Monday, March 7, 2011

አባት ለልጅ ምኑ ነው?

ተረቱ “አባት ሳለ አጊጥ፣ ጀንበር ሳለ እሩጥ” ይላል። ብዙ እናቶች ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ “ኧረ ባክህ አንተ ልጅ፣ ሴት ያሳደገው አታስብለኝ” ይላሉ። ነፍሳቸውን ይማረውና እማማ አስካለም “ኤዲያ፤ ለመውለድ ለመውለድ እበትም ትል ይወልዳል” ይላሉ የማይረቡ አባቶችን ሲተቹ ወይም “አባትን አባት የሚያደርገው ልጅ ለመውለድ ባለው ተፈጥሯዊ ፀጋ ከሴት ማኅፀን ልጅ እንዲገኝ ማድረጉ ብቻ አይደለም” ለማለት ሲፈልጉ። ሌላም ሌላም የአባትን ምንነት የሚያስታውሱ ሥነ ቃሎችን መጥቀስ ይቻላል። እንዲያው ግን አባት ለልጅ ምኑ ነው?

ባለፈው ሳምንት በንባቤ መካከል የ“ኢትዮፒያ ፈርስት www.ethiopiafirst.com” ድረ ገጽ አዘጋጅ/ ኤዲተር አቶ “ቤን” የጦመራትን አንዲት ገጠመኝ አነበብኩ። በአጭሩ ለማስቀመጥ እና በአማርኛ ለመመለስ ያህል ቅዳሜ ፉብሩዋሪ 19/2011 አቶ ቤን ወደ አዲስ አበባ ስታዲዮም ሄዶ ነበር። መግቢያው በር ላይ አንድ አባት እና ልጅ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በፖሊስ ተይዘው ያገኛል። ምን እንደተፈጠረ አባትየውን ይጠይቃል። አባትየውም እንደሚከተው ይተርክለታል።

... አንድ ሌባ ነው የተባለ ሰው ከፖሊስ እየሸሸ ይሮጥ ኖሯል። ወጠምሻ ቢጤ ነው። ፖሊሶች ወደ አባትየው እየተጣሩ ሌባውን እንዲያደናቅፍላቸው ይጠይቃሉ። ሕጻን ልጅ የያዘው አባት፣ ከሌባው ጋር ግብግብ መግጠሙ ለልጁ አደጋ እንደሚሆንበት የተፈጥሮ ደመነፍሱ የነገረችው አባት፣ ልጁን እቅፍ አድርጎ ሊመጣ ከሚችል አደጋ ለመከላከል ይሞክራል።

ሌባም ያመልጣል፤ ፖሊስም ይናደዳል። ከዚያስ ምን አደረገ ጋሽ ፖሊስ? አባትየውን አስሮ ያስቀምጣል። በምን ወንጀል? ሌባውን ለመያዝ ስላልረዳቸው። አቶ ቤን እንደጻፈው ከሆነ ፖሊሶቹ በአባት ለቅሶ መቀለድ ይይዛሉ። ትንሽ ቆይቶም ይፈቱታል። እግር ኳስ ለማየት የመጣው አባት በተፈጠረው ልብ የሚሰብር ድርጊት አዝኖ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ገጠመኙ ተፈፀመ። ...

ያ አቶ “ቤን” በስም ያልጠቀሰው የአዲስ አበባ አባት በዚያን አጋጣሚ ምን ሊሰማው እንደሚችል ለመገመት ሞከርኩ። በእርግጥ አባትም ልጅም ምንም አልሆኑም። አካላዊ ጉዳት አልደረሰባቸውም። በደህና ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። ነገር ግን ክብራቸውስ? አባት በልጁ ፊት መዋረዱስ?

እኔ ራሴ ልጅ አለኝ። እግዚአብሔር ይመስገን። አባት ስለልጁ ምን እንደሚሰማው አውቃለኹ። ራሴን በዚህ አባት ቦታ አስቀምጬ ባስበው አደጋ የሚመጣ መስሎ ከተሰማኝ አስቀድሜ ልጄን ከአደጋው ለመከላከል እንደምሞክር አውቃለኹ። የወላጅነት ተፈጥሮዬ ያንን እንዳደርግ ያስገድደኛል። የተፈጥሮ ሕግ ነው። እግዚአብሔር የፈጠረን እንዲህ አድርጎ ነው። ያ አዲስ አበቤም ያደረገው ይኼንኑ ነው።

የዚያ ታሳሪ ሰው የአባትነት ኃላፊነቱ ልጁን መከላከል ነው እንጂ በማምለጥ ላይ ያለ ወንጀለኛ መከላከል አይደለም። ወንጀለኛውን ማባረርም የፖሊሱ ተግባር ነው። ለዚያ ነው የሰለጠነው። ለዚያ ነው ሕዘቡ ደሞዙን የሚከፍለው። ለዚያ ነው መሣሪያ የታጠቀው። እንጂ ማንኛውንም ተርታ ዜጋ በየመንገዱ እጅ ለማስነሳት አይደለም።

በተለይም በምዕራቡ ዓለም ያለውን የፖሊስ ተግባር ለምንመለከት ሰዎች እንዲህ ዓይነቱ ክብረ-ነክ ተግባር እጅግ ያበሳጫል። ምንም እንኳን የፖሊስ ምግባረ ብልሹነት በየትም ዓለም ያለ ቢሆንም ስለ ሠሩት መጥፎ ድርጊት ያለመጠየቅ፣ ያውም በአደባባይ ዜጋን ማጎሳቆልን እንደመብት የመቁጠር አባዜ እንደ አፍሪካ (እንደ ኢትዮጵያ) የተንሰራፋበት የለም። ፖሊስም ሆነ ማንም “ብረት አንጋች” ያጠፋል፣ ሲያዝ ደግሞ በሕግ ይዳኛል። ሕጉ በትክክል አልዳጅ ሲል ደግሞ ሕዝብ መብቱን ያስከብራል።

የዛሬ 20 ዓመት ገደማ (March 3, 1991) “Rodney King” የተባለ አንድ አፍሪካዊ-አሜሪካዊ በፖሊስ በመደብደቡ ምክንያት በተነሣ ተቃውሞ ሎስ አንጀለስ በእሳት ስትንቀለቀል ተመልክተናል። እሳቱን ያስነሳው የዚያ ጥቁር አሜሪካዊ መደብደብ ብቻ ሳይሆን ጉዳዩን ለመዳኘት የተቀመጠው ፍርድ ቤት ደብዳቢዎቹን ፖሊሶች በነጻ መልቀቁ ነበር። 

በዚህ አጋጣሚ አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ። በ2004 አካባቢ ይመስለኛል። ከመስቀል አደባባይ ወደ  መገናኛ በሚወስደው ጎዳና አካባቢ ባለ ክትፎ ቤት ምሳ ተጋብዤ ሄጄ ነበር። ምሳችንን አጣጥመን ስንወጣ የግንብ አጥሩን ታክኮ ባለ ትልቅ ድንጋይ መሰል የግንቡ አካል ላይ አንድ ፖሊስ ተቀምጧል። አሁን በትክክል ትዝ ባይለኝም በአካባቢው ያሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ለመጠበቅ የቆመ ይመስለኛል። ከፊታችን አንዲት ወጣት መልከ መልካም ልጅ ትጓዛለች። ፖሊሱ ወደ እርሷ ድምጹን ከፍ አድርጎ እየተናገረ ዋዛ ፈዛዛ ያበዛል። የአራዳ ልጆች “ለከፋ” እንደሚሉት በአንድ እጁ ክላሹን ይዞ በቀረው ደግሞ ጣቱን አፉ ውስጥ ከትቶ ያፏጭላታል። መጀመሪያ ገረመኝ። ከዚያ አናደደኝ።

ልጅቱን እንደዚህ ከሚያደርጉ ተተናኳሾች ሊጠብቃት የሚገባው ሰውዬ ራሱ “ተላካፊ” (ልክፍተኛ ልበለው) ሲሆን “ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡታል” የተባለው ዓይነት ነገር ሆነብኝ። በወቅቱ ገና የውጪውን ዓለም ኑሮ እና በሕግ ፊት የሰውን ልጅ ክብር ማየት የጀመርኩበት ወቅት ስለነበረም ሊሆን ይችላል መናደዴን መደበቅ አልቻልኩም ነበር። “ቤን” ያካፈለን ገጠመኝ ከዚህኛው በብዙ ይበልጣል። የቤተሰብ ጉዳይ ስላለበትም ይሆናል የበለጠ በኅሊናዬ የተቀረጸው።

“አንድ ፖሊስ ወይም የተወሰኑ ፖሊሶች እንዲህ ማድረጋቸው በርግጥ ይህንን ያህል መጋነን አለበት?” ብሎ ለሚጠይቅ መልሴ “አዎ አለበት” የሚል ይሆናል። ምክንያቱም ይህ የሚያሳየው ብረት የጨበጡ ሰዎች የሌላ ተርታ ዜጋቸውን መብት የመርገጥ አባዜ ምን ያህል እንደተጠናቀታቸው እንድንመለከት ስለሚያደርገን ነው። የፖሊስ መለዮ በመድፋቱ አንድን ሌላ ኢትዮጵያዊ ለማንገላታት መብት እንዳለው ከተሰማው ነገ ትልቅ ጦር ማዘዝ ሲጀምር በብዙ ኢትዮጵያውያን ላይ ጦር ላለማዝመቱ ምንም ማረጋገጫ የለውም። መጽሐፍ እንደሚል “በጥቂቱ ያልታመነ በብዙው ላይ” እንዴት ይታመናል።

ከሁሉ የሚያሳዝነው አንድን አባት ከፈጣሪ በታች እንደ አድራጊ ፈጣሪ በሚመለከተው ልጁ ፊት ክብሩን ማዋረዳቸው ነው። በርግጥ የአባትየውን ቅስም መስበራቸው ብቻ ሳይሆን የታዳጊውንም ሕጻን ተስፋ መግደላቸውን አልተረዱት ይሆናል። ጨካኝ እና ዘር አጥፊዎች በሚነሱባቸው አገራት ከሚፈፀሙ ጥቃቶች መካከል ብዙ ጊዜ የሚደጋገሙት በልጆች ፊት ወላጆችን ወይም በወላጆች ፊት ልጆችን ማዋረድ ናቸው። ሁለቱም ድርጊቶች ለዘወትር ከልቡና የማይጠፉ ጠባሳዎች ጥለው የማለፍ ችሎታ አላቸው። ለአንድ ትንሽ ልጅ ወላጆቹ ሁሉም ነገሩ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፈርስት ድረ ገጽ አዘጋጅ አቶ ቤን በነካ እጁ ይህንን ጉዳይ ገፋ ቢያደርገው ጥሩ ነበር። በዚያ ክሽን ባለ ካሜራው (የቀረጻቸውን ቪዲዮዎች ከዚህ በፊት እንደተመለከትኩት) ይህንንም ገጠመኝ በካሜራው ይዞት ቢሆን ደግሞ የተሻለ ይሆን ነበር። አሁንም ቢሆን በዚያ ቀን እና ሰዓት በቦታው ተሰማርተው የነበሩት ፖሊሶች ስለሚታወቁ እዚያ ያስነበበንን ገጠመኙን ከዳር አድርሶት መልሱን በድጋሚ ቢያካፍለን ይመሰገን ነበር። ለማንኛውም የአቶ ቤን ጦማር የምትከተለው ነበረች።


Ben's Blog from the Stadium  
Written by Ben  
Saturday, 19 February 2011 21:55
(By: Ben) This afternoon I went to the stadium to watch St. George’s game against Banks. However, I’m not here to blog about the game. For those who care to know the result, St. George won 2 to 0.
At the gate of the stadium, I saw a father holding his son while weeping in helplessness. Since he was apprehended by police, I approached the guy and asked him what really happened. The guy told us the police officers were running after a thief by the time he was walking with his baby son. The cops shouted for the father to intercept the thief (the robber was a big guy). The father, who was scared for his baby’s safety, held tight his son & didn’t confront the robber.
16 comments:

Anonymous said...

Impressive and touchy !!!!!!

Anonymous said...

May GOD bless u.This is actually the biggest problem in Ethiopia.We may not reduce it even.because the police also blame innocent man instead of the thief.Therefore we mustn't let to be continue.Christ be with u!!!

Anonymous said...

ወንድሜ ኤፍሬም ኢትዮጵያ ላይ ይሰውረን ብሎ መማጸን ካልሆነ በቀር ለጊዜው ይሄ መፍትሄ የለውም ክዚህ የከፋ ገጠመኝ ይጠፋል ብለህ ነው

እግዚአብሔር ጥበቃውን ያብዛልን

AD

Anonymous said...

Thank u Dn. Efrem, but the history of most of the police that recruited in the institution are tiff before and they are unethical.

Anonymous said...

እጅግ ልብ የሚነካ አጋጣሚ ነው ሃገራችን ይህቺ ናት እንግዲህ ቀኑን ሙሉ ልብ የሚያደማ ነገር የሚደመጥባት...እግዚአብሄር አንድ ቀን ቀና ያደርገን ይሆናል...እዚህ ጋ የዲያቆን ዳናኤልን አስገራሚ ተስፋ ልጋራ ብዙ ጊዜ በጡመራዉ ምንም በማላይበት ስለዚህች ሃገር ጥሩ ተስፋ ሊያሳየኝ ስለሚሞክር እጽናናበታለሁ::

Anonymous said...

የእኛ ሀገር ፖሊስ (ስርዓት ያላችውን አይመለከትም። ያውስ ካሉ አይደል)። አንዱ ቀልደኛ እንዳለው ውሻን በዱላ ዝሆን ነኝ እንድትል የሚያሳምን ነው። በዱላና በአነገተው ትጥቅ ሰርዓት ከማስጠበቅ ይልቅ ህዝብን በማስፈራራትና በማስጨነቅ የሚኖር ነው። ተኩሶ ጥሎ ቁም የሚል ነው። ምን እንደሚሻል እንጃ። በማህበረሰቡ የሞራል ልእልና (ሞራል አማርኛ አጣሁለት። ያለው ቢያበድረኝ)ሊኖራቸው የሚገቡ ተቋማት እንደ ፖሊስ፤ የእምነት ቤቶች የመሳሰሉት በዘመናችን ባሳፋሪ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። ለእኔ ትልቁ ጥያቄ እንዴ ከዛ ጨዋ ማህበረሰብ እንደነዚህ አይነት ጉዶች ሊወጡ ቻሉ የሚለው ነው።

እስኪ እርሱ ይታረቀን

Anonymous said...

ሰላም ጤና ይስጥልኝ “መርፌ ቢያብጥ በምን ይበጡታል” ይባላል ወይስ "ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡት " ነው የመሚባለው እስኪ አብራራልኝ።

Anonymous said...

አንድ ወዳጄ በአሜሪካ የሚታየው የህግ የበላይነት የተገኘው ጥሩ ህግ፤ ጥሩ ህግ አስከባሪ እና ጥሩ ህግ አክባሪ ህዝብ ስላለ ነው ያለኝን አስታወስከኝ የእኛን አገር ዘረፈ ብዙ ችግረማ ቢያወሩት አሳዛኝ ሆኖ ከዚህም በላይ ብዙ ያስጽፋልም ያስብላልም

Anonymous said...

Bizu Binagerut Hod Bado Yikeral yilala abati simekregn, Ye'Egnan neger tewewu Efrim, gudachin bizu newu. Egzizbihir Yihunen.

Anonymous said...

I think this can happen. But I doubt that Ben has asked the victim because a police who arrested a clean doesnt have the gut to allow others to communicate prey. As usual Ben is writing fiction especially when he is telling us he asked the poor father.

Anonymous said...

ጎበዝ የትኛውም አገር ከሰብአዊነት ጥሰት ነጻ አይደለም፡፡ ልዩነቱ መጠኑ ነው፡፡ ኢትዮጵያን በአሜሪካ ጣሳ እየሰፈሩ እንዲህ ናት አይደለችም ማለት ትንሽ ፍርደገምድልነት ይመስለኛል፡፡

አዎ ኢትዮጵያ በከፋ መልኩ ሰብአዊ መብት ይጣስባታል፣ የፖለቲካ ተቃውሞ እንዲመክን ረቂቅ ማኮላሻ ያለባት አገር ናት፣ በምግብ እጦት ሁሌም በዓለም መድረክ ሳትሳቀቅ የምትለምን ነች፣ አሁን አሁን ደግሞ የበጀት ጉድለትን ለማሟላት የውጭ ድጎማ እንደ መብት የሚጠየቅባትም ነች፡፡ ሌላም ሌላም ...

የኢትዮጵያ ችግር ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ ዛሬ የተጀመረ አልነበረም፡፡ ጥሩ ርዕይ ያለው መሪ ሲመጣ አሳልፋ ሰጥታለች (አፄ ቴዎድሮስ) ኃይለሥላሴን ምንም እንዳልፈየዱ፣ኢምንት አድርጋ እንደምናምን ቆሻሻ ጥላለች፣ የአገር መሪዎችን አርዳ በድኑን ለጅብ ለአሞራ፣ ደሙን ለውሻ ገብራለች፣ በአገር አንድነት ስም እምነት የለሹ ሶሺያሊዝም (ደርግ) ኢትዮጵያን ከፈጣሪ ጋር ያጣላበት መቶ ሺህዎችን በጦርነት እቶን ያቀለጠበት፣ የትውልድ ድልድይን የደረመሰች አገር ናት፣ የዛሬዋ ኢትዮጵያም(ኢሕአዴግ) እኮ ያው ናት፡፡ ማን ከማን ምን ተቀበለ? ብለን ከጠየቅን አገሪቱ በዘመናት ዥረት ውስጥ ግፍና በደልን ስትካንበት ኖራለች፡፡ ስለመንግሥት ስናወራ ማውራት ያለብን ስለአገሪቱ ነው፤ መንግሥትማ ፍጹማዊ፣ ዘላቂ አይደለምና፡፡

ሰብአዊ መብትቶችን ማክበር የሚቻለው ሕዝብ በእውቀት የደረጀ ሲሆን ንቃተ ኅሊናው በተራ የካድሬ ፕሮፖጋንዳ ሳይሆን የማኅበረሰብ መሪዎች በሚባሉ ተቀባይነት ባለቸው ዜጎች እየተመከረ እየታሸ መስመር እንዲይዝ ሲደረግ ነው፡፡ ለዚህ ዓይነቱ መልካም ዜጋ መሠረቱ ደግሞ መልካም ቤተሰብ፣የሃይማኖት ተቋማትያለ ልዩነት ፣መልካም የማኅበረሰብ ወግና ሥርዓት በተወራራሽነት ትውልዱ እንዲታጠቃቸው ሲደረግ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ሲፈተሽ የኢትዮጵያ መሪዎች የተለዩ አይደሉም፣ እንደውም በግፉ ዘመን የተነሱ እንደመሆናቸው የሰቆቃውን ዓይነታ ጨልጠው ጠጥተውታል፣ የጭካኔውንም ዘግናኝነት ተመልክተውታል፤ ግን ደግሞ እርሾ የለምና ያ ሁሉ ተረስቶ የራስን ወይም የጥቂት ልሂቃንን ወይም የጥቂት ፋኖዎችን ሕልውና ለማስጠበቅ ያ ትናንት እነርሱን ለጥቂት የሳታቸውን አጸያፊያዊ የአገዛዝ ስልት እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡

አሜሪካ ዛሬ ዛሬ በሐሰት ቅንብር የተሞላ እየተባለ የሚብጠለጠለውን የ9/11 ጉዳይ ጋር በተያያዘ በሥውር የምታደርገው ተግባር እንደ ጭካኔ አይቆጠርም ከተባለ የሚገርም ነው የሚሆነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ እንኳን አትላንታ ላይ የተፈጠረውን ስናየው የዴሞክራሲ እናት አሜሪካ በገሃድ ከሰብአዊ መብት ጥሰት እንዳልነጻች መረዳት ይቻላል፡፡ ታዲያ የ200ዓመት ዴሞክራሲን ከዜሮ ጋር ማነጻጸር ይቻላል? እንግሊዝ ኢራቅን ለመውረር ያቀረበችው ምክንያት ነጭ ውሸት መሆኑን ያጋለጠው የፓርላማ አባል ዶ/ር ኬሊ በጭካኔ ተገድሎአል፡፡ ዛሬ ድረስ ሞቱን መበቀል እልተቻለም፡፡ የዴሞክራሲ ሀሁ ዎች ከእኛው ፐፑ ጋር ይነጻጸሩ ከተባለ የልጅ ጨዋታ ነው የሚሆነው፥ ቢያንስ በ200ዓመት ይበልጡናልና፡፡

ከዚህ ይልቅ እንደ ዴሞክራሲ ጣኦቶቻችን በተራዘመ የጊዜ ሂደት ዴሞክራሲን ለመገንባት ጥንስሱ ዛሬ መጀመር ያለበት ይመስለኛል፡፡ ያውም በስመ ዴሞክራሲ አሰር ገሰሱን እየጋፈፉ ሕግ፣ መመሪያ፣ ስምምነት፣ መግለጫ በሚል ቅራቅንቦ በመደረት ሳይሆን ኢትዮጵያዊ አስተምህሮን፣ ኢትዮጵያዊ የማኅበረሰብ ወግና ሥርዓት ን፣ የሃይማኖታዊ እሴቶችን ያገናዘበ ከራስ አልፎ ለሌላው የሚተርፍ ሕግ አዘጋጅቶ መመራት ከተቻለ፡፡

በዚህ ረገድ የፖለቲካ ፓርቲዎቻችንና ምሑራን፣ ታዋቂ ዜጎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ለዚህ አዲስ ሥርዓት መፈጠር የመጀመሪያውንና ወሳኙን ኃላፊነት የሚወስዱ ናቸው፡፡ ይሁንና ሁሉም ማለት ይቻላል በዚህ መንገድ ኢትዮጵያን ለመገንባት ሲጥሩ አይታዩም፡፡ አሉ ቢባሉም እንኳን ጠማማውንና የክርክርና የመወጋገዝ ስልት መከተልን በመረጠው አካል የተዋጡ ናቸው፡፡ በተለይም የልሂቃኑና የፖለቲከኞቻችን ነገር እጅግ አስቀያሚና አርአያነት የማይታይበት ነው፤ በሁለት ምክንያት አንደኛ ምሑራን የሚባሉት እነማን እንደሆኑ መለኪያ እስኪጠፋለት ድረስ የግሳንግሱ ጥርቅም ሁሉ የሚጠራበት ድብልቅል በመሆኑ ይህን ክፍል መለየት የሚቻል አልሆነም፡፡ ሁለተኛ የእውቀት ስርጸት አእምሮአቸውን ያላፍታታቸው በመሆኑ ከማኀበረሰብ ምልክትነት ይልቅ ቡድናዊነት፣ግለኝነት የተሞላ የሽኩቻ መስመር የሚከተሉ በመሆኑ ነው፡፡

ስለሆነም ፖሊሱን ሳይሆን ፖሊሱን ያስገኘውን አስከፊ ትብታብ መቆራረጥ መድኃኒቱ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ምሑራንና የፖለቲካ ሰዎቻችን የመሪነት ሚናቸው ተጽዕኖ ሊፈጥር በሚችል የመንግሥትን እኔ ብቻ ባይነት የሚቀናቀን፣ከዚያም ሲያልፍ የሚያንበረክክ ሊሆን ይገባል፡፡

ሰላም ሁሉችን፣ ሰላም ለኢትዮጵያ አገራችን

Anonymous said...

Ato Anonymous minewu aranba ena kobo hone negerih? "ኢትዮጵያን በአሜሪካ ጣሳ እየሰፈሩ እንዲህ ናት አይደለችም ማለት ትንሽ ፍርደገምድልነት ይመስለኛል፡፡"....."አዎ ኢትዮጵያ በከፋ መልኩ ሰብአዊ መብት ይጣስባታል፣ የፖለቲካ ተቃውሞ እንዲመክን ረቂቅ ማኮላሻ ያለባት አገር ናት፣ "......የዴሞክራሲ ሀሁ ዎች ከእኛው ፐፑ ጋር ይነጻጸሩ ከተባለ የልጅ ጨዋታ ነው የሚሆነው፥ ቢያንስ በ200ዓመት ይበልጡናልና፡፡Ena min yitebes?

Anonymous said...

ምንም አይጠበስም፡፡
ዴሞክራሲም ተፈጥሮአዊ እድገት አለው፡፡ በአንድ ጊዜ ማጎልመስ አይቻልም፡፡ ምዕራባውያን የሚጣፍጠውን ዴሞክራሲ እንደ ኬክ ለመግመጥ የብዙ መቶ ዓመታት ጉዞን በመስዋዕትነት ማሳለፋቸውን ልብ በል፡፡ የዛሬዎቹ የብልጽግና ፋኖዎች በቅኝ ግዛትና በሃብት ዘረፋ ብዙ መቶ ሺህ ወገኖቻቸውን መሥዋዕት ገብረዋል፡፡ እኔ እና አንተ በየትኛው ዓለም ብንጓዝ የተዋራጅነት ስሜት የማይፈጠርብን በአድዋ በተሰጠን የነጻነት መንፈስ ነው፡፡

ስለሆነም እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ የሚለው በሃይማኖት ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ ጥረት ሁሉ ይሠራልና ቢቻል የገበያ ግርግር ዓይነት ወቅታዊ ጉዳይን እየተመለከቱ ሳይሆን ዘላቂውን እያሰቡ ሃገራችንን እንዴት እንደምንገነባ በሰከነ መንገድ መተለሙ የተሻለ ይመስለኛል፡፡

ስላም

Anonymous said...

Tadiya bemin melku newu menegager yemichalewu, bezihu aydel???

Anonymous said...

ውድ አነኒመስ (እገሌ)የአሁኑ መልዕክት በጣም ደስ የሚል ነው፡፡ ስክነት ይታይበታል፡፡ ቀደም ባለው ጽሑፍህ ግልፍ ብሎህ መጻፍህን ለመረዳት ብዙም አይከብድም፡፡ ድሮ ልጅ፥ ዘንድሮ አዋቂ ሆነን ብስጭት ስንል ምን ይጠበስን በጾሙም በፍስኩም መጥራታችን ምስክር ነው፡፡

በበኩሌ በጣም የተግባባን ይመስለኛል፡፡ ጸሐፊው በራሱ እይታ ያቀረበልንን ዘገባ እንደወረደ እንድንቀበለው ቢሆን ኖሮ ይህ የአንባቢ አስተያየት አይኖርም ነበር፡፡ በመሆኑም ከእርሱ እይታ ተነስተን የየራሳችንን እንሰጣለን፡፡ ያ ማለት ግን ሁሉም የተዋጣለት ወይም ሁሉም የተጨማለቀ ሃሳብ ነው ብሎ መደምደም አይቻልም፡፡ ስለሆነም ለንባብ የሚጋብዘውን፣ በአሉታዊም ይሁን በአዎንታዊ ይዘት የሚቀርብ የአንባብያን አስተያየትን በመረዳት ሰፋ ያለ ግንዛቤ ማግኘት ይቻላል፡፡ በበኩሌ ከጣማሪው ዘገባ በኋላ ሁልጊዜም የቤተኞቹን ሃሳብ ማንበብና ተጨማሪ ግንዛቤ መያዝ የዘውትር ተግባሬ ነው፡፡ ያንተም እንዲሁ መሆኑን ተገንዝቤአለሁ፡፡

ውድ ታዳሚ፥ ያጣነው፣ በእጅጉ የሚጎድለን ነገር ኢትዮጵያን ባሰብን ቁጥር አገዛዟን ባሰብን ቁጥር እጅግ የምንበልጠው የሚመጣብን ስትራቴጂ ብግነትና ጥላቻ ነው፡፡ ለመሆኑ ተናድደህ በተናገርከው ወይም በፈጸምከው ድርጊት ምን ያህል ጊዜ ተጸጽተህ ታውቃለህ? እኔ የራሴን ግምት ልስጥ ቢያንስ ከአሥር ጊዜ የበለጠ፡፡

የኢትዮጵያ ነገር ሲነሳ ቁጭ ብድግ በሚያደርግ ግንፍልተኝነት ቀረርቶ በሚያሰሙ የፖለቲካ መሪዎችና እነ ምሑር ስሙ በሚደሰኩሩት ብቻ ተቀይደን መጓዝ የለብንም፡፡ ስለኢትዮጵያ ስናስብ ስለተበላው እቁብ (ያለፈውን ጥፋትና ሰቆቃ በማጦዝ) ሳይሆን ስለወደፊቱ (የሁሉም ዜጎች መክበሪያ የምትሆነውን የበለጸገች ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን) መሆን ይገባዋል፡፡ (የማንዴላን ብልሃት እንዘንጋው)

ፖለቲካ የአዲስ አፍቃሪ(የጮሌ)ቋንቋ በሆነበት ዘመን መዋጀትን አንዘንጋ፡፡ በመታገሳችን እንሰክናለን፣ በመተጋገዛችን ከሰንሰለት ይልቅ እንቆራኛለን፡፡ እናም ወንድሜ አትጥፋ፥ በቃላት ሳይሆን በሃሳብ ፍጭት እየተሟረድን ስል የሆነውን በጎ ነገር ለማምጣት እንጣር፡፡

ሰላም

Anonymous said...

Psalms 133

The Blessings of Brotherly Unity
A Song of degrees of David


1 Behold, how good and how pleasant it is

for brethren to dwell together in unity!
2 It is like the precious ointment upon the head,

that ran down upon the beard,
even Aaron's beard:
that went down to the skirts of his garments;
3 as the dew of Hermon,

and as the dew that descended upon the mountains of Zion:
for there the LORD commanded the blessing,
even life for evermore.