My Twitting

Monday, September 12, 2011

በ“መስከረም ሁለት” ትዝ የሚለኝ

እንዲህ እንደ አሁኑ ዓመታት አልፈው፣ አገር ቤቱም እንደ ጨረቃ ርቆ፣ ትዝታም የሕልም ያህል ቀጥኖ፣ ልቡና ዛሬን ሳይሆን ትናንትን፣ የዛሬን አዋቂነት ሳይሆን የትናንትን ልጅነት ሲናፍቅ … መስከረም ሁለትም ከአዲስ ዘመን ተርታ በትዝታ መስኮት መምጣቱ አይቀርም። የኔ ትውልድ፣ የልጅነታችን ወራት ያለፈው፣ ከመስከረም አንድ ይልቅ መስከረም ሁለት “ርዕሰ ዐውደ ዓመት” ሆኖ ነው። እንቁጣጣሽ ከዘመን መለወጫነቱ ይልቅ የመስከረም ሁለት ዋዜማ መሆኑ የታወቀ እስኪመስል ድረስ በልጅነት አዕምሯችን የተሳለው ዐቢዩ በዓል የቅ/ዮሐንስ ማግስት ነበር ማለት ይቻላል።

Friday, September 9, 2011

“To Fear or Not To Fear”፤ 9/11

በዚህ ሰሞን ቢያንስ ሁለት ጊዜ ሚዲያዎችን ሁሉ ያጥለቀለቀ የማስጠንቀቂያ መልእክቶች በየሚዲያው በመተላለፍ ላይ ናቸው። የመጀመሪያው “ሂዩሪኬን አይሪን”/ “ማዕበል-አይሪን” መጣሁ መጣሁ  ባለችበት ባለፈው ወቅት ሲከናወን የቆየው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሰሞኑን አሥረኛ ዓመቱ በደረሰው የ9/11 ጥቃት ዙሪያ ያለው ነው። ብዙ ሰው በእንደዚህ ዓይነቱ “ማስጠንቀቂያ” ላይ ያለው አመለካከት ይህንን ጽሑፍ ጋብዟል።