ይህ ጽሑፍ ለብፁዕ አቡነ አብርሃም ሽኝት ለተዘጋጀ መጽሔት የተጻፈ እና እዚያም
ላይ የወጣ ነው።
(ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ):- አበው ሲተርቱ “የሰው አገሩ - ምግባሩ” ይላሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ አባባል ካስቀመጥነው “መልካም ስም ከብዙ ባለጠግነት ይሻላል” (“መጽሐፈ ምሳሌ22፥1) ወይም በሌላ ሥፍራ “ከመልካም ሽቱ መልካም ስም … ይሻላል” (መጽሐፈ መክብብ 7፤1) ካለው ጋር አንድ ነው። መልካም ስም እና ምግባር የተባሉት ሁለቱ ቃላት
በአነጋገር የተለያዩ በመንፈስ ግን አንድነት ያላቸው አገላለጾች ናቸው። ምግባር ከአገር፣ መልካም ስምም ከመልካም ሽቱ እና ከብዙ
ባለ ጠግነት እንደሚበልጥ ተገልጿል።



