Friday, April 15, 2011

ሕማማት እና ትንሣኤ በብላቴ

ብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛ፣ የዛሬ 20 ዓመት (ክፍል አራት)
ይህ መጣጥፍ በአንድ የታሪክ ወቅት በነበርን ተማሪዎች ገጠመኝ ዙሪያ በማጠንጠን የዛሬ 20 ዓመት ወደ ብላቴ የጦር ካምፕ ያደረግነውን ጉዞ፣ የገጠመንን ገጠመኝ፣ እግዚአብሔር ያደረግልንን ውለታ የምንዘክርበት ይሆናል፤ በወቅቱ በዚያ የጦር ካምፕ የነበሩ ተማሪዎችን ትዝታ ከራሴው ጋር ጨምሬ ለማቅረብ እሞክራለኹ ባልኩት መሠረት የሚከተል አራተኛ ክፍል ዝግጅት ነው። አስቀድመው ግን ክፍል አንድን ሁለትንና ሦስትን ማንበብ አይርሱ።
___________________________________________________________________________________________________________________________________
ሥልጠናው ከመጀመሩ አስቀድሞ ለዚያ የሚያስፈልጉ ነገሮች ተሟልተው ተሰጥተውናል። አንድ ጫማ፣ ቱታ፣ ካልሲ፣ ካናቴራ፣ አዣክስ ሳሙና፣ “ብሬዢኒቭ” የሚሉት ቁምጣ። ቁምጣውን በቀድሞ የሶቪየት ሕብረት ፕሬዚደንት ስም ለምን እንደተሰየመ አላውቅም። አለ ነገር ግን እንደዚያ አላሉትም። የኛ ሰው እንዲህ ነገሮችን እያገናኙ ስም የመስጠት ልዩ  ሥጦታ አለው። ይቺ ብሬዢኔቭ ቁምጣ ተማሪው በከፍተኛ “የዲያሪያ” (ሸርተቴ) ወረርሽኝ በተቸገረ ጊዜ ብዙ ውለታ ውላልናለች። በቦታው አነሣዋለኹ።

ወታደራዊ ሥልጠና ከሥርዓት ነው የሚጀምረው። አስቀድሞ ተማሪው በብርጌድ፣ በሻለቃ፣ በሻምበል፣ በመቶ እና በጓድ ይከፋፈላል። የአንድ ሰው ወታደራዊ አድራሻው ይህ ነው። ከፍተኛ፣ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር … እንደማለት ነው። አንድ ብርጌድ 3 ወይም 4 ሻለቃ ሊኖረው ይችላል። ብርጌዱ 4 ሻለቆች የሚኖሩት “አጥሻ” ከሚባለው ከአስተዳደርና ጥበቃ ሻለቃ ጋር ሲደመር መሆኑን አንድ ሰው በቅርቡ ነግሮኛል። አንድ ሻለቃ 3 ሻምበሎች፣ አንድ ሻምበል ደግሞ 3 ወይም 4 የመቶዎች ሊኖሩት ይችላሉ። አንድ የመቶ 32 ሰው ይይዛል። ሁሉም የየራሱ ተጠሪ እና ኃላፊ አለው። ጠዋት በሌሊት ስንነሣ የመጣውና ያልመጣው የሚታወቀው በዚሁ መሠረት ነው። የታመመው፣ በሥንፍና የቀረው ሁሉም ሁሉም “ሪፖርት” የሚደረገው በዚሁ የአደባባይ ሥርዓት ነው። ጦርነት ሜዳ ውለን ቢሆን ኖሮ የሞተው፣ የቆሰለው፣  የከዳው፣ የገባበት ያልታወቀው፣ የተማረከው በዚሁ ከብርጌድ እስከ ጓድ ድረስ በተዘረጋ የዕዝ ሰንሰለት የሚለይ ይመስለኛል።

ጠዋት ተነሥተን የምንሰለፍበት እና ቆጠራ የሚደረግበትን ሥነ ሥርዓት “ፎሌን” ቆጠራ ይሉታል። ቦታው ደግሞ “ፎሌን ሜዳ” ይባላል። ትርጉሙን አትጠይቁኝ።

ሰልጣኙ በመጀመሪያ ጠዋት የሚያከናውነው አካል ማጎልመሻ ወይም ስፖርት ነው። በወታደር ቤት “ላብ ደምን ያድናል” የሚለው አባባል የተለመደ እና አካል ማጎልመሻን የሚያሳይ ነው። በስፖርት ያልተገነባ እና በብቃት ያልቆመ ወታደር ዋጋ የለውም። በአንድ ጊዜ ከ25 ኪሎ ግራም ያላነሰ ሸክም ተሸክሞ ተራራውን ለመውጣት፣ ቁልቁለቱን ለመውረድ ሰውነቱ ብቁ መሆን አለበት። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ያሉ ወታደሮች አብዛኛውን መንገድ በእግራቸው የመጓዝ ግዴታ ስለሚኖርባቸው ጥንካሬ መኖሩ የግድ ነው። አሜሪካን የመሳሰሉ ያደጉ አገሮች ወታደሮቻቸው ከ50 እስከ 90 ፓውንድ ሸክም ቢኖራቸውም በእግራቸው የሚጓዙት መጠነኛ ስለሚሆን ሸክሙ ይህንን ያህልም አይጎዳቸው ይባላል። ለዚህ ሁሉ ግን ወታደር እና ስፖርት መዛመድ አለባቸው።

የወታደሮች ስፖርት ትዝ የሚለኝ ገና ከሆለታ ጀምሮ ነው። ቤታችን ከከተማ ወደ ጦር ካምፑ ባለው ዋና መንገድ ላይ በመሆኑ ሁል ጊዜ ጠዋት ጠዋት (ከሌሊቱ 10 እና 11 ሰዓት አካካባቢ) ከእንቅልፋችን የሚቀሰቅሰን አንደኛው የወታደሮቹ ሩጫ ነው። የብዙ ወታደር ኮቴ ከጥቁሩ አስፓልት ጋር ሲጋጭ የሚፈጠረው ድምጽ ሌሊቱን ያደምቀዋል። በመካከል በመካከሉ የአሰልጣኛቸው ድምጽ ወይም ፊሽካው ይሰማል። ከዚያ ውጪ ያለው “እረም-እረም” የሚለው የብዙ ሰዎች እግር ነው። በብላቴ ግን እረም እረም የሚያደርግ አስፓልት የለም። አፈር ብቻ።

ብላቴ ቀስ ብሎ ከሚደረገው ጉዞ በመለስተኛ ሩጫ በ“ሶምሶማ” የሚደረገው ይበልጣል። ከሥልጠና መልስም ሆነ ወደ ሥልጠና ሲኬድ ዱብ ዱብ እያሉ መሔድ የተለመደ ነው። በተለይም ከቀን ሙሉ ድካም በኋላ ወደቤት መልስ ሲሆን “ሞራል እያወጡ” (የጋራ ዘፈን እየዘፈኑ) የሚደረገው የሶምሶማ ሩጫ መንገዱን አጭር፣ ድካሙን ቀላል ያደርገዋል። አለበለዚያ እንደ ከተማ ሽርሽር በ“ዎክ” እየተንቀራፈፉ ልሒድ ካሉት እግርም ከመሬት አይነሣ፣ መንገዱም ማለቂያ አይኖረው። ወታደሮች በጋራ ዘፈን እየዘፈኑ በሩጫ የሚያደርጉት ጉዞ ነው “ሞራል ማውጣት” የሚባለው።

ሥልጠና የጀመርነው የዐቢይ ጾም የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ነው። ሐሙስ ገብተን ተከትሎ የመጣው እሑድ በዓለ ሆሳዕና፣ ሰኞ ደግሞ የሰሙነ ሕማማት መጀመሪያ ሆነ። ክርስቲያኖች እንደመሆናችን ይህንን ሳምንት እንዲሁ ልናሳልፍ አልቻልንም። ብዙዎቻችን በየግቢዎቻችን መንፈሳዊ ጉባዔዎች ስለነበሩን ያንኑ ለመቀጠል ወሰንን። ነገር ግን ቦታው የጦር ካምፕ ነውና ያንን ለማድረግ ሥጋት ነበር። ለማንኛውም ግን ከየዩኒቨርሲቲዎቹ እና ኮሌጆቹ የምንተዋወቀው በማታ ተገናኝተን መወያየትም መጸለይም ጀመርን። ለመሆኑ እንዴት ተዋወቅን?

አሁን እንደሚደረገው በዚያ ወቅት ብዙዎቹ ግቢዎች መንፈሳዊ መርሐ ግብሮች አልነበራቸውም። ጉባዔያት ያሏቸው በጣት የሚቆጠሩ ነበሩ። ለምሳሌ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ፣ ደብረ ዘይት ኮሌጅ እንዲሁም ጅማ ጤና ሳይንስ ሊጠቀሱ ይችላሉ። የተዋወቅነው ግን በየግቢያችን ባሉት ጉባዔያት አማካኝነት ሳይሆን መንፈሳዊ ሥልጠና ለመውሰድ ወደ ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅ/ገብርኤል ገዳም እና የካህናት ማሰልጠኛ ገብተን የነበርነው ነን። ያንን ትውውቅ መሠረት አድርገን ለመገናኘት ብዙም አልተቸገርንም።  

የኮሌጅ ተማሪ ወደ አቡነ ጎርጎርዮስ ዘንድ ወደ ዝዋይ ቅ/ገብርኤል ገዳም ሲገባ እኛ ሦስተኛ ዙር ነበርን። 1982 ዓ.ም። ብፁዕነታቸው ያረፉት እኛ እዚያ እያለን ነው። በወቅቱ ከተለያዩ ኮሌጆች የመጣን 45 ተማሪዎቸ ነበርን። ከእነርሱ ውስጥ ብላቴ ከብዙዎቹ ጋር ተገናኝተናል። ከስድስት ኪሎ ታደሰ ደጀኔ እና ጓደኞቹ፣ ከአራት ኪሎ ዝናዬ እና ሙሉጌታ ኃ/ማርያም፣ ግርማ ወ/ሩፋኤል፤ ከኮተቤ ኤፍሬም እሸቴ፣ ክብረት መኳንንት፣ ተሾመ አይቼው እና ጓደኞቻቸው፤ ከጅማ ጤና ሳይንስ ንዋይ ገሰሰ፤ ከጅማ እርሻ ኮሌጅ አልአዛር አድነው፤ ከደ/ዘይት እንስሳት ሕክምና አሁን ስሙን የዘነጋሁት ወንድም ነበሩ። እኛ ዝዋይ የምንተዋወቀው በወቅቱ ዝዋይ ያልነበሩትን ጓደኞቻችንን ጨመርን። ከኮተቤ ዳንኤል ክብረት፣ ከጅማ እነ ዲ/ን ዘላለምና ያየህ፣ ሌሎችም ብዙ ብዙ ወንድሞች ነበሩ።

ዝዋይ፤ 1982 ዓ.ም (ምረቃ)
ይህ ስብስብ እግዚአብሔር ባወቀ የተገኘ ልዩ አጋጣሚ ነበር። በተለይም የተማረ የሚባለው ወጣት ወደ ቤተ ክርስቲያኑና እና እምነቱ ቀርቦ፣ ማንነቱን አውቆ ለአገሩም ለቤተ ክርስቲያኑም የሚጠቅም ጥሩ ዜጋ ለማግኘት ትልቅ ሕልም የነበራቸው የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ተስፋ የተፈፀመበት ቦታ ነው ብል አላጋነንኩም። በመላዋ ኢትዮጵያ የሚገኘውን እጩ ምሩቅ በሙሉ በአንድ ሥፍራ ስብስብ ብሎ ከማግኘት የበለጠ ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ።

እንግዲህ ጸሎቱ ሲጀመር ከላይ የዘረዘረኳቸው ሰዎች አንድ ላይ ለመገናኘት ቻሉ። በምሽት ለጸሎት የምንገናኝባት ሥፍራ ቀን ቀን በፀሐይ ወቅት ጥላ ፍለጋ ለሚቀመጡ ሰዎች ተብላ የተሠራች ሚጢጢ ጎጆ ቤት ናት። መብራት የላትም። በአካባቢዋም መብራት ያለው ምንም ነገር የለም። ከከዋክብት በስተቀር። ጨለማ ነው። የሰው ድምጽ ካልሆነ መተያየት የሚባል ነገር የለም። ቀደም ብለን ከምንተዋወቀው በስተቀር ኋላ የመጡት ማን ማን መሆናቸውን ያወቅነው ዘግይቶ በቀንና በብርሃን መገናኘት ስንጀምር ነው። እና በዚያ በምሽቱ የዕለት ጸሎታችንን እያደረስን ሰሙነ ሕማማትን አሳለፍን እና ዋነኛው ዕለት አርብ ደረሰ። በአርቡ ያውም በስቅለቱ ዕለት በየኬስፓናችን ማሳለፍ አልቀፈድንም። ከማሰልጠኛው ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቆ የቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንደሚገኝ ስለሰማን ወደዚያው ለመሔድ ወሰንን።

የዕለቱ ዕለት ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የሄድነው ሁላችንም በአንድነት አልነበረም። እንዳደረሰን በቡደን በቡድን ሆነን ለመሔድ ሞከርን። እኔና ጓደኞቼ ሰባት ኪሎሜትር አካባቢ ርቀት ላይ ወደሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ለመሔድ ዋናውን አውራ ጎዳና ይዘን ስንጓዝ ከማሰልጠኛው የጥበቃ ሠራተኞች ጋር ተገናኘን።
“ወዴት ልትሔዱ ነው?” ጠየቁ።
“ወደ ቤተ ክርስቲያን። ዛሬ ስቅለት ነው።” መለስን።
“አይቻልም፤ ተመለሱ።”

ከዚያ በኋላ ያደረግነው ጉንጭ አልፋ ክርክር ነው። የመሔዳችንን አስፈላጊነት ለማሳየት ብዙ ለፋን። አንዲት መልስ ናት መልሳቸው። “አይቻልም” የምትል።

“ሞኝ ሁል ጊዜ ያሸንፋል” የሚለው አባባል ትዝ አለኝ። ምን ብሎ ነው የሚያሸንፈው ቢባል “እምቢ ብሎ” ይሏል። ተረኛ ጥበቃዎቹ ጅሎች አይመስሉኝም። ነገር ግን መልሳቸው ጅል ያስመስላቸዋል። የመለሱልን ግን በሥርዓት ነው። ማንጓጠጥም ሆነ ማመናጨቅ የለበትም። ለዚያ አመሰግናቸዋለኹ። እዚያ ግቢ በቆየንባቸው ቀናት በሙሉ ወታደሮቹ አንድም ቀን ተማሪ ሲያመናጭቁ አይቼ አላውቅም። በፈንታው ተማሪው እንትን እንደነካ እንጨት ሲያደርጋቸው እያየኹ ብዙ ጊዜ አዝኛለኹ። እናም ወደ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የመሔዳችን ነገር እንማይቻል በቁርጥ ስንረዳ ከመመለስ ውጪ ምንም አማራጭ አልነበረንም። ጥቂት ወንድሞች (በግቢው አጠራር ደግሞ- “ጓዶች”) ግን እኛ ይዘነው የሔድነውን ቀጥታ መንገድ ትተው አሳብረው ጥሻ ለጥሻ ሔደው ከቤተ ክርስቲያኑ ደርሰዋል። እኛ አልቀናንም።

ወደመጣንበት ስንሰመለስ የተወሰኑ ወንድሞች ሰብሰብ ብለው የራሳቸውን ጸሎት በአንድ ዛፍ ሥር ማድረጉን ቀጠሉ። እኔና አብረን የሔድነው ግን ወደ ብርጌዳችን ስንመለስ ማንም ሰው የማይኖርበት እና ገና በመገንባት ላይ ያለ አዲስ “ኬስፓን” አገኘን። (ትርጉም፤ ኬስፓን የግማሽ ጨረቃ ቅርጽ ያለው የብረት ቤት ሲሆን ብላቴ ያሉት ቤቶች በሙሉ እንደዚያ ዓይነት ናቸው።) ለአንድ ሳምንት ያህል በሚጢጢ ጎጆ ቤት ውስጥ ያውም በጨለማ ስንጸልይ መቆየታችንን ትተን ወደዚያች ኬስፓን በድፍረት ገባን። ባዶ ናት። ከውጪ ከተደረደሩ ጡቦች እየለቀምን ጠረጴዛ ቢጤ ሠራን። እዚያም ላይ ሥዕለ ማርያማችንን አደረግን። ከዚያ ስቅለቱን በስግደት አሳለፍን።

ጨርሰን ስንወጣ ሥዕለ-ማርያማችንን አላነሣናትም። በበነጋው እንደምንመለስበት እርግጠኞች ነበርን። ቅዳም ሥዑር፣ “ቅዳም ሹር” - በሕዝብ ቋንቋ። ብቸኛዋ ቅዳሜ። ብቸኛዋ ከጥሉላት ብቻ ሳይሆን ከማንኛውም ምግብ የምንጾምባት ቀዳሚት ሰንበት። በወታደር ካምፕ። ቅዳሜ ነውና ሥልጠና የለም። አርፈን ነው የዋልነው። ማታ ላይ የጸሎት ቦታችንን አስተካክለን አሰናድተናል። መዝሙር የሚያቀርቡት መዘምራኑ ቆርኪያቸውን ቀጥቅጠው ጸናጽሉን፣ የላስቲክ ጀሪካኑን ለከበሮነት አውለዋል። ቀኝ ጌታ ይቻለዋል ጎሽሜ ከነእጩ ዶ/ር ንዋይ ገሰሰ ጋር መዝሙሩን አቀናብረዋል። ዲ/ን አልአዛር አድነው የከበሮው ጌታ ነው። ዲ/ን ሙሉጌታ ኃ/ማርያም እና ሌሎች ዲያቆናት ወንድሞች ኪዳንና ቅዳሴው ሲቀር ያለውን ሥርዓተ ጸሎት አቀናብረዋል። ዳንኤል ክብረት፣ ታደሰ ደጀኔ፣ ግርማ ወ/ሩፋኤል ወዘተ ወዘተ መርሐ ግብሩን አሰናድተዋል። እኔንም አትርሱኝ ዝርዝሩ ውስጥ።

ያዘጋጀው ማን እንደሆነ ባላስታውስም በሶው ተበጥብጦ ለጾመኛው ሊታደል ቀርቧል። በየት በየት ስክትክት እንዳለ እግዜር ይወቀው። ዓመት የተደከመበት እንጂ የአንድ ቀን ሐሳብ አይመስልም። ከዚያም የሚጠበቀው መዝሙር መጣ። “አማን በአማን ተንሥዓ እምነ ሙታን” የሚለው። በረሃው አስተጋባ። የጨለማ ድምጽ ከሩቅ ይሰማል። ራቅ ብሎ ሦስተኛ ብርጌድ ካሉት ሴቶች ዘንድ ሳይቀር መዝሙሩ ደምቆ ይሰማ እንደነበር ነግረውናል። ከማደሪያቸው ወጥተው ሲያዳምጡ አምሽተዋል። ግማሹም በእንባ።

መዝሙሩ መዘመር ሲጀምር ወታደሮች በአካባቢው  ነበሩ። ለመግባት ግን አልደፈሩም። ተዉም አላሉንም። እንግባም ቢሉ ተማሪው ግጥም አድርጎ ሞልቶታል። ቦታ የለም። ያ አጋጣሚ ወታደራዊውን መንግሥት ይዞት የነበረው “አምላክ የለሽነት” ዋጋ ማጣቱን፣ ዘመን መቀየሩን በገሃድ የሚያመለክት ነበር። በርግጥም አንድ ክስተት በታሪክ ሚዛን የሚመዘነው ካለፉ በኋላ እንጂ በዚያን ወቅት ራሱ ታሪክ በመሠራትና በመገንባት ላይ መሆኑን ለመረዳት በአስተሳሰብ ምጡቅ መሆን ወይም ነቢይነት ይጠይቃል።

(ይቀጥላል) 

47 comments:

Anonymous said...

Dn Ephrem thanks for sharing.Cant wait to read part 5!!!

Anonymous said...

wow I love the way you present it!!! Keep it up ..........Menew Yemayalek Bihone.

Anonymous said...

A thrilling experience, please don't make it short, we are waiting for the next part.

Anonymous said...

Dn Ephrem, KHY

Hiwot

nani said...

What a great short memoir! Thank you for sharing such a wonderful encounter of your life. That is what we lack today...the drive, the love, the bond between one another....

Anonymous said...

Very Nice...sweet... Please keep on writing.... we are eager to hear the next. Make it long.Thank You

tariku said...

"መዝሙር የሚያቀርቡት መዘምራኑ ቆርኪያቸውን ቀጥቅጠው ጸናጽሉን፣ የላስቲክ ጀሪካኑን ለከበሮነት አውለዋል። ቀኝ ጌታ ይቻለዋል ጎሽሜ ከነእጩ ዶ/ር ንዋይ ገሰሰ ጋር መዝሙሩን አቀናብረዋል። ዲ/ን አልአዛር አድነው የከበሮው ጌታ ነው። ዲ/ን ሙሉጌታ ኃ/ማርያም እና ሌሎች ዲያቆናት ወንድሞች ኪዳንና ቅዳሴው ሲቀር ያለውን ሥርዓተ ጸሎት አቀናብረዋል። ዳንኤል ክብረት፣ ታደሰ ደጀኔ፣ ግርማ ወ/ሩፋኤል ወዘተ ወዘተ መርሐ ግብሩን አሰናድተዋል። እኔንም አትርሱኝ ዝርዝሩ ውስጥ።"

Dn. Yemigerim Tsinat ena koratinet new. Ene gibi gubae hogne Ye 10 dekika menged heden Yetemuala agelgilot bemiset betekiristian yebereketu tesatafi lemehon yeneberenin sinfina sasibew...eneena wendimochen tazibiyalehu. Yihe tarikachu birtat honognal.Yihe tiwilidem yegubae admaki kemehon balefe yekiristina waga eskemin dires endehone yimaribetal biye asibalehu.

Ahunim Yebetekiristian fertoch nachu ena mechereshachihun yasamirew. Amen.

Tariku
Addis Ababa

Anonymous said...

ኤፍሬም ምን እንደምል አላውቅም፡፡ ደሰ ይላል፡፡ ግን በጣም አጠረ ምነው? የእኛ ልብ በመንጠልጠሉ ምን ትጠቀማለህ? ማንጠልጠሉን አንተን ደስ ካለህ አንጠልጥለው ግን…………እባክህን አፍጥነው፡፡

Anonymous said...

Selamt D/n Ephrem. Hamusim, Arbim Tebqen yaw ketef bilehal. Thank you. I thought I read somewhere that Daniel Kibret did not join you due to health? Now you are telling us he is participant? Just an observation.
yekanadaw

Anonymous said...

i heared many good thnigs about Dr Neway,who is he?please say something in your article

Anonymous said...

Dn Ephrem i really like z experiences u're sharing.keep it up!!!

Anonymous said...

Tks Ababaye,

I saw it late and i cant leave with out reading it. And I missed my bus. Tks for making me late :)

Pls let me get the next part when i come back.

Hiw

Anonymous said...

በጣም አመሰግናለሁ።” ማን ያርዳ፣ የቀበረ፤ መነረ ይንገር፣ የነበ”ረ። እንዲሉ ካንተ መስማቱ ያረካል። መጨረሳውን ለመስማት በጣም ነው የምጓጓው። እንዲህም ስል ለመጨረስ ብለህ እንዳታሳጥረው። አደራ;; ለትረካውም ጥሩ ጊዜ ነው የመረጥከው። መድሃኔዓለም በረከቱን ያብዛልህ
መንግሥቱ አሰበ

Eccle. said...

በግዜው ባልኖርም ሁሌ በተነሳ ቁጥር እንደ አዲስ የሚያጓጓኝ ታሪክ ቢኖር የብላቴ ነገር ነው:: 4ቱንም ክፍሎች ባንድ ቀን ማንበቤ በጀኝ ልቤ ተንጠልጥላ ቀርታ ነበር:: ሳስበው ጎበዝ ሰው ቢያገኝ ከመጣጥፍ አልፎ አሪፍ ፊልም የሚወጣው ይመስለኛል:: ታስቦም ከሆነ እሰየው ካልሆነ እስቲ እንሞክረው(ያቅሜን አግዛለሁ)

መክ.

D.L.G said...

በወቅቱ በቦታው ነበርኩ የጻፍከው ሁሉ እውነት ነው። ያን ጊዜ ዲያቆን አሁን ቀኝ ጌታ ይቻለዋል ጎሽሜ የጀሪካኑን ከበሮ ሲመታው ልክ እውነተኛ ከበሮ ነበር የሚመስለው።ከሁሉም ግርማ መታፈሪያን እወደው ነበር ጠና ያለና በምክር የሚያረጋጋን ነበር ደግሞ ከሁሉም ትንሹና ያን ጊዜ እኔን ይመስለኝ የነበረው ኤፍሬም እሸቴ ስለእመቤታችን ሲሰብክ ልቤ ይነካ ነበር።ከሁሉም ግን ዲያቆን ዳንአል ክብረት እያዝናና/እያሳቀ የሚሰብከው ስብከት አይረሳኝም። ተገርፎ ተሰቅሎ የሞተው አንበሳ ተገንዞ በጨርቅ ተቀብሮ እንደሬሳ በሞት እጅ ተይዞ አልቀረም ተነሳ እናምናለን ትንሳኤህን በስልጣንህ መነሳትህን አርአያ ነውና ለሁላችን….ዲ.ይቻለዋል በልቤ የቀረጸው መዝሙር ነው ለትንሳኤ 1983ዓ.ም በብላቴ ኬስፓን ውስጥ። ከ1ኛ ብርጌድ፣1ኛ ሻለቃ፣1ኛ የመቶ 2ኛ ጓድ የነበርኩ ነኝ ይቆየን!

Emuye said...

Wey gud Ababaye, Endet des yilal? be and wekt and wendime yalewu neger tiz alegn. "Egna yane yasalefnewu chigir zare enante betestekakele huneta lay honachihu endtageleglu kalhone tadya ya hulu mekera lemindinewu?" leka endih honachihu newu zare lay lalewu yamechachachihulen yezarem tesfawochachin nachihuna Egziabher yabertachihu.


ENWEDACHIHUALEN!!!

Lake said...

ደሰ ይላል፡፡ ግን በጣም አጠረ ምነው? የእኛ ልብ በመንጠልጠሉ ምን ትጠቀማለህ?
lake sheto

Anonymous said...

“ያ አጋጣሚ ወታደራዊውን መንግሥት ይዞት የነበረው “አምላክ የለሽነት” ዋጋ ማጣቱን፣ ዘመን መቀየሩን በገሃድ የሚያመለክት ነበር።”
ድንቅ እይታ።
እግዚአብሔር እጆችህን ይባርክ።

Anonymous said...

EPh - kante ga 5 birged ina 4gna shaleqa neberku .ineziya Amlake qidusan Igziabher yefeqedachew yebereha mishtochachin min yahl waga indeneberachew sasb hilm inji iwn aymeslum .yebinbi quntchawn ina Shertatewn chemro yeberehawn welafen,sinelibunawi chanawochachinn bemulu be tibeb yalefnbachew gizeyat neberu . ye Abatochachin Amlak yetemesegene yihun .Mihmenan hoy hulachiu zare yetesebesebachihu... iyale sizemr yeneberewn sew tastawsewaleh ? isu negn

Anonymous said...

God bless you Dn Ephrem,

I can't say anything!!!!! what I can is, to feel my hot tears flowing on my face, but I like it. In one way or another we are part of this history. I like it very much my dearest brother. Keep it up!!!

Anonymous said...

Dn Epherem,

Thank you very much for sharing your real experience. It is unforgettable history... It also play vital role in our modern church services...It will also bring many changes in our country very soon.

Tesfa , Uk

Anonymous said...

Sorry, I did n't read carefully so I missed about Daniel. Now I got it. Thanks Aleqa!
yekanadaw

Anonymous said...

ዲያቆን ኤፍሬም በጣም እናመሰግናለን፡፡ እባክህ በወቅቱ የነበሩትንም እህቶች እንዳትረሳቸው፡፡ በቦታው ባንኖርም ለግንቦት ልደታ በአጭሩ ዶክተር ንዋይ እና ሌሎቹም ሲናገሩ ሰምቻለሁና አደራ በደንብ ጻፈው፡፡ ቢቻል በመጽሐፍ መልክ ቢዘጋጅ፡፡ የማኀበረ ቅዱሳን መሠረቶች ናችሁ፡፡ የቤተክርስቲያን ጌጦች መድመቂያዋ ፈርጦች በርቱ፡፡

ኤፍሬም እሸቴ said...

@ Yekanadaw,

I know you overlooked it. No worries my "Canada". lol

Mahlet (እሚ) said...

Weye gud Ababa I feel like I am in and I have been on Belate now.This is the revival of a great spirit.Please tell us more

Thank you

sewit said...

መዝሙር የሚያቀርቡት መዘምራኑ ቆርኪያቸውን ቀጥቅጠው ጸናጽሉን፣ የላስቲክ ጀሪካኑን ለከበሮነት አውለዋል!!! I really want to share my feeling but I couldn’t find words and I don't know where to start and stop!!! መድሃኔዓለም በረከቱን ያብዛልህ

Anonymous said...

inspiring!!

ሰማሀኝ said...

በጣም እናመሰግናለን ዲ.ን ኤፍሬም
ይሄንን ለማያውቀው ትውልድ እንደዚህ በጽሁፍ መቅረቡ ጥሩ ነው
ያኔ የነበራችሁን ትጋት እና ቅናት እና ዛሬ ያለውን ዝለታችንን አይተን እንድንተጋ ይቀሰቅሳል ብየ አስባለሁ:: ነገር ግን ትንሽ ዘርዘር ብታደርገው እና አንዳንድ ለየት ያሉ አሳዛኝ እና አስገራሚ ገጠመኞችን ያንተንም ሆነ የሌሎችን ፈቃደኛ ከሆኑ ማለት ነው ጠለቅ አድርገህ ብታቀርባቸው ጥሩ ነው:: የበለጠ ያረካል ያስተምራልም:: ሌላው ደግም የዚህ ታሪክ ገጠመኝ
አሁን ላለው ትውልድ ያለውን አንድምታ አብረህ ብትገልጸው የበለጠ አስተማሪ ይሆናል::

ሰማሀኝ

Anonymous said...

I have known Dr Neway for many years in Jimma tena sayenes ...He is devout christian...sacrificed his life during medical school for ETOC...created awareness and converted so many nonfollowers to our great church.His christianity was beyond lipservice ...I crowned him to the highest level in church hierarchy...

Ameha said...

ሠላም ዲ/ን ኤፍሬም! ለረጅም ዘመን ስናፍቀው የነበረውን የብላቴን ውሎዋችሁን በእግዚአብሔር ፈቃድ ካንተ በ"መስማቴ" (በማወቄ) በጣም ደስ ብሎኛል። በየዕለቱ የምታወጣው ጽሑፍ ግን በጣም አጠረ። ልቤ ተንጠልጥላ፣ ተንጠልጥላ ጉሮሮዬ ጋር ልትደርስ ትንሽ ቀርቷታል። እስኪ በዚህ አጋጣሚ ዕንቆቅልሽ ሆኖ የቀረውን የአቡነ ጎርጎርዮስ አሟሟት ሁኔታን አስረዳን።
በተረፈ ይህንን ጽሑፍህን በመጽሐፍ መልክ አዘጋጅተህ ብታወጣው በአንድ በኩል እንደ እኔ ዓይነቱ ሰው ታሪኩን አንብቦ ብዙ ትምህርት ሊያገኝበት ይችላል፤ በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፉ ተሽጦ ለማህበሩ ሕንፃ ማጠናቀቂያ ሊውል ይችላል ብዬ አምናለሁ።
እኛ በማናውቀው፣ እግዚአብሔር በሚያውቀው እናንተን በዚያ ቀውጢ ዘመን ያለ ነገር ብላቴን አላስገባችሁም። ዛሬ ላይ ቆሜ ያንን ዘመን ሳስበው፣ እግዚአብሔር እናንተን ባያስነሳ ኖሮ ዛሬ ቤተ ክርስትያናችን ምን ዓይነት አዘቅት ውስጥ ትገባ ነበረ? ለማንኛውም፣ እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን ይባርክ!

Anonymous said...

OMG i feel like i have been their with you guys...i will never get bored hearing about Blate. Especially we, mekelle university students were very lucky since we had one of those brothers from blate...D/N Hilu...he usedto tell us about it repeatedly and we were listining and listening......you know what makes me happy you guys are alive and we don't need story teller to hear about it....long life brothers, you are our strangth.Thank you for sharing Dn.Epherem

Anonymous said...

Dn Ephrem,

I have been in Jimma around 1998 G.C. Although Dr. Neway was not there at that time, we invited him (Gibi Gubae) with his wife sort of "mels", I know him very well since I got a chance to meet him in different programs. But, I think you overlooked one critical person for Jimma Gibi Gubae Dn. Asamnew, he may not want to be mentioned in public medias, but he was part of the Blate history. Me as a person and all my colleagues at Jimma have benefited a lot from vast experience of him. He used to tell us about Blate, especially about Abune Gorgorios, OMG, it was very impressive, thanks for the "tach bet" anyways just to mention him in this history.

Thank you

Anonymous said...

batame atara tareko

Anonymous said...

ኤፍሬም ትንሳኤ ሊሆን ነው እኮ የብላቴውን ህማማት ሳትጨርሰው፡፡

Tzedallas said...

thank you ababa

Anonymous said...

What a great history. Please keep it up!!!

ጥበበ ስላሴ said...

መታወቅ ያለበትን የማህበሩን ታሪክ እየነገርከን ስለሆነ እግዚአብሔር ይስጥህ፡፡ የናንተ የበዓል ዝግጅት በወቅቱ በኢትዮጲያ ሬድዮ ተላልፎ ሰምቼው ነበር፡፡ እንዴት እንደተላለፈ ብትነግረን መልካም ነው፡፡

Anonymous said...

Ere befetereh cherisilin tarikun....what a sespence??? i just can't wait.

ኤፍሬም እሸቴ said...

Dear all,
I beg your patience and apology for more time. I am working on the articles and come to you as soon as possible.
Thank you and God bless.
Melkam Semune Himmamat!!!

Anonymous said...

My dear Efrem, I appreciate your flash back. I understand the difficulty of going back and remember everything, but I crucially advise to take time and include prominent figures in the making of history. My Heart is telling me that the guys you mentioned are not as illustrative as they have to be. It is better to write this altogether with the guys you mentioned and those you forgot, b/c it may diminish the contributions of others and will only give blurred view of the past.
How Could you forget Abrham, the Jimma, Dn Assaminew the Jimma, Dn Abayneh of the Building College, Tariku of the Black Lion....etc

Though the pre-meeting in Zeway had helped very much in the coming together, the most important contributor is the gubae which was being held in 'sewaswo birhan kidus Paulos keftegha menfesawi timhert bet'. There most of children of the church come to know each other and was simple for them to unite in Bilate.

ኤፍሬም እሸቴ said...

Dear Last Annonym,
Thank you for your comments, suggestions and reminders. As you might have noticed, I write only about my recollections from my mind, and so far I covered one week time of our stay in Bilate. I hope other brothers like yourself will remind me more of events and people. This, however, is no detail recount of events. I am sure others will add up their experiences. Don't take my recollections as total and final.

EE

Anonymous said...

ጤና ይስጥልኝ።
የሚቀጥለውን መጠበቅ ገደለኝ። እዚህ አሜሪካ ነፃ (fee staff)
ነገር ለምደን። ማንበብ የተውኩትን እየመለስከኝ ነወ። መድሃኔዓለም ጥበቡን ያብዛልህ

መ አ
ከሓገረ ማርያም

Anonymous said...

የምትመልሳቸውን መልሶች በአማረኛ ብትመልሳቸው መልካም ነው እንደኢትዮጵያዊነታችን በተረፈ እግዚአብሄር ያበርታህ

Anonymous said...

Dn Ephrem

bekedemy enkon le semon hemamat aderseh eyalh yemenafkwen ena zeweter be leba yalewen neger besefew selastmarhg Egzare Amelak yetmsegen yehon
Yehen ye belatn neger stecreshe bezawem telant mesarey chebetw yenaberw egoch , telant swen lemegedel bonb chebetw yenberw egoch zare be Egzabehar cherent enzeh egoch Mesekel Kerstosen chebetw endalwm bedenb beteterkeln melekam newe
Egzabehar amelak segawen yabezalh s Z canada.

Anonymous said...

pleassssssssssssssssssssssssssssssssssssss the next parts. I can't wait.

Beakal said...

Ababaye betam des yilal

Anonymous said...

ምን ያደርጋል ታዲያ ጅማሬው እንደዚህ መልካምና ደስ የሚያሰኝ ሆኖ ሳለ አሁን የሚታየው ፍሬ ግን ክፋት ተንኮልና ከወንጌል ውጭ የሆነ ፓለቲካዊ ይዘት ያለው እንቅስቃሴ ሆኖ እርፍ አለው እንጂ:: ምናልባት ቆም ብሎ እራስን በቃሉ መስተዋት ማየት ሳይሻል የሚቀር አይመስላችሁም:: አዎ ወጣቱማ ምንጊዜም ንጹህ ህሊናና ቅን ልብ ይዞ ነበር በብላቴንም በአሲምባም ለወገኑና ለአገሩ መሻሻል የተንሳው ብሎም መስዋእት የከፈለው:: ጩልሌዎች ትኩስና ችኩል ስሜታዊነቱን ተጠቅመው መጨረሻውን ውጤት አልባና ከንቱ አደረጉበትን እንጂ:: ይኸን የመሰለው ድርጊታችን/ድካምና ውድቀት ለምን ይደጋገምብናል? እስቲ አሁን እየሆነ ያለውን የማ/ቅንን እንቅስቃሴ እንስተውለው? 'ወንድሜ' ኤፍሬም አስውቦ እንዳቀረበው ጅማሬ ነው እየሆነ ያለው? ይህ ለወገን ተብሎ በለጋ ወጣቶች ቅን አስተሳሰብ የተመሰረት ማህበር (ያውም ቅዱስ በሚል ስም) ተግባሩ ይፈተሽ የተነሳለትን ሕዝብ እንደ መሪዎቻችን በዘር ማነካከስና ቤት ክርስቲያናችን ከእውነተኛው የጌታ ቃል የባሰውኑ እንድታፈነግጥ ማድረግ ነውን??? እባካችሁ መልስሉኝ?? በትናንት መልካም የጅማሬ ታሪክ ብቻ ሆዳችንን አትሙሉት የደረስንበትንም እንጠቃቅሰው እንዘርዝረው እናስርዳው የሚታይ ስለሆነ::

ቸሩ አምላክ ለቤ/ክርስቲያናችንና ለሕዝባችን ይድረስ!!

ክብር ለአምላካችን ይሁን!!!

ብዙ ተሳትፎ ባይኖረኝም የጅማሬው በረከት ተቋዳሽ የነበርኩ ነኝ

ፍቅር

Blog Archive