(READ IN PDF)ድፍን ኢትዮጵያን እስቲ ልጠይቀው፣
ምኑ እንደሆነ አክሱሙ አድዋው፤
ተጠየቅ ጦቢያ መልስ መልስ ካለህ፣
ምን ትርጉም እንዳለው አድዋ መዝመትህ።
ተጠየቅ ና! መልስ እኮ ምን ምን አለህ?
ካገር ጥግ ተምመህ ከትግራይ መድረስህ፤
አንተ የዳር አገር ሰው ባለ ምንሽሩ፣
ባለ ዲሞትፎሩ ባለ ጦር መውዜሩ፣
አገሬን አትንኩ ብለህ የከተትከው፣
ተጠየቅ ና መልስ አድዋ ምንህ ነው?
ቋንቋህ ቅይጥ ልዩ ዘርህ ከዳር አገር፣
ሀብትህ አንዲት ቁና አፈር ገፊ አፈር፣
ቁናህን ወርውረህ አፈርህን ጥለህ፣
ዘገርክን ነቅንቀህ ጋሻህን አውርደህ፣
አገር ብለህ ዘምተህ አገር ብለህ ሞተህ፣
ካድዋ ተዛምደህ ታድዋ ተዋልደህ፣
ከትግራይ ተግርየህ ከጎንደር ጎንድረህ፣
ከሸዋው ሸውተህ ከኦሮሞው ውለህ፣
ጦቢያ ነኝ ብለህ ደምህን ገብረህ፣
“ምንህ ሆነ አድዋ” እስቲ ልጠይቅህ።
የሰበርከው አጥንት የፈሰሰው ደምህ፣
የበተንከው ትዳር ያጎደልከው ጎንህ፣
አገር አቆም ብለህ አንተ ላገር ወድቀህ፣
ምንህ-ሆነ አድዋ እስቲ ልጠይቅህ።
(ለእንትና እና ለእንትና “አድዋ ምኑ ነው?” ለሚሉት ለነ እንቶኔ፤
እንደወረደ የተጻፈ።)
ማርች 1/2012፤ ሲልቨር ስፕሪንግ፤ ሀገረ ማርያም።

9 comments:
Best one!thanks!
I think the last sentence should end with question mark .I like it very much , if possible it is better to send through e-mail to 'Entenana entna, lenentone'
well said!
dink new dink getem kalehiwot yasemalen
Ephi,betam dinq gitim new. Kale Hiywet yasemalin.Mar tebitawa endmitim endihu yichim gitim anjete teb alech.
ልዩነት ውበት ነው ሲሉ እውነት መስሎኝ
ያስተርጓሚ ያለህ ባቢሎን በሳሎን፣
አዲሱ ኢትዮጵያዊ ትውልድ በምን ይግባባ ይሆን ? ምን አልባት በእንግሊዝኛ?
I'M SOORY D EPHREM I don't underestand what you trying to say . after u said a good thing..@the end
there is some thing wrong. you said MENEH HONE ADWA?? [weyne gude yemeselenge neger balhone??
Dear anonym,
"ምንህ-ሆነ አድዋ እስቲ ልጠይቅህ።" is a question posed to you, the reader. Don't ask me back. :) It is your turn to reply to my question. Aymeslotem? "Weyne gude" yalutenem binegrun teru temehert enagegn nebere.
ይህን ለመጻፍ የዘገየህ አይመስልህም?
Post a Comment