ጌታዬ፦
እንደ ሙሴ አንደበተ ጎልዳፋ ብሆን፤ አንተ አንደበት ሆንከኝ።
እንደ ኤልያስ እኔ ብቻ ለአንተ የቆምኩ መስሎኝ ብታበይ ስለ ብዙዎቹ ወዳጆችህ ብለህ ማርከኝ፤
እንደ ጴጥሮስ ቸኩዬ ወድጄህ ቀድሜ ብከዳህ፤ በንስሐ ዕንባ ተቀበልከኝ፤ አብልጠህ አከበርከኝ፤
እንደ ያዕቆብ ደዌ ሥጋ ደዌ ነፍስ ቢጸናብኝ፤ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን ሰጥተህ ፈወስከኝ፤
እንደ ዮሐንስ ብታፈቅረኝ የእናትህን ጣዕም በአንደበቴ ፍቅሯን በልቤ ሳልክልኝ፤ በአማላጅነቷ ጠበቅኸኝ።
ጌታዬ፦ ስለ ቸርነትህ በደብረ ታቦር ክብርህን የገለጥክላቸው የነዚህ ወዳጆችህ ፀጋ በረከት ይድረሰኝ።
አሜን
7 comments:
አሜን አሜን አሜን። እንኳን አደረሰን።
መልካም በዓል ከነመላው ቤተሰብህ።
ቸር ያሰንብተን
Amen! dink tshuf! kale hiwots yasemaln!
Sara Adera
ቃለ ህይወት ያሰማልኝ !!!
እጅግ በጣም ደስ የሚል አገላለጽ ነው። እኔም እንዳንተ ... ስለ ቸርነትህ በደብረ ታቦር ክብርህን የገለጥክላቸው የነዚህ ወዳጆችህ ፀጋ በረከት ይድረሰኝ። ጌታ ሆይ አደራህን አለሁ በለኝ። አሜን!!!!
አሜን
Damay
አሜን
"እንደ ዮሐንስ ብታፈቅረኝ የእናትህን ጣዕም በአንደበቴ ፍቅሯን በልቤ ሳልክልኝ፤ በአማላጅነቷ ጠበቅኸኝ።"
Amen Dn. kale hiwot yasemalin
amen
Post a Comment