Sunday, March 20, 2011

ስለ “ግለሰብ እና ሕዝብ፤ ታሪክ እና ያለፈ ጉዳይ” (Part I)

Sunday, March 20, 2011:- ሰሞኑን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሰፊ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ተመልከቼ ነበር። በተለይም በሊቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ እንዲሁም በጅማ እና አካባቢው ያለውን የሃይማኖት ግጭት በተመለከተ ምን እንዳሉ በስፋት ለመስማት ፈልጌ ነበር። በዩ-ቲዩብ ተቆራረጦ ከተቀመጠው የጠ/ሚኒስትሩ ቃለ ምልልስ ጥያቄና መልስ መካከል ባሰብኩት መልኩ ባይሆንም የ“ቁምነገር” መጽሔት ጋዜጠኛ ያነሣቸው ጥያቄዎች እና አቶ መለስ የሰጧቸው መልሶች ይህንን ጽሑፍ እንዳዘጋጅ ምክንያት ሆኑኝ።


ጥያቄው ለአጼ ኃ/ሥላሴ ሐውልት እንዲቆምላቸው ይደረግ ወይም አይደረግ እንደሆነ የሚያነሣ ሲሆን በመልሳቸው አቶ መለስ ስለ ሐውልት፣ ስለ ሕዝብ እና ግለሰብዕ በሰፊው አትተዋል። “ሐውልት ማቆም ላይ የግሌ አስተያየት በተቻለ መጠን የግለሰቦችን ተክለ ሰውነት በሚያሳይ መልኩ ወይም ያንን በሚያጠናክር መልኩ ባይሆን ይመረጣል” የሚሉት አቶ መለስ “ግለሰቦች አይደሉም ታሪክ የሚሠሩት ሕዝብ ነው ታሪክ የሚሠራው። ስለዚህ የግለሰቦች ሐውልት፣ አንድ ለየት ያለ መልዕክት ለማስተላለፍ ካልሆነ በስተቀር ያንን ግለሰብ በተምሳሌት በመውሰድ ለሕብረተሰቡ አንድ ለየት ያለ መልዕክት ማስተላለፍ የሚችል ካልሆነ በስተቀር የሚመረጥ ጉዳይ አይደለም ብዬ ነው የማምነው” ሲሉ ያትታሉ።

በዚህ አጭር አነጋገር ብዙ ጉዳይ አንሥተዋል፤ ወይም እንዳነሡ ተሰምቶኛል። መቼም ስለ ሐውልት አሁን ለመነጋገር ጊዜው አይደለም። ባይሆን ቅዱስነታቸው ሐውልታቸውን ያቆሙ ሰሞን ጠቅላይ ሚኒስትራችን ይህንን ብለው ቢሆን ኖሮ ሐውልቱን መገንባት የምንቃወምበት አንድ ተጨማሪ “ነጥብ” ይሰጡን ነበር። በትምህርተ-ተዋሕዶ መሠረት የተነገራቸውን እና አልቀበለው ያሉትን፣ ቅ/ሲኖዶስ ከወሰነውም በኋላ አልፈጽመው ያሉት ውሳኔ “ኧረ ጠቅላይ ሚኒስትሩም አይቀበሉትም እባክዎ ቅዱስ አባታችን” ብለን ይሉኝታ ውስጥ እናስገባቸው ነበር። ግን ሳይሆን ቀረ።

በጠ/ሚኒስትሩ አመለካከት ግለሰቦች ሐውልት እንዲቀረጽላቸው ብዙም ፍላጎት የላቸውም። በጣም የተለየ እና “በሐውልት እና በሐውልት ብቻ” ካልሆነ በስተቀር በሌላ መልኩ ሊተላለፍ የማይችል መልእክት ያዘለ ካልሆነ በስተቀር። በሌላ ነገር የማይገለጽ፣ ሐውልት በመቅረጽ ብቻ የሚገለጽ ነገር ምን ሊሆን ይችላል? ለጊዜው አልመጣልኝም።

በዚሁ አጋጣሚ ደግሞ ጠ/ሚኒስትሩ “ግለሰቦች አይደሉም ታሪክ የሚሠሩት ሕዝብ ነው ታሪክ የሚሠራው” ሲሉ ትልቅ ጉዳይ አነሡና አስደመሙኝ። ቃለ ምልልሱን ገታ አድርጌ ከራሴ ጋር ትንሽ ተወያየሁ። ይህንን አባባላቸውን በሌላ አማር ከዚህ በፊትም ሰምቼው አውቃለኹ። ያኔም አልተቀበልኩትም ነበር። ቀላል ሒሳብ ነገር ነው ልበል? “አንድ” የብዙ “ቅንጣት” ነው። ብዙ አንዳንድ-ቅንጣቶች ደግሞ ብዙ መሆናቸው እርግጥ ነው። አንድ ከሌለ ብዙ ከየት ይመጣል? አንድ ሰው ከሌሎች አንድ ሰዎች ጋር ሲደመር ሲደማመር ብዙ አንዶች ይሆናል። ያንን ብዙ ሰዎች ሕዝብ እንበለው። እና ከግለሰብ ወደ ሕዝብ ደረስን ማለትም አይደል? “የምን ፍልስምና ነው?” ለሚለኝ ጥንት ሳይገባኝ ባለፈው “ፊሎዞፊ 101” እኔም የራሴን መሞከሬ ተደርጎ ይወሰድልኝ። ከዚህ በታች ያለውን ሐሳብ ግን በቅጡ ማቅረብ እችላለኹ።

ግለ ሰብዕ ከሌለ ሕዝብ የሚባል ነገር የለም። እኛ ግለሰቦች ነን ሕዝብ የምንሆነው። ግለሰቦች ታሪክ ስንሠራ ሕዝብ ታሪክ ሠራ ሊባል ይችል ይሆናል። ሕዝብ ብቻውን እንኳን ታሪክ ሊሠራ ህልውናም የለው። እኛ ግለሰቦች ነን ለራሳችን የጋራ ስም ስንፈጥር ራሳችንን ሕዝብ ያልነው። ምናልባት በምሥራቁ እና በምዕራቡ ካምፕ የተነሡ የተለያዩ ሊቃውንት “ሕዝብ ይበልጣል፣ ግለሰብ ይበልጣል፤ ሕዝብ ነው ቅድሚያ ማግኘት ያለበት፣ ግለሰብዕ ነው ቅድሚያ ማግኘት” ሲሉ የተከራከሩበት ብዙ ዶሴ ይኖር ይሆናል። ሙያዬም ንባቤም እዚያ ስላላደረሰኝ ያንን መጥቀስ አልቻልኩም። የማንንም “ማርክስ”፣ የማንንም “ሌኒን”፣ የማንንም “ማርቲን ሉተር ኪንግ” ሳልጠቅስ ለባዊት ነፍሴ የነገረችኝንና እኔም ትርጉም የሰጠኝን “እንደወረደ” እጽፋለኹ።

አገር የሚለውጥ፣ የታሪክ ሒደት የሚቀይረው ግለሰብዕ ነው። ዓለማችን በዚህ በኩል ሊጠቀሱ የሚችሉ ብዙ አብነቶች ስላሏት ብዙም የሚያስቸግር አይሆንም። ጥያቄው ሰዎቹ በዚያ በፈፀሙት ድርጊት ውስጥ ያላቸው ቦታ ነው። ለምሳሌ አቴዎድሮስን እናንሣ። ለእርሳቸው እዚያ መድረስ የጓደኞቻቸው እና የወታደሮቻቸው አስተዋጽዖ የሚካድ ባይሆንም ካሣ ባይነሡ ኖሮ ቴዎድሮስ የሚባል ንጉሥ ይኖር ነበር? በካሣ ቴዎድሮስነት ውስጥ የካሣ የብቻቸው ድርሻ ምን ያህል ፐርሰንት ነው? አጼ ክ አድዋ ላይ ጣሊያንን ድል ሲነሱ የእርሳቸው በዚያች የታሪክ አጋጣሚ ንጉሥ መሆን ለድሉ አስተዋጽዖ ነበረው ወይስ አልነበረውም? ንጉሡ ማንም ይሁን ማን “ሕዝቡ” እስካለ ድረስ ጣሊያን በአድዋ ድል መሆኑ አይቀሬ ነበር? አስተዋዩዋ ጣይቱ ባይኖሩ የሚቀየር የታሪክ ውጤት አይኖርም ነበር? ሌላውን ሁሉ ብንተወው ኢሕአዴግ ያለ መለስ ዜናዊ አሁን ያለውን ኢሕአዴግ ይሆን ነበር?
 ከላይ ላነሣኋቸው ጥያቄዎች ሁሉ መልሴ አይሆንም ነው። ካሣ ኃይሉ ራሱን አጼ ቴዎድሮስ አድርጓል። ምኒክ እና ጣይቱ ባይኖሩ አድዋ አሁን እንደምንኮራበት ላይሆን ይችል ነበር። መለስም ባይኖሩ ኖሮ ኢሕአዴግ አሁን ባለው መልኩ ላናገኘው እንችል ነበር። ያለ መንግሥቱ ኃ/ማርያም “ደርግ” ከኮሚቴነቱ አልፎ ለ17 ዓመታት የዘለቀ መንግሥት መሆን አይችልም ነበር።

ምኖርበት የምዕራቡ ዓለም የአስተሳሰባቸው እና የዕድገታቸው መሠረቱ ግለሰባዊ የማሰብ ነጻነታቸው እና የግለሰቦች ከፍ ያለ የፈጠራ ምንጭ መሆኑን እንድረዳ አድርጎኛል። የጥንቱን የፍልስፍና እና የቴክኖሎጂ ዓለም እና ግለሰቦች ያመጡትን ለውጥ መጥቀስ እንኳን ብንተው ባለፉት 10 ዓመታት የዓለምን የቴክኖሎጂ አስተሳሰብ የለወጡትን ግኝቶች ብንመለከት ለውጦቹ የመጡት በጥቂት ግለሰቦች ፈጠራ መሆኑን እንረዳለን።

ማይክሮሶፍት የተመሠረተው በኮሚቴ አይደለም። የ“ኮሎጅ ድሮፕ አውቱ” (የኮሌጅ ትምህርቱን ያቋረጠው) የቢል ጌትስ አዕምሮ ማይክሮሶፍትን ፈጠረ። ጓደኛው ስቲቭ ጃብስ (Steven Paul Jobs) አፕል/ App ኩባንያን እና ዓለምን ያስደነቁትን የአይፎን/ አይ.ፓድ ውጤቶች አመጣ። ለግላጋው ወጣት ማርክ ሱከርበርግ ፌስቡክን አስገኘ፣ ጓደኛሞቹ ሰርጌይ ብሪን እና ላሪ ፔጅ (Sergey Brin and Larry Page) ጉግልን ፈጠሩ። ሁሉም የግለሰቦች ውጤት እንጂ ሕዝብ የምንለው ነገር ውጤት አይደሉም።
ጓደኛሞቹ ሰርጌይ ብሪን እና ላሪ ፔጅ
የምዕራቡን ዓለም ትተን ወዳገራችን አስተምህሮ ብንመጣ እና የጥንታዊቱን ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ በወፍ በረር ብንመለከት የቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት እና የፍልስፍና መዋቅር በግለሰቦች ዙሪያ የሚያጠነጥን ሆኖ እናገኘዋለን። ጥንታዊው የኢትዮጵያ ትምህርት በመምህራኑ ማንነት ላይ የተመሠረተ ነው። መምህሩ ባሉበት ትምህርት ቤቱ አለ። መምህሩ በምንም ምክንያት ይሁን በዚያ አካባቢ ሊኖሩ የማይችሉበት ሁኔታ ቢፈጠር ተማሪዎቹ እና ት/ቤቱም አይኖሩም። “ወንበሩ” በመምህሩ ማንነት ላይ የተመሠረተ ነው።

በሌላ ምሳሌ ቅ/ያሬድ ባይኖር አሁን የምናውቀው ጥንታዊ የኢትዮጵያ ዜማ አይኖርም። የአቡነ ተ/ሃይማኖት መነሣት ባይኖር ክርስትና በመካከለኛው እና በደቡብ ኢትዮጵያ አሁን ባለው መልክ ላይገኝ ይችል ነበር። በመካከለኛው ዘመን ያለውን ታሪካችንን ስንቃኝ እንኳን “አህመድ ኢብን ኢብራሒም አል ጋዚ” ወይም በተለምዶ እንደምናውቀው አህመድ ግራኝ ባይነሣ ኖሮ አሁን በምሥራቅ አፍሪካ እና በኢትዮጵያ ያለው ዓይነት የእምነቶች ሚዛን አይፈጠርም ነበር።

አገር እንዲያድግ ከተፈለገ ሰዎች በግላቸው ያላቸው የማሰብ፣ የመፍጠር እና ራሳቸውን የመሆን ነጻነታቸው ሊጠበቅላቸው እና ሊከበርላቸው ይገባል። ሕዝብ በሚባለው ግዑዝ ፍጥረት ስም ግለሰብዕነት ከተጨፈለቀ ራሱ ሕዝብ የሚባለው ነገር ይጨፈለቃል። የምሥራቁ የኮሚኒስት ዓለም ለመፈረካከሱ የተለያዩ ሙያዊ አንድምታዎች እና የአሜሪካ እና የምዕራቡ ዓለም ሴራ ቢሰጡም ቢጠቀሱም ዋናው ምክንያቱ ግን ኢ-ተፈጥሯዊ የሆነው “ግለሰብዕነትን” የመጨፍለቅ መመሪያው ይመስለኛል።

ሁሉንም ነገር ልክ እንደ ጠጅ ብርሌ፣ እንደ አህያ ልጅ መልክ የማመሳሰል ፍልስፍናው አልተሳካለትም። በአገራችንም ከልብስ አቅም እንኳን የተለያየ ልብስ መልበስ ቁምነገር ሆኖ ሁሉ ካኪ ካልለበሰ በሚለው አባዜ ብዙ ችግር ተፈጥሮ ነበር። ሁሉ እንደ “ሃይ ስኩል” ተማሪ አንድ ዓይነት ካኪ ለብሶ ሲቸገር ማየት አስቂኝ አጋጣሚ ነበር። ይህ ሁሉ ግለሰባዊ ማንነትን ያለመቀበል ነገር ነው።

ይሁን እንጂ ሥነ ተፈጥሮ የሚያስተምረን ከዚህ ተቃራኒ ነው። አንድ አዳም አስቀድሞ ተፈጠረ፤ ከዚያም ብዙ አዳሞች መጡ። የአዳሞችን መብት ለማክበር ቀላሉ መንገድ አዳምን ማክበር ነው። ለአዳሞች (ለአዳሜ) ተብሎ የአንዱ የአዳም ፍላጎት መጨፍለቅ የለበትም። ለዚህ ነው ጠ/ሚኒስትሩ “ታሪክ ሰሪው ሕዝብ እንጂ ግለሰብ አይደለም” ሲሉ የማልቀበላቸው። ይህ አስተያየታቸው በማያሻ መልኩ ስሑት መሆኑ የታየው የምሥራቁ ካምፕ አስተሳሰብ ቅጣይ ነው።

(ይቀጥላል)

26 comments:

Anonymous said...

Nice observation Epherem!!!

abebe said...

ተመችቶኛል

ኤርሚያስ said...

ግሩም የትዝብት ቅኝት ነው። የህዝብ ፍቅርና አክብሮት ይሆን እንዲያ ያስባላቸው ወይስ ለሳቸው ይቁም ስላልተባለ ምቀኝነት ይሆን? ለዚህ አይደል በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ ተብሎ ፈሊጡ የተፈለጠው። ሌላው ደግሞ በታሪክ እንደሰማሁት አጼ ሃይለስላሴ በብዙ ቁጥር ስሌታዊና ህዝባዊ ቋንቋ ይናገሩ እንደነበር ረስተውት ይሆን? ወይስ አያውቁም።ወይስ ለራሳቸው ያላቸው ግለሰባዊ ዋጋ ተመንን ዝቅ አድርገውት ይሆን?....

Anonymous said...

Yiketil bilenal,
Entebikalen

Anonymous said...

BELELA NEGER YEMAYIGELTS HAWILT BEMEQIRETS BICHA YEMIGLETS NEGER MIN ALE? :- 1. YEQERATSIW CHILOTA
2. HAWILT YEMEQRETS FILAGOT.

Anonymous said...

አይ ሕዝቡ!

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የ1993 የኢሕአዴግ ሱናሚ ጥቅል ጥፋት ያላደረሰው ለምን ይመስልዎታል? ሕዝቡ የሚሉት ስለነበር አይደለም፥ እርስዎ የሚበልጠውን ሕዝብ ጥቂቶችን በሚቃወምበት መንገድ ጠምዝዘው መንዳት ስለቻሉ ነበር፡፡ ያንን አስቸጋሪ ወቅት ለማለፍ የእርስዎ መኖር ተገቢ አልነበርም ብሎ መደምደም ይቻላል?

እርስዎም እንደደርግ እንደ ሶሺያሊዝም ታሪክ ሰሪው ሰፊው ሕዝብ ነው እያሉን ነው፡፡ እነዚያ በምናብ ርዕዮት ሲዳጭሩ በመኖራቸው የግለሰብ ማንነትን ጨርሶ እንዘጭ አድርገው አውርደው ነበር፤ የራሳቸውን ግን ከቀበሌ ጽ/ቤት ጀምሮ በቢል ቦርድና በሐውልት ሳይቀር ቀርጸዋል፡፡

እርግጥ እርስዎም ሲጀማምሩ አልባንያ ምናምን እያሉ በሶሺያሊዝም ጥግ ጥግ እተራመዱ እንደነበር የሩቅ ትዝታ አይደለም፡፡ ምናልባት ሕዝብ የሚሉት አባዜ የተጠናወተዎ ሶሻሊዝም እንደኩፍኝ ነቅሎ ስላልወጣልዎ ይመስላል፡፡ ሕገ መንግሥቱ ሳይቀር ሕዝቡ የሚለውን አጠራር የቡድን መብት እያለ ሶሺያሊዝምን በሾርኒ እያራመደ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡

መሪ፣ ጀግና ከሌለ እኮ ታሪክ አይኖርም፡፡ አንድ ሁለት ምሳሌ ላቅርብ፥

ኢትዮጵያ የማራቶን አገር፣ በማራቶን ታሪክ የሰራች እየተባለች የምትሞካሸው አገራችን፥ ታሪኩ ገለጥ ተደርጎ ሲነበብ እኮ የሚያወራው ስለሻምበል አበበ ቢቂላ ጀግንነት ነው፡፡ የእርሱ ባዶ እግር የሻምበል ማሞ ወልዴ ተተኪነት ባይኖር እኰ ኢትዮጵያ የማራቶን ታሪክ አይኖራትም፡፡ ስለሞስኮ፣ ስለባርሴሎና፣ ስለሲድኒ፣ ስለቤዢንግ ኦሎምፒኮች ስናወራ የምናወራው ስለጀግኖቹ ሻምበል ምሩፅ ይፈጠር፣ ስለሻለቃ ደራርቱ ቱሉ፣ስለሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ፣ ስለመሠረት ደፋር፣ ስለጥሩነሽ ዲባባ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ የጀግኖች አትሌቶች ታሪክ ነው፡፡

ይኸው የሕወሃት ታሪክ የመለስ ዜናዊ ታሪክ እየሆነ አይደለም እንዴ? ኮራንብህ፣ ብልሁ፣ አስተዋዩ መሪያችን እየተባሉ እይደለም? ከ2002 ምርጫ ጀምሮ ደግሞ በፎቶዎች የምናቀው ምስልዎ ግዘፍ እየነሳ ወደትልልቅ ባነርነትና ቢልቦርድነት እየተቀየረ ነው፡፡ ነገ ደግሞ ሐውልት ይቀረጽልዎታል፡፡ በበኩሌ እስማማለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ የራስዎ የሆነ አዎንታዊም አሉታዊም ድርሻ አለዎና፡፡

እንደው ሌላው ይቅር ምርጫ 97 የሕዝብ ሱናሚ ቤተመንግሥቱን ሲያርደው፣ ከምርጫው በኋላ በሽንፈት ኢሕአዴግን ሲያርበደብደው የርስዎ ብልጠት የተሞላበት ታክቲክ ከፀሐይ በታች የማንደራደርበትና የማንስማማበት አንዳች ነጥብ የለም በሚል ስልት ሙጃ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አጭዶ ባይከመራቸው ኢሕአዴግ የሚል ግንባር ቀርቶ ከንፈር ማየት ይቻላል?

ታሪክ ሰሪው ማነው? ሕዝብ አይበሉ፥ ካሉም ከሕገ መንግሥቱ የቡድን መብት አንቀጽ ጋር እንዳይጣረስ ነው፡፡

ከዚያ ውጪ ታሪክ ሰሪው የታሪክ ዕድል በእጁ የወደቀችለት ጀግና ግለሰብ ነው፡፡ ያ ግለሰብ የሚያስጨበጭብ ወይም የሚያሸማቅቅ ታሪክ ሊሠራ ይችላል፡፡ ግን ታሪክ ነው በትውልድ ጅረት ውስጥ ሲፈስ ይኖራል፡፡

እናም ሕዝብ ታሪክ አይሠራም፣ የታሪክ ሱታፌ ግን ይኖረዋል፡፡ አፄ ምኒልክ በብዙ መቶ ሺህ ሕዝቦች ተጋድሎ እንዳሸነፉት፣ ሕወሃት በብዙ መቶ ሺህ ተጋዳላይ ለድል እንደበቃው

አበቃሁ፡፡

መብሩድ said...

ከማኅበረ ቅዱሳን ጀርባ አቡነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ ትዝ የሚሉኝ ለዚ ይሆን እንዴ?

Anonymous said...

"መለስም ባይኖሩ ኖሮ ኢሕአዴግ አሁን ባለው መልኩ ላናገኘው እንችል ነበር።" ምን ማለት ነው?

"ያለ መንግሥቱ ኃ/ማርያም “ደርግ” ከኮሚቴነቱ አልፎ ለ17 ዓመታት የዘለቀ መንግሥት መሆን አይችልም ነበር።" .... ማን ነው ይህን ያለው? እሰኪ ደግመህ አስብበት። አንድ ስቦ አንድ አስቦ...ሲባል መቼም ሳትሰማ የቀረህ አይመስለኝም።

ቸር ያሰንብተን

Anonymous said...

ወንድሜ "አንድ ስቦ አንድ አስቦ" ያልከው፣

መለስ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የሚለውን ሕወሃት ለ17ዓመታት የተጠቀመበትን ሃሳብን የማንሸራሸርና ውሣኔን የመወሰን አሠራር ወደጎን ብለው ግለሰባዊ ብቃታቸውን ተጠቅመው ተጽዕኖ ባይፈጥሩ ኖሮ በእነ ገብሩ አስራትና ሥዬ አብርሃ፣ ጻድቃንና አረጋሽ የማመራው ቡድን ኢሕአዴግን አሁን ባለው ቅርጹ እንዲቆይ ሊያደርጉት አይችሉም፡፡ ምክንያት ❶ ሌላ የተሻለና የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ፍላጎት የሚያረካ አደረጃጀት እንዲኖረው በማድረግ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በኢሕአዴግና በሌሎች ፓርቲዎች ጤናማ ፉክክር ላይ ተመሥርቶ አገሪቱ ሚዛን የጠበቀ የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ መግባት እንድትችል ያደርጋታል፡፡ ❷ ከመለስም በባሰ ከብሔርም ወርዶ በወንዜነት ታጥሮ አገዛዙ አሁን ካለውም በከፋ የብዙኃኑን ኢትዮጵያዊ ተቃውሞ ማስተናገድ የግድ ይለው ነበር፡፡ ❸ ኢሕአዴግ በሕወሃት የበላይነት አጭቆ ጠርቅቆ የያዛቸው አጋሮች መፈናፈኛ መንገድ በማግኘታቸው የሚያደርጉት የመዋዋጥ ትግል ሌላ የአለመረጋጋትና የሲቪል ጦርነትን ሊያስከትል ይችል ነበር ባይ ነኝ፡፡

ስለ ስለመንግሥቱ ኃይለማርያምም "ማነው እንዲህ ያለው?" የሚል ጥያቄ አንስተሃል፡፡ የእኛ የኢትዮጵያውያን መሠረታው ችግር ብቻም አደለም ትልቁ በሽታ ይኸው መረጃን ከተማራማሪ፣ ከታወቀ ግለሰብ(ከፕሮፌሰር ወይም ዶ/ር እገሌ) ብቻ መጠበቅ፡፡ ጸሐፊው ከረዥም ዘመን የንባብ ልማዱ ወይም በጉዳዩ ላይ ካጠራቀመው ግንዛቤ ተነስቶ ደርግ ከመንግሥቱ ወጪ መንግሥት መሆን አይቻለውም ማለት ይችላል፡፡ በጉዳዩ ላይ ቅሬታ ካለን በምን በምን ምክንያቶች በሚል ተጠየቃዊ ሙግትህ ወጥሮ መያዝ ነው፡፡፡ አንተ ግን አላደረግኸውም ከዚያ ይልቅ የግለሰብ አስረጅነትን የፈለግህ ይመስላል፡፡ ግለሰቦች በቅርበታቸው ወይም በቅሬታቸው ወይም በገለልተኝነታቸው ምክንያት የታሪክ ልኬታን ሊያዛቡ አይችሉም ብለህ ፍጹማዊነታቸውን የምታምን ነህ?

መንግሥቱ የታሪክ ባለተራ ሆኖ አጭዶ በመከመር ለአሳፋሪው የታሪክ ዘውግ የተመረጠ ባለፍዳ (ተወቃሽ) መሪ ነው ከዚያ ውጪ በሆነ መንገድ ከኰሚቴነት ያለፈ ሥልጣን ይኖረዋል ብዬ እኔም አልጠብቅም፡፡

እናም ዘይቤው እንዲህ ዓይነት ነጻ የሃሳብ ሽርሽርና ፍጭት ለሚካሄድበት አቀራረብ ተዛምዶ ያለው አልመሰለኝም

ከአክብሮት ጋር

Anonymous said...

I realy like your comment አንድ አዳም አስቀድሞ ተፈጠረ፤ ከዚያም ብዙ አዳሞች መጡ። የአዳሞችን መብት ለማክበር ቀላሉ መንገድ አዳምን ማክበር ነው። ለአዳሞች (ለአዳሜ) ተብሎ የአንዱ የአዳም ፍላጎት መጨፍለቅ የለበትም።
Demissie

123... said...

When we respect individuals right, the mass right will be respected by defult.In this modern world individuals are history makers.
Thank you Ephi.

Anonymous said...

Ethiopian Endih siweyayu endit dessssssssssss yilal??????? God Bless Ethiopia &Ethiopian

Getachew said...

ይህንን የ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ቃለ ምልልስ በቀጥታ በ ETV አይቼዋለሁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ አፄ ኃይለሰላሰም ቀብር በ አግባቡ አለመደረጉ ሲጠየቁ
''ሲሞቱ በ ንጉስነት ክብር ላይ ስላልነበሩ አንደማንኛውም ሰው ነበር አሟሟታቸው ----ከመሞታቸው በፊት ከ ንግሥናቸው መውረዳቸውን ደርግ አሳውቆ ነበር-----አና ከብራቸው አንደማንም ሰው ተፈፅሟል'' የሚል ነበር ባለፈው ወር ''ታይም'' መፅሄት በ ዓለም ላይ በ ክፍለ ዘመኑ ከነበሩት አይኮን መሪዎች አንዱ ብሎ የመረጣቸው ሲሞቱ ከ ንጉስነት መውረዳቸውን ደርግ ማወጁን አልሰማ ይሆን? በ ተዘዋዋሪ የደርግ ድርጊት አንደ መከራከርያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀረቡት ማለት ነው አንዴ? የ ቀድሞው ንጉስ ተብለው በክብር መከበርም ሆነ ሃውልት ሊሰራላቸው አይችልም ማለት ነው? ቀጥለውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ '' የንጉሡ አድናቂዎች ሃውልት ሲሰሩ ዋና የ ሕዝብ አደባባይ መጠቀም አይችሉም'' ምክንያቱም አንደ አቶ መለስ አባባል '' የ ንጉሱን ተቃዋሚዎች አንዳያስቀይሙ'' ብለዋል። ማንኛውም ሃውልት አኮ ደጋፊም ተቃዋሚም አለው።የ አፄ ምኒልክን ሃውልት የ ጣልያን መንግስት አንድደግፈው ይጠበቃል? ሀውልቱ ግን የ አድዋን ድል አያበሰረ ይሄው አለ።የምአስገርመው ግን አፄ ሃይለስላሴ ዛሬም ትውልድ ተሻግረው የ ሀገር ''አይኮን'' ሆነው የ አመለካከት መለክያ ሲሆኑ ብዙ ነገር አንድንታዘብ ያረጋል።

Solomon Getachew said...

በእርግጥ ጠ/ሚኒስትር መለስ ጥሩ ብለዋል ፡፡ ግን ክቡርነታተቸው ታዲያ ምነው ህዝብ ይፍረስ ያለው የአቡኑንስ ሀውልት ???

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !!!

Anonymous said...

ወንድሜ „"አንድ ስቦ አንድ አስቦ" ያልከው „ ላልከው ወንድሜ፤
አሁንም እኔ „አንድ ስቦ አንድ አስቦ አይሆንም“ እላለው ። መቼም በአቶ መለስብቻ (ብቻቸውን) እነ ገብሩ፣ ስዬ ፣ ጻድቃንና አረጋሽ እምቅ እንቅ አድርገው ኃይል አልባ ተደረጉ ብለህ አስበህ ከሆነ እንደው የዋህነት ነው ። ለምን? ብትል የአቶ መለስ ኃይል እነዚያን ተርብ የነበሩ ሰዎችን ልክ ለማሳያ አይበቃም ነበርና። ሌላ አንተ አንድ ሁለት እያልክ ያስቀመጥከው ነጥብ ከሰጠሁት ሃሳቤ ጋር ምንም ሰለማይገናኝ ምንም አልልም። ምክንያት፦ እነ ገብሩና ስዬ የተሻሉ ወይንም የሚብሱ ይሆኑ ነበር ወደሚለው መላምት እንደአንተ መግባት ስለማልፈልግ።
ሰለ መንግሥቱ ኃይለማርያምም "ማነው እንዲህ ያለው?" ያለኩት መንግስቱ ባይኖሩ …እንዲ ይሆን ነበር ብሎ ዲ/ን ኤፍሬም ላለው እንዴት እሳቸው ብቻቸውን እንዲ ሰሩ እንዲ ፈጠሩ ማለት ይቻላል ለማለት እንጂ አንተ እንዳሰብከው ፕ/ሮ ወይንም ዶ/ር ካላለ የሚል አባዜ የለኝም። የጹሁፉ ባለቤትማ ዲ/ን ኤፍሬም መሆኑ ግልጽ እኮነው። አይደለም እንዴ?!
በድጋሚ አንድ ሰው ብቻውን አጋዝ ተባባሪ ካሌለው ምንም አይፋጥርም። አንድ ብቻውን ታሪክ የሚሰራ፣ የሚለውጥ አምላክ ብቻ ነው።
ሳስብው ወንድሜ ሃሳቤ ን በደንብ የተርዳህልኝ አይመስለኝም። ለማንኘውም ስለ አስተያየትህ አመሰግናለው።
ጥያቄህ፦ “ግለሰቦች በቅርበታቸው ወይም በቅሬታቸው ወይም በገለልተኝነታቸው ምክንያት የታሪክ ልኬታን ሊያዛቡ አይችሉም ብለህ ፍጹማዊነታቸውን የምታምን ነህ? „ አልገባኝም።

ቸር ያሰማን

Anonymous said...

ወንድሜ ኤፍሬም ሰላምታዬ ይድረስህ እንደው እንደዋዛ ባህሪያችን ተረሳህ መሰለኝ? ለመሆኑ ይሉኝታ የሚይዘን ቢሆን ኖሮማ ስንት ከይሉኝታ ያለፈ አንገት የሚያስደፋ ለዓመታት የጋዜጦች መቀለጃ ያደረጉን ጉዳዮች ነበሩ አይደል እንደው በቀላሉ ይሉኝታ የሚይዘው ፈጣሪውን የሚያስብ ማን ነው ብለህ

ከአቡዳቢ

Anonymous said...

heey
We are expecting part II soon.
Ke kanadaw wedajih

Ameha said...

ወንድሜ ዲ/ን ኤፍሬም! ትዝብትህ እና ትንታኔህ አስደስቶኛል። ሰዉ ሊነካው የማይደፍረውን ጉዳይ አንስተህ የግልህን አስተሳሰብ አስፍረሃል። ጥሩ ጅማሮ ነው። እንደ አቶ መለስ አገላለጽ ለዚህ አስተያየትህ መመስገን የሚገባው ሕዝቡ እንጂ አንተ አይደለህም አይደል?
"ለአፄ ኃይለሥላሴ ሐውልት ይሠራላቸው/አይሠራላቸው?" የኔ የግሌ አስተያየት ሐውልት ሊያሠራ የሚችል ምን የተለየ ተግባር ኖሯቸው ነው? ገና ለገና ንጉሥ ስለተባሉ? ሕዝቡ ፋሺስት ጣሊያንን ሲዋጋ እሳቸው ከአገር ስለፈረጠጡ? አገራችን በጣሊያን መንግሥት ተወራለች ብለው የመንግሥታቱ ጉባዔ ላይ ስለተናገሩ? ብዙ ሕዝብ የሳቸውን ግፍ አያውቀውም። አንዳንድ ጊዜ "እግዚአብሔር የሥራቸውን አይቶ ነው ሽንት ቤት ሥር የቀበራቸው" እላለሁ። ብዙዎቻችሁ ሰምታችሁትም ይሁን አልሰማችሁትም እርግጠኛ ባልሆንም እሳቸው ከሥልጣን ከመውረዳቸው በፊት "ቢሸፍቱ ሐይቅ ቢሄዱ ኖሮ ያ የሚገብሩለት ነገር ያድናቸው ነበር" እየተባለ ያን ጊዜ ይነገር እንደነበረ አስታውሳለሁ። ለዛ ለተባለው ሐይቅ ስንት ቅንድቡ የገጠመ ወገናችን ለግብር ቀረበ? ወደ ወንዝና ወደ ሐይቅ የሚሮጠው ምን ወይም ማንን ፍለጋ ይሆን? የሚያም ብዙ ነገር አለ። ለዚህ አስተያየቴ የሚሰጠኝን ውርጅብኝ በፀጋ እቀበለዋለሁ።

የአንተን አስተሳሰብ የሚደግፍም ሆነ የማይደግፍ ወገን ሊያበረታታህም ሆነ ሊነቅፍህ እንደሚችል ይረዳኛል። በዚህ መልኩ ሀሳብን በግልጽ አስቀምጦ የመተንተን ባሕል በህብረተሰባችን ውስጥ ያልተለመደ በመሆኑ "ተነካን" የሚሉ አካሎች በጭብጥ ላይ ያልተመሠረተ ተቃውሞ ሊያነሱብህ እንደሚችሉ ግልጽ ነው። በዚህ አጋጣሚ እነዚህ ወገኖች በጭብጥ ላይ የተመሠረተ ወይም መሠረት ያለው አስተያየት /ተቃውሞ/ ቢያቀርቡ ለሁላችንም ትምህርት ይሆናል ብዬ አምናለሁ። ይህ መድረክ የመማማሪያ መድረክ ነው ብዬ ስለማምን። ነገር ግን ሰው ሊገልጸው የፈለገውን ነገር በቅጡ ሳይረዱ "እንዲህ ስለሆነ ነው፣ እንዲህ አስቦ ነው...ወዘተ" እያሉ ሰውን መኮነን (labeling) የኋላቀርነት ምልክት እንጂ የጤና አይደለም። ለሁላችንም አስተዋይ ልቡና ይስጠን

The Architect said...

ህዝቡ ይህን መሰል ጽሑፍ ስላሰነበበን እናመሰግነዋለን፡፡ የሚጽፈው ግለሰብ አይደለም! ሕዝብ እንጂ ! ቂቂቂቂቂ…

Anonymous said...

Your philosophy doesn't work. It is not revealed to you the different between the role of leader and subordnates.

Anonymous said...

great article.God keep u safe

aklilu said...

ጥሩ እይታ ነው ወንድም ኤፍሬም። አምናለሁ አለምን የቀየሩ ታላላቅ ሰዎችን ታሪክ ስናጤን ግለሰቦች ቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ። ነገር ግን አንድ ነገር ሊገባህ ይገባል ማንም ከራሱ ተነስቶ አያውቅም፣ ማንም ከራሱ ተነስቶ አይፈጥርም፣ ማንም ከራሱ ተነስቶ
አይፈላሰፍም። የሰው ልጂ አዕምሮ ምትሐታዊ ነው አንተ ያሰብከውን ነገር በዚያችው ቅጽበት ሌላውም ያስበዋል ወዳጀ ስብሰባ ላይ አንተ ልትሰጠው የነበረውን ሐሳብ ሌላው ሞጭልፎ ሲቀድምክ አላጋጠመህም፣
አሌክሳንደር ግርሐም ቤል ስልክን ፈጥሮ የ ፓተንት ራይቱን አስከብሮ ሲወጣ አንድ ሌላ ሰው ስልክ ፈጥሮ የ ፓተንት ራይቱን ሊጠይቅ ሲገባ በር ላይ ነበር የተገናኙት። እውቀት የህዝብ ነው። ሌላው ቀርቶ እነኚህ ታላላቅ ሰዎች ያልናቸው ራሱ ያገኙትን ግኚት እንዴት ደረሱበት ስንል ከህዝብ የገኙት ትምህርት ከህዝብ የገኙት እውቀት ሆኖ እናገኚዋለን። እነኚያ ሰዎች እኮ ነገሮች አልጋ ባልጋ ሆነውላቸው እንጂ እግዚአብሄር ሲፈጥር አላዳላም። ምክንያቱም ጎደኛየ በአንድ ነገር ቢበልጠኝ እኔም በአንድ ነገር እበልጠዋለሁና። "የ አንድ ሳንቲም ሑለት ግልባጭ" ይባልስ የለ

Anonymous said...

ቀልድኛ!!! እስቲ አቶ መለስን የደርግን መንግስት ለመገርሰስ ታርክ የሠራው የህዝብ ትንሹ ሥባሪ የሆነው ኢሕአዴግ ሳይሆን ሕዝብ ነው እንበለው ያኔ ታሪክ የሚሠራው ሕዝብ ሳይሆን ?... የሚለውን እነሰማለን.

Anonymous said...

በጣም የሚገርም ትዝብት ነው ፡፡ ለነገሩ አማረኛችን በራሱ በፈለጉት መልኩ ለመመንዘር ቀለል የለ የመስለኛል፡፡ አብዘኛዎቻችወን ማለት የስደፍረኛል የሆነ ሀሳብ ከተሰነዘር ሀሳቡን ወደራሰችን ልምድ በመውሰድ የራሳችን የውሰጥ ሀሳብን በማድረግ ፀሀፊ ባለሰበው መንገድ የምንል ሞልተናል፡፡ ችግሩ የሄ ሳይሆን የፃፊውን ወይም የተነገሪውን ሀሰብ ከምን መነሻ እነደገለፀው ሳይረዱ በተፃጻሪ ማቅረብ ግን አዋቂነት አይመስለኝም፡፡ጠቅላይ ሚኒስተሩ ታሪኮች የሚሰራው በህዝብ ነው ለማለተ ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን የግለሰብን የሚጫወተውን ሚና በመረሳት የተነገረ አባባል አይደለም፤፤ ንግግሮች ሆነ ጽሁፎችን ከራስ ሰሜት ወጣ ብሎ ማየት ይጠቅማል፡፡

Anonymous said...

ከብላቴ ጔደኞችህ አንዱ

ኤፍሬም በጣም ጥሩ ነው በርታ:: ክፉ አረም የታሪክ ነቀርሳን መለስንና አባ ጳዉሎስን እግዚአብሄር ይንቀልልን:: የኢትዮጵያን ትንሳዔ ለማየት ያብቃን::

Anonymous said...

To the world you may be one person but to one person you may be the world