(ኤፍሬም እሸቴ):- “ግብጻውያን ወደ ታህሪር አደባባይ የወጡበትን እና ከብዙ ደም
መፋሰስ በኋላ በፈረጠም አገዛዛቸው ጥንታዊቱን ምስርን አስጨንቀው የገዟትን ሆስኒ ሙባረክን ከሥልጣናቸው አሽቀንጥረው የጣሉበትን
ምክንያት ብዙ አሜሪካውን ይረዳሉ፤ በደመ ነፍስም ቢሆንም ይስማሙበታል። የራሳቸው ወገኖች “ዎል ስትሪት”ን ለመቆጣጠር የተነሡበትንምክንያት ግን ሁሉ በአንድ ልብ አልተገነዘቡትም” ይላል የኒውዮርክ-ታይምሱ ጦማሪ (Damon Winter/The New
York Times) ዴሞን ዊንተር። Monday, October 24, 2011
እኛ፣ 99 ፐርሰንቶቹ
(ኤፍሬም እሸቴ):- “ግብጻውያን ወደ ታህሪር አደባባይ የወጡበትን እና ከብዙ ደም
መፋሰስ በኋላ በፈረጠም አገዛዛቸው ጥንታዊቱን ምስርን አስጨንቀው የገዟትን ሆስኒ ሙባረክን ከሥልጣናቸው አሽቀንጥረው የጣሉበትን
ምክንያት ብዙ አሜሪካውን ይረዳሉ፤ በደመ ነፍስም ቢሆንም ይስማሙበታል። የራሳቸው ወገኖች “ዎል ስትሪት”ን ለመቆጣጠር የተነሡበትንምክንያት ግን ሁሉ በአንድ ልብ አልተገነዘቡትም” ይላል የኒውዮርክ-ታይምሱ ጦማሪ (Damon Winter/The New
York Times) ዴሞን ዊንተር። Thursday, October 20, 2011
የጋዳፊ የወርቅ ሽጉጥ
ጋዳፊ እና ቤተሰቡ ሊቃወሙት የወጡትን የራሱን ዜጎች የገለጸበት አንድ
ቃል ብትኖር “አይጦች” የምትለዋ የጽርፈት ቃል ነበረች። በመጨረሻ ግን እንደ አይጥ ጉድጓድ ውስጥ ተደብቆ የተገኘው ራሱ ኮሎኔል
ጋዳፊ ሆነ። የወርቅ ሽጉጡም ብትሆን ከጠላቶቹ እጅ አላተረፈችውም። ሊቢያን በብረት እጁ አድምቶ፣ ሕዝቧን እየጨፈጨፈ የኖረው (1969-2011)
“ብራዘር ሊደር/ Brother Leader” በትውልድ መንደሩ ጎዳናዎች ላይ አስከሬኑ ተጎተተ። የዲክቴተሮች አስቀያሚ መጨረሻ፦ ባለ ወርቅ ሽጉጥ እንደጨበጡ፣
አስከሬናቸው እንደ ውሻ ሜዳ ላይ መጣል። Wednesday, October 12, 2011
ቃላት እና ቋንቋ እንደየዘመኑ፣ እንደየመንደሩ፣ እንደየመንግሥቱ
(ኤፍሬም እሸቴ):- ሁል ጊዜም አዲስ ዘመን አዲስ ቃል
እና አገላለጽ ይዞ ይመጣል። አዲሱ ቃል መምጣቱ ሳይታወቅ የሚረሳውን ያህል አንዳንድ አገሮችና ባሕሎች ግን እነዚህን አዳዲስ ቃላት
የመመዝገብ እና የማጥናት ልምድ አላቸው። የዓመቱን አዲስ አባባልና ቃል መርጠውም ያስታውቃሉ። አዲስ በሚታተም መዝገበ ቃላት ውስጥም
ያስገባሉ። ለምሳሌ በ2010 በዚህ መልክ መነጋገሪያ ከነበሩት መካከል ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት የተወዳደሩት የጆን ማኬይን ምክትል
ወይዘሮ ሣራ ፔሊን አንዷ ናቸው። ሴቲዮዋ በንግግር መካከል ተሳስተው
የተናገሩት ቃል የ2010 ምርጥ አዲስ ቃል (“New Oxford American Dictionary 2010's Word of the
Year”) ተብሎ አዲስ የ“American lexicon” ለመሆን በቅቷል።
Tuesday, October 11, 2011
Subscribe to:
Posts (Atom)