Thursday, April 21, 2011

ብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ፣ የዛሬ 20 ዓመት (ክፍል አምስት)

ቢጫ ወባ፣ “ሻምበል ደቤ” እና ዱካክ 
ይህ መጣጥፍ በአንድ የታሪክ ወቅት በነበርን ተማሪዎች ገጠመኝ ዙሪያ በማጠንጠን የዛሬ 20 ዓመት ወደ ብላቴ የጦር ካምፕ ያደረግነውን ጉዞ፣ የገጠመንን ገጠመኝ፣ እግዚአብሔር ያደረግልንን ውለታ የምንዘክርበት ይሆናል፤ በወቅቱ በዚያ የጦር ካምፕ የነበሩ ተማሪዎችን ትዝታ ከራሴው ጋር ጨምሬ ለማቅረብ እሞክራለኹ ባልኩት መሠረት የሚከተል አምስተኛ ክፍል ዝግጅት ነው። አስቀድመው ግን ከክፍል አንድ እስከ አራት ያሉትን ማንበብ አይርሱ። 
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ዘንግቼ አልፌው የነበረ እና አንድ ወንድሜ ያስታወሰኝን የ1983 ዓ.ም የስቅለት በዓል ጉዳይ ላካፍላችሁ።  ልክ እንደ 1984 ዓ.ምሕረቱ የሚያዚያ 16 ዕለተ ኪ/ምህረት ስቅለት፤ እንደ 1997 ዓ.ም ሚያዚያ 21፣ እንደ 1999 ዓ.ም መጋቢት 28 የአማኑኤል ቀን፣ እንዲሁም በጻድቁ አቡነ ተ/ሃይማኖት ቀን እንደዋለው የመጋቢት 24/2002 ዓ.ም ስቅለት የዚያን ዓመት፣ የ1983 ዓ.ምሕረቱ በዓለ ስቅለት ደግሞ የዋለው መጋቢት 27 ቀን የመድኃኔ ዓለም ዕለት ነበር። በሃያ ሰባት እንደመዋሉ አንዳንዱ "እንስገድ" ሲል ሌላው ደግሞ “አይ፣ መሰገድ የለበትም፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ይከለክላል” ይላል። አንዳንዱ ደግሞ “ግዴለም ከወገባችን ብቻ ጎንበስ ጎንበስ እያልን እናስበው” ይላል። ክርክሩ ቀጠለ። በቦታው ሊቅ የለም። ሊቃውንትም የሉም። ተማሪው ከተገናኘ ገና ሳምንቱ ነው። እርስበርሱ የሚተዋወቀው ጥቂቱ ነው። እናም ክርክሩ ጊዜ ወሰደ። በመጨረሻ ግን መሰገድ እንዳለበት ያብራሩት ወንድሞች ሐሳብ ተቀባይነት ኖሮት ዕለቱን ስንሰግድ ዋልን። 

የሚገርመው በብላቴ ይነሣ የነበረው ዓይነት ጥያቄ ዛሬም ድረስ ሲመላለስ እንመለከታለን። ሊቃውንቱ ቢናገሩም፣ መምህራኑ ቢያስተምሩም፣ መጻሕፍቱ ቢነግሩንም ጌታ የተሰቀለባት፣ ደሙን ያፈሰሰባት፣ ሥጋውን የቆረሰባት፣ ወደ መቃብር የወረደባት ያቺ ልዩ አርብ ውለታዋ አማናዊ ምሥጢር ዛሬም የደበዘዘብን ይመስላል። የሆነው ሆኖ ያቺን ስቅለት በስግደት አክብረናት አለፍን። ትንሣኤውንም።

ምናልባት ካልተሣሣትኩ በስተቀር በአንድ ኢትዮጵያዊ የጦር ካምፕ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ፍጹም ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ሲካሔድ የብላቴው የመጀመሪያ ይመስለኛል። ዛሬ ላይ ቆሜ የ1983 ዓ.ምሕረትን ትንሣኤ የምገመግመው በዚህ ሐሳብ ብቻ ነው። በዚያች ኬስፓን ዙሪያ ተኮልኩለው መዝሙሩን ሲያዳምጡ የነበሩት ወታደሮችም በዓይነ ልቡናቸው ወደየቤተሰቦቻቸው እና ወደ ቅድመ--ውትድርና ዘመናቸው ሳይሄዱ የሚቀሩ አይመስለኝም። አብዛኛው ወታደር ከገጠሩ ክፍል የተገኘ፣ ክርስቲያናዊ ባህሉን ብዙም ያልዘነጋ እንደመሆኑ በወታደር ካምፕም ቢሆን ልቡ ከዚያቹ የገጠር ቀዬው ናት። በስድስት ወር የወታደር ቤት ሥልጠና ለዓመታት የኖረበትን ማንነቱን አጥቦ መድፋት፣ አለቅልቆ ማውጣት አጥቻልም።

መቸም የዘመናዊት ኢትዮጵያ ዘመናዊ ኢትዮጵያዊ ምሁራን በአብዛኛው ካደጉበትና ከኖሩበት ኢትዮጵያዊ ባህልና እምነት ተነቅለው የመውጣት ለውጥ አሳይተዋል። ይህ ደግሞ ከንጉሣዊ አስተዳደር መፍረስ በኋላ በይፋ እና በአዋጅ ተገልጿል። “የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ መመሪያ ሶሻሊዝም” ሆኖ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የ3000 ዘመን ሃይማኖታዊ ዳራ ያላት አገር በአንድ ጊዜ ተጠቅልላ “አምላክ የለሽ” ሆናለች ሲባል እጅግ የሚገርም ስሜት ይፈጥራል። ለወታደሩ የተረፈው ከምሁሩ ሲቪል የመጣው ነው።

“አምላክ የለሽነት” በአገር አቀፍ ደረጃ የታወጀው ከ1966 ዓ.ምሕረቱ አብዮት በኋላ ቢሆንም ምሁራዊው የኢትዮጵያ የአስኳላ ተማሪ ከቤተ ክርስቲያኑ መራቅ የጀመረው ቀደም ብሎ ጀምሮ ነው። አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖታዊ ባህል በሰለጠነባት ኢትዮጵያ የነበሩት የተማሩ ኢትዮጵያውያን በይፋ መጾም ቢያቅታቸው “ሽፍንፍን” የሚባል ምግብ አመጡ ሲሉ ይናገራሉ።  “ሽፍንፍን” የፍስክ መሆኑ እንዳያስታውቅ “ተሸፍኖ” የሚቀርብ ምግብ መሆኑ ነው። የምግቡ ሽፍንፍን በእምነቱም ነበር ማለት ይቻላል። ከላይ በይፋ ቤተ ክርስቲያንን ያልካዱ በውስጣቸው ግን ከቤተ ክርስቲያኒቱ የራቁ ብዙ ምሁራን እየተፈጠሩ ነበር። ቤተ ክርስቲያን ይህንን ጀርባውን በመስጠት ላይ ላለ የኮሌጅ ተማሪ የሚሆን ማኅበር አቋቁማም ነበር። ነገር ግን የታሰበውን ግብ ሳይመታ ቀረ። ይልቁንም በውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የነበረው የተማሪው አብዮታዊ እና የለውጥ እንቅስቃሴ እያደገና እየሰፋ ሄዶ ሥር ነቀል አብዮት እና ለውጥ በአገሪቱ አመጣ። በኢትዮጵያ ለነበረው ሁሉን አቀፍ ችግር ተጠያቂ ከሚደረጉት አካላት መካከልም አንዷ ቤተ ክርስቲያን መሆኗ በይፋ ተነገረ። አብዮቱ የቅዱስ ፓትርያርኳን ሕይወት ቀጠፈ። “አብያተ ክርስያናት እንዲከስሙ፣ አብያተ አምላክ የለሽነት እንዲያብቡ” ኢትዮጵያውያን ተንቀሳቀሱ። ክርስትና ማስነሳት፣ ሃይማኖተኛ ሆኖ መታየት፣ ጾምና ጸሎት፣ ቤተ ክርስቲያን እና ጥንታዊ የኢትዮጵያ  ትምህርት ያረጁ ያፈጁ፣ ዘመን ያለፈባቸው ተደርገው ተቆጠሩ። እሑድ ለስብሰባ እንጂ ለቤተ ክርስቲያን መታሰባቸው እየደበዘዘ መጣ። ዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች አምላክ የሌለው ትውልድ የሚፈበረክባቸው ይሆኑ ዘንድ ታሰቡ። “አምላክ የለም” ማለት ሥልጣኔ፣ ዕድገት፣ ተራማጅነት ሆኖ ተቆጠረ። እግዚአብሔር ግን ራሱን ሊክድ አይችልምና መኖሩ አልቀረም። መኖሩንም አሳየ።

በብላቴ እግዚአብሔር መኖሩን በዚያው በአደባባያቸው ተናገረ ብል ማጋነን አይሆንም። ኢትዮጵያ አምላኳን በይፋ ሰቅላ፣ ቀብራ ትኖር ጀምራ ነበር። ያ የተሰቀለው አምላክ፣ የተቀበረው አምላክ፣ ዘመን ጠብቆ ትንሣኤውን አወጀ። እኛም በወታደር ካምፕ “ትንሣኤከ ለእለ አመነ፣ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ፤ ትንሣኤህን ለምናምነው ለእኛ ብርሃንህን (በላያችን) ላክ/ላክልን” ብለን ዘመርን። ዛሬ ሳስበው ይህንን ሁሉ ትርጉም ሰጠሁት እንጂ ያን ጊዜማ የአጋጣሚ ነገር ሳይመስለኝ አልቀረም። በእግዚአብሔር ዘንድ ግን “አጋጣሚ” የሚባል ነገር የለም። ለዕውቀቱ ገደብ የሌለው አምላክ ሁሉን “በጊዜው ውብ አድርጎ እየሠራው” ነበር።

በጥንቱ ዘመን ወታደር እና ሃይማኖት የተሳሰሩ ነበሩ። ወታደሩ የሚሞተው ለአገሩ፣ ለቤተሰቡ እና ለሃይማኖቱ እንደሆነ ስለሚነገረው እና ስለሚያውቅ ሞቱም ክብር አለው። ከወታደሩም ጋር የንስሐ አባቶች እና ባራኪ ካህናት አብረው መሔዳቸው ያንኑ ያጠይቃል። ልጅ ሆኜ ሲነገር እንደማስታውሰው የጦሩ አካላት የሆኑ ካህናት በሆለታ ገነት  ጦር ት/ቤት ውስጥ ነበሩ። አገልግሎታቸው የጦሩን መንፈሳዊ አቅም ማጎልበት ይመስለኛል።

ከስድሳ ስድስቱ የመንግስት ለውጥ በኋላ ግን ጦሩ ከዚህ ዓይነቱ ባህል ተቆራርጦ ፍፁም አምላክ የለሽነትን እንዲቀበል ይጫንበት ጀመር። መሣሪያ እና አምላክ የለሽነት በአንድ ሰው እጅ እኩል ከተገኙ ሊመጣ የሚችለውን ነገር ኢትዮጵያም አየች። መሰከረች።
“መላኩ ተፈራ የግዜር ታናሽ ወንድም፣
የዛሬን ማርልኝ ሁለተኛ አልወልድም”
እስኪባል ድረስ ወጣት መሆን የማይፈለግበት ዘመን መጣ። ኢትዮጵያውያን ግማሹ በቤተ መንግሥት ተቀምጦ፣ ገሚሱ በመንደር ተቀምጦ፣ ግማሹ ፋኖ ተሰማራ ብሎ … ብቻ እርስበርሳቸው ተላለቁ። የከተማው የእርስ በርስ ጦርነት ሲቆም በየተራራው፣ በየገደሉ መገዳደሉ ቀጠለ። በዚህ ጎራ፣ በዚያ ጎራ ሆነው ተታኮሱ። ተጋደሉ፣ ተገዳደሉ። ሁሉም ግን የአንድ አገር ልጆች ነበሩ።

በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የእኛው ቢጤ ተማሪ “ዕድገት በሕብረት” ተብሎ አገር ለማቅናት፣ ለማስተማር ወደ ገጠር ነጎደ። ወደ አራቱም አገራችን አቅጣጫዎች ዘመተ። ዚያ ትውልድ አባላት የሆኑ የያኔ ተማሪዎች ዛሬ ጎልማሶች እና ባለ መካከለኛ ዕድሜ ‘ሽማግሌዎች’ ናቸው። ከዘመተው የዚያን ጊዜ ተማሪ ሁሉም በደህና አልተመለሰም። በየመንገዱ የቀረ፣ እንደ ወጣ የቀረ ብዙ ነው።

ከዚያም ቀጥሎ በ1977 ዓ.ም የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በሙሉ “ለመንደር ምሥረታ ዘመቻ” ወደየገጠሩ ነጎደ። ሙላቱ ውብነህ (Mulatu Wubne) የተባሉ ተመራማሪ እንደጻፉት በወቅቱ የነበረው መንግሥት ስድስት መቶ ሺህ (600,000) ሕዝብ ከተለያዩ አካባቢዎች በማንሣት ለም እና የሚታረስ ድንግል መሬት ወዳላቸው የምዕራብ እና ደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች አዘዋውሯል። ከዚህ ውስጥ ከ250,000  በላይ የሚሆኑት በወለጋ፣  150,000 አካባቢ የሚሆኑት በጋምቤላና ኢሉባቦር፣ ከ100,000 በላይ የሚሆኑት በፓዌ ሠፍረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ወደ 78,000 የሚሆን ሕዝብ በከፋ፣ በሸዋ እና ምዕራብ በጌምድር እንዲሰፍር ተደርጎ ነበር።

ተማሪው በጋምቤላ፣ በመተከል፣ በወለጋ … ጎጆ ቤት ሲሠራ፣ ተፈናቃዩን ሲያቋቁም ቆይቶ ተመለሰ። በደህና ወጥቶ ለመመለስ ያልቀናውም ነበር። እነዚያ መንደር ሊመሠርቱ የወጡት ታላላቅ ወንድሞቻችን በየዛፉ ሥር፣ በየመንገዳቸው ጸሎተ ማርያም ማድረሳቸውን፣ ሲችሉም ተገናኝተው ቃለ እግዚአብሔር መስማታቸውን እንዳላስታጎሉ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። እኛን ቃለ እግዚአብሔር ያስተማሩን የዚያ “መንደር መሥራች ትውልድ አካላት የሆኑ ወንድሞች ናቸው። ወደ ዝዋይም የላኩን እነርሱ ናቸው። እኛ እና እነርሱ በአንድ ላይ ስንሆን ጊዜ በጋራ “ማ/ቅዱሳን” ተባልን።

ከዚያም ተራው ለእኛ ትውልድ ደረሰ። ወደ መሠረተ ትምህርት ሳይሆን፣ ወደ መንደር ምሥረታም ሳይሆን የእኛ ተራ ደግሞ ወደ ወታደራዊው ካምፕ ሆነ። የእኛን ዘመቻ የተለየ የሚያደርገው ቀደም ብለው እንደነበሩት ታላላቆቻችን ተበታትነንና ወደተለያዩ አካባቢዎች ሳይሆን ሁላችንም በአንድ ቦታ መሰብሰባችን ነው ያውም በሺዎች የሚቆጠር ወጣት። እግዚአብሔር ያቀደው ነገር ነበረው። ትንሣኤን በደመቀ ሁኔታ ስናከብር በርግጥም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዲስ ዘመን እየመጣ መሆኑ እርግጥ ሆነ።

የትንሣኤ ዕለት ግሩም ምሳ አበሉን። ምሳ ሰዓት ላይ “የወባ ክኒን ነው” ተብሎ ሁለት-ሁለት ክኒን እንድንውጥ ተሰጠን። ዋጥን። ከዚያ በኋላ ግን ሁላችንም ደንዝዘን ዋልን። ግሹ በመኖሪያው አዳራሽ (ኬስፓን) ግማሹ በየዛፉ ሥር ውድቅድቅ ብሎ ዋለ። ከመጠን በላይ የሆነ ነገር ሰጥተውን ይሁን ወይም ሌላ ምክንያት ይኑረው አላወቅኹም። ብቻ ጅላጅል ሆነን ማሳለፋችን ትዝ ይለኛል። "ቢጫ ወባ እንዳያጠቃችሁ" የሚለው አባባል ብዙ ጊዜ ስለሚነገር ከፍተኛ ፍርሃት ነበረብን። ዝዋይ ለጥቂት ወራት በነበርኩበት ጊዜ ወባ አልያዘኝም። የብላቴውን “አውጣኝ፣ አውጣኝ” እያልኩ ከረምኩ። በተለይ የብላቴው “ጭንቅላት ላይ የሚወጣ እና ቶሎ ሕክምና ካላገኘ አሳብዶ የሚገድል ነው” (cerebral malaria) ስለሚባል በሕጻንነታችን እንፈራው ነበረው “ጭራቅ” ዓይነት ስሜት ፈጥሮብን ነበር። በየስድስት ወሩ ለሥልጠና ይገባ ከነበረው በሺዎች ከሚቆጠረው ምልምል ወታደር ውስጥ ቁጥሩ ጥቂት የማይባለው በዚሁ “ቢጫ ወባ” ያልቅ እንደነበር አሰልጣኞቻችን ሲናገሩ ሰምቻለኹ።

ከቢጫው ወባ ውጪ የግቢው ዋነኛ በሽታ የሆድ መታወክን የሚያስከትለው እና በተማሪው አጠራር “ሸርተቴ” የሚባለው ተቅማጥ/ Diarrhoea ነው። (በሌላ አማርኛ መግለጽ ብችል ደስ ይለኝ ነበር። 'ስለተፈጠረው የቴክኒክ ችግር ይቅርታ' እንዲል የኢትዮጵያ ሬዲዮ):: ይህንኑ በሽታ ነፍሱን ይማረውና ገጣሚ እና ጋዜጠኛ የነበረው መስፍን አሸብር ግሩም በሆነው ግጥሙ “ሸርተቴ” በማይጠፋ መልኩ አስቀምጦት አልፏል። ተማሪው የዚህን ግጥም ዋና ዋና አንጓዎች እና አዝማቾች በቃሉ አጥንቶት ነበር። በተለይም ከዚህ በታች ያለውን ብዙዎቻችን ዛሬ ድረስ እናስታውሰዋለን።

ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑ
ኩሩ ዘለግላጋው፣ ሸርተቴ ጅንኑ
ኩልል እንደ ውሃ፣ ፍስስ እንደ ጅረት
ቀጭን ኩታ መሳይ
አረንጓዴ ብጫ፣ ባለቀይ ጥለት።” እያለ ይቀጥላል። “ጠብታ ፍቅር” ከሚለው መጽሐፉ ላይ ነው ያገኘኹት።

መቸም እንዲህ ባለው ነገር፣ ያውም ታሞ ባለ ሰው፣ መቀለድ ደግ አይደለም። ግን ደግሞ ችግሩንም በሽታውንም እያሳሳቁ እና እያዋዙ ካላለፉት፣ ቢያለቃቅሱ ምን ይገኛል እንጂ ሸርተቴስ ቀላል ተማሪው ላይ አልተጫወተበትም።

ገጣሚው መስፍን እንዳለው “Diarrhoeaየሆድ በሮች እና መስኮቶች የማይገቱት ቀጭን እና ፈጣን ሯጭ ነው። መጣሁ ሲል ወዲያው ካላስተናገዱት፣ በር ካልከፈቱለት “ግምኛ” ሰውን ያበላሻል፤ ያዋርዳል። ሲመጣ ቦታ አይመርጥም። ጊዜ አይለይም። ከች ሲል ታማሚው እንደ ጥይት ተተኩሶ ከሽንት ቤት ወይም ከአንድ ዛፍ ሥር መገኘት አለበት። ለዚህ እንዲረዳ ታማሚው ልብሱን ማስተካከል አለበት። አንዳንድ  ሰልጣኞች “ሽርጥ” ያደርጉ ነበር። ለሌላቸው ደግሞ “ብሬዢኔቭ ቁምጣ” ምቹ ነው።

ባለ ሽርጡ ታማሚ ሸርተቴው ሲመጣ የሚጠበቅበት ወደ ዛፍ  ሥር መሮጥ እና ሽርጡን በፍጥነት መግለጥ ብቻ ነው። ሱሪ ማድረግ ለመበላሸት ካልሆነ በስተቀር ተመራጭ አይደለም። ብሬዢኔቭ ቁምጣ እግሩ ሰፋፊ፣ ቶሎ ለማውለቅ ምቹ ስለሆነ የተማሪው ባለውለታ ሆኗል። ብዙው ታማሚ ሰልጣኝ ቀን ቀን አየር ለመቀበል፣ ለሽንት ቤት እንዲቀርበውም ውጪ ጎጆዎች ውስጥ መቀመጥን ይመርጣል።

በዚህ ጉዳይ ላይ "AN INVESTGATION OF DIARRHOEAL DISEASE OUTBREAK AT BILATE MILITARY TRAINING CENTRE" በሚል ጥናት ያደረጉት ዶ/ር መኮንን አድማሱ እና አበራ ገይድ (Makonnen Admassu, MD & Abera Geyid, MSc) እንዳስቀመጡት ከሆነ በወቅቱ በብላቴ ገብቶ የነበረው እንዲህ ቀላል በሽታ ሳይሆን “ወረርሽኝ” ነው።
  

ክሊኒኮች

በተለያዩ በሽታዎች የታመሙ ተማሪዎች ብዛት

በሸርተቴ የታመሙ ብዛት
 አንደኛ ብርጌድ
 524       
 72 (13.7 %)
ሁለተኛ ብርጌድ      
 347       
 74 (21.3 %)
ሦስተኛ ብርጌድ
 911       
 117 (12.8 %)
አራተኛ ብርጌድ
 1,345
 845 (62.8 %)
አምስተኛ ብርጌድ
1,060
176 (16.6 %)
 ስድስተኛ ብርጌድ  
1,011
332 (32.8 %)
ጠቅላላ ድምር                         
5198
1,616 (30.8 %)

ጥናቱ ያተኮረው ከMarch 5 to 22, 1991 ድረስ ብቻ ያለው ጊዜ ላይ በመሆኑ ከዚያ በኋላ የታመሙትን አልተመለከተም። ለዚያውም ቢሆን 1616 ተማሪ መታመሙ ጥቂት የሚባል አይደለም። በዚያው ተመሳሳይ ወቅት ደግሞ በሌሎች በሽታዎች የተጠቁ 3582 ተማሪዎች መኖራቸውን ልብ ይሏል (THE ETHIOPIAN JOURNAL OF HEALTH DEVELOPMENT )። ሸርተቴ ሰው ቢሆን ኖሮ “ምን አቅብጦኝ እነዚህ ተማሪዎች ጋር መጣሁ፣ ምነው ባልያዝኳቸው ኖሮ” ሳይል አይቀርም። ምክንያቱስ? ቀለድንበት፣ አሾፍንበት፣ ብዙ ሳቅንበታ። ገጣሚውም በግጥሙ እንዲህ አሞግሶ ተሳለቀበታ።

ሸርተቴ”
እንቅልፍ የምትነሳ፣ ሌት የማታስተኛ
ህሊና ሞጋቹ፣ ክፉ ወንጀለኛ
መቼም አንላቀቅ፣ አንተ ተንኮለኛ
ክስ አቅርቤያለሁኝ፣ ለፈራጁ ዳኛ
ሳትታይ አድፍጠህ፣ ተሰውረህ ከ’ኛ
ገብተህ የተገኘህ፣ ከዚች ከብላቴ
በላ ልበልሃ፣ ተጠየቅ ሸርተቴ!
ይዘን የመጣነው፣ የጠራ ሆድ ነበር
አምጦ ሚያገሳ፣ ድምፁ የሚያሸብር
ሲሻው የሚያሽካካ፣ ልክ እንደመትረየስ
አሊያም እንደ ፈንጂ፣ ሙት የሚቀሰቅስ
ወይም እንደ ጎማ፣ ምስማር እንደበሳው
ብሶት ‘ሚተነፍስ፣ ሰው ሳያይ ሳይሰማው።
ሸርተቴ ባንተ ግፍ፣ ተንኮል ሳይሰራ
ሆዳችን ነበረ፣ የኮራ የደራ
ልሳኑ ያማረ፣ ኮስታራ ቀብራራ፤
ምን ያደርጋል ታዲያ በጦርህ ተወጋ
ድምጹ ጥፍት አለ ልሳኑ ተዘጋ
ህገ-ሥርዓቱ፣ ፈረሰ ተናጋ።

አቤት ያንተ ተንኮል፣ አቤት ያንተ ሥራ
አብሪ ጥይት የለህ፣ መንገድ የሚመራ።
ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑ
ኩሩ ዘለግላጋው፣ ሸርተቴ ጅንኑ
ኩልል እንደ ውሃ፣ ፍስስ እንደ ጅረት
ቀጭን ኩታ መሳይ
አረንጓዴ ብጫ፣ ባለቀይ ጥለት።
አይ አወራረድህ፣ አይ አተኳኮስህ
ቴትራ ሳይክሊን፣ ሚዝል አይመልስህ
“ብሬዢኔቭ ቁምጣ”፣ ሱሪ አያግድህ
ሆድን ፈለጥለጥለጥ፣ ቁርጥ ቁርጥርጥርጥ
ሸርከት ሸርከትከትከት፣ ዓይናችንም ፍጥጥ
ሸራ ለመሸረር፣ ፋታ የማትሰጥ
በቀላው አሸዋ፣ በሚቆረቁረው
ጀግናን በባዶ እግር፣ ይዘህ ያሯሯጥከው
ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑ
ሸርተቴ ጅንኑኩሩ ዘለግላጋው፣
ስንቱን አደረከው አጉል ኩራተኛ?
ሰው የማያናግር ሌሊት የማይተኛ።
….
ከሞቀ ጨዋታ፣ ወጉ ከደራበት
ስንቱ ፈረጠጠ፣ ዘለለ በመስኮት?
ከመኖሪያ ታዛ፣ ከኬስፓኑ ነቅለህ
ከጎጆ ከተትከው ፍራሽ አስነጥፈህ።
ሆዱን ሊያስታግሰው ተርቦ ተጠምቶ
እጁን ሲሰነዝር፣ ‘ከሜስ’ ቤት ገብቶ
አንተ መጣህና፣ ገበታውን ትቶ
ስንቱ ፈረጠጠ፣ ሾርባውን ጎልቶ?
አንጀቱን ሰርስረህ፣ ከግርጌ ከስሩ
አይ አፈጣጠንህ፣ የሥራህ ነገሩ።
ሲሻህ አረንጓዴ፣ ሲልህ ትቀላለህ
ወይም ቢጫ ሆነህ፣ ትቀይረዋለህ
አንዳንድ ጊዜማ፣ ድብልቅልቅ ትልና
ትመሳሰላለህ ከቀስተ ደመና።

ሸርተቴ ሸበላው፣ ሸርተቴ ፈጣኑ
ኩሩ ዘለግላጋው፣ ሸርተቴ ጅንኑ
ኩልል እንደ ውሃ፣ ፍስስ እንደ ጅረት
ቀጭን ኩታ መሳይ
አረንጓዴ ብጫ፣ ባለቀይ ጥለት
(መስፍን አሸብር፣ በ1983 ዓ.ም ብላቴ ጽፎት፣ “ጠብታ ፍቅር” በሚል ከታተመው መጽሐፉ የተወሰደ።)

ከሸርተቴው እና ከወባው ባሻገር ዱካኩ እና ቅዠቱ ብላቴ ላይ ሰልጥኗል። ወታደሮቹ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ መንፈስ “ሻምበል ደበበ ወይም ሻምበል ደቤ” ይሉታል። እንደዚያ የተባለበት ታሪክ አለው። ታሪኩን ወዳጄ ዳንኤል ክብረት “ሁለቱ ሰይጣናት” በሚለው ጽሑፉ በመጠኑ ጠቅሶታል። ነገሩ እንዲህ ነው።

በግቢው ውስጥ አንድ ሻምበል ደበበ የሚባሉ መኮንን ነበሩ አሉ። መኮንኑ እጅግ ቁጡ እና በበታቾቻቸው ዘንድ እጅግ የሚፈሩ ነበሩ። ታሪኩን የተረኩልን ሰዎች እንደሚያቀርቡት ከሆነ ጥፋት ያለበት ወታደር ከተገኘ ሻምበል ደቤ እንዲህ በቀላል አይለቁትም። በወታደሩ ቤት እንደተለመደው አንድ ሻምበል ወደታች ወርዶ አንድ ተራ ወታደር ቁጭ በል፣ ብድግ በል እያለ አይቀጣም። ግን ያስቀጣል። ትዝ እንደሚለኝ ሆለታ ጦር ካምፕ ውስጥ አስር አለቃ በቀለ የሚባሉ አንድ ረዥም ወታደር፣ በመቅጣት የሚታወቁ ነበሩ። ከርሳቸው ከፍ ሲል ደግሞ መቶ አለቃ (ምትኩ ይመስለኛል ስማቸው) በጣም ይፈሩ ነበር። አስር አለቃ በቀለ ሲቀጡ በመጀመሪያ ወታደሩን ቀበቶውን ያስፈታሉ። የጫማውን ማሰሪያ ያስወልቃሉ። ከዚያም በሩጫም ይሁን ብዙ ፑሽ አፕ በማሠራት ልቡን ያጠፉታል። አስር አለቃ በቄ የሚታወሱት “ኢኔ ዲረስ፣ ቦንባ ዲረስ፤ እኔ ድረስ፣ ቧንቧው ድረስ” በሚለው ወዲያ ወዲህ የሚያሯሩጥ ስፖርታቸው ነው። የብላቴውም ሻምበል ደቤ እንዲሁ የሚፈሩ መኮንን ኖረዋል። ሻምበሉ መቅጣት ከፈለጉ አንዱን ሻለቃ ጦር፣ ወይም አንዱን ሻምበል ጦር፣ ወይም አንዱን የመቶ ጦር በስፖርት ልቡን ያጠፉታል። አንድ ወታደር ብቻውንም እንደዚያው።

ታሪኩ እንደሚያትተው፣ አንድ ቀን ጦሩ ሁሉ ለጥ ብሎ ከተኛበት “የሻምበል ደቤ ፊሽካ” በቀጭኑ ትሰማለች። ጦሩ በርግጎ ተነሥቶ ይወጣል። ሻምበል ደቤ አንድ ሰበብ ፈጥረው ብቻ ያንን ጦር በጭለማ ሲያሯሩጡት ያድራሉ። ከዚያም ቅጣቱ ያልቅና ውልቅልቅ ያለው ጦር ወደ አልጋው ተመልሶ ይዘረራል። ቆየት ብሎ፣ “ፎሌን ሲነፋ” የሚነሣ ሰው ይጠፋል። አለቆች ወደ ጦሩ ቢመጡ ሁሉም ወዳድቋል። “ተነሥ!” ቢባል ማን ይነቃነቅ። “ምን ሆናችሁ?” ሲባል “ሻምበል ደበበ ሲቀጡን አደሩ” ይላል ጦሩ። በነገሩ ሻምበል ደበበ ራሳቸው ይገረማሉ። ለካስ በሻምበል ደቤ ተመስሎ የመጣው “አጅሬ ሰይጤ” ኖሯል። ከዚያን ጊዜ ወዲህ “ሰይጣን፣ ዱካክ” ማለት ቀረና በቁልምጫ “ሻምበል ደቤ” ተባለ።

ወታደሮቹ የሚናገሩት ሌላም ብዙ ነገር አላቸው። ለምሳሌ ጦሩ ቀን ቀን ሲዘፍን የሚለውን ዘፈን ሻምበል ደቤ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ የራሱን ጦር ሲያዘፍን ሰምተናል ይላሉ።  “ቡቄሳ ኮረብታ” የምትባለውና ወታደሩ የሚማርባት ትንሽ ጉብታ መሬት ቀን ቀን ጦሩ፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ የሻምበል ደቤ ጦር ይዘፍኑባታል እየተባለ ይቀለዳል። እንግዲህ ሰይጣን “ሞራል እያወጣ” ወደየትኛው ውጊያ እንደዘመተ እግዜር ይወቀው። በደፈናው ግን “ውሸት ነው፤ ሲጋነን ነው፤” ማለቱን አልመረጥኹም።

እኔ የማውቀውን ግን ልንገራችሁ። ተማሪው ሌሊት ሌሊት በጣም ይቃዥ እንደነበር ትዝ ይለኛል። ሙቀቱ ይሁን፣ ሻምበል ደቤ ይሁን፣ ወይም የሁለቱ ጥምረት ይሁን እንጃ። እናም ቤተ ክርስቲያን እንደምንሔድ የሚያውቁ የሌላ እምነት ተከታዮች ሳይቀሩ “እባካችሁ ዱካክ አስቸገረን እኮ” ይሉን ነበር። ያለችንን ውዳሴ ማርያም አካፍለን “ትራስህ ሥር አድርገኸው ተኛ” እንላቸዋለን። እውነትም “ሰላም አደርን ዛሬ” ይላሉ - ሌላ ጊዜ። ለእግዚአብሐር ምን ይሳነዋል።

እንደማስታውሰው እኔም ራሴ አንድ ቀን አሞኝ ከሥልጠና ቀርቻለኹ። ሐኪም ቤት አልሄድኹም። ለጥ ብዬ ዋልኩ። ጉልበት አጥሮኝ ነበር። መቸም የፀሐዩ ነገር አይነሣ። ቆዳችን በዋዕዩ ክስል ብሎ ያረረ የጥቁር ጤፍ ቂጣ ይመስላል። ስለ ሥልጠናውና ስለ ፀሐዩ በሌላ ጊዜ ብመለስበት ይሻላል።

(ይቀጥላል)

33 comments:

Anonymous said...

indet tolo ilki alebign meseleh!!!!

Melkam ye sikilet ina ye tinsae beal yihunilih!

Ke AA

Anonymous said...

thanks D.Ephrame to share us

Anonymous said...

Dear Dn Ephrem,

As usual we are following your impressive story. Keep up the good work.

Anonymous said...

...እኛ እና እነርሱ በአንድ ላይ ስንሆን ጊዜ በጋራ “ማ/ቅዱሳን” ተባልን።ማቅ ማቅ ማቅ ማቅ ማቅ go go go go .... and long live

Ameha said...

ዲ/ን ኤፍሬም አመሰግናለሁ! የሕማማቱን ድርሻዬን አንስቻለሁ። እንደገና የምትመለሰው ከፋሲካ በኋላ እንደሆነ እገምታለሁ። ለማንኛውም መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆንልህ እመኛለሁ።

ድርሻዬ። said...

ዲ/ን ኤፍሬም በወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ የምታሳልፋት እያንዳንዷ ቀን ልዩ ትዝታን ጥላ ነው የምታልፈው። ከሌሎች ቀናቶች እጅግ የተለዩ ናችው። ያንተን ውብ ፅሁፍ አያነበብኩ የኔም ልብ ወደ ሁርሶ ተጉዞ ከሁለት ኣሥርት ኣመታት በፊት ስላሳለፍኩት የህይወት ገጠመኝ እያሰላሁ ነበር። ክፍል 6 በጉጉት አንጠብቃለን። መልካም ትንሳኤ።

ኤፍሬም እሸቴ said...

አመሰግናለኹ ድርሻዬ። አንተም ከነመላው ቤተሰብህ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልህ። ያንተን ገጠመኞች ደግሞ እንደምታስነብበን ተስፋ አደርጋለኹ።

Anonymous said...

ዲ/ን ኤፍሬም መቼም የሆለታ አገራችን ትዝታ አመጣሀዉ፡፡ በነገራችን ላይ ሁሉንም በጣም እየተከታተልኩኝ ነዉ በርታ፡፡ መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆንልህ እመኛለሁ።

Anonymous said...

Nice article. Hsve s blessed EASTER.

Anonymous said...

"ትንሣኤከ ለእለ አመነ፣
ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ፤
ትንሣኤህን ለምናምነው ለእኛ
ብርሃንህን (በላያችን) ላክ/ላክልን"

Anonymous said...

Nice memoir.
More clarification about
"እኛ እና እነርሱ በአንድ ላይ ስንሆን ጊዜ በጋራ “ማ/ቅዱሳን” ተባልን።" !
I mean, who is EGNA and ENESU?

Anonymous said...

ዲያቆን ኤፍሬም እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሰህ!

Anonymous said...

I'm waiting for part six. I think you have a blessed Easter and now back to work okey please post part six......

Anonymous said...

Dear Ephrem Thanks for sharing the Belate history of Part Five but you are too late to Share the next part what happen to You we are waiting eagerly .Let me ask you one question why you became late i think You are enjoying in the holiday of Easter week I mean You didnt finish to eat meat??????????( siga alalekem ende???) or what please even if be ale hamsa we need to eat the article soon.

Thank you

Anonymous said...

ሰላም ላንተ ይሁን እህ ነገሩ እንዴት ነው?የሰው ልብ ሰርቆ ዝም ማለት በል ወዳጄ ልቤን መልስ ብጠብቅ ብጠብቅ ምንም መልስ የለም እረ ተንፈስ ልበል ፖስት አድርገውና

Anonymous said...

እንደምን አለህ ዲያቆን ኤፍሬም ምን ሆነህ ነዉ በሰላም ነዉ ክፍል አምስት ላይ ደርሰህ በዛዉ የጠፋኸዉ በርካታ አንባቢዎችህ በጉጉት እየጠበቅን ነዉና ቀጣዮቹን ክፍሎች ፈጠን ፈጠን ብለህ አስነብበን ……………………………ይገርማል ምንም ሳትለን ሁለት ሳምንት ማለፉ እኮ ነዉ

Anonymous said...

በእውነት የምታውቁ እባካችሁ ዲያቆን ምን እንደሆነ ንገሩን ከጽሁፉ ያስጨነቀን የሱ መጥፋት ነው እባክህ ቢያንስ አለሁ ደህና ነኝ በለን ደህና ከሆንክ

Anonymous said...

Endemin aleh? D/N Ephrem, beselam new yetefahew?

Anonymous said...

Dn. what is going on? are u okay. in the first week I was annoyed with the delay. but now I am worried 'bout your well-being.
Mercy on U

yafral said...

it is so interested article please keep it up
kale hiwot yasemaligne

Anonymous said...

ቂቂቂ…… ኤፍሬም ጉድህ ፈላ፡፡ ልብ ሰርቀህ ጠፍተሀል አሉ፡፡ በል ቶሎ የሰው ልብ መልስ ሌላ ቦታ ሳንዳረስ፡፡

Anonymous said...

Dear Dn Ephrem

So many people shared my feeling and already said it. I didn't expect that, it took such a long time to read part VI. Especially, at this time, Ginbot Lideta has its own historical coincidence with your life at Blate. Hope, you are fine with your family, that is the most important thing even to read different topics in the future.

Blessed life

Anonymous said...

እንደምን ከርመሃል ዲን ጽሑፎችህን እጅግ ከመናፈቄ የተነሳ ደግሜ ደጋግሜ ወደ ጡመራ መድረክህ እመላለሳለሁኝ ግን ምንም ነገር መመልከት አልቻልኩም ዝምታህ በደህና ከሆነ ይሁና ብያለሁኝ ለሁሉም ክፉውን ይጠብቅልህ ብያለሁኝ የብላቴን ታሪክ በጣም ብዙ ነገር እየጠበኩኝ ስለሆነ እባክህን አለሁኝ በለን

Anonymous said...

i heared this story about 10 years ago but can't wait for the rest. Yeah ofcourse everything was not a coinsidence, it was God's plan.keep going pls

Anonymous said...

ኤፍሬም ምንድነው ጉዱ ለማን ነው አቤት የሚባል  የአፋልጉኝ ማስታወቂያ እስከሚወጣ ድረስ! ኧረ ባክህ አታስጨንቀን ብላቴም ይቅር በቃ…… አንተ ደህና መሆንህን ብቻ ንገረን፡፡

Anonymous said...

ዲ ኤፍሬም ምነው በደህናህ ነው?

Anonymous said...

እነዚህን ተከታታይ እና የማይጠገቡ ታሪኮች መንበብ የጀመርኩት ዘግየት ብየ ስለነበር እንደ ሌሎች አንባቢዎች "ኧረ አሳጠርከው" ወይም "ኧረ ዘገየህብን" ወይም "plz come back soon" እና የመሳሰሉትን አስተያየቶች መስጠት አላስፈለገኝም ነበር። ምክንያቱም ዘገይቼ ማንበበ በመጀመሬ ብዙ ታሪኮችን እና ተከታታይ ክፍሎችን በአንዴ ማንበብ በመቻሌ:: ዛሬ ግን ከሌሎች አንባቢዎች ሃሳብ ጋር የምስማማበት ጊዜ በስተመጨረሻ የመጣ ይመስለኛል::So, plz come back soon...

ዘ-ኤልያስ ነብይ said...

እድለኛ ባለ ታሪክ . . .

Anonymous said...

ሀይ ኤፍ

ስለ ሻምበል ደቤ የተመለከተው ታሪከ ብቻዬን ቢሮ ውስጥ ሁኜ በጣም እንድሰቅ አድርጎኛል…..በጣም ደስ የሚል ገጠመኝ ነው እርግጥ አኔም በወቅቱ ተማሪ የነበርኩ ቢሆንም አልዘመትኩም ነገር ግን ያልዘመተ ስንመለስ አይማርም የሚለውን ማስታወቂያችሁንም አካተው እባክህ….ሁሉም ያልዘመተ ተማሪ ዳግም ምዝገባ እንዲጀመር ሲወተውትና ተመዝግቦም ለመዝመት ሲሯሯጥ እንደነበረ ልንገርህ…..ከዚያም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰፈሩትን የወታደር ሬሽን የያዙትን መኪኖች መዝረፋችን ትዝ ይለኛል….ምክንያቱን ታውዋለህ….

Anonymous said...

wegenoche kifele sedist wetoal or genna new, Some how confused. I am lucky to read all 1-5 today but where is Kifil 6?

Anonymous said...

thank you
continue

Beakal said...

“ኢኔ ዲረስ፣ ቦንባ ዲረስ፤ እኔ ድረስ፣ ቧንቧው ድረስ”betam new yemiyasikew ababayee

Des said...

ከማስታውሰው በሸርተቴ የሁሉም ካምፓስ ተማሪ ተጠቅቶ ስለነበረ ኮመን ኮርስ ይባል ነበር

Blog Archive