Thursday, December 1, 2011

“ሴክስ ቱሪዝም” ያውም እስከ ሰዶማዊነት ድረስ?


(ኤፍሬም እሸቴ/adebabay.com/ READ IN PDF)

በዚህ ሳምንት መጨረሻ አዲስ አበባ በሚደረግ እና ሰዶማዊነትንና ሰዶማውያንን “ለመከላከል” ቀድሞ በተጠራ የ"International Conference on AIDS and STLs in Africa – ICASA" ቅድመ ጉባኤ ምክንያት ሚዲያዎች እና ጦማሪዎች ሐሳባቸውን በመግለጽ ላይ ሲሆኑ “የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ” የተባለው በአገራችን የሚገኙ ዋና ዋና ቤተ እምነቶች በጋራ የሚሳተፉበት ጥምረትም ተቃውሞውን ገልጿል። ይሁን እንጂ የ ICASAን ጉባኤ በዋነኝነት የሚያዘጋጀው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሃይማኖት ጉባኤው ጋዜጣዊ መግለጫውን ከሚሰጥበት ሥፍራ ሚኒስትሩን በመላክ መግለጫ እንዳይሰጥ አድርጓል። በወቅቱ ጋዜጠኞች ያነሷቸው ፎቶግራፎችም በፖሊሶች እንደ ተደመሰሱ ሪፖርተር ጋዜጣና ሌሎች የጡመራ መድረኮች ዘግበዋል።

ወደ ዝርዝሩ ከመግባታችን በፊት ነገሩ ምን እንደሆነ በአጭሩ እናቅርበው። ነገሩ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ሲሆን 16ው “ዓለም አቀፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የአባላዘር በሽታዎች ጉባኤ በአፍሪካ” (16th International Conference on AIDS and STLs in Africa – ICASA) ይባላል። አለመግባባቱን የፈጠረው ግን ይህ ጉባኤ አይደለም። አለመግባባቱን የፈጠረው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ሊደረግ የታሰበው የአፍሪካ ግብረ ሰዶማውያን የቅድመ ኮንፈረንስ ማነቃቂያ ስብሰባ” ነው። ይህንን የግብረ ሰዶማውያን ጉባኤ በመቃወም መግለጫ ለመስጠት የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች ቢሰበሰቡም የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ በቦታው ተገኝተው ከልክለዋል። ጥያቄው ከዚህ ይጀምራል።

1. አዲስ አበባ አፍሪካ መዲና እንደመሆኗ ለቁጥር የሚታክቱ ስብሰባዎች የሚደረጉባት ከተማ እንደሆነች የታወቀ ነው። (ከዜናው 90% ስብሰባ የሚዘግበው ምስክሩ ኢቲቪ ነው።) ስለዚህ ከተማዪቱ ብዙ ስብሰባ ባዘጋጀች ቁጥር ሆቴሎች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ጥሩ ገቢ እንደሚያገኙ እና አገርም ሕዝብም እንደሚጠቀም እናውቃለን። ስለዚህ በተቻለ መጠን ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች በናይሮቢ እና በሌሎች ተቀናቃኝ ከተሞች ከሚደረጉ ይልቅ በአዲስ አበባ ቢደረጉ ተጠቃሚዎች ስለምንሆን ጤና ጥበቃ ጉባኤውን ለማድረግ መጣሩ ተገቢ ነው። ነገር ግን ይህ ጥረቱ የሕዝብን ሃይማኖታዊ መሠረተ እምነት እስከመጣስ ድረስ መሆን የለበትም።

2. ግብረ ሰዶማዊነትን ክርስትናም ሆነ እስልምና አጥብቆ ይቃወመዋል። በክርስትናም ሆነ በእስልምና ሰዶማዊነት ኃጢአት ነው። ይህ ሃይማኖት ነው። ቤተ እምነቶቹ ደግሞ ምእመኖቻቸው ከግብረ ሰዶማዊነት እንዲጠበቁ ማስተማር ግዴታቸው ነው። ግብረ ሰዶማዊነትን ለማስፋፋት እና ሰዶማውያንን ለማበረታታት ጤና ጥበቃ ጉባኤ እንዲደረግ መድረኩን እንዳመቻቸው እና እንደተጋው ሁሉ እነዚህ ቤተ እምነቶችም ሰዶማዊነት ኃጢአት መሆኑን አጥበቀው መናገራቸውን መከልከል አይገባም። ይህ ትልቅ የመብት ጥሰት ነው። መንግሥት በቀጥታ በሃይማኖት ጣልቃ መግባት ብቻ ሳይሆን የጋዜጠኞችንም መብት በመጣስ ያነሷቸው ፎቶግራፎች በፖሊሶች እንዲደመሰሱ መደረጋቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቦልናል። እንዴት ነው ነገሩ?

3. ጤና ጥበቃ ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ መደረጉ ለአገር ኢኮኖሚ ይጠቅማል ብሎ ከሆነ በሌላ አማርኛ “ሴክስ ቱሪዝም”ን እያስፋፋ ነው ማለት ነው። ከአገሪቱ ሕዝብ ከግማሽ በላዩ ወጣት እና ሥራ አጥ በሆነባት አገር ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ለሴክስ ቱሪዝም እንዲጎርፉባትና አገሪቱ ካለባት ቅጥ ያጣ ችግር በላይ እንዲህ ዓይነቱ የባህል ወረራ እንዲካሄድባት መንግሥታዊ ማበረታቻ መስጠት ስሕተት ብቻ ሳይሆን እጅግ በጣም አሳዛኝ ተግባር ነው። በሌላው ዓለም ቢሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ለማቋረጥ ከመሔድ ይልቅ ከሕዝብ ሊያገኙት የሚገባቸውን እምነት ስላጎደሉ ሥልጣናቸውን ወደ መልቀቅ ይሄዱ ነበር።  አገሩ ኢትዮጵያ ስለሆነ አንድ ሚኒስትር የሃይማኖት መሪዎች ያዘጋጁትን ጋዜጣዊ መግለጫ ለማስተጓጎል ቻለ።

4. ድርጊቱ ኢትዮጵያውያን እንዲሸማቀቁ፣ እንዲያፍሩ፣ ራሳቸውን እንዲጠሉ የታሰበበት ያስመስለዋል። መንግሥት እርሱ ከፈቀደው ሐሳብ ውጪ ያሉ ሐሳቦችን ሁሉ በመጨፍለቅ እስከ ሃይማኖታችን ድረስ መድረሱ አስደንጋጭ ነው። ሰዶማዊነት ኃጢአት ነው። ቅዱስ መጽሐፍ የሚነግረን ይህንን ነው። ጤና ጥበቃ የጣሰው ይህንን መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት ነው።

5. ከዚህ አንጻር ሕዝቡ በሃይማኖቱ የማይቀበለውን ነገር መቃወሙ ተገቢ ስለሆነ መንግሥት የራሱን አስተሳሰብ ለመጫን መሞከር የለበትም። ሕዝቡ ስብሰባው እንዲሰረዝ ለማድረግ አቅሙ ባይኖረውም እንኳን እንደማይቀበለው ለመናገር መታገድ የለበትም። ከውጪ አገር የሚመጡ የተወሰኑ የጤና ጥበቃ እንግዶችን ለማስደሰት በሚሊዮኖች የሚቆጠረው ሕዝብ እምነት መዳጥ አይገባውም። ነውር ነው። ነውር ነው። በጣም ነውር ነው። አደራ ይህንንም “ፖለቲካ ነው” እንዳትሉን እነ እንቶኔ።


75 comments:

Anonymous said...

Yigermal.....በሌላው ዓለም ቢሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ለማቋረጥ ከመሔድ ይልቅ ከሕዝብ ሊያገኙት የሚገባቸውን እምነት ስላጎደሉ ሥልጣናቸውን ወደ መልቀቅ ይሄዱ ነበር። አገሩ ኢትዮጵያ ስለሆነ አንድ ሚኒስትር የሃይማኖት መሪዎች ያዘጋጁትን ጋዜጣዊ መግለጫ ለማስተጓጎል ቻለ።

Anonymous said...

I agree Ayate, በጣም በጣም በጣም ነውር ነው

Anonymous said...

ፍፁም ፖለቲካ የለውም፣ መንግስት በህገ መንግስቱና በህዝቡ ያለው ንቀት የገለፀበት እውነታ ነው:: በዚህ አላፊ ጠፊ ምድር አለን ብለን የምንኮራበት ቢኖር ኢትዮጵያዊ ባህላችንና ሃይማኖታችን ብቻ ነው:: ይንንም ካጣን ደግሞ በሰማይም በምድርም ድህነት ይጠናወተናል! ኦ እግዚኦ ተዘከረነ እምመከራ ስጋ ወነፍስ !!!!!!

Anonymous said...

SO sad..cause more than 70% of my HIV patients are gays.Please say NOooooooooooooo.I have seen it in the western world where I live....

Anonymous said...

Now the crackdown escalates and dare to slam the voice of our Religions. The visionary Ethiopians, although a few in number, have long been calling the people of Ethiopia to pay attention that the now EPRDF is DEVASTATING BY NATURE. They have exerted a lot not only to oppose the political philosophy but they let the people know the danger of ethnocentric federalism which is a lethal injection that would dismantle the unity and sovereignty of Etiopia.

For me this act of EPRDF didn't make me feel furious for I know that EPRDF , let me quote among the many, had done bomb plotting in the capital that demanded the lives of innocent civilian.

Recently, It began terrorizing the nation with anti-terrorism law. Journalists set to exile, politicians of big caliber thrown in to Ma'ekelawi, the Great People of Great Nation prescribed to take what I would like to say "FLU Shot" injection called "Akeldama" with no fee.

We must accept the fact that when there is a time rulers go mad with religion (when they become against God), there has to be chaos which is a pretext to big punishment.

May God Bless Ethiopia and Its People Amen

Anonymous said...

Marer metiken new lela min madreg yichalal,Ezih kuchi bilo mambeb mesmat tiruwun medegef metifowun mawugez...

Anonymous said...

ስለ ፖለቲካና ዘማቾዋ ሳይሆን በቃ የሃገራችን ጉዳይ በዚህ ይናቀቅ? ምን አለ ከድሃው ወገናችን ላይ እጃቸውን ቢያነሱ? እግዚያብሄር ሃገራችንን ይባርክ ፡፡ እባካችሁ እንፀልይ እናልቅስ ሁሉም ይደርሳል ማንነታችንን ኢትዮጸያዊነታችን እንዳይበተን፡፡

Anonymous said...

mingist lihizbu bahilina haymanot gidyilish eko yihonew awen eko adilim beadibabay yi Ethiopia tarik ye 300 amet adirigo siyawira,bandira chirk bilo yashofe,Ethiopia ye kirstian desat ayidelichim yale mengist yihan biyadirg agirmem. EPRDF or birasu siltan yimita bicha new tilatu.

Anonymous said...

ኡኡኡኡኡኡኡ ኧረረረረረ የት እንሂድ ተቃጠልን እኮ! አሁንስ ማነው ተስፋችን ? ስለ ሀይማኖታችሁ አትናገሩ ከተባልን ....... እነዚህ ይሉኝታ የለሽ ጅቦች እኮ በልተው ሊጨርሱን ነው፡፡ መሬቷን፣ ቅርሷን፣ ባህሏን፣........ ሸጠሸጠው አለቀባቸው እና እኛኑ መብላት ጀመሩ ኧረ ኡኡኡኡኡኡኡ ..............................

Anonymous said...

ነውር ነው። ነውር ነው። በጣም ነውር ነው።
ሀገሬ ምን መጣብሽ ???

Elizabeth said...

ግብረሰዶማዊነት ኃጢያት ነው በሀገርና በህዝብ ላይ መዓት ያመጣል፡፡ ሰዶማውያን በሰሩት ተመሳሳይ ግብር እግዚአብሔርን ምን ያህል እንዳስቆጣው እና እሳትም ከሰማይ ወርዶ እንዳጠፋቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ተቀምጧል፡፡ ቅዱስ ዳዊትም ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ የሚጠፉ እንስሳትን መሠለ ይላል፡፡ ይህ ግብር ፈጽሞ የእንስሳ እንጂ የሰው ተፈጥሮ መሥራት ያለበት አይደለም፡፡ በዘመናችንም ቢሆን መድኃኒት ያልተገኘለት በሽታ ኤች.አይ.ቪም መጀመሪያ የተከሰተው በዚሁ ግብር ውስጥ ባሉ መካከል ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ አይነቱን ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ሥራን መቃወም ሁላችንም ሃይማኖታዊም ሆነ ሰብዓዊ ግዴታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይቅር ይበለን! ከእንደዚህ አይነቱ ፈተና እግዚአብሔር ህዝባችንን ይጠብቅልን፡፡

Anonymous said...

Ensesatem behone yihen ayadregum, sew gen k'ensesam eyanese new, lezeh demestachin'n masemat aleben ,,,, Egzio Maharen Kirstos

Anonymous said...

May God's mercy and help upon us.We know that we have negligent government seeking only absolute power.

Anonymous said...

በእዉነት ምን አይነት አፀያፊ ነገር ነዉ በኢትዮጵያችን እየተካሄደ ያለዉ የተከበረዉ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባዋል The World Health Organization (WHO) defined health in its broader sense as "a state of complete physical, mental, and social well-being (ይህንን ልብ ይሏል) and not merely the absence of disease or infirmity."
ታዲያ የቱ ጋ ነዉ የብዙሃኑ እምነትና ባህል የተከበረዉ ለጥቂቶቹ መብት ሲባል የብዙሃኑን መብት እና እምነት ይጨፍለቅ የሚል የምድርም የሰማይም ህግ የለም ስለዚህ ይህን ተግባር በግልም ሆነ በተቋም ደረጃ ልንቃወመዉ የሚገባ ጉዳይ ነዉ

Anonymous said...

it is really shame shame!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

ንጋቱ said...

ነዉር ነዉ! ነዉር ነዉ! ነዉር ነዉ! ተዉ ባይ ያጣ መንግስት የት ሊደርስ እንደሚችል ያሳያል

Anonymous said...

በጣም አሳዛኝና አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡ ያሳፈረንና ያዋረደን ደግሞ የራሳችን የምንለው ህገ መንግስቱን በሃይል ለመናድ የሚንቀሳቀሱትን እቀጣለሁ የሚል በስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት ነው፡፡ ታድያ በህገ-መንግቱ ግብረ-ሰዶማዊነትን የሚቃወም አንቀጽ ኖሮ ሳለ ግብረ-ሰዶማዊያን በሃገራችን ሊያደርጉ ያሰቡትን እንቅስቃሴ የሀይማኖት መሪዎቻችን መቃወማቸውን ለህዝባቸው እንዳይገልጹ መከልከላቸው ምን ይባላል፡፡ መንግስት እራሱ ህገ-መንግስቱ የሚቃወም ስራ ሲሰራ ማን ይቅጣው? ህዝቢን ሲደፍር ሞራሉ ላይ ሲሄድበት ማን ይቅጣው?
ኧረ ተደፈርን እኮ ጎበዝ፡፡

Anonymous said...

Please all pray!!!pray!!!pray!!!

Anonymous said...

አንዳንድ ግዜ እኛ አበሻወች ራስ ወዳድ እየሆንን ይመስለኛል ሰዶማዊነትን ያለጥርጥር 99 የሆነዉ ህዝብ ይፀየፈዋል ነግር ግን ትንሽ ቢሆኑም እንኩአን ስራቸዉ አፀያፊ ቢሆንም እንኩአን እንሱም እንደዜጋ ተፈጥሮ አበላሽቶ የሰጣቸዉን ባሕሪ ያለማንም ከልካይ ተሙአግተዉ ሕጋዊ ለማድረግ ቢሞክሩ ምንም ክፋት የለዉም፡፡ አንድ የማይገባኝ ነግር ሰዉ ለምን ከሃይማኖት ጋር እንደሚአገኛኘዉ ነዉ ክርስትናም ሆነ እስልምና አታድርጉት እንጅ አታስደርጉት ያሉ አይመስለኝም ሃገሪቱ እኮ በህገ መንግስት እንጅ በመፅሃፍ ቅዱስ ወይም በ ሸሪያ አትተዳደርም ህገ መንግስቱም ለሃይማኖት ጥገኛ ቢሆንም ቅሉ እዚህ ላይ ግን የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸዉን ማስተማር ሊከለከሉ አየገባም ነበር ማስተማር የነሱ ሓላፊነት ነዉና፡፡ ሓገር ወራሪ ጠላት እንደመጣ ሁሉ መሰባሰባቸዉ ግን ገርሞኛል ሕዝብ እና ሕዝብ ሲጨፋጨፍ ዝም እንዳላሉ ሁላ መምህሮቻቸዉ በ VCD ሲናናቁ ዝም እንዳላሉ ሁላ . . .

Anonymous said...

መንግስት ለሐይማኖት ያለውን ንቀት የገለጸበት መንገድ ነው ውድ ወገኖቸ መፍተሔው ከእግዚአብሔር ነውና እርሱ በቸርነቱ ሐገረ እግዚአብሔር የተባለች ኢትዮጵያን ይጠብቅልን

Essu said...

besemeab min aynet gud metaben..............

Anonymous said...

Please all pray!!!pray!!!pray!!! to stop this.

tensae said...

People should do somthing.

Anonymous said...

please all pray to stop this!!!

Egzo egzo egzo ere wegen egzota new yemaseflgew ebacachu ye haymanot abatoch ahune le haymanotachen tedegegfen inkum said...

Egzo mharen crstos betam asferi zemen dersen ere yantyaleh yasegal ehas zemyembal aydelem gezam yemstew aydelem

Anonymous said...

ሚኒስትሩ አይተ ቴዎድሮስ አድሃኖም አሁን በጣም ተሳሳቱ፡፡ እኔ ግብረ ሰዶማዊነትን አለመቃወም በራሱ ግብሩን እንደመደገፍ ነው የምቆጥረው፡፡ እናም የአቶ ቴዎድሮስ ጀርባ በደንብ መታየት ያለበት ይመስለኛል፡፡

Anonymous said...

አረ በጣም አሳፋሪና አሳሳቢ ጉዳይ ነው ወደሱ ወደ እውነተኛ ማልቀስ ነው በሀገራችን ያለን ሀይማኖታችን ባህላችን እንጂ ምን አለን የቅዱሳን ሀገር ሀገራችንን ጌታሆይ ታረቀን ከዚህ ክፉ ዘመን አድነን አቤቱ እንደበደላችን ሳይሆን እንደቸርነትህ

Anonymous said...

That is EPRDF! Is there a country in the world that have no freedom of speech like Ethiopia? ኡኡኡኡኡኡኡ....... Freedom Freedom Freedom Freedom of speech...God Bless Ethiopia!

Anonymous said...

ኣዎ ግብረ ሶዶማዊነት ባገራችን ነውር ነው!
ነገር ግን ከልብ ስለ ሃይማኖታቸው የሚጨነቁ ጥቂቶች ናቸው
ሌሎች ለፖሊቲካ ፍጆታ ነው ይህንን የሚጽፉ ኤፍሬምም ጭምር
ጤና ሚኒስትሩ ስለ ሕዝባቸው ሃይማኖትና ክብር ከማንም በላይ ያስባሉ ይጨነቃሉ ይህንን ያደረጉበት ምክንያት ይኖራቸዋል
ነገር ግን እነ ኤፍሬም ሌላ መግቢያ ስለሌላቸው ይህንን ሲለፍፉ ይውላሉ

Anonymous said...

ፈጣሪ ያውቃል! ሀገራችንን ከእንደዚህ አይነቱ መአት ይጠብቅልን::

Anonymous said...

ነውር ነው። ነውር ነው። በጣም ነውር ነው። አደራ ይህንንም “ፖለቲካ ነው” እንዳትሉን እነ እንቶኔ።

Anonymous said...

ethiopiaye min meat metabish degmo egiziabher hoy ere bekachihu belen EGZIO MEHARENE

Anonymous said...

(እንደ ሰዶምና ጐመራ እንዳንሆን) እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ነገር እንዲደረግ እንዴት ይፈቀዳል የማንኛውም ሃይማኖት የማይፈቅደው ነገር ነው፡፡ አምላክ ሆይ አንተ ተመልከተን ሰይጣናዊ የሆነው ምግባር በሀገራችን እንዳይሆን እርዳን አሜን፡፡

wen said...

Shame on the so called "leaders" .they ignored us all.They know they can do whatever they want to do on these scared people.I am wandering where that all "Zeraf" thing goes? we just can't even talk but when it comes to whispering, we are the first.Damn it. It is shame to be known by being enemies of each other. Don't ever act as if you proud of being Ethiopian.

Anonymous said...

Embetee meftehe testen!!!

Anonymous said...

what a shame on our government,this means the government is not responsible for this country , God protect this will generation ....

Anonymous said...

Selam Le'enant yihun
ድርጊቱ ኢትዮጵያውያን እንዲሸማቀቁ፣ እንዲያፍሩ፣ ራሳቸውን እንዲጠሉ የታሰበበት ያስመስለዋል። መንግሥት እርሱ ከፈቀደው ሐሳብ ውጪ ያሉ ሐሳቦችን ሁሉ በመጨፍለቅ እስከ ሃይማኖታችን ድረስ መድረሱ...........................
አገሩ ኢትዮጵያ ስለሆነ አንድ ሚኒስትር የሃይማኖት መሪዎች ያዘጋጁትን ጋዜጣዊ መግለጫ ለማስተጓጎል ቻለ።
min yidereg gize yesetew kil gan yisebral ayidel yetebalew. be 20 ametat wist tayto tesemto yemaytawek meat be ageritua lay aweredubat ahunima hizbua teleblibo tekatilo denzizoal enesuna enesu bicha honewal. Yehizib neger aketemelet bilew malet new. Yetedafene esat andit ken tebiko siweta mefeterachewin eskitelu dires chink yihonibachewal. ahunim tesfachin Amlakachin bicha new Ethiopia yeasrat hager nat. Ethiopian godto yetetekeme yelem. Yihinin tarik yasayenal.
ነውር ነው። ነውር ነው። በጣም ነውር ነው።
ሀገሬ ምን መጣብሽ ???

Anonymous said...

በጣም ያሳዝናል እንዲህ ካለው ጊዜ አደረሰን ኧረየት እንድረስ??????????

Anonymous said...

YASAZENAL MENE ENADEREGE????

Anonymous said...

It will not be so far
mane
tekel
fares
To be written on the walls of the hall and the palace.

Anonymous said...

ነገሩ እኮ በጣም ግራ የሚያጋባ ነው። በአንድ በኩል ኤድስን ከዓለም ጠራርጎ ለማጥፋት በሚል በቢሊዮን ያሚቆጠር ዶላር ያወጣሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ይህን መሰል ከሰውነት የወጣን (በእኔ ኢ-ሰበአዊ) ድርጊት በገንዘብ እየደለሉ ያበረታታሉ። ኤድስ እኮ ኤድስ ከመባሉ በፊት "የሶዶማዊያን ካንሰር" ነበር የሚባለው። እነ አጅሬማ ዶላሩ ይምጣ እንጂ ለህዝቡ ጉዳያቸው አይደለም። በሰው ደም እየነገዱ አይደል እዚህ ያደረሱት። እኔ በበኩሌ "እንደ ሰም አቅልጦ እንደ ገል ቀጥቅጦ" ወገኔን የገዛ ክፉ ገጥሞን አያውቅም ባይ ነኝ። ጋዜጣዊ መግለጫው እንደው ለይስሙላ ነበር። እነርሱ እነማን ሆነው ነው?! ከእግዚአብሔር ጋር ወግነው ያውቃሉ? ይህማ ቢሆን ኖሮ አገሬን አንድዬ በታረቃት ነበር። ስንት አስርት ዓመታት በለቅሶና በዋይታ ታለፈ? ለመሆኑ እግዚአብሔርን እንደው እነ አባ እና እንቶኔ ያውቁታል? እግዚአብሔርን አይፈሩ ሰውን አያፍሩ።

ምን ይባላል?! ቸር ያሰማን? እኔ እንጃ ..... ቸር ወሬ ጠፋ በተለይ አገሬን የሚመለከት

Anonymous said...

እዝ መንግስቲ ናይቶም ሰዉአት ጀጋኑ ዐጽሚ ከይተፈለጦ ክረግጽ ጀሚሩ
ክሳብ ሀጂ ዝሰራህኩሞ ኩሉ ከንቱ ጌርኩሞ
Even if it costs us loose the African hub, I'm sure we are ready to deal with it. Because we will loose everything if we host this big SATAN's meeting.

Anonymous said...

ABETU YIKIR BELEN, KEZIH MEAT AWTAN, AGERACHININ TEBIKILIN.

Anonymous said...

+++
As a Christian and Health professional, I see the interference of the government as a provocation and a move to undermine the question of God fearing people. Even scientifically we should dare to say HIV/AIDS is a curse upon the human race. We see it day in and out that because of moral deviation of the people it is upon Us.The first case and still the majority of cases are Gays and people who are not faithful to their marriage or do premarital sex. So my suggestion is we need to stand together and say HIV/AIDS is a seed of our behavior. It is based on data and science we should argue with those non believers!!!!Let us say no in Ethiopia!!!We have a Culture of our own so we don't want others to impose something upon us!!!

Anonymous said...

I am getting sick of this. Why should you guys take your standard of morality (purity) and try to impose it on others. You are saying being homosexual is a sin in reference to the bible. well there are others who don't share your standard and say being homosexual is biological if not personal preference...so if they want to take about issue like HIV and others stuff that affect their wellbeing, don't you think it is violating their right to self expression? if your argument is ethiopian culture and value, we as ethiopians have a lot to be ashamed about, are you referring to the male dominant culture?, a repressive culture?, the culture that degrade women rock bottom?, the culture that allows kids to be sold while their fathers are having teje? without their consent!!!...the genital mutilation of women so that they will be decent when they grow up...people, there are a lot of mess in our culture as it is, let alone to try to be proud of it because it doen't come from the civilized world...to the religious guys isn't Ethiopian a county full of MECHACHAL!!! christian orthodox and Muslim religion leaders sitting on the same table and agree on different issues cause that is civilized...where the each religion precisely teach that it the ONLY way....so endezi mechachal balebet hager yetewesenu sewoch gibresedom hono tebelo bura kereyo mebalu yasazenal...aseteyayet mesetet ende mebet (right) endale hono, yelochen gen mebet megafat asafari new

Anonymous said...

Amen yesweren bemgemry telote /sorry pray/ (subya)ydregbet egzyahbhar yesmalena.yhibret telote awge(TERE)lhezbe crestyaen yetlalef Ethiopia banhcell ezhe maneme aykllklnme wonaw telote new!!!!!this is fact.may GOD BlESS ETHOIOPIA!!!!!!!!

Anonymous said...

GAYS,TRANSGENDERS are too high risk groups for HIV/AIDS ,HEPATITIS AND ADDICTIONS.I HAVE DAILY ENCOUNTER WITH THESE PATIENTS AND ALL NEED BIG TIME TREATMENT AND extended THERAPY TO CONVERT THEM TO HUMAN.SMOKING KILLS THE PERSON.ALCOHOL DOES THE SAME.THE GAY ISSUE KILLS THE WHOLE SOCIETY.GAY IS A PSYCHIATRY ILLNESS LIKE SCHIZOPHRENIA AND BIPOLAR AND ALL GAYS SHOULD SEEK MEDICAL HELP.

Anonymous said...

Newer weyem hatiat bihon byehon! You can not infringe upon people's freedom of their sexuality. Let God be the judge and you live your life the right way.

Anonymous said...

NEGERU POLOTICA NEW WYES HAYMANOT MASAYA

Anonymous said...

one thing you dont understand is, Homosexuality is prohibited by law. But there are lots of gay government officials up there, so the law is nothing unless there is a body which will execute what is written as law. And some of the executive members are Gays and everybody knows that. Here i dont see the woe and the cry?!

http://www.facebook.com/Yony Konjo said...

Eregobeze selemtenagerute negere betekekele mergageca benorachu dese yeleyale ene beca aydelhume alememe dese yelwelae bezuwoche selaweru lke yehonacu kemeselacu betame betame new yemtasazenute ahunme almesebachume ena anbebu!!! polticana yehe negere yesemayena yemedere leyunte alew atesasatu enze sewoche agereneme hone wegenene kemanachume belaye yemetekemu sewoche nachew eske bezuryacu selalute hagerene yemtekemu sewoche eyuna mene endehonu asebu??? gawoche mebtachewne mageyetachew yenate chigere aydelme endezeweme yehgerta selkedesena lemawerate enate erasacu hegune bemgeba tebeku wendemochaculaye kemeferedacu befte ahune ahuneme degemeacu yemetenagerubeten negere asebu asebu!! eske zare enkuane selematawekute negere lalemenagere mokereu beethiopiyawentachu lemekurate degagemacu anbebu cifene telacha yeteme aydersachume....................Gobeze ebakcu asebu, wendemacu, ehetacu, legocacu enatachu abatachu hlu alubete beze hiote wesete yetune newe yemetatefute eske? ezelaye new chigeru.....

DEGEME DEGEME ELACUHALEW ETHIOPIYAWE HONO BEZE HIWOTE YEMNORE SEW ADDIS ABEBA ENA TELELEKE YEHAGERTU KETMAWOCHE WESETE KE 38% BELAYE SEWE ALE BEMERGA YETEREGAGETE EWENTE. GENE HULUME SELZENEGERE BEGELSE BETEYEKE AYDEGEFEME ENATE ALCHUNA...............AMELAKE ESERALE YELEBACHUNE BERHANE YABERALCHU

Anonymous said...

እኔ የሚገርመኝ እንዲህ ዓይነት ለወሬ የሚመቹ ነገሮች ሲኖሩ የሚጽፈው እና የሚለፈልፈው ሰው መብዛቱ !!! እስከዛሬ የት ነበር ይሄ ሁሉ ሰው ?? ቀደም ባሉት ጊዜያት የግብረሰዶማውያን እና የነሱ አፈቀላጤዎች በተለያየ መድረክ ሲናገሩ (ሲቀባጥሩ ማለት ይሻላል) ግድ የለም ይናገሩ እነሱም የመናገር መብት አላቸው ሲሉ እኮ እናስታውሳለን:: ያኔ ለምን ይሄ ድርጊት ከህገ መንግስታችን ድንጋጌዎች ጋር ይጣረሳል አልተባለም ?? "ምነው እናቴ ያኔ በ ዕንቁላሉ ጊዜ..." ሆነ እኮ ነገሩ::
በነገራችን ላይ እነኚህ ቅድመ, ጊዜ እና ድህረ ICASA ስብሰባዎች በደምብ የታሰበባቸው ናቸው :: በቅድመ ICASA ወቅት የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ አሁን ከላይ ከላይ በደፈናው እንደሚቃወማቸው, የሃይማኖት አባቶች እንደሚቃወሟቸው ያውቁ ነበር እና እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው እኮ ያውቁ ነበር:: ለዚህም ነው የመንግስት ባለስልጣን እጁን ያስገባው ጉዳዩ ላይ:: በስብሰባው ወቅት እንዴት ጥበቃ እንደሚደረግላቸው እራሱ አስቀድመው ተዘጋጅተውበታል እና እኔ ሳስበው አንድ እርምጃ የቀደሙን ይመስለኛል::

ሰለሆነም አንዴ ጮሀን ዝም የምንለው ጉዳይ መሆን የለበትም... ጦማሪውም ሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያ በዚህ ኢተፈጥሯዊ ድርጊት እንዳትጎዳ የሚፈልግ ሰው ጩሀቱን መቀጠል አለበት... አደራ በዚህ እንዳይቆም... ልክ እንደው ወጥ ረገጥክ እንዳትሉኝ እንጂ ሴቶቻችን ላይ እንደሚደርሰው የአሲድ ጥቃት የ ሚዲያ እና የጦማሪ ሽፋን እንዳይሆን.... ለአንድ ወቅት ስለጥቃቱ በሰፊው ይነገር እና ከዛ ጉዳዩ የት እንደደረሰ ማንም የሚያውቅ የለም... እንደ እግር ኳሳችን ሁሉ... እንደ አትሌቲክሳችን ሁሉ...

እስኪሰለቻቸው መጨቅጨቅ አለብን.... ውጤት እንዲኖረን ከፈለግን...

በጊዜ እና ድህረ ICASA ደግሞ ምን እንደሚፈጠር አብረን የምናየው ይሆናል::

Anonymous said...

ወይኔ ወይእኛ ወዮልን…እነዚህ ጅቦች፣ አደራ በላዎች፣ ከሀዲዎች የኢትዮጵያን ሀብት በሙሉ በልተው ሲጨርሱ እኛን ደግሞ ሊበሉን/ሊያስበሉን ነውና እባካችሁ በያለንበት የነፍስ አድን ሥራ እንሥራ!!!

w/micael said...

....Tenisiwu letselot!!!!!!!!!!!!
Egizio tesehalene!!!!
Bekeme mihiretike amilakine we ako bekeme abesane!
Abetu wedegna atimeleketim kifu meriwochin gin tayaleh..be metebekiya ginbachin(bebetekrstiyan) hunen zim bilen yemitaregewin enayalen....(belisane enibakom yekerebe tematsino!)
abetu menigist restonal fredilin!!!!!!

arg said...

woyanen masweged bichegnaw amarach new.

Anonymous said...

Hey Guys,
PLEASE DO NOT FRUSTRATE, IT'S JUST PART OF A PROCESS ON THE WAY TO DESTRUCTION. THIS IS A PLAIN TRUTH THOUGH IT'SEXCRUCIATINGLY SAD. WE MUST GATHER TOGETHER AND PRAY HARD WITH A BROKEN HEART'NON-STOP'. JUST LIKE YENENEWE SEWOCH, GOD WILL RESCUE US FROM THIS HUGE EMBARASSMENT. BUT WE REALLY REALLY REALLY HAVE TO WAKE UP AND ASK GOD FOR FORGIVENESS TOGETHER. THAT IS THE ONLY WAY OUT. PLEAS READ TINBITE EZKIEL CHAPTER 29-30. GOD BLESS ETHIOPIA

Anonymous said...

TO annonymous "i am getting sick of this" There is no mechachal menamen with this nasty gay issue!!!Being gay is maddnes.There is no genetic or bilological factor for being gay. According to DSM (bible of psychiatry to define disorders) homosexuality is a disease.After 1973 ,DSM definition of homosexuality was changed to as if it is a normal behaviour.I am still working/practicing medicine with this kind of population.The truth is most of them are depressed,drug addicts,full of personality disorders,societal burdens.

Anonymous said...

We all of us have to save our Country form this Haynes Government, because the wants to avoid the sprite of Ethiopianism through the Coming generation.
We have a Country,We have Religion,we have Culture and we have people who live together by respecting each other so Let us do our best to keep our identity.pry!!! pray!!! pray!!!!

Anonymous said...

አይ ዲ/ን ወንድሜ ኤፍሬም እሸቴ ፓለቲካኮ ይኅው ነው:: ሌላ የለውም እንግዲህ አንተም ከኛ እንዳንዱ ሆነህልናል ማለት ነው :: እንኳን ደህና መጡ ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደዚህ ስለ እውነት የሚቆምላት የሚያስፈልጋት ወቅት ቢኖር ዛሬ ነው:: እግዚአብሄር አምላክ ምን ጊዜም ቢሆን እንደዚህ እውነትን ደፍሮ የመናገር ፀጋውን ለሁላችን ይስጠን አሜን!!በርታ ወንድሜ እግዚአብሄር ካንተ ጋር ይሁን !!!

Anonymous said...

በእግዚአብሄርም፣ በሰውም ዘንድ ነውር ነውና እንቃወማለን፡፡ አምላክ ከመአቱ ይጠብቀን!!

generation said...

koshasha!!!,civilization

Selamawit said...

Be EGZIABHEREM besewem zend Newer newena gebresedomawineten Abzeten Enet'eyefalen!!!!!!!!!!!!!!!!
Abetu cheru AMLAKACHEN Lemeriwochachenem Yemiastewelubeten Lebuna set'elen!

Anonymous said...

በእግዚአብሄርም፣ በሰውም ዘንድ ነውር ነው! ነዉር ነዉ! ነዉር ነዉ! ነዉር ነዉ!

Mehari Zemelak Worku said...

በሌላው ዓለም ቢሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ለማቋረጥ ከመሔድ ይልቅ ከሕዝብ ሊያገኙት የሚገባቸውን እምነት ስላጎደሉ ሥልጣናቸውን ወደ መልቀቅ ይሄዱ ነበር።

You wish!

Anonymous said...

oh god pleas do SOME THING 4 those who can't think,really 1000% THIS IS THE END OF THE WORLD "4GIVE US GOD FOR OUR SIN AMMMMEEENNNNN"

Anonymous said...

If u wana be free ,give freedom to others! but on this case,it is different.Before certain years,AIDS was not the disease in Africa.IT WAS COME FROM WESTERS.Now it becomes our agenda.homosexuality is not a problem in afica but they are going to do so.please let we keep our social capital ,culture,religion and our belive.That is the only ASSET THAT KEEPS US FROM BEING DOWN.

Anonymous said...

እሄ የወሬ ሱሱ ምንድነው?ወገን እንደዚህ አይነት መአት የምታወሩብን መአታሞች ይህን ኑሮ የከበደውን ህዝብ ለማስነሳትና በሁዋላ እሳቱን ለመሞቅ ነው አትጠብቁ ማንም በማንም ላይ አይነሳም ዲስኩራችሁን አታብዙ ኢትዮጵያ እኮ የእኔም የእናንተም ናት አትዶልቱ አውሮፓውያን እኮ ምንም አገራቸው ባትመቻቸውም ለማሳደግ ይጥራሉ እንጂ በአገራቸው ላይ አይዶልቱም ወንድ ከሆናችሁ እስከ ሞት ድረስ ዋጋ መክፈል ትችላላችሁ፡፡ ለሁሉም ነገር የተሳሳተ ትርጉም የመስጠት አባዜ የተጠናወታችሁ ውስጣችሁ ነገር የተሞላችሁ እናንተ ፈሪዎች የዌብ ሳት ጀግኖች ወንድነታችሁን ፊትለፊት ለምን አታሳዩም ፡፡ እስኪ ወገን ከምናወራና ህዝብን የሚነሳሳ ወሬ ከምናበዛ እስኪ ለስራ እንነሳ በወሬ ያደገ ማንም አገር ስሌለለ እንስራ እግዚአብሄር ቀናና በጎበጎውን እንድታስቡ ይርዳችሁ አሜን፡፡
እህታችሁ፤ኢትዮጵዊት

Ephrem Eshete G. said...

Lasr anonym,

Egna yalnew lela, erso yemilut lela. Thank you anyway.

Anonymous said...

WEY TENA TEBEKA ! ,I WONDER HOW ONE SAFE GARD THE HEALTH OF THE PUBLIC BY INTERFERING RELIGIOUS GROUP WHO ARE TRYING TO SAFE GARD THE PUBLIC'S HEALTH .TO MY UNDERSTANDING THE CHURCH IS THERE TO SAFE GARD ALL OF US FROM SUCH DISGUSTING ACT.ESTI AMLAK YERDAN

FOR OUR SISTER FROM ETHIOPIA WHO TRY TO PREACH US TO PAY A SACRIFICE TO DEATH, FIRES I DO NOT GET YOUR IDEA ,WHAT ARE YOU TRYING TO SAY ?WHAT YOU WROTE IS FEYEL EZIHE KEZEM ZEM EZYA YOU DID NOT TELL US ANY THING ...JUST SHUT UP ! WILL YOU ?

Yewudasse Abat said...

ኢትዮጵያዊት የተባልሽው ስምሽን ብታስቀይሪ ይሻላል፡፡
ለነገሩ የስምሽንም ፊደል በሚገባ አታውቂው፡፡

ተባብሮ ስለመስራትማ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ቀኑን ሙሉ ሲያደነቁሩን ይውላሉ፡፡ አሁን እየተባለ ያለው ግብረሰዶም ኢትዮጵያ ውስጥ በጭራሽ አይታሰብም ነው፡፡

በእርግጥ በድብቅ እንደምትንቀሳቀሱ ይታወቃል፡፡ በአደባባይ ግን ከመገለጣችሁ በፊት ሰዶምና ገሞራ ላይ የወረደው የእግዚአብሔር ቁጣ ይገላግላችኋል፡፡

Anonymous said...

the snake

now a days we the people of Ethiopia are in a very serious headache because of a venomous snake on our head. we can not speak because our mouth socked with bloody swab. Every thing is very difficult ,WE THE PEOPLE are effortless to bring ,change & enhance rightful future to next generation . However we can not tolerate this shameful ,that drop our dignity , activity . Truly we can not tolerate issue. never!!!!!!!!!!!!!!

lily said...

weyi gud! gud eko new endew. endezi yalew seyitan betsomina betselot kalihone ayiwetam yetebalew endezi ayinetu new engidh yiholachu.weyi grum!

Anonymous said...

ከላይ ኮሜንት ያደረከው አሁን አወራህ ማለት ነው ብቃት ያለው ሰው ምክንያቱን በግልፅ ያስቀምጣል እንጂ በደፈናው አይቃወምም.......ኤፍሬም ደግም ስለጡመራህ በጣም እናመሰግናለን

Anonymous said...

"...ለስራ እንነሳ በወሬ ያደገ ማንም አገር ስሌለለ እንስራ ..." what an insight! I'm sick and tired of bigots and bunch of narrow minded self-sanctifying hypocrites.

No wonder why this land is full of biases and double-standards, while you all claim freedom is necessary, but you choose to oppress the minority, just because they fall under "sinful" category according to your religion. it is absurd!!!
Yes, everyone can voice opinion and throw support to any cause. but, corroborating to raise public uproar on the minority, and enticing hatred and bigotry is pure ignorance!!!
Ethiopia is a land of many; Islam, Orthodox, Protestant, Pagan, Atheist etc...
If you don't accept others as who they are, don't expect your right to be respected and accepted...
read your own "golden rule" - from your bible.

Anonymous said...

Egiziabhare enanim hone lelawin kehatiyatachin yikir yibelen. Hulachinim hatiyategnoch mehonachinin anizenga. Anifired yiferedibinal. Neger gin dirgitun enawigiz, enimiker, enastemir wendimochachin nachew newina. egnam endenesu hatiyategnoch nen ena.