Thursday, April 7, 2011

ብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ፣ የዛሬ 20 ዓመት (ክፍል አንድ)

ይህ መጣጥፍ ከዚህ እትም ጀምሮ ለተወሰኑ ሳምንታት ይቀጥል ዘንድ የተዘጋጀ ነው። በአንድ የታሪክ ወቅት በነበርን ተማሪዎች ገጠመኝ ዙሪያ በማጠንጠን የዛሬ 20 ዓመት ወደ ብላቴ የጦር ካምፕ ያደረግነውን ጉዞ፣ የገጠመንን ገጠመኝ፣ እግዚአብሔር ያደረግልንን ውለታ የምንዘክርበት ይሆናል። በወቅቱ በዚያ የጦር ካምፕ የነበሩ ተማሪዎችን ትዝታ ከራሴው ጋር ጨምሬ ለማቅረብ እሞክራለኹ። 
(ክፍል አንድ)
ብላቴ በቀድሞው የሲዳሞ ክፍለ ሀገር፣ ከሐዋሳ ከተማ ወደ 90 ኪ.ሜትር, ከአዲስ አበባ ደግሞ 395 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ነው። ከባሕር ጠለል በላይ 1000- 1400 ሜትር በበረሃማው የስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኝ ሞቃት ቦታ። በበጋ ወቅት እጅግ በጣም ሞቃት እና ደረቅ ሲሆን በክረምት ደግሞ ዝናባማ እና የሚተነፍግ ውሃ አዘል አየር (rainy and humid) ይበዛበታል። 
ልክ የዛሬ 20 ዓመት በወቅቱ በአገራችን የሚገኙ የኮሌጆች እና የዩኒቨርሲቲዎች በጠቅላላው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች በዚህ ወታደራዊ ካምፕ ከትመው ነበር። በእስክሪፕቶ ፈንታ ጠመንጃ፣ በወረቀት ፈንታ ጥይት፣ በዶርሚቴሪ ፈንታ ወታደራዊ “ኬስፓኖች”፣ በሲቪል ፕሮፌሰሮች ፈንታ መለዮለባሽ ወታደሮች ተተክተዋል። 

ተማሪው የቀለም እና የሙያ ትምህርቱን ትቶ መሣሪያ መግጠም እና መፍታት፣ መሣሪያ አያያዝና አተኳኮስ፣ የሰውነት ማጎልመሻ ስፖርት፣ የቦንብ አያያዝ እና አወራወር፣ ድንገተኛ መቁሰል አደጋ የደረሰበት ሰው ሊያገኘው ስለሚችለው ጊዜያዊ ርዳታ አሰጣጥ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ በምሽግ የተደበቀ ጠላት እንዴት ማጥቃት እንደሚቻል፣ በፈንታው ራሱ ምሽግ ውስጥ ቢሆን እንዴት መከላከል እንደሚችል፣ ሌሊት ቢሆን እንዴት እንደሚያጠቃ ወይም እንደሚከላከል ወዘተ ወዘተ ትምህርት ይሰጠው ነበር። እኔም እዚያ ነበርኩ። ዘንድሮ 20 ዓመት በሞላው በዚያ ለብዙዎቻችን አዲስ በሆነ የሕይወት አጋጣሚ ካየሁት እና ትዝ ከሚለኝ ላካፍላችሁ ወደድኹ።
U.S. Army Spc. Zaani Branch, of 1st Battalion, 294th Infantry Regiment (Light), Guam Army National Guard, trains Ethiopian National Defense Force soldiers on vehicle search procedures in Bilate, Ethiopia, Oct. 31, 2006. U.S. Air Force photo by Tech. Sgt. Joseph McLea
ወቅቱ በመላዋ ኢትዮጵያ “የጦር ወሬ”፣ የምጥ ጣር የሚሰማበት ከባድ ወቅት ነበር። መንግሥትም ሕዝቡም ተጨንቋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በአንድ በኩል የመንግሥት ለውጡ ደግ ነገር ይዞ ይመጣ ይሆናል በሚል ተስፋ ሲጠብቁት በሌላ በኩል ደግሞ “ኤርትራ ትገነጠላለች” ከሚለው ጀምሮ ሰሜነኞቹ ይዘውት ሊመጡት የሚችሉት መአት እያስፈራው በመንታ ልብ ይጠብቃል። “ከወንበዴዎቹ” ከድተው የገቡት ሁለቱ መሪዎቻቸው አብርሃም ያየህ እና ገ/መድህን አርአያ ይናገሩ የነበሩት ነገር ሊመጣ ያለውን መከራ እጅግ አክብደው አቅርበውት ነበር። ሰሎሞን የተባለ ፀሐፊ ከሱዳን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ያደርስ የነበረው እና የኢትዮጵያ ሬዲዮ ያነበው የነበረው ጽሑፍ ድባቡን በማክበድ ረገድ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥሯል። በዚህ መካከል ኮ/ል መንግሥቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሊያናግሩ ወደ 6ኪሎ ግቢ ተጓዙ። እናም ተማሪዎቹን በአንድ ቀን ከፀረ መንግሥቱ ኃ/ማርያምነት ወደ ፀረ-“ወያኔነት ቀይረው “እንዘምታለን” አስባሏቸው። ፕሬዚደንቱም “ይኼው ነው” ብለው ተነሡ። ከዚያማ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት ተባለ። “ወንበዴዎ የሚባሉት በረኸኞችም በበኩላቸው “አሁን ወደ ብላቴ የሚገባው ወታደር ከሌሎቹ የሚለየው እንግሊዝኛ በመናገሩ ብቻ ነው” ሲሉ ቀለዱ ተባለ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “እንዘምታለን” ማለታቸው እንደተሰማ በብዙዎቻችን ውስጥ የፈጠረው የተመሰቃቀለ ስሜት ነበር። አንዳንዱ መንግሥት ሌላውን ለማበረታታት እንጂ እነዚህን ሕጻናት አይማግዳቸውም ሲል ሌላው ደግሞ ሚሊሻውንም፣ አባት ጡረተኛውንም፣ ወጣቱንም ከላከ በኋላ የቀረው ተማሪው ስለሆነ ያንን ከማድረግ እንደማይመለስ በማስረገጥ ጭንቀታቸውን መግለጽ ጀመሩ። ተማሪው ግን ድጋፉን በየግቢው መግለጽ ቀጥሎ የመዝመቱ ነገር ቁርጥ ሆነ። መንግሥትም ነገሮችን ቶሎ አመቻቸ።

አንድ ቀን ስለዚሁ የዘመቻ ጉዳይ ያለንን ሐሳብ በእርግጠኝነት እናውቀው እና እንቀበለው ዘንድ ኮተቤ በሚገኘው የቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ባለን ሣምንታዊ ጉባዔ ጸሎትም ምክክርም አደረግን። ተማሪው በሁለት የተከፈለ ሐሳብ እንዳለው ግልጽ ነበር። መሔድ የሚፈልግ ተማሪ ያለውን ያህል መቅረቱን የሚመርጠውም ብዙ ነው። መሔድ የፈለገው ሁሉ ግን “ወንበዴዎቹን ለመዋጋት” ቆርጦ አልነበረም። ከቀረ በኋላ እንደሚባረር እርግጠኛ በመሆን ከዚያ ለማምለጥ መሔዱ ላይ የወሰነ ብዙ ነበር። በስንት መከራ የተገኘ ዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጅ እንዲህ በቀላሉ የሚተው አልሆነም። እናም ጭንቅ ሆነ።

በወቅቱ መንፈሳዊ ምክር እና ትምህርት እንዲለግሱን የጠራናቸው አባት እንደሁሌው ከሚደረገው ትምህርት በዘለለ መልክ ቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ገብተው ምክራቸውን በሰፊው ለገሱን። “ጭንቀታችሁ ይሰማኛል። መሔድ የምትፈልጉ አላችሁ፣ መቅረት የምትፈልጉ አላችሁ። ሒዱም ቅሩም ለማለት አልችልም። አንድ ነገር ግን ልንገራችሁ። መሔድ የምትፈልጉ በእምነት ሒዱ። መቅረት የምትፈልጉ በእምነት ቅሩ። የምትቀሩ ከትምህርታችን እንባረራለን ብላችሁ አትፍሩ። የምትሔዱም እናልቃለን ብላችሁ አትስጉ። ምንም አትሆኑም።” ሲሉ እስከዛሬም የማይዘነጋኝን ምክር ሰጡን። እናም ልባችን ተጽናና። መሔድ የሚፈልገውም ወሰነ፤ መቅረት የሚፈልገውም ወሰነ። እኔ መሔድ መረጥኹ።

ለምን ለመሔድ ወሰንኩ? የማስታውሰው ለመቅረት አስቤ እንደማላውቅ ነው። በዚያን ወቅት ግን ብሰለጥንም ጦርነት ውስጥ እገባለኹ የሚል ስጋት አልነበረኝም። ብዙም አላሰላሰልኩትም ልበል። ተማሪው በሙሉ ሲሄድ መቅረት ግን ሌላውን ተማሪ እንደመካድ ሳልቆጥር አልቀረኹም። በወቅቱ ኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ አብረን እንማር ከነበሩ ተማሪዎች መካከል በተደረገልን ፈጣን የጤና ምርመራ መሔድ አትችሉም ከተባሉ ተማሪዎች መካከል አንዱ በመሔጃችን ቀን አብሮኝ ቁጭ ብሎ ነበር። እኛ ሔደን እርሱ መቅረቱን ከጥፋት ሳይቆጥረው አልቀረም። ያ ወዳጄ አንድ እጁ በሕጻንነቱ ወድቆ የተሰበረ በመሆኑ ለወታደራዊ ሥልጠና አያበቃውም ተብሎ ተከልክሎ ነበር። እርሱ ግን ሻንጣውን ሸክፎ ለመሔድ ተዘጋጀ። ያ ወዳጄ ዳንኤል ክብረት ነበር።

(ይቀጥላል)

22 comments:

Anonymous said...

Dear brother,

I love to hear this story.

I hope u ll post the second part soon.

Hiwot M

Anonymous said...

Ephrem,min waga allew,asaterkew!Aderahn be tolo te melles! Egzer yisttlign!!!

ኤፍሬም እሸቴ said...

I will continue bit by bit, no worries.

Anonymous said...

Dear Dn Ephrem,

This is one of the critical historical part of our generation. Though some of us may be to kid to be part of this history, in one way or another, we are highly influenced by this specific movement. I think all of you who read this can understand what I want to mean. So we are eager to more and more about it, but it has to have different perspective on what we have read on different megazine.

Anonymous said...

Ere Ephrem betam atere eko. bayihon rinsh rezem rezem adrgewu enji. Gututachinin atabizawu.

Anonymous said...

በወሬ ብቻ እሰማው ስለነበረው ታሪክ ለማንበብ ጓጉቻለሁ፡፡ እፍጥነው እሽ ኤፍሬም?

Anonymous said...

Thank You
Like to hear the next soon.

Anonymous said...

Waw Efe I am one of those student's who strongly protests the marching. Fortunately I was not gone to the training center I harbored in 6 Kilo campus until the dawn fall of the dergue. This is because one of the Doctor's helped me that i was unfit for the march even if i was fully in good health. But I wasn't support the idea because you knew it....Weyane was by then in the near by city of North shewa so what was the benefit....the only benefit is not to the people but to the Dergues....What were they doing when the Weyane's smells their nose in every part of Ethiopia....Thanks A lot for sharing your memory of Blate.

Anonymous said...

ኤፍሪዬ ልባችንን አንጠለጠልከው፡፡

Anonymous said...

Hi Ephrem, I get the story interesting. Sure you will make best and fast for the upcoming part. Thank you for sharing.

Anonymous said...

Dn Ephrem, I have missed Bilate, coz it was a year after my graduation. I am eager to read, but for sure made it too short. ha ha !

Anonymous said...

Abet Lewre sinchekul, Ephrem Tinish koy kkkkkkkkkkk Enem eko chekuyalew

Anonymous said...

Are Betam Atere... Ketsafik And hulet gets Tsaf enji bedenb endinaneb...

dawit said...

መሔድ የምትፈልጉ በእምነት ሒዱ። መቅረት የምትፈልጉ በእምነት ቅሩ።

Anonymous said...

realy i am so much eager to hear this news.

Desalew said...

Efrie! I love it! y ETHIOPIA betekirstyan tilk miraf newna!!!

BORKENA said...

interesting. I did not have the opportunity to go to Blate. Yet, I remember the mobilization,the president's speech and students response. I am awaiting the next part.

Anonymous said...

I am waiting for the second part of your writing...sentochu alefu end zebet...Ashenafi from Technology Faculty amist kilo he was dead in Bilate wenze while he was trying to swim...and other's...Mesfin Asheber of course he was dead after Blate while he was working in Radio Fana ..did u remember his poem "Arenguade Becha shertete"........waiting for more memories...

Anonymous said...

እኛ ሔደን እርሱ መቅረቱን ከጥፋት ሳይቆጥረው አልቀረም። ያ ወዳጄ አንድ እጁ በሕጻንነቱ ወድቆ የተሰበረ በመሆኑ ለወታደራዊ ሥልጠና አያበቃውም ተብሎ ተከልክሎ ነበር። እርሱ ግን ሻንጣውን ሸክፎ ለመሔድ ተዘጋጀ። ያ ወዳጄ ዳንኤል ክብረት ነበር።

Amazing Amazing ............

Tizta said...

Yibel Yibel!!!!!

ትንሣኤ said...

መሔድ የምትፈልጉ በእምነት ሒዱ። መቅረት የምትፈልጉ በእምነት ቅሩ።የትም ቦታ የሚሰራ ግሩም ምክር ነው፡፡

የሚገርመው ነገር ሰው የዩኒቨርስቲን እድል እንዳያጣ ብሎ ህይወቱን ሊያጣ መወሰኑ ነው ያውም ባላመነበት ጦርነት፡፡ ተማሪው ብቻ ሳይሆን ወታደሩም ጭምር ያላመነበትን በግዳጅ ማድረጉ ብዙ ኪሣራ ነው

Anonymous said...

እኛ ሔደን እርሱ መቅረቱን ከጥፋት ሳይቆጥረው አልቀረም። ያ ወዳጄ አንድ እጁ በሕጻንነቱ ወድቆ የተሰበረ በመሆኑ ለወታደራዊ ሥልጠና አያበቃውም ተብሎ ተከልክሎ ነበር። እርሱ ግን ሻንጣውን ሸክፎ ለመሔድ ተዘጋጀ። ያ ወዳጄ ዳንኤል ክብረት ነበር።
እጅግ ለብዙ ጊዜ ስመኘው የነበረውን ታሪክ ስላስነበብከኝ ዲያቆን ኤፍሬም እጅግ አመሰግንሃለሁ! የዲን.ዳኒ ቆራጥነት ልቤን ነክቶታል እግዚአብሔር በብዙ ነገር ያበረታው ሰው !!! ረጅም እድሜ ይስጣችሁ! ዳኒ. . . . . . . . አንድ ሰው አይደለህም ብዙ ነህ!!!!!!!!!