Monday, February 20, 2012

ለምን ሞተ ቢሉ

ለምን ሞተ ቢሉ
ለምን ሞተ ቢሉ
ንገሩ ለሁሉ
ሳትደብቁ ከቶ
ከዘመን ተኳርፎ
ከዘመን ተጣልቶ።
(ደበበ ሰይፉ 1968)
"አዲስ አበባ፣ የካቲት 122004 (ኤፍ ) አንጋፋው ደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ባጋጠመው ህመም ምክንያት ሆስፒታል ገብቶ የነበረው ደራሲ ስብሃት ባለፈው ረቡዕ ከሆስፒታል በመውጣት ወደ ቤቱ ቢመለስም ዛሬ ንጋት ላይ ህይወቱ አልፏል። የደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር የቀብር ስነ ስርአት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰአት 4 ኪሎ በሚገኘው የቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል።"

Wednesday, February 15, 2012

ፊደል የመቁጠር ዕዳ

READ IN PDF.
“የተማረ ይደለኝ” የሚል ተረት ስሰማ ሁሌም ያስቀኛል። እንዲያው በቀጥታውና በጥሬ ትርጉሙ “ከሞትኩ አይቀር” … “ፊደል የቆጠረው ጭጭ ያድርገኝ” ማለት ሳይሆን “የተማረ ሰው ምንም ቢሆን ይሻላል፣ ምሥጢር ይገለጥለታል፣ ክፉና ደጉን ይለያል” የማለት ዓይነት ምስጋና አዘል አባባል ነው። በእርግጥ “የተማረ ይግደለኝ” ብለን ብንል ምሳሌያዊ አባባሉን በጥሬው እንደመነዘሩ ሁሉ፣ የተማሩት ገድለውን፣ እርስ በርሳቸውም ተገዳድለዋል። ቀድሞ በቀይ እና ነጭ ሽብር አልቋል፣ ወይም አገር ጥሎ ተሰዷል፣ ወይ እንትኑን ልፎ ተቀምጧል። ወይም የነእንቶኒ አገልጋይ ሆኗል። እንዲህ እንዲህ እያልኩ “ልወርድበት” አሰብኩና ተወት አድርጌው፣ አስቀድሜ “ይኼ የተማረ ሰው ምን ሊያደርግ ይጠበቅበት ኖሯል?” ብዬ መጠየቅን መረጥኹ።

Tuesday, February 7, 2012

መሪ ቃሎች - መፈክሮች

READ IN PDF. አሜሪካ በምርጫ እና የአንድ ፓርቲ ቅድመ ምርጫ ውድድር ተወጥራለች። የሪፐብሊካን ፓርቲ በዚሁ የፈረንጆች ዓመት በሚደረገው ፕረዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ፓርቲውን ወክሎ የሚቀርበውን እጩ ለመምረጥ እየተፎካከሩ ነው። በዚሁ አካሄድ የመረጡት አንድ የፓርቲያቸው ተወካይ ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር ይፎካከራል ማለት ነው። ለውድድሩ ከገቡት ተፎካካሪዎች መካከል እስካሁን መዝለቅ የቻሉት አራት ሲሆኑ በሚቀጥሉት ቀናት በሚደረጉ ድምጽ አሰጣጦች የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ይቀራሉ ተብሎ ይጠበቃል።