
ባለፈው ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የፖለቲካ ውዝግብ የሚፈጥር ነገር የሚመረጥ አይደለም። በመጪ ጉዳዮች ላይ ብንወዛገብ አንድ ጉዳይ ነው፤ አገራችን እንዴት እናልማ፣ በየት አቅጣጫ እንምራ በሚለው ጉዳይ ላይ ብንከራከር ብንወዛገብ አንድ ጉዳይ ነው። በተወሰነ ደረጃ ገንቢ ገጽታ አለው። ተወያይተን ተመካክረን አንድ የጋራ አቋም ልንይዝ እንችላለን። ባለፈ ጉዳይ ላይ ብንነታረክ ግን ይኼን ያህል ገንቢ ጉዳይ የለውም። ያለፈ ጉዳይ ነው።” ሲሉ ያስታወሱኝን አስተሳሰብ ደግሞ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ ባልኩት መሠረት እነሆ የጫርኩትን።
