Friday, April 8, 2011

ብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ፣ የዛሬ 20 ዓመት

ይህ በአንድ የታሪክ ወቅት በነበርን ተማሪዎች ገጠመኝ ዙሪያ በማጠንጠን የዛሬ 20 ዓመት ወደ ብላቴ የጦር ካምፕ ያደረግነውን ጉዞ፣ የገጠመንን ገጠመኝ፣ እግዚአብሔር ያደረግልንን ውለታ የምንዘክርበት ይሆናል በወቅቱ በዚያ የጦር ካምፕ የነበሩ ተማሪዎችን ትዝታ ከራሴው ጋር ጨምሬ ለማቅረብ እሞክራለኹ ባልኩት መሠረት የሚከተል ክፍል ሁለት ዝግጅት ነው። አስቀድመው ግን ክፍል አንድን ማንበብ አይርሱ

ነገረ ወታደር በልጅነት አእምሮ

መቼም ወታደር የመሆን ትንሽ የለውም። አንድ ጊዜ ካምፕ ከገቡ እና መሣሪያ ከጨበጡ ያው ወታደር ተኮነ ማለትም አይደል? ድንገት አይበለውና ነገር ተገጣጥሞ ጦርነቱ አውድማ ላይ የምንውልበት ሁኔታ ቢፈጠር “ግዴለም እነርሱ የኮሌጅ ተማሪዎች ናቸው፤ ሳይፈልጉ መጥተው ነው” ወዘተ ወዘተ የሚል አይኖርም። ስለዚህም የጦር እና የጦርነት ወሬው እያየለ ሲመጣ ነገሩ ከባድ መሆኑ አይቀርም።


Holeta Genet Military Academy 
ስለ ወታደር እና ውትድርና እንዲሁም በወታደር ሙያ ተሰማርቶ ሲዋል ስላለው ውጤትና መዘዝ በመጠኑም ቢሆን የማወቅ ዕድሉ ነበረኝ። የጦር ካምፕ ባለበት እንደ ሆለታ ገነት ባለው አካባቢ ለሚያድግ ልጅ ውትድርናን ገና ከልጅነቱ እያየው እና እየኖረው ማደጉ ሳይታለም የተፈታ ነው። አንድም በጥሩ አንድም በክፉ።

ልጆች ሆነን ከፊልሙ ዓለም ጋር የተዋወቅነው አዲስ አበባ አካባቢው እንዳደጉ ልጆች በሆሊዉድ ወይም በሕንድ ፊልም አልነበረም። ዓይናችንን የገለጡት ለጦር ሠራዊቱ እና ለእጩ መኮንኖች ተብለው የሚታዩ የሶቪየት ሕብረት የጦርነት ፊልሞች ናቸው። የተሠሩበት ቋንቋ ራሺኛ እንደመሆኑ እኛ ሕጻናቱም “ካዴቶች” የሚባሉት እጩ መኮንኖችም ምንም ነገር ሳይገባን በራሳችን ቋንቋ እየተረጎምን “እንዲህ አለው፤ እንዲህ ተባባሉ፤ አክተሩ እንዲህ ሲላቸው እነርሱ እንዲህ አሉት” እያልን የራሳችንን አንድምታ ፈጥረን እንፈታዋለን። ለፊልሞቹም የየራሳችን ርዕስ እንሰጣቸዋለን። በተለይ “የአምስቱ” እና “የሰባቱ” የምንላቸው ፊልሞች የሕጻንነት ልቡናችንን ሰርቀው ያሸፍቱን ነበር። (ዋነኛ አክተሮቹ አንዱ ላይ አምስት፣ ሌላው ላይ ደግሞ ሰባት በመሆናቸው እንደዚያ ተብለዋል።)

ከዚያም አንድ ቀን እቤት ገብቼ “ወደፊት ወታደር ነው መሆን የምፈልገው፣ ኤየር ቦርን ነው የምሆነው” አልኩ። ጎረቤታችን የነበረ ወጣት የአየር ኃይል ባልደረባ ነገሩ ማታ ቡና ላይ ሲወራ ሰምቶ በሳቅ ሞተ። እናቴን “ማዘር፣ አንድ ቀን ጥሩ ዶሮ ሥሩለትና እርሱን በልቶ ከጣራ ላይ ዘሎ ይውደቅ፤ ያኔ ይረዳዋል” ብሎ አሾፈብኝ። ከዚያን ቀን በኋላ እኔም አየር ወለድ ካልሆንኩ ብዬ ስመኝ የነበረውን ነገር ለማንም ላለመናገር አፍሬ ዝም አልኩ።

በልጅነት የራሺያ ፊልሞች ከምናያቸው በላይ ጥሩ ተራኪዎች አግኝተው ስንሰማቸው ደግሞ የተለየ ፍቅር ያጭሩብን ነበር። በሰፈራችን በዚህ የትረካ ሥራ ታዋቂ የነበረው ጊዮን ነበር። በዕድሜ ከእኛ ከፍ የሚል አንደበተ ርቱዕ፣ የፊልም ብልት አዋቂ “አክተራችን” ነበር። ማታ አብረን ያየነውን ፊልም እርሱ ቀን ጥሩ አድርጎ ሲተርከው ልክ እንደ አዲስ እንከታተለዋለን። ሰውነቱ ደንዳና፣ አቋሙ ለፊልምም ለውትድርናም የሰጠ ነበር። ታዲያ ፊልሞቹን በአክሽንም በአንደበቱም ሲናገር አብሮ የሠራ ራሺያ ቋንቋ አዋቂ ይመስላል። ኋላ እርሱ ራሱም ወደ አየር ወለድ ማሰልጠኛ ገብቶ የተመሰከረለት ወታደርና አሰልጣኝ ሆነ ሲባል ሰምተናል። አሁን የት እንዳለ እንጃ።

ሆለታ የሚገኘው የጦር ት/ቤት የዘመነ ጣሊያን ጀግና ከነበሩት ከኮሎኔል አብዲሳ አጋ ጀምሮ (አብዲሳ አጋን አላውቅም የሚል ይኖር ይሆን?) አያሌ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የጦር ሰዎችን ያፈራ ከመሆኑም በላይ የመንግሥት ለውጥ እስከተደረገበት እስከ 1983 ዓ.ም ድረስ መኮንኖችን ያሰለጥን የነበረ በኢትዮጵያ ቀዳሚው ዘመናዊ የጦር ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ነው። ልጆች በነበርነበት ወቅት በዕድሜያቸው እጅግ በጣም ወጣት የሆኑ ለግላጋ እጩ መኮንኖች አለባበሳቸውን አሳምረው ወደላይ ወደታች ሲሉ የእኛን የሕጻናቱን ልብ ይሠርቁ እንደነበር ትዝ ይለኛል። ምናልባት ለዚህ ይመስለኛል የከተማችን ብዙ ወጣቶች በተለይም አየር ወለድ የሚባለው የጦሩ ክፍል አባላት እየሆኑ በብዛት ይቀጠሩ የነበረው።

አየር ወለዶቹ ሰልጥነው፣ እጅጌው የታጠፈ ነብርማ ዩኒፎርም ልብሳቸውን ለብሰው፣ በፓራሹት የወረዱበትን መለያ አሞራ መሰል ሜዳሊያ አድርገው፣ ከሌላው የወታደር ጫማ (ከስክስ) ለየት የሚለውን እና የሚያምረውን ባለ ቡሽ ጫማ ተጫምተው ሲመለሱ ጨረቃ ደርሶ ከመጣ ሰው እኩል እናያቸው ነበር። ነገሩ የሚለወጠው መርዶ መምጣት ሲጀምር፣ እኛም በዕድሜ ማደግ ስንጀምር ነው። እርሱም ቢሆን በብዛት ትርጉም የሚሰጠው ለትልልቆቹ እንጂ ለእኛ አልነበረም። ለእኛ ሁሉም የራሻ ፊልም ነው።

በዚያን የልጅነት ወራት ዋነኛው መዝናኛችን አንድም እግር ኳስ ወይም ደግሞ ፊልም ነው። ከእግር ኳስ ሜዳ አንጠፋም ወይም ዕድል ሲገኝ ፊልም ለማየት አንደኞች ነን።

ኮሌጅ ስንገባ በእርግጠኝነት ውትድርናን እና እንደዚያ ዓይነቱን ሕይወትን አደጋ ላይ የሚጥል የሥራ መስክ አመለጥን የሚል ሐሳብ ወደ ልቡናችን ገብቶ ነበር። በዚያን ወቅት በመላው ኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመቀበል ከሚቀመጡ ተማሪዎች መካከል የማለፍ ዕድሉን የሚያገኘው እጅግ በጣም ጥቂቱ እንደመሆኑ ማለፊያ ነጥብ የሚያመጣው በሙሉ ነገ ሥራ እንደሚጀምር ሁሉ ደስታው ወሰን አልነበረውም። ገና ኮሌጅ ገብቶ መማር እንዳለ፣ ከዚያም ተሰናክሎ መቅረት እንዳለ እስከሚዘነጋ ድረስ ቤተሰብም፣ ራሱ ተማሪውም፣ ደስታቸው ወደር ያጣል። የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያየ ምክንያት ለማለፍ ያልቻሉ ወጣቶች ወደ ወታደራዊ የመኮንኖች ማሰልጠኛዎች በመግባት የሕይወት መሥመራቸውን በአቋራጭ ይቀይሳሉ። እንደ ሆለታ ባለው አካባቢ ይህ ነገር በጣም የተለመደ ነው። እንግዲህ ኮሌጅ ገባን የተባልነው ተማሪዎች “ወደ ጦር ካምፕ ግቡ” ስንባል ነገሩ ይህንን ሁሉ የልጅነት ትዝታ ጎትቶ ማምጣቱ፣ እናም “ወታደር ልሆን ነው ማለት ነው?” የሚል ሐሳብም ማጫሩ አይቀርም።     

(ይቀጥላል)

16 comments:

melkamu said...

pls don't make it short Dn.
plsssssssssssssssssssssssssss

Anonymous said...

ወይ ኤፍሬም ! መቼም ልባችንን አንጠልጥለህ ልትገለን ነው፡፡ እስኪ ይሁን……….. ለማንኛውም ከቻልክ ቶሎ ቶሎ ልቀቅብን፡ ካልቻልክ ደግሞ እንደምንም እንጠብቅሀለን፡፡

Anonymous said...

Hi Efrim, I cant see the picture, if u can pls adjust it.

Solomon Getachew said...

አይ ባለውለታዋ ብላቴ !
ውድ ዲ/ን ኤፍሬም እንደምን አለህ ? በእርግጥ ብላቴ እንኳን በዚያች አስቸጋሪ ሰዓት ለነበራቹህት ይቅርና ታሪኩን ለምንሰማ እና ለምናነብ እጅግ ትዝታው ብዙ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ግን አንድ ዓላማ ነበረው ይህ ደግሞ አሁን ለቤተ ክርስቲያን አለኝታ የሆነውን ማህበረ ቅዱሳንን ማግኘት የተቻለው በዚህ አጋጣሚ ነው እናም ብላቴ ውለታዋ ብዙ ነው ፡፡ ግን ዲ/ን ኤፍሬም መቸም በርካታ ገጠመኝ አላቹህና የነበሩ ገጠመኞቻችሁን የተወሰኑት በዚህ ብሎግ ብታወጣቸው በጣም ደስ ይለኛል ፡፡ በተለየ የጸናጽሏ ገጠመኝ ማለቴ ወረብ ስታጠኑ መቼ ትረሳለች ……
እግዚአብሄር ቸር ወሬ ያሰማን !!!

Anonymous said...

So what happened Daniel? please tell us the story about Dani. I hope it is interesting?
Thank you !!!

Anonymous said...

+++
ተናፋቂው ወንድሜ ብላቴ ውለታዋ ብዙ ነው :: አ/አ ጥሩ ጀምረህዋል ሰፈር ሳትገባ በወል እንደጀመርከዉ ብላቴ ብዙ ይቀርሃል ከዚ በሞርቾ ዲላ ሃገረ ማርያም ሜጋ ሞያሌ ወዘት ሰንጋ ተራ እንዳይቀሩ____ ብላቴ ምንድን ነው ለሚሉ መልሱን ስጣቸዉ:: እንወድህአለን ሰላም ሁንልን
ከ/ኩ

Anonymous said...

ኢላማ ወረዳ ወርደህ ቀለህ ለቅመህ ቀላጭ ጨምረህ ክብሪት ከተህ እያፈነዳህ፣ ዚልና ኦራል፤ ዋዝና ማዝዳ ባትነዳም አፈራርቀህ አይተህ፣ የመንግሥቱን የካዴት ምረቃ እየኮመኮምክ፣ የሁለተኛውን የዓለም ጦርነት ፊልም ብቻ ሳይሆን የሕንዶቹንም እነ ዳይመንድራድን በነጻ ስትልፍ አድገሃልና ብላቴን ክስተት በክስተት መተረኩን አደራ፡፡

ብላቴ ፖለቲካዊ፣ ማኅበረሰባዊ፣ ሃይማኖታዊ ክስተቶችን አስተናግዳለች፡፡ እናም እንደወረደ አቅርብልን፡፡

ዘማቹ ነኝ
ቡቄሳ ኮረብታ ብላቴ

Anonymous said...

Kestafki Ayiker Enhi newa.. Ahun des Alegn... Berta Eski wendime

Anonymous said...

Min Maneltih New Anony... If you can not see the picture.. read it again.. If you can not see the picture after reading it again. do not read.... I can see the history.....

Anonymous said...

ወይ ዲን ኤፍሬም! በወቅቱ የሰባተኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ በልጅነት አእምሮየ ሽው ሲልብኝ የነበረውን ታሪክ አብሬ ከቦታው ያሳለፍኩት እስኪመስለኝ ለዛ ባለው አቀራረብ ማንቆርቆር ጀመርህ። ምን ዋጋ አለው---ከይቀጥላል እኔ ከብላቴ ትዝታ መመለስ አልቻልሁም!
በተስፋ ልጠብቅ እንጂ ምን አማራጭ አለኝ!

Mahlet (እሚ) said...

The past 20 years we were burning the bridge we crossed on ,this is a redefinition of that - the missing link.

Thank you ,thank you Ababaye

Anonymous said...

d ef sanebew germonail betariku wist alife ke bilate camp oda kenya , walda kenya ,kakuma kenya ,nairobi kenya ,ke asra simnt amet buhala ahun canda new yalehut betam yemgerm tizta egziabher yistlin tebarek wendimachin ef

Anonymous said...

kifil 3n filega zare snte temelalesku.

Anonymous said...

Yeah, i am still following your essay. Please try to add more stories of Blate. I knew Mahbere Kidusan was established after the return. I am very glad of it. Still Mahber Kidusan is the leader of our religion next to our beloved church father's.
Pls forward your other memories urgently.....

Desalew said...

Efrie ygerekan keberon yetsenatslun y MEregeta Yichalwal Goshimaen tarekim endatresa!!

Tesfaye said...

Selam wendm EF endemn alehlgn enem ke 20 amet behuala yihn tarik saneb berket yalu tiztawochi metubgn beziyan wekt YEKOTEBE D/L K:GEBREL agelgay neberku ena antenm tarikunm slemawukew betemesto new yanebebkut E/R ystln

Tesfaye

Blog Archive