ግን ለመናገር አልፈቀዱም። ይህ ጥቃት የደረሰባቸው “ቻይና ከሚገኝ” የኢንተርኔት አድራሻ መሆኑን ከመግለጽ በስተቀር። ምናልባት በዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ልክ እንደ ራሺያ በብዛት የምትታማው ቻይና ካናዳዎቹን ጉድ ሰርታቸው ይሆናል።


በአጠቃላይ የሆነው ሁሉ ሆኖ በግለሰብ ደረጃ ኢ-ሜይላችንንም ቢሆን ላለማጣት የሚከተሉትን የጥንቃቄ መንገዶች መከተሉ አይከፋም። 

  • “Yahoo, Facebook, Google etc” ሊዘጋ ስለሆነ “ስምዎትን፣ አድራሻዎትን፣ ፓስ ወርዶት ያስመዝግቡ የሚሉ ጥያቄዎችን አለመቀበል፤
  • ለኮምፒተሮት ሁል ጊዜ “አንቲ ቫይረስ” መጠቀም፤
  • ኮምፒውተሮት ያለውን “ፋየር ዎል” መጠቀም፤
  • XXXXXX ሚሊዮን ፓውንድ ሎተሪ አሸናፊ ስለሆኑ አድራሻዎን ይላኩ የሚሉ ቀልደኛ መልእክቶችን ተቀብሎ ምንም አለማድረግ፤
  • ከማያውቁት አድራሻ እና ግለሰብ የተላኩ ኢሜይሎች ከሆኑ አለመክፈት፤ ወዘተለጊዜው ለኮምፒውተሩ ሙያ ካለኝ አናሳ ዕውቀት የታየኝ ይኸው ነው። ባለሙያዎቹ ደግሞ ሊጨምሩበት ይቻላሉ። እንዲህ እንዲህ እያለ ይቀጥላል። ኢንተርኔቱ ያለውን ጥቅም ያህል ጉዳቱም እንዲህ ከፍ ያለ ነው። መቸስ ምን ይደረጋል፤ ሕልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደር።


ቸር ያሰንብተን።


Further Reading:


http://www.arcsight.com/collateral/whitepapers/Ponemon_Cost_of_Cyber_Crime_study_2010.pdf


© ይህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “ሮዝ መጽሔት” ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም። 
(ሮዝ / አዲስ ጉዳይ ቅጽ 5 ቁጥር  84፤ የካቲት 2003 ዓ.ም)

14 comments:

ፍሰሓ በሁሉ said...

እንደ መፍትሔ ተጨማሪ አማራጮች:

1. በተቻለ መጠን የኢ-ሜይል አድራሻ ቁልፍ (password) በተለያየ የጊዜ ወሰን ውስጥ መቀየር፤

2. ገንዘብ ነክ ነገሮችን ሲሊኩ በተቻለ መጠን የምስጢር መረጃዎችን በ የኢ-ሜይል ከመላክ ይልቅ በስልክ ደውሎ መንገር ይመረጣል፤

3. ሌላው ትልቁ ሃብታችን ደግሞ ፊደላችን ስለሆነ መጻፍ ካለብንም ምስጢራዊነት ያላቸውን ነገሮች በአማርኛ መለዋወጡም ከሰለባው ያድናል፤

ተመሳሳይ መልዕክቶች እኔንም ደርሰውኝ ስለነበረ ብዙ ሰዎች በዚህ ጉዳይ ጥንቃቄ ማድረጉ አይከፋም::

የገጠመኝን ለማካፈል ያህል: አንድ ጊዜ የጓደኛዬ አድራሻ ተሰርቆ የእርዳታ ጥያቄ ይደርሰኛል:: የሚገርመው እኔም ጓደኛዬም አንድ መሥሪያ ቤት ነበር የምንሰራው:: እናም በወቅቱ ውጪ ሃገር ያሉ ጓደኞቻችን እርዳታ አሰባስበው ለመላክ በመዘጋጀት ላይ ሳሉ እኔ አስቀድሜ "ጓደኛችን ደህና ነው ተረጋጉ" የሚል መልዕክት ለሁሉም ምላሽ ሰጠሁአቸው:: ስለዚህ ተመሳሳይ አይነት ነገር ሲከሰት በቅርብ ያለን ሰዎች ቶሎ መሃል መግባትና እንዲህ ዓይነት ተንኮሎችን ማፍረስ::
ፍሰሐ

Anonymous said...

Interesting! Thanks For sharing!!!!

Anonymous said...

Really thank you very much for your concern. That is what is expected from the responsible citizen. U shared us great things
Thank you God bless u!

Anonymous said...

የኢንተርኔት ነገር ከተነሳማ ...
ለዓለም አቀፉ መረጃ መረብ ቀዘፋ ቅርብ ነኝ፡፡ ኢንተርኔተን ሁሌም እጠቀማለሁ፤ ከኢሜል ጀምሮ ማኅበራዊ ገጾችን ጨምሮ፡፡ ቪኦኤንም የምከታተለው በኢንተርኔት፤ ያውም በቀጥታ ስርጭት፡፡ እንደተባለው ክፍት ሳደርግ ነበር ታዲያ የሆነውን ያየሁት፣ ቢከብደኝም ያመንኩት፤ ቪኦኤ ተማርኳል፡፡
ከዚህ በታች የማካፍላችሁ ታሪክም ኢንተርኔትን በጥንቃቄ እንድንጠቀምበት የሚያስገነዝብ ይመስለኛል፡፡
1. የረዥም ጊዜ የሰንበት ት/ቤት ወዳጄ ካለፈው ሐምሌ 2002ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ የቅብብሎሽ መልእክት ይልክልኛል፡፡ (Fwd message and link attachment with no subject) የወዳጄ በመሆኑም ደጋግሜ ከፍቼ አንብቤዋለሁ፡፡ የድረ ገጽ አድራሻው የሚመራኝም፣ Canadian Health & Care Mall http://radiantlifechurch.com/images/asw.php ወደሚባል ገጽ ሲሆን ይህ ገጽ 99 በመቶ ኢትዮጵያውያን (የሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግ) ጨርሶ የማይቀበሉትንና በሃይማኖታችንም ሆነ በባሕላችን ቁብ ስለማይቆጠር ወሲብ ቀስቃሽ ክኒን ቫያግራና መሰሎቹ ሊነግረን የሚሞክር ነው፡፡
ጓደኛዬን ግን ስለ ጉዳዩ ጠይቄውም ሆነ ምላሽ ሰጥቼው አላውቅም ምክንያቱም መረጃው በእኔ ዘንድ ሚዛን የሚደፋ አልነበረምና፡፡ ከቆይታ በኋላ ስለጉዳዩ የነገርኩት ቢሆንም ከሌሎችም እንዲህ ዓይነት አስተያየት መስማቱን ገልጾ የምስጢር ቁልፉን (password) በመቀየር ተንፈስ ብሏል፡፡

ባለተራ ሆንኩና በስልክ የተዋወቅሁትና አንድ ቀን ብቻ ያየሁት ሰው፣ የተለዋወጥነው ኢሜይል ሁለት ብቻ ብትሆንም በሶስተኛው በእኔ ስም ጉዳይ አልባ መልእክት ከላይ እንደተገለጸው ዓይነት ደረሰው፡፡ እርሱም ፈጣን ነበርና ይህን ነገር አውቀኸው ነው የላክልኝ ወይስ የምሥጢር ቁልፍህ ተሰርቋል የሚል መልእክት እንዲደርሰኝ አደረገ፡፡ እኔም ከምስጋና ጋር ምላሽ ሰጥቼ የምሥጢር ቁልፌን ቀየርሁት፡፡
2. የሴነጋል የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረ አባቷ በሞት በመለየቱ ምክንያት እንጀራ እናቷ እያሰቃየቻችና በግፍ የአባቷን ሃብት ልትወስድት እንደሆነ አድርጋ ከዚያ መከራ እንዳወጣት አዲት መልከ መልካም ልጅ ጻፈችልኝ፡፡ እውነት ለመናገር የምዕራብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊ ቆንጆ የሚለው የሚገልጻት ይመስለኛል፡፡ መልእክቱ እንደወረደም ባይሆን ሙሉ ስሜቱ የሚከተለው ነው፡፡
“የተወደድክ ሆይ እንደምን ነህ፡፡ አንተን በማግኘቴ የተሰማኝ ደስታ ወሰን የሌለው ከመሆኑም በላይ ከገጠመኝ ከፍተኛ ችግር የምወጣበት መሰላል ስለሆንክ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፡፡ ታሪኬ ባጭሩ የሚከተለው ነው፡፡ አባቴ የሴኔጋል የቀድሞ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ነበር፣ በደረሰበት ሕመም ምክንያት ከሞተ በኋላ እንጀራ እናቴ ያወረሰኝን በርካታ ውድ ስጦታና ገንዘብ ከሌሎች ሃብቶች ጋር ልትወስድብኝ ጥረት እያደረገች ነው፡፡ እዚህ ከአባቴ በስተቀር ሌላ ዘመድ የሌለኝ በመሆኑና የእንጀራ እናቴም ከዘመዶቿ ጋር በመተባበር ልታጠፋኝ እየጣረች ስለሆነ እባክህ ፈጥነህ ድረስልኝ እሽታህንም በአስቸኳይ ግለጽልኝ፡፡” የሚል የመጀመሪያ ኢሜይል ደረሰኝ፡፡ በቀጣዩ ኢሜይል የአባቷ ገንዘብ የሚኝበትን የእግሊዝ አገር ባንክ አድራሻ የሰጠቺኝ ሲሆን የባንክ ሂሳብ ቁጥሩንና የምሥጢር ቁልፉን እርዳታ እያደረጉላት ከሚገኙ መነኩሴ ለመቀበል የሚያስችለኝን አድራሻም ገለጸችልኝ፡፡ ነገር ግን ሂሳቡን ወደእኔ አካውንት ለማስተላለፍ እንዲቻል የባንክ አካውንት መረጃዬን እንድልክላት ጠየቀችኝ፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ እያለሁ ከላይ ለገለጽሁት ጓደኛዬ ኢሜሉንና ፎቶዋን ሳይቀር አሳየሁት፤ እየሳቀ የውልህ ይህቺ ሴት የኢሜሉ ባለቤት አይደለችም፤ እዚህ የተለጠፈችው ለሽፋን ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ውንብድና ባለቤት ከጀርባ ያሉት ናይጄሪያውን ናቸው ብሎኝ አረፈው፡፡ ደግነቱ ለእርሷ ፍጆታ ሊውል የሚችል አካውንት ያልነበረኝ ሲሆን ጥርጣሬዬን ያጎላው ደግሞ የሚኒስትር ልጅ በኢንተርኔት አስጥሉኝ፣ ድረሱልኝ ማለቷ ነበር፡፡

ማጠቃለያ፣ ከላይ የተገለጹት ታሪኮች አጀብ የሚያሰኙ ብቻ አይደሉም፤ ጥልቅ መልእክታቸው የዋዛ አይደለም፡፡ በዋናነት የተፈለገውም መልእክት ማስተላለፍ ነው፡፡
1. በቫያግራ ስም ክፉ ልማድን ወደሰዎች ለቡና ማስረግ፡፡ ከኃጢአት ይልቅ ልማድን ፍራ እንዲሉ ክኒኑ ለአጠቃቀም የተመቸ፣ ሲያዩት የሚያምር፣ ሲወስዱት ፍቱን ዘፍ. 3፥6 እነደሆነ አድርጎ አንደቀል ማለማመድ ነው፡፡ ከዚ በኋላ ራሱ እየተሳበ ወደ ማረጃው እንደሚገባ ጥርጥር የለውምና፡፡ ከዚህ አስልቶ አራጅ፣ አዋራጅ አካሄድ ዛሬውኑ እንጠበቅ፡፡
2. ገንዘብ የተሰረቀ አንድ ሰው ነው፡፡ የሚሰርቁት ግን በቡድን በተደራጀ ስልት ነው፡፡ እንዴት ሰርቼ ሳይሆን እንዴት ሰርቄ ማግኘት እችላለሁን ለብዙኃኑ የማስተማሪያው ቀላሉና ውጤታማው መንገድ ይኸው ነው፡፡

Anonymous said...

ሰው በቆረጠው ልምጭ ሲጠበጠብ ማየት ያስደምማል። ይህ ግን የአሜሪካንን የመከላከያ ሚኒስቴር ብቻ የሚመለከት ነው። ለእኔ ቢጤው ግን መልካም ምክር ነው። ሰነባበተ እንጂ እኔንም አንዱ ሞጭልፍ በዶላር ሊያቀልጠኝ ነበር፤ ወዳጄ ነገሩን በጊዜ ደርሶበት እፎይ አስባለኝ እንጂ የተጠየቁት የዶላር መጠን ጥያቄው በአጓጉል ወቅት ስለነበር አይይይይ....ልቤን ቀጥ ሊያደርገው ነበር።
ወንድሜ የእግዚአብሔር ሰላም ይብዛልህ።

kagnew said...

Dear Ephrem,

You raised a very interesting problem. The internet for me is a filed in which two groups run; one group for knowledge sharing and success, the other for wicked iniquities and evil acts - Abel and Cain. Let me share you my recent experience.

I received the same message on February 2, 2011. Here follows are the message and my reply:

From: -----@yahoo.com
Subject: I need your urgent assistance ASAP!
To: my email address
Date: Monday, February 21, 2011, 9:55 PM

How are you? How is everything with you?. I want to inform you that I came for a program here in London , I have been doing bad financially and in Health ...wise. At this time I'm out of cash and very sick. I was not successful in transferring money on line to my external account before leaving, my attention was urgently needed. Please, I need to pay my bills at the Hotel and also get some drugs for my health. I have contacted my bank for money transfer, but they said nothing can be done because i need to sign some papers before funds can be transferred to me here.

Please, I need you to kindly send me £2300.00 or any amount you can afford for my upkeep, I suggest you send the money today via Western Union Money Transfer with this Information's.

Name:-----
Address:- 39, Marylebone Road . London , NW1 6JQ . United Kingdom .

I promise to refund the money back as soon as i return. I will be waiting to hear from you as soon as possible with the transfer information's including the MTCN number on the receipt so that I can take necessary actions. Am sorry for any inconvenience this may cause you.

With Best Regards,

Name of the individual,

The message seem shocking for an innocent addressee who is ignorant of email Hackers. I just replied in the following way:


Here I am. I really am very sorry for what has happened to you. But, am sorry to tell you that I don't have that much money in my pocket right now. I sent you £1300 via Western Union money transfer. Your secret number is 12191617. For the remaining amount you also may contact other friends. All my best. Kikikikik.

Their reply (here they seem genuine and...):

Dear (my name with my title):

How are you? I hope everything is going on good with your side. Thank you so much for the money you sent, I appreciate your kind assistance, Please can you scan me the receipt for the wire transfer. I need the receipt to claim the money.

Please e-mail me ASAP!

Ur. Sis. in Christ,
Tsehayedingil.

My reply;

Here attached is your transfer of receipt for the wire transfer.
All my best.

What I sent them was in fact a one page Microeconomic problem set. The did not come again. I changed my email password. Dozens of messages and invitations for chats come to my account everyday. The best strategy I think and what I am following is to ignore them.

I really appreciate your concern, and thank your for posting your advice in the blog.

Anonymous said...

Thanks for posting a very interesting issue (problem) on this blog. The internet for me is a field in which two groups run; one group for sharing knowledge, success and blessing and another for wicked inequities and evil acts - the worlds of sons of Abel and sons of Cain. Let me share my recent experience which is related to the point under discussion.

I received the following message on February 2, 2011.

From: <---------@yahoo.com>
Subject: I need your urgent assistance ASAP!
To: my email address
Date: Monday, February 21, 2011, 9:55 PM

How are you? How is everything with you?. I want to inform you that I came for a program here in London , I have been doing bad financially and in Health ...wise. At this time I'm out of cash and very sick. I was not successful in transferring money on line to my external account before leaving, my attention was urgently needed. Please, I need to pay my bills at the Hotel and also get some drugs for my health. I have contacted my bank for money transfer, but they said nothing can be done because i need to sign some papers before funds can be transferred to me here.

Please, I need you to kindly send me £2300.00 or any amount you can afford for my upkeep, I suggest you send the money today via Western Union Money Transfer with this Information's.

Name: ------
Address:- 39, Marylebone Road . London , NW1 6JQ . United Kingdom .

I promise to refund the money back as soon as i return. I will be waiting to hear from you as soon as possible with the transfer information's including the MTCN number on the receipt so that I can take necessary actions. Am sorry for any inconvenience this may cause you.

With Best Regards,

Name of the individual,

The message seem very shocking for anyone who is ignorant of the hacking business. I did not want to decline their request out-rightly. I rather sent them the following reply:

Here I am. I am very sorry for what has happened to you and that you are in a serious problem. However, I am sorry to tell you that I don't have that much money in my pocket right now. I just sent you £1300 via Western Union money transfer. Your secret number is 12191617. For the remaining amount you also may contact other friends. All my best. Kikikikik.

Their reply (here they seem genuine and...):

Dear (my name with my title):

How are you? I hope everything is going on good with your side. Thank you so much for the money you sent, I appreciate your kind assistance, Please can you scan me the receipt for the wire transfer. I need the receipt to claim the money.

Please e-mail me ASAP!

Ur. Sis. in Christ,
Tsehayedingil.

I replied them,

Here attached is your transfer of receipt for the wire transfer. All my best.

What I sent them was in fact a one page advanced Microeconomic problem set. They did not appear again. I immediately changed my email password. Dozens of messages and chat invitations flow to my account everyday. My best strategy so far is to ignore them all. The internet is full of wheat and tare and weeds. Chose the wheat and you will have peace and....

Once again I thank you Dn.Ephrem for showing your concern and posting your advice on this blog.

Kagnew

Anonymous said...

I received the same message from my best friend. However, I forwarded the message to herself and her friend who live in the same city to check if the message was true. She emailed for all people in her address book.

Thank you for sharing

Anonymous said...

Another method to feel secure from internet treats is use the https: protocol. For example, if u want to open www.gmail.com use https://www.gmail.com. https is secure http.

Seble said...

Thank you for sharing.

Buruk said...

ፈቃዳችሁ ከሆነ እኔ በ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቅ እና በዘርፉም የተለያዩ ስራዎችን፣ ስልጠናዎችን ፣ ጥናቶችን፣ መጽሃፍትን አነባለሁ፣ድረ-ገጾችን ወዘተ መከታተል ስራዬ ስለሆነ ልረዳችሁ ፈቃዴን እነሆ ስል ደስ እያለኝ ነው፡፡
ሃሳቦቼንም በጡመራ መድረኬ(ብሎግ) እንድትጎበኙ ይቻላችሁ ዘንድ አድራሻዬን እነሆ
www.burukbubuz.blogspot.com

Anonymous said...

ይህን ጽሑፍ ሳነብ አንድ ነገር አስተወሰኝ እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የምኖረው አንድ አስራአምስት ቀን ይሆነዋል ኢትዮጵያዊ ስም ያለው አንድ የማላቀው ግለሰብ በኢ-ሜል አድራሻዬ እንዲህ የሚል ጽሁፍ ላከልኝ
Hi,
I'm writing this with tears in my eyes, I came down here to Madrid for a short vacation unfortunately I got mugged at the park of the hotel where I lodged,all cash,wallet,credit card, passport and cell were stolen from me, I've been to the Embassy and the Police here but they're not helping issues at all, I was restricted from making use of the hotel phone due to the huge amount of money I am owing, I was given limited access to internet, but I am having problems settling my hotel bills and the hotel manager won't let me leave until I settle the bills,I'm freak out at the moment.I will like you to assist me with a loan of 2,800euros to sort-out my hotel bills and to get myself back home. I will appreciate whatever you can afford to assist me with, I'll Refund the money back to you as soon as I return, let me know if you can be of any help. Please let me know immediately.
ግለሰቡ አውቀው ይሆን የሚል ነገር የፈጠረብኝ ከስሙ ስረ የፃፈው ዩኒቨርስቲ ስም እኔ የተማርኩበት ነው እና በጣም ጭቅላቴን አሰራሁት ግን ማወቅ በፍፁም አላውቀውም ከባለቤቴ ጋር ስለጉዳዩ አወራን ቢሆንም እንደኢትዮጵያዊነቴ የሚሰማኝ ነገር ቢኖርም ወዲያው የምልከው ብር ግን እጄ ላይ አልነበረም ግን አሁነ ይህን ፅሁፍ ሳነብ እንደው ገረመኝ ጥሩ ነገር ነው ኤፍሬም ያሳወከን፡፡

Say Sorry said...

yap,yap ye security issue alemn eysassebe betleyem be technology keftega deregea dersaleche yemtebalewen american chemr? have u heared about the shadowcrew.com..now it's not available down by USS agents u can read on wiki..but..i pretend to be security stuff reader and doier for basic steps who u could stay secure,from my expirence u can see @ dannyhackz.blogspot.com...drop me a line for ur question ...i m starting it..may be it would help be confidence post any security qustion u have?

Anonymous said...

Hellο there! Do youu know if they make аny plugins to
safetuard аgainst hackers? I'm kiոd paranoid about losіng еverything I've worrked hard on.
Any tips?|

My blog post ... pit 2014 program

Blog Archive