ያልተበለሻሸ
ያልተቀላቀለ፣
ከተራሮች ዕድሜ ከዛፎች የላቀ፣
ከተራሮች ዕድሜ ከዛፎች የላቀ፣
ከወንዞቹ
ቀድሞ ከቋጥኙ በፊት
ከሜዳ አራዊት
ከቤቱ እንስሳት
እዚያም አለ
ሕይወት።
“ያገሬ ጎዳና
ውሰደኝ አርቀህ፣
እኔ በተጓዝኩት
አንተ ምን ቸገረህ”፣
በታሪክ በባሕል
ፋፍቶ የዳበረ፣
በፈሪሃ እግዚአብሔር፣
በአንተ-ትብስ-አንቺ
ጠብቆ የደደረ፣
እዚያም
ሕይወት አለ።
በኃይለኞች
ጡጫ በበሽታና ሞት፣
በጦርነት
ዋዕይ በረሃብ እርዛት፣
ተቆርጦ ያልደረቀ
በመከራ ስደት፣
እዚያም አለ
ሕይወት።
ለሺህ ሺህ
ዓመታት ዳፍኖ የኖረ፣
በሞት አጥር
መሐል ፋፍቶ የዳበረ፣
በቡትት በክሳት
ከስሞ ያልወደቀ፣
ወርቅ አልማዝ
በማጣት ያልተደቀደቀ፣
እዚያም ሕይወት
አለ።
(ፌብሩዋሪ
20/2002፣ በርሊን ጀርመን)


6 comments:
አወ ኤፍሬም በትክክል አለ
batame dase yelale
በኃይለኞች ጡጫ በበሽታና ሞት፣
በጦርነት ዋዕይ በረሃብ እርዛት፣
ተቆርጦ ያልደረቀ በመከራ ስደት፣
እዚያም አለ ሕይወት።
wow it's very interesting!!!!!!!!
yamral!
HOW THAT IS INTERSTING.
Post a Comment