Wednesday, July 13, 2011

ት/ቤት ሲዘጋ … በአሜሪካ

በዚህ በአሜሪካ አሁን በጋ (Summer) ነው። ብዙ ሠራተኞች እረፍት ለመውጣት ጥሩ አጋጣሚ አድርገው የሚጠቀሙበት ጊዜ ይህ የበጋው ወራት ነው። ት/ቤትም ተዘግቷል። ልጆቹ በሙሉ በየመንገዱ፣ በየመዝናኛው ይተረማመሳሉ። በተለይ ወደ ማታ ላይ ሕጻናቱን አምጥቶ የሚያፈሳቸው ማን እንደሆነ እንጃ።


ት/ቤት ሲዘጋ ወላጅ ሁሉ ሕጻናቱን የሚያስቀምጥበት ሥፍራ መፈለግ አለበት። ት/ቤት የሚፈለገው ልጆቹ ሔደው ዕውቀት እንዲቀስሙ ብቻ ሳይሆን መዋያም እንዲያገኙ ነው። ልጆችህን ት/ቤት ካልላህክ የት ታደርጋቸዋለህ? ጎረቤት ትቻቸው ልሒድ ወይም ሠራተኛ ልቅጠርላቸው አይባል ነገር። ሠራተኛ እንኳን አሜሪካ ኢትዮጵያም እየጠፋ ነው። ዕድሜ ለት/ቤት፤ እዚያ አስቀምጦ ወደ ሥራ።

እንዲህ ዓይነቱ የአሜሪካው የበጋ ወራት ሲመጣ ደግሞ ልጆቹን ማስቀመጫ ቦታ፣ የሚሠሩት ሥራ መስጠት ያስፈልጋል። አለበለዚያ ት/ቤት ይዟቸው የነበሩት ልጆች ተለቀው የማይሆን ነገር ውስጥ ሊገቡ ይቻላሉ። ይህንን ለመታደግ “ልጆቻችሁን እንያዝላችሁ፣ እናስጠናላችሁ፣ ስፖርት እናሰልጥንላችሁ” ወዘተ ወዘተ የሚሉ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን ማየት የተለመደ ነው። እናም ልጆቻችንን በአንዱ ቦታ በጋውን እንዲያሳልፉ በማስመዝገብ፣ ካለችን ቆጥበን በመክፈል ልጆቹ ትምህርትም መዝናኛም ባለበት ሁኔታ እረፍታቸውን እንዲያሳልፉ እናደርጋለን።

ይህ ዓይነቱ አጋጣሚ መቸም እኔ ራሴ ልጅ በነበርኩበት ጊዜ፣ ት/ቤት ሲዘጋ እንዴት አሳልፍ እንደነበር እንዳስታውስኝ ያደርገኛል። ያኔ ት/ቤት መዝጊያ ሰኔ 30 ነበር። “ሰኔ 30፤ የተማሪ አበሳ” ይባልም ነበር። የሚያልፈው እና የሚወድቀው የሚለይበት፤ ካርዳችንን ተቀብለን ግማሹ በደስታ፣ ግማሹ በልቅሶ ወደቤቱ የሚሔድበት የልጅነታችን አጓጊ ቀንም ነበር።

ተማሪዎች ሲጣሉ እና ቂም ሲያያዙ “ቆይ፣ ሰኔ 30 ያገናኘን” መባባል የተለመደ ነበር። በክረምቱ ምክንያት ት/ቤት ስለሚዘጋ የተጣሉትን ደቁሶ፣ ዓመቱ ሙሉ አንጀት ሲያቃጥል የነበረውን ሁሉ ዋጋውን ሰጥቶ እስከ መስከረም ነገሩ ስለሚረሳ ከአስተማሪ ቅጣት ለማምለጥ ስለሚያስችል ነበር - ሐሳቡ። አንዳንድ ጊዜ አስተማሪውም “ሊቀምስ” ይችላል። ተማሪ ጥጋበኛ አይደል?

ት/ቤት ከተዘጋ በኋላ ተማሪው ከጭቃው እና ከዝናቡ ጋር ጭቃ እና ዝናብ ሆኖ ወደሚያሳልፍበት የሁለት ወራት ጊዜ ይገባል። ከገጠር አካባቢ የመጣው ተማሪ ወደ እርሻው፣ ወደ ጉልጓሎው፣ ወደ ጥጃ ጥበቃው ይመለሳል። የከተማውም ልጅ ቢሆን፣ ከጥቂቱ በስተቀር፣ ቤተሰቦቹን በአቅሙ ወደ መርዳት የመሔድ ግዴታ አለበት። እንደማስታውሰው ክረምት በመጣ ቁጥር ጭቃ መስለን እና ጭቃ ሆነን የአቅማችንን “ለወላጆቻችን ለመታዘዝ” እንሞክር ነበር።

ክረምት ለጨዋታ እና ለመዝናናት አይመችም። ኳስ ለመጫወት ሜዳው በሙሉ በውሃ ይሸፈናል። እንኳን የመንደራችን ሜዳዎች አዲስ አበባ ስቴዲየም ራሱ ውሃ ይቋጥራል። የቤት ውስጥ መጫወቻ ሥፍራ፣ ኳስ ሜዳ የሌለባት ብቸኛ አገር መቸም ኢትዮጵያችን ሳትሆን አትቀርም። እንኳን በየመንደሩ ያለን ሕጻናት ብሔራዊ ቡድኑም በክረምት የሚጫወትበት ሜዳ የሌለበት አገር ነው።

በክረምቱ ትልቁ መዝናኛችን፣ ከቤተሰባችንም ቁጣ ለመዳን፣ ኩሽኔታችንን እየነዳን የማገዶ እንጨት ሰበራ ወደ ጫካ እንወጣለን። ብዙ ጊዜ ዝናሙ የሚዘንበው ወደ ከሰዓት በኋላ ነው። ለምን በዚያ ፕሮግራም እንደሚመጣ እግዜር ይወቀው። ቁልፉ በእርሱ እጅ ነው። ብቻ ጳጉሜን ላይ ካልሆነ ዝናቡ በጠዋቱ አያስቸግረንም። ቁርሳችንን በልተን ወደ ጫካ የተተኮስን የማታው ዝናብ ሳይጠምደን እንመለሳለን። አንዴ ከያዘ የማይለቀው አህያ የማይሸከመው ዝናብ ከመጣ የልጅ ጀርባችን ያጎብጠዋል፤ በረዶው መላጣ ራሳችንን እየቀጠቀጠ መግቢያ ያሳጣናል። ቆረቆራችንን ያፈርጠዋል።

ቢሆንም ቤት ስንደርስ የወላጆቻችን ፈገግታ እና ምርቃት ያንን ሁሉ ነገር ያስረሳናል። ትኩስ ትኩሱ ይቀርብልናል። ከትኩስ ሽሮ እስከ ትኩስ አሹቅ (ዲዘርት መሆኑ ነው) በደስታ ይቀርብልናል። ያንን በራበው ሆዳችን ላክ ላክ እያደረግን እንቅልፍ ሰዓታችንን እንጠብቃለን። ቴሌቪዥን የለ፣ ፊልም የለ፣ እንዳሁኑ ልጆች “ጌም የለ” ….።

ሐምሌን እንዲህ ጨርሰን ነሐሴ ሲመጣ ከእንጨት ለቀማውም ከሌላውም ሥራ የሚገላለግለን የፍልሰታ ጾም ነው። ፍልሰታ የልጆች ጾም ስለሚባል አንገታችን ላይ ሚጢጢ ያንገት ልብስ እየጠመጠሙ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይልኩናል። እውነቱን ለመናገር ከጽድቁ ይልቅ ትዝ የሚለን ከቅዳሴ በኋላ የምንበላው ንፍሮ እና ቆርበን ስንመጣ እቤት የሚጠብቀን እንክብካቤ ነው። የቆረብን ቀንማ ምን ብናጠፋ ማን ንክች ሊያደርገን? ባይሆን ባይሆን በዕዳ ለሌላ ቀን ያስተላልፉታል። በሚቀጥለው ጊዜ በጥፋት ስንገኝ የቆረብን ዕለት ያናደድናቸውን ደምረው ቂማቸውን ይወጡብናል።

እዚህ የፈረንጁ አገር፣ ልጆቹ ትምህርት ቤታቸው ሲዘጋ ምን እንደሚሆኑ እና ምን እንደሚያደርጉ ማሰብ የወላጅ ትልቁ ጭንቀት ነው። አንዱ ቦታ አስቀድሞ ተመዝግቦ እና ከፍሎ መዘጋጀት የወላጅ ግዴታው ነው። ገና በሙዓለ ሕጻናት ዕድሜ ካሉት እስከ ወጠጤ ጎረምሳዎቹ (Teenagers) ድረስ የሚውሉበት ሥፍራ አላቸው። ያንን የሚያዘጋጁት ደግሞ የግል ተቋማትም፣ የመንግሥት ተቋማትም ጭምር ናቸው። መንግሥት ለወጣቱና ለሕጻኑ ካላሰበ ምኑን መንግሥት ሆነው?

በምኖርበት አካባቢ ልጆችን በዚህ የዕረፍት ወቅት ከሚያስተናግዱት መካከል የአካባቢው መስተዳደሮች (ቀበሌ እንበላቸው?) አንደኛዎቹ ናቸው። በመጠነኛ ክፍያ ለሕጻናቱ እና ለወጣቶቹ መርሐ ግብሮች ያሰናዳሉ። የተለያዩ ስፖርቶች፣ ጉብኝቶች፣ ዋናዎች፣ እንደየዕድሜያቸው ከእኩዮቻቸው ጋር ትውውቆች እና ጨዋታዎች ያዘጋጁላቸዋል። ለአንድ ልጅ በቀን ከ50 ዶላር ያላነሰ ያስከፍላሉ። የግሎቹ የሚያስከፍሉት ከዚህ በጣም ይወደዳል። ይህ የቀበሌዎቹ ሰርቪስ ገሚሱም በተለያየ መልኩ ሳይደጎም የሚቀር አልመሰለኝም። አለበለዚያ እንዲህ ርካሽ ሊሆን አይችልም ነበር።

ከወደድኩላቸው ዝግጅት አንዱ ሕጻናቱን እና ወጣቶቹን ይዘው ወደ ሙዚየም ጉዞ ማድረጋቸው ነው። እንደየዕድሜያቸው የሚመጥናቸውን ያሳዩዋቸዋል። ስለ አገራቸው እንዲያውቁ ያስተምሯቸዋል። በዚያ ዕድሜ “ሙዚየም መሔድን” እንዲለምዱም በልቡናቸው ይቀርጹባቸዋል። እዚያ ባለው ቤተ መጻሕፍትም እንዲያነቡ ያበረታቷቸዋል።

መሸት ሲል ወላጅ ሁሉ ልጁን ከያስቀመጠበት ይሰበስባል። ወራቱ በጋ ስለሆነ ፀሐይ ቶሎ አትጠልቅም። ይህንን ጽሑፍ እየጻፍኩ ባለሁበት ሰዓት (ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ) ውጪው ወከክ ብሎ ይታየኛል። ፀሐይ ወደ ቤቷ ተጠቃላ ለመግባት ትንሽ ይቀራታል። ስለዚህ ልጆቹን ወደ ውጪ ይዞ መውጣት ለሚችል ወላጅ ጊዜው ይመቻል። ሳይመሽ ወደቤት ከገቡ ተሽቀዳድመው እዚያው ቴሌቪዥኑ ላይ እንዳያፈጡ ወላጅ የቻለውን ያህል ይሞክራል። አሜሪካ ላለ ልጅ መቸም ጠላቱ ቴሌቪዥን እና ይኼ ስኳር የሚበዛበት ጣፋጭ ምግብ ነው።

የዚህን የቴሌቪዥንን ነገር፣ በየጣራቸው ላይ ዲሽ የሰቀሉ የአገር ቤት ወላጆችም ሊያስቡበት ይገባል። ዲሽ መግጠማቸውን እንጂ ልጆቻቸው ምን እንደሚያዩ ሳያዉቅ የልጆቻቸው መጥፊያ እንዳይሆንባቸው ብርቱ ጥንቃቄ ይፈልጋል። ቴሌቪዥን ሕጻናቱን ያደንዛል። ያደነዝዛል። ከማንበብ ይልቅ ፊልም እና “ጌም” ብቻ የሚወዱ ስልቹዎች ያደርጋቸዋል። ብዙ ሰዓት ቁጭ ስለሚሉም ሰውነታቸው አላስፈላጊ በሆነ ውፍረት ይወጠራል። ገና በልጅነታቸው የበሽታ ዓይነት ይሸከማሉ።

ድሮ ድሮ ወፍራም ልጅ ስናይ “የሀብታም ልጆች” እያልን ስንቀናባቸው ኖረን አሁን ቀጭን መሆን ዋጋ ያለው አገር መጣንና በተራችን ልጆቻችን እንዳይወፍሩ እንጨነቃለን። በየጊዜው የነርሱን ኪሎ መለካቱ፣ ወፈሩ አልወፈሩ እያሉ ማሰቡ የአሜሪካ ወላጅ አንዱ ግዴታ ነው። “ሁሉ ተፈቅዷል ሁሉ ግን አይጠቅምም” እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ያገኙትን ሁሉ መብላቱ ዕዳው ብዙ ነው። ድሮ አገር ቤት “ምነው ልጄ ወፍራም በሆነልኝ” ሲባል ሰምተን አሁን ደግሞ (አሜሪካ) “ኧረ ልጄ ወፈረብኝ/ እየወፈረብኝ ነው/ ሊወፍርብኝ ነው” የሚል ጭንቀት መስማት ግርምት ይፈጥራል።

በሁሉም በሁሉም፣ በአሜሪካ ት/ቤት ሲዘጋ፣ ከውፍረታቸው እስከ መዋያ ቦታቸው፣ ከትምህርታቸው እስከ መዝናኛቸው ወላጅ የቤት ሥራ የሚበዛበት ጊዜ ይሆናል። እናም አንዳንዴ “ምናለበት የሀገሬ ልጆች እንዲህ ዓይነቱን የልጆች መዋያ በየመንደሩ ባገኙ” የሚል ቁጭት ውስጤን ይበላኛል። ሜዳው ሁሉ ዛኒጋባ እየተቀየሰበት፣ ልጆቹን አንድም ለሥራ ፈትነት፣ አንድም ለጫት ቃሚነት፣ አሁን እንደምሰማው ደግሞ “ለሺሻ ሱሰኝነት” አሳልፈን እየሰጠናቸው ነው።

ቢያንስ ቢያንስ እነዚህ አሁን የሚገነቡትን “ኮንዶሚኒየም” ሕንጻዎች እና አዳዲስ መንደሮች እንኳን በሕግ ደረጃ ለሕጻናት መጫወቻ የሚሆን ቦታ እና አረንጓዴ ሥፍራ እንዲኖራቸው በማስገደድ ልጆቻችን እንደ ማንኛውም ልጅ የሚቦርቁበት፣ የሚጫወቱበት፣ ወደ አስፓልት ከመውጣት ይልቅ ከመንገድ የሚርቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል። ተደርጎ ከሆነም ደግሞ እሰየው ደስ ያሰኛል። እንቅፋት የእግራችንን ጥፍር እየነቀለውም ቢሆን፣ የወዳደቁ ነገሮች እየወጉንም ቢሆን ኳስ ያንከባለልንበት “እንትና ሰፈር ሜዳ፣ ቀበሌ ምንትስ ሜዳ” ናፈቀኝ። ለአሁኖቹም ሕጻናት ተመኘሁላቸው።


18 comments:

Abes Feleke said...

Having a child in America is a big and a tough responsibility ; even sometimes it is like being in jail, especially for a certain period of time, until he/ she goes to school.

One need to watch the child 24/7, otherwise one has to pay a lot of money, which you wouldn't even make it. It is very expensive to raise a child, takes too much time and energy, it also needs to take some marriages away, and working night shifts. Going to school may be very difficult (time and money constraints).

The good news, though, is that taking care of your own kid will give you the best satisfaction life can offer. It also gives you a chance to build a parent-child relationship.

What I would like to pass here, from my own experience, to people who wants to have a baby or wants to bring a child from home is that Considering so many things/ factors, including I mentioned above, must be vital.

It is a different experience for Ethiopian dude being a father and taking care of his own child at home, probably the whole day.

Anonymous said...

Girum new Dn. Ephrem! Egziabher Yestlen!

ቢያንስ ቢያንስ እነዚህ አሁን የሚገነቡትን “ኮንዶሚኒየም” ሕንጻዎች እና አዳዲስ መንደሮች እንኳን በሕግ ደረጃ ለሕጻናት መጫወቻ የሚሆን ቦታ እና አረንጓዴ ሥፍራ እንዲኖራቸው በማስገደድ ልጆቻችን እንደ ማንኛውም ልጅ የሚቦርቁበት፣ የሚጫወቱበት፣ ወደ አስፓልት ከመውጣት ይልቅ ከመንገድ የሚርቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል።

I know all Ethiopian Engineers know the significance of having a "Green Area", but not sure why they don't consider it as a mandatory requirement when they design those constructions.

Anonymous said...

ስለ ጽሑፉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ። አንድ ያልገባኝ ነገር ግን አለ።ይህም
ለምን በዚህ ጊዜ ት/ት በአሜሪካ ተዘጋ?
እኛ ሀገር እንደሚታወቀው ይህ ወቅት የዝናብ ወቅት ነው ለትምህርት አይደለም ስራም ለመስራት በጣም አስቸጋሪ ነው።
ዋናው ግን አብዛኛው ህዝብ ገበሬ ተማሪውም የገበሬ ልጅ ነው። ይህም በመሆኑ የስራ ወቅት ነው በዚህ ስአት ካልሰራ መማሪያ ያጥራል። እንዳውም በገጠሩ አካባቢ ያሉ ት/ት ቤቶች እስከ ጥቅምት አጋማሽ ድረስ ት/ት አይጀምሩም ነበር ቤተሰብ አይልክም ልጁን።
እኔን ያልገባኝ በሀገረ አሜሪካ ያለው ምክንያት ምንድን ነው?

Anonymous said...

ረምቱ ትልቁ መዝናኛችን፣ ከቤተሰባችንም ቁጣ ለመዳን፣ ኩሽኔታችንን እየነዳን የማገዶ እንጨት ሰበራ ወደ ጫካ እንወጣለን betame dn eframe
teztayene charkbege
bertalene

በፍቃዱ ኃይሉ said...

የልጅነት ትዝታዬን ቀሰቀስክብኝ:: አሪፍ ጽሁፍ ነው::

Anonymous said...

Nice article!!! Please keen on writing Dn Efriem

Anonymous said...

lejochachenen bazeh geza tatakeman konekachenen benasetamer tero nawe

Anonymous said...

የልጅነት ትዝታዬን ቀሰቀስክብኝ

Anonymous said...

" የቤት ውስጥ መጫወቻ ሥፍራ፣ ኳስ ሜዳ የሌለባት ብቸኛ አገር መቸም ኢትዮጵያችን ሳትሆን አትቀርም። እንኳን በየመንደሩ ያለን ሕጻናት ብሔራዊ ቡድኑም በክረምት የሚጫወትበት ሜዳ የሌለበት አገር ነው "

እርግጥ እውነት ነው። ግን ብቸኛ ሀገር?! ምነው?! የግድ እንደዚህ መጋነን አለብት። የሚመስለኝ ብትል እንዴት ባማረብህ። ምክንያቱም ምን አልባት አንተ ኢትዮጵያንና አሜሪካንን ብቻ ይሆናልና ያወዳደርከው። እንደው ስታሰበው ሌላው ቀርቶ ስንቱ አፍሪካዊ ሀገር ይሆን ይህንን ያሟላ?
እንደው የጹሁፉ አላማና አጻጻፉ ሽጋ ሆኖ ሳለ፤ እንዲህ ነገሩን መለጠጥ አላስፈላጊ ነበር።

ቸር ያቆየን

Anonymous said...

እርግ እርግ አይይይይይ....እንደው ሰንቱን ትዝታ ቀሰቀስከው አያ። ጭልጥ አልኩ እሳ...ተባረክ።
take me HOME, country Roads to the place i belong.... ልበላ።

ማለፊያ ነው

ኤፍሬም እሸቴ said...

ከፍ ብለው ያሉት ፀሐፊ ያሉት ጥሩ አስተያየት ነው። ትንሽ ለጠጥኩት አይደል? ምናለ ለሌላው ጊዜ አስተካክላለሁ። እርስዎም እንዲሁ አስተያየትዎን መለገስ አያቋርጡኝ።

ዘቢለን ጊዮርጊስ said...

ኤፍሬም ሀሳብህ ጥሩ ነው በርታ አንዳንድ ጊዜ በጣም ትዘገያለህና እባክህን ቢያንስ በሳምንት አንድ ጽሁፍ አስነብበን

ኤፍሬም እሸቴ said...

ዘቢለን፣ አመሰግናለሁ።

Anonymous said...

http://debelo.org/

http://www.zeorthodox.org/

http://www.melakuezezew.info/

http://www.kesisyaredgebremedhin.com/

http://www.adebabay.com/

http://www.betedejene.org/

http://www.aleqayalewtamiru.org/

http://www.mahletzesolomon.com/

http://degusamrawi.blogspot.com

http://www.eotc-mkidusan.org/site/

http://www.mahiberekidusan.org

http://www.tewahedomedia.org

www.tewahedo.org


http://suscopts.org/

http://www.dejeselam.org/

http://mosc.in/

http://www.eotc-nassu.org/

Anonymous said...

Dear Deacon Efrem Eshete,

I appreciate for your posts on every aspect,
but for now i think it is time to discuss on Mahbere Kidusan status.Because it is a big issue to me.

Please say something Deacon

Anonymous said...

እንደ እኔ እንደ እኔ ስለ ማህበሩ አሁን ባለው ሁኔታ በአደባባይ በድጋሚ ዳንኤል እንዳቀረበው መወያያቱ ትንሽ ጊዜ የሚያስፈልገው ይመስለኛል። ለምን ቢባል እሳቱ በነደደበትና ፍሙም ትርክክ ባለበት ሰዓት ቤንዚን መጨመሩ አብሮ ተያይዞ ከመተላቀቅ በቀር ለማንም አይበጀምና፤ በተለይ ለቤተ-ክርስቲያናችን! እርግጥ ዲ. ኤፍሬም በነገሩ ካአመነበት የራሱን አስተያየት መስጠት ይችላል። በእርግጥም በእርሱ የሚያምርበት ይመስለኛል።
1ኛ- የማህበሩ ነባር አባልና በኃላፊነትም ለረጅም ጊዜ የሰራና እየሰራ ያለበመሆኑ፤
2ኛ- የዳንኤልም ወዳጅ በመሆኑ (ደግሞ ይህን ከየት አመጣህ እንዳልባል)።
የሆነው ሆኖ አሁን ግን ጊዜው ነው ብዬ አላምንም። ለማህበሩ ፋታ ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ።
እስኪ መልካሙን ያሰማን።

tibebe said...

i agree with comments presented above...........we are silently losing everything and dying as a nation....as a member of EOTC....brothers living in and outs must work together,discuss to save mk.............

Anonymous said...

Hey Guys I think u all are come forgetting this site is open to public.