(ኤፍሬም እሸቴ/adebabay.com/ TO READ IN PDF)
ዛሬ “Thanksgiving”
ላይ ቆሜ ስለዚህ በዓል ለብዙ ጊዜ ልጽፈበት እየፎከርኩ አለማድረጌን እየወቀስኩ ጥቂትም ቢሆን ልልበት ወሰንኩ። ምናልባት
የፈረንጅ በዓል ስለሆነና ገና ስላልተዋሐደኝ ባዕድ ሆኖብኝ ይሆን እንጃ በተከታታይ ሦስት ዓመታት ብዕሬን አንስቼ ሳልፈጽመው ቀርቻለኹ።
ዘንድሮስ አይሆንም ብያለኹ። በተለይ ለረዥም ዘመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያን
በሐላፊነት ሲመሩ የነበሩትና በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ “እኛ ልመና እንጂ ምስጋና አናውቅም፤
ማመስገን ያስፈልገናል” ይሉት የነበረው አባባላቸው የበለጠ አበረታቶኝ የግል ሐሳቤን ለመጠቆም ደፈርኩ።

