Tuesday, March 27, 2012

ኑ “እንፍጠር” - ነፍሰ ቆንጆዎች


(READ THIS IN PDF) የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያምን መጽሐፍ (ትግላችን፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ የትግል ታሪክ) እያነበብኩ ነበር - ባለፈው ሰሞን። በራሳቸው በኮሎኔሉ ተጽፎ፣ በፀሐይ አሳታሚና አከፋፋይ ድርጅት ታርሞ እና ተስተካክሎ በአሜሪካን አገር የታተመ ጥርት ክሽን ያለ ደረጃውን የጠበቀ (ይዘቱን አላልኩም) መጽሐፍ ነው። ብዙ ጊዜ እንዲህ የፊደሉ መጠን ለዓይን ሳይደቅቅ፣ ወይም ባቄላ ባቄላ አክሎ ለአረጋውያን ብቻ ወይም ለሕጻናት ፊደል ማስተማሪያነት የተዘጋጀ ሳይመስል፣ በሌላ አገር ቋንቋዎች በእንግሊዝኛው ወይም በጀርመንኛው ያነበብኳቸውን መጻሕፍት የመሰለ ደረጃውን የጠበቀ መጽሐፍ ነው።

Wednesday, March 21, 2012

ታላቅ ምስጋና


ታላቅ ምስጋና በዝቋላ እየተካሄደ ላለው የእሳት ማጥፋት እንቅስቃሴ ርዳታ በማድረግ ላይ ላላችሁ በሙሉ። ከመቶ በላይ የሚቆጠሩ ወንድሞች እና እህቶች በዚህ የአጭር ጊዜ አፋጣኝ ጥሪ ምላሽ ሰጥተዋል። ሌሎችም በመለገስ ላይ ይገኛሉ። እናመሰግናለን። በርቱ፤ ግፉበት። በአሁኑ ወቅት እሳቱን ለማጥፋት ከየአካባቢው በነቂስ ለወጣው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ጉሮሮውን ማርጠቢያ ውኃ፣ ጉልበቱን መደገፊያ ዳቦ ማቅረቢያ እንዲሆን የታሰበ ነው። በባዶ እጁ፣ በቅጠል እና በአፈር ቋያ እሳት ለማጥፋት እየታገለ ላለው ወገን አለኝታነታችንን ለመግለጽ ነው። ስለዚህም በሚከተለው አድራሻ እየገባችሁ የግላችሁን ልገሳ መስጠት የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናስታውቃለን። 

በደኖቹ መቃጠል ማን ብዙ ይጎዳል?


(ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ/ To Read in PDF)
በዚህ በሰሞኑ የገዳማቱ ደኖች መቃጠል አንድ ያስገረመኝ ነገር ቢኖር ኦርቶዶክሳዊ ከሆኑት ዉጭ ከሌሎቹም ብዙም ጉዳዩን ጉዳይ የማድረግ ነገር አለማየቴ ነዉ፡፡ ሁኔታዉን ደጋሜ ሳስብበት ቢያንስ ሁለት ችግሮች እንዳሉብን ገመትኩኝ፡፡ አንደኛዉ እንደ ዜጋና ሀገር የደኖችን ጠቀሜታ በዉል አለማወቃችን ይመስለኛል፡፡ ሁለተኛዉም ራሳችን ተቆርቋሪዎች ነን የምንለዉም ብንሆን ቦታዉ የእኛ መሆኑ የጣለብን ሓላፊነት አድርገን ስለቆጠርነዉ እንጂ ከዚህ ያለፈ ምን ያህል ጉዳት እንደሚያመጣ ማስረዳት የቻልን አልመሰለኝም፡፡ ይህንን ማድረግ አለብን ወይም ነበረብን የምለዉ ዛሬዉን ማለቴ አይደለም፤ ቀደም ብለን፡፡ እንማን? እኛ፡፡

Tuesday, March 20, 2012

አፋጣኝ ርዳታ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በዝቋላ ገዳም እና አካባቢው ደን ላይ የተነሣውን እሳት ለማጥፋት ለሚደረገው ጥረት ለማድረግ የግል ልገሳዎን ይስጡ በሚል ሐሳብ በማ/ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል፣ በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና በማኅበረ በዓለ ወልድ አስተባባሪነት በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ ኦርቶዶክሳውያን አስቸኳይ የገንዘብ ማሰባሰብ ሒደት ላይ እንገኛለን። ዓላማው በአሁኑ ወቅት እሳቱን ለማጥፋት ከየአካባቢው በነቂስ ለወጣው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ጉሮሮውን ማርጠቢያ ውኃ፣ ጉልበቱን መደገፊያ ዳቦ ማቅረቢያ እንዲሆን የታሰበ ነው። በባዶ እጁ፣ በቅጠል እና በአፈር ቋያ እሳት ለማጥፋት እየታገለ ላለው ወገን አለኝታነታችንን ለመግለጽ ነው። ስለዚህም በሚከተለው አድራሻ እየገባችሁ የግላችሁን ልገሳ መስጠት የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናስታውቃለን። 

Monday, March 19, 2012

የዝቋላ እሳት - ዝምታው ይሰበር


የዝቋላ እሳትን በተመለከተ ብዙ መልእክቶች ከአዲስ አበባ ወዳጆቼ ሲላኩልኝ ነበር። ሁሉም በቁጭት “ኧረ ምን ይሻለናል?” የሚል የጭንቀት፣ የጥበት አስተያየት ነው። እንግዲህ ተረቱ እንደሚለው “ፈረሱም ይኸው፣ ሜዳውም ይኸው” ነው ወገኖቼ። ማንንም መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም። ቁጭ ብለን በማልቀስ ወይም በፌስቡክ ላይ በመንጫጫት እሳቱ አይጠፋም።

Friday, March 16, 2012

ዉኃም አነቀ፤ ምላጭም አበጠ


 (ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ፤ ፌስቡክ ላይ ካስቀመጠው። በፀሐፊው ፈቃድ የተወሰደ። Birhanu Admass Anleye on Monday, March 12, 2012 at 4:51am/ READ THIS IN PDF)
 ብዙ ዓይነት ችግሮች እንደሚኖሩ ሁሉ እንዲሁ ብዙ ዓይነት መፍትሔዎችም አሉ፡፡  ችግሩን አስወግደዉ ነገር ግን መጠነኛ ሌላ ችግር ትተዉ የሚሄዱት መፍትሔዎች በእኔ ግምት ሰፊዉን ቦታ የሚይዙ ይመስለኛል፡፡ እንደ መድኃኒት ማለት ነዉ፡፡ ዋናዉን በሽታ ያስወግዳሉ፤ ነገር ግን የራሳቸዉን ተጓዳኝ ተጽእኖም(side effect) ፈጥረዉ ያልፋሉ፡፡ ሆኖም  ዋናዉንና ቢቆይ ሊገድል የሚችለዉን ችግር (በሽታ) ስለሚያስወግዱ ተጓዳኝ ተጽእኗቸዉን እንታገሰዋለን፡፡ ከችግርነታቸዉ ይልቅ ችግር አስወጋጂነታቸዉ በእጂጉ ይበልጣልና፡፡ ዐለማችንና የዐለማችን ሰዎች የኑሮ ሁኔታ በአብዛኛዉ በዚህ ዓይነት የችግር ማስወገጃ ዘዴዎች ይጠቀማሉ፡፡ ይሁን እንጂ ሌሎች ጠባያት ያሏቸዉ የመፍትሔ መንገዶች መኖራቸዉም  የሚረሳ አይመስለኝም፡፡

Monday, March 12, 2012

አገር በስኳርና በቢራ ፋብሪካ ብቻ አገር አይሆንም፤ በባህልም፣ በቅርስም፣ በማንነት፣ በሃይማኖትም እንጂ

READ IN PDF.

ቅድመ ነገር

ሰሞኑን የተለያዩ ጦማርያን (ብሎገሮች)፣ የአገር ቤት ጋዜጦች እና የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ስለ ዋልድባ ገዳም ይዞታ መነካት ጉዳይ ዘገባዎችን አቅርበዋል። “ደጀ ሰላም” የጡመራ መድረክ (ብሎግ) የገዳሙ አባቶች ለጠቅላይ ሚኒስትር ያቀረቡትን ደብዳቤ ከማቅረቡም ባሻገር “በገዳሙ ክልል እና ዙሪያ (በዓዲ አርቃይ ወረዳ በኩል) የፓርክ ይዞታ ለመከለል እና የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም በሚል በሚካሄደው የጥርጊያ መንገድ ሥራ (ከማይ ፀብሪ እስከ ዕጣኖ ማርያም) የቅዱሳን አበው ዐፅም እየፈለሰ መሬቱ እየታረሰ” መሆኑን (ARTICLE) አስነብቦናል። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ደግሞ ነገሩን ሰፋ አድርጎ ከገዳሙ ተወካይ ጋር ያደረገውን ውይይት አስደምጦናል።

Friday, March 2, 2012

አድዋ ምኑ ነው?


(READ IN PDF)

ድፍን ኢትዮጵያን እስቲ ልጠይቀው፣
እንደሆነ አክሱሙ አድዋው
ተጠየቅ ጦቢያ መልስ መልስ ካለህ፣
ምን ትርጉም እንዳለው አድዋ መዝመትህ።

Blog Archive