Saturday, May 19, 2012

የኛ ሰው በላስ ቬጋስ

(ክፍል አንድ/ PDF)

ወደ ላስ ቬጋስ ስሔድ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በመጀመሪያው ጉዞዬ ወደ ከተማይቱ የገባኹት በቀን ነበር። አሁን ደግሞ በማታ። አውሮፕላኑ ለማረፍ ሲግደረደር፣ በግማሽ ክንፍ ከተማይቱን ሲዞር ላስ ቬጋስ ሰፊ ደረቷን ሰጥታ ተንጣልላ ትታያለች። በረሃማዋ የአሜሪካ ገነት፣ የቁማር ከተማ። በቀን ሲመለከቷት ዙሪያዋን ጭው ባለው በረሃ ውስጥ ተሰድረው በተሰለፉ የዓለት ኮረብቶች ተከብባለች። ሙቀት እንጂ ልምላሜ የሚባል ነገር የለባትም። ክሽን ብለው የተሠሩት መንገዶቿ በሌሎች ከተሞች ከማውቃቸው መንገዶች በተለ መልኩ ሰፋፊዎች ናቸው። የላስ ቬጋስ ትንሽ የሚባለው ጎዳና የሌሎቹ ከተሞች ዋና መንገድ ሊሆን ይችላል። ደግሞም መልክዓ ምድሩ ለ….ጥ ያለ ሜዳ ስለሆነ ሁነኛ ባለሙያ በደብተር ላይ ያሰመረው መስመር እንጂ በውን ያለ መንገድ አይመስልም። 

ላስ ቬጋስ የምትታወቀው በቁማሯ እና በመዝናኛዎቿ ነው። ከአውሮፕላን ወርጄ ወደ ዋናው መውጫ መንገድ ስጓዝ አንድ ማስጠንቀቂያ የሚመስል ማስታወቂያ ተሰድሮ ተመለከትኩ። "What happens in Vegas, Stays in Vegas” ይላል፤ “በቬጋስ የተደረገ ነገር (ምሥጢርነቱ) በቬጋስ ይቀራል” ይልና የምታነሣውን ፎቶም የሆነ የምታደርገውን ነገር ቴክስት እንዳታደረግ ሲል ያስጠነቅቃል። ከነጭራሹ አንዱ ማስታወቂያ “ወደ ኃጢአት ከተማ እንኳን በደህና መጡ” ይላል። የኔ አገር ሰው ቢያየው “በስማ …. ብ” ብሎ ሲያማትብ በዓይነ ኅሊናዬ ታየኝ።
“ለመሆኑ ስንት አበሻ ነው እዚህ አገር የሚገኘው?” አልኩ፣ እንደደረስኩ። “ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ወደ 30 ሺህ ሰው ይኖራል ሲባል ሰምቻለኹ” ሲሉ መለሱልኝ - በከተማው የሚገኘው የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ካህን። ይኼ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ቬጋስ ከተማ ውስጥ ይኖራል? አንዲት ትንሽ የኢትዮጵያ ከተማ ሕዝብ እንደማለት ነው። ያደግኹባት ሆለታ ስንት ሕዝብ ይኖራት ይሆን ብዬ ስጎረጉር ያገኘኹት ወደ 26 ሺህ ነዋሪ እንዳላት ነው።
አብዛኛው ወንድ ኢትዮጵያዊ በታክሲ መንዳት ላይ የተሠማራ ነው። ያውም በቀን 12 ሰዓት። ከዚያ በታች መሥራት የሚባል ነገር የለም። አንድ ሺፍት የሚባለው 12 ሰዓት ነው። ታዲያ 12 ሰዓት ሙሉ ቬጋስ የታክሲ ተጠቃሚ አላት። ያውም ቱሪስት። “ስንት ታክሲ እንዳለ ታውቃለህ ኤፍሬም” አለኝ አንዱ ወዳጄ። “20 ሺህ ታክሲ ነው እኮ”። ያውም ጽድት ያሉ ታክሲዎች።
የታክሲ ሥራው ረዥም ሰዓት ለመሥራት የሚያስገድድ ቢሆንም የሚገኝበት ገንዘብ ጥሩ ስለሆነ በተለይ ወጣት ኢትዮጵያውያን ይስማማቸዋል። “ጥሩ ከሠራችሁ ስንት ታገኛላችሁ?” አልኩት ያንን ወዳጄን። “ዌል፤ ጎበዝ ሠራተኛ ከሆነ እስከ 4 ሺህ ዶላር ሊሠራ ይችላል። ሰነፍ የሚባለው ደግሞ መቼም ቢያንስ ቢያንስ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ዶላር ይሠራል”።
 ሴቶቹ ኢትዮጵያውያን ከተማይቱን በሞሏት ቁማር ቤቶች በተለያየ መስክ ተሠማርተዋል። ቁማር የከተማይቱ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ነው። በዓመት ከሰባት ሚሊዮን የማያንስ ቱሪስት ከመላው ዓለም የሚመጣባት ቬጋስ ቁማሯን እያጫወተች፣ በመጠጧ እያሰከረች፣ በአስረሽ ምቺው የጎብኚዋን ቀልብ ትሰውራለች። በዚህ እብደት ውስጥ የሚነሣ ፎቶ ቢኖር የሚስማማው ለጌጋስ ብቻ ያውም ለዚያ የአስረሽ ምቺው ወቅት እንጂ ለሌላ ጊዜ ላይሆን ይችላል። "What happens in Vegas, Stays in Vegas” እንዲል።
ገና ከአውሮፕላን ማረፊያ ሲደረስ የሚገኙት ዋነኛ ነገሮች የቁማር መጫወቻ ማሺኖች ናቸው። የቁማር ሱስ ያለበት ሰው ከዚያ ይጀምራል። ወይም ቬጋስን ተሰናብቶ ከመውጣቱ በፊት የማሳረጊያ ቁማር ይጫወታል። የቀረችው ተረፈ-ሳንቲም ብትኖር እዚያች አሟጦ እንዲሄድ ሁሉ ነገር ተዘጋጅቶላታል። ቁማር ከሲጋራና ከጫት የበለጠ አደንዛዥ መሆኑን ቲቪውም፣ ባለሙያውም ሁሌ ይናገራል። ምስክሩ ቬጋስ ነው።
ወደ ከተማዋ ስንዘልቅ አስፓልቱ ጽድት ብሎ ሳየው “ከተማችሁ በጣም ንጹህ ነው” አልኩት ወዳጄን። “እንዴ፣ በየማታው እየታጠበች እንዴት አትጸዳ?” ሲል መለሰልኝ። ቁሽሽ ያሉ የዲሲ መንገዶች በዓይነ ኅሊናዬ መጡ። “ቆሻሻ መጣል ክልክል ነው፤ እስከ ሁለት ሺህ ዶላር ያስቀጣል” ይላል አንዱ ማስታወቂያ። ያበደ ታልሆነ ደፍሮ ቆሻሻ ወደ መንገድ አይወረውርም። ፖሊስ ወዲያው ከች ነው።
መቸም የአሜሪካ ፖሊስ ዋነኛ ሥራው የአገር መሪ ሲያልፍ ሕዝቡን በዱላ ወደ ጓሮ ማባረር አይደለም። ሥርዓት ከማስከበር ጀምሮ መንገድ ላይ መኪናህ ነዳጅ አልቆበት ቢቆም ወደ አንዱ ማደያ የሚያደርስ 2 ሊትር ዘይት እስከ መስጠት፣ አቅጣጫ እስከመጠቆም ድረስ ነው። “ሰላም ኦፊሰር” ብለው መጀመር ነው። “ሰላም ኦፊሰር፣ መንገድ ጠፍቶብኝ ነው። እንዲህ እንዲህ የሚባል ቦታ መሔድ ፈልጌ ነበር” ይሉታል። ሲመልስሎት “በዚህ አርገው፣ በዚህ ሔደው፣ በዚህ ታጥፈው” ያብራራል። “በሰላም ይንዱ” ብሎ ይሰናበታል።
በዚያ በረሃ ውስጥ እንዲህ የቱሪስት መዲና የሆነች ከተማ መገንባቱ ገረመኝ። የበረሃ የበረሃ እኛስ ስንት አልነበረን አልኩ በሆዴ። ለረዥም ዘመን በአፋር የተለያዩ ከተሞች የኖሩ ወዳጄ ሲነግሩኝ “ራሷ ዱብቲ ማለት ነው እኮ” ብለውኛል። ሙቀቱ - ዋዕዩ። በተለይም የበጋ ወራት እስከ 47 ዲግሪ ሴንትግሬድ የሚደርሰው ሙቀቷ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ያሰኛል። ውጪ መንገድ ላይ ሲሔዱ። ማን መንገድ ላይ ይሄዳል ታዲያ? ቶሎ መኪና ውስጥ ጥልቅ ነው። ከዚያም ቶሎ ወደ ሥራ ቦታ ወይም መኖሪያ ቤት ግብት። ሙቀቱ የሚታወቀው ከቤትም ከመኪናም ውጪ የመሆኛ አጋጣሚ ካለ ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ በመኪናም በቤትም ያለው ማቀዝቀዣ አየሩን ገርቶታል። ውጪው ንዳድ-ቃጠሎ ይሁን እንጂ ውስጡ ግን ለስለስ ያለ አየር ነው። ቴክኖሎጂው ተፈጥሮውን ገርቶታል። “ተፈጥሮን በቁጥጥራችን ሥር እናደርጋለን” ብለው ረሃብ በረሃብ ያደረጉን ሰዎች መፈክሩን ለቬጋሶች መመለስ አለባቸው።
ዋነኛ ገቢዋ በቁማር እና በመዝናኛ ላይ የተመሠረተው ቬጋስ እንግዶቿ ከመላው ዓለም ይጎርፋሉ። ቀን ከሌት የለ። የአዘቦት ቀን የለ፣ ሰንበት የለ። ሁሌም ብልጭ ድርግም የሚለው መብራቷ ፋታ የለውም። መቸም የመብራት ብዛት እንደ ቬጋስ አላየሁም። በመጀመሪያው ጉዞዬ ቀን ነው የገባኹት ብያችኋለሁ። በአሁነኛው ደግሞ እኩለ ሌሊት ላይ ነበር አውሮፕላናችን ያረፈው። ከተማይቱን ወደ ታች ሲመለከቷት በመብራት ትነድዳለች። “ክሪስማስ ነው የማስመስለው” ያለው የክበበው ገዳ ቀልድ ትዝ ይሏችኋል? ግማሽ ኪሎ ሥጋ ይዞ የሚፎክራት የሰካራም ፉከራው? ይልቅ “ክሪስማስ” የምትመስለው ቬጋስ ናት፤ በማታ ከአውሮፕላን ላይ ቁልቁል ስትታይ። መኪናው ውር ውር ሲል ቁልጭ ብሎ ይታያል።
“እንዴት ነው ያገራችን ሰው በቬጋስ?” ብዬ መጠየቄ አልቀረም። “ድሮ ጥሩ ነበር። የአገሬውም ሰው፣ ፖሊሱም በደህና ነበር የሚያዩን። አሁን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ስማችን እየተበላሸ ነው” አለኝ ታክሲ የሚነዳው አንዱ። “ምነው?” አልኩት። “ባክህ፣ አሁን አሁን የመጡ ልጆች መኪናውን እንዴት እንደሚነዱ ብታይ ይዘገንንሃል። ፖሊሶቹ ራሳቸው ‘የኔ ወንድም፣ ይህ አዲስ አበባ አይደለም’ ማለት ጀምረዋል። ኢትዮጵያዊ ከሆንክ እና ፖሊስ ካስቆመህ አይምርህም። በቃ ስማችንን እያበላሹት ነው። ብትነግራቸው ደግሞ አይሰሙህም። ባለጌ ስድብ ሊሰድቡህ ይችላሉ።” ቀጠለ ወዳጄ።
“እንዲያውም አንድ ገጠመኜን ልንገርህ። አንድ ቀን እንግዳ የምናገኝበት ቦታ ስሔድ ከፊቴ የቀደመ አንድ ታክሲ አይቼ አሳለፍኩት። እኔ ከኋላው ሄጄ ወረፋዬን ያዝኩ። ከዚያ ቅድሚያ የሰጠኹት ባለ ታክሲ፣ ፈረንጅ ነው፣ ከመኪናው ወርዶ መጣና ‘አንተም ከኢትዮጵያ ነህ?’ አለኝ። ‘አዎ’ ስለው ‘እንዴ እንደዚህ ጨዋ ሰዎችም አሉበት እንዴ?’ ሲል መለሰልኝ። ተናደድኩ። እዚህ ከተማ ታክሲ መንዳት ከጀመርኩ 10 ዓመት ሊሞላኝ እንደሆነ ገልጬ እኛ ኢትዮጵያውያን ጨዋና ሰው አክባሪዎች መሆናችንን ለማስረዳት ሞከርኩ። ሰውየው ያየው ለካስ የዚያ ተቃራኒ ነበር። ጫት እየቃሙ የሚነዱ አበሾች ብዙ ናቸው። ጫት እንደ አደንዛዥ ዕጽ ነው የሚታየው በቬጋስ ሕግ። ያስቀጣል። መቼ ፈርተው” አስረዳኝ - በረዥሙ።
በዓይነ ኅሊናዬ የአዲስ አበባ ታክሲዎች ትዝ አሉኝ። ብዙዎቻችን ጎበዝ መኪና ሾፌር የሚመስለን እንዲያ ነፍስ እና ሥጋ በድንጋጤ የሚለያየው ነጂ ሊሆን ይችላል። ከፊታቸው ያለውን ታክሲ ቀድመው ቦታ ለመያዝ መሽቀዳደም የሥራው አንዱ አካል ነው - በአዲስ አበባ። እዚህ ግን “ያልሰለጠነ ሰው ጠባይ” እንጂ የጉብዝና ምልክት አይደለም።
ያ ወዳጄ አንድ ሌላ ገጠመኝ ጨምሮ አጫወተኝ። ታክሲ ሥራ ላይ የማውቀው አንድ ፈረንጅ ነገረኝ ብሎ የነገረኝ ነው። ሰውየው ወደ ቬጋስ ከመምጣቱ በፊት በነበረበት ከተማ ውስጥ ይሠራበት በነበረበት ቦታ ኢትዮጵያውያንም ነበሩ። አንድ ቀን ሁነኛ ዕቃ ይጠፋና ለፖሊስ ይደወላል። ከዚያ ፖሊስ የካምፓኒውን በር በሙሉ ዘግቶ ሠራተኛው ከመውጣቱ በፊት ቁጥጥር ለማድረግ ሲጀምር አንዱን ኢትዮጵያዊ መካከላቸው ያየዋል። “ከኢትዮጵያ ነህ?” ብሎ ከጠየቀው በኋላ “አንተ መውጣት ትችላለህ” ብሎ በመጀመሪያ አሰናበተው። “ኢትዮጵያውያን አይሰርቁም” የሚል ንግግርም እንደጨመረበት ፈረንጁ ለዚያ ለወዳጄ አጫውቶታል።
እንዲህ ዓይነቱ አገላለጽ የኢትዮጵያውያኑን ልብ በኩራት የሚሞላ ነው። ያ ወዳጄ “አሁን የመጡት ልጆች” የሚላቸው ታክሲ ነጂ ኢትዮጵያውያን “ይህንን ስም አናግተውታል” ባይ ነው። በዚያ አነዳዳቸው የሚያደርሱትም አደጋ ዘግናኝ እንደሆነ አጫውቶኛል። ማንኛውም የአዲስ አበባን የመኪና አደጋ ብዛት የሚያስታውስ ሰው ይህ ወዳጄ ያለው ትክክል ሊሆን እንደሚችል ይገምታል።
የቬጋስ ወዳጆቼ ከተማውን እና የቱሪስት መስሕቦቿን ካስጎበኙኝ በኋላ ሳላየው መሔድ የሌለብኝ ሁለት ወሳኝ ቦታ እንዳለ ነገሩኝ። አንደኛው ከከተማዋ ለሁለት ሰዓታት በመኪና ተጉዘው ጭው ባለው በረሃ መካከል የሚገኘው የግብጾች ገዳም እንዲሁም ከቬጋስ 28 ማይል አካባቢ ስለሚርቀው ታዋቂው የ“ሑቨር ግድብ”። በሚቀጥለው ስለ ሁለቱ (ስለ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ስለ “ጥቁሩ ሙሴ/ ሙሴ ጸሊም” ቤተ ክርስቲያን ጨምሮ) እና ሌሎች ቀሪ የቬጋስ ጉዳዮች አካፍላችኋለሁ። ዕድሜ ይስጠንና።
 
© ይህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው አዲስ-ጉዳይ መጽሔት ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም::

18 comments:

Anonymous said...

you shared us good info

Kagnew Wolde said...

Well done, Dn. Ephrem. Your piece has taken me to a place, I have never heard much about and never imagined so... I really felt sorrow inside while I started thinking of how the daughters of Ethiopia, our sisters,could live a pious life in Vegas... Eager to read the remaining part.

Anonymous said...

Ababa, thanks for sharing . And I can't wait to hear about the Saint Antony Monastery.

Tade Tekle said...

Yetim bihon yet Zemenun Waju.

Anonymous said...

Hey Ephrem, I read ur articles "yegna sew belasveags". Oh my God, I was really ashamed of my people. What happen to them, Ephrem? Yehe Ethiopian yematelalat neger bearabu nation becha meslogn neber ahun gin wed Westernm eytezamete new. Beka wedefit eko bemanenetachen endenafer eytegededen new malet new. Ephrem, mechem Amlak lehulachenem asteway lebona yesten, and can't wait to read part two, bro. thanks for sharing. (Yemisirach)

ኤፍሬም እሸቴ said...

Thanx, Kagnew.

Anonymous said...

GREAT ARTICLE! Dn.Ephrem kezhi befit Ye'Bilate tizitawoch jemireh hoden sitkortew neber ahun demo lelaw bereha Lasvegas ....Ebakihin Tolo ketayun kifil asnebiben. And I also heard about the great church unity there and unlike other state EOTC churches ;they do there clergy(Kidase) on Thursday , I wish you could tell us more on your next part. keep up the good job(Sharing what u know and think better). GOD BLESS YOU AND YOUR FAMILIES !!!!

Anonymous said...

Dear Ephrem,

Short , Precise and sweet. Thank You for sharing your travel essay.

This is "Yegna Sew be Vegas?" Didn't you hear about "Yegan Sew be Reagan Building?" I invite you the ''intro" from Teddy Afro's Tikur Sew ... Minilik "Singelata, Singelata ... ei, u, ei, u ..." The victory of Adwa on Reagan Building Wahsingto DC. I said Thank you the Late Balcha Aba Nefso - Abebe Gellaw.

Anonymous said...

Dn,ephrem u saw things as different angles,i was read belatie it wondareful and good lesson,also yegna sew belasevegas article are also handsome.god be with u forever with his mother.

Zemedkun said...

Dn,Ephrem what a wondareful article u wrot,thanks alot for your experiance sharing,also thanks for belatie.God be with u forever with his mother,

Zemedkun said...

Dn,Ephrem what a wondareful article u wrot,thanks alot for your experiance sharing,also thanks for belatie.God be with u forever with his mother,

Anonymous said...

በጣም ጥሩ ፅሁፍ ሲሆን በኔ እይታ የተዛቡ ነገሮች የምላቸውን ከታች ላስቀምጥልህ::

“20 ሺህ ታክሲ ነው እኮ” በከተማው እንኩዋን 20 ሺህ ታክሲ ሊኖር 20 ሺህ ታክሲ ነጂ የለም በቅርቡ እኔ በርግጠኝነት የማውቀው በሳምንቱ መጨረሻ እና ማታ ላይ ከ 3,000 በለጥ የሚል ታክሲ በከተማዋ ይንቀሳቀሳል:: ከዚህ ውስጥም ወደ 10,000 የሚሆን ታክሲ ነጂ ሲኖር ቢያንስ ከግማሽ በላይ ኢትዮጵያውያን(በጣም ብዙ) እና የምስራቅ አፍሪካ ተወላጆች ናቸው::

ሌላው
“እንዴት ነው ያገራችን ሰው በቬጋስ?” ብዬ መጠየቄ አልቀረም። “ድሮ ጥሩ ነበር። የአገሬውም ሰው፣ ፖሊሱም በደህና ነበር የሚያዩን። አሁን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ስማችን እየተበላሸ ነው” አለኝ ታክሲ የሚነዳው አንዱ። “ምነው?” አልኩት። “ባክህ፣ አሁን አሁን የመጡ ልጆች መኪናውን እንዴት እንደሚነዱ ብታይ ይዘገንንሃል። ፖሊሶቹ ራሳቸው ‘የኔ ወንድም፣ ይህ አዲስ አበባ አይደለም’ ማለት ጀምረዋል። ኢትዮጵያዊ ከሆንክ እና ፖሊስ ካስቆመህ አይምርህም። በቃ ስማችንን እያበላሹት ነው። ብትነግራቸው ደግሞ አይሰሙህም። ባለጌ ስድብ ሊሰድቡህ ይችላሉ።” ቀጠለ ወዳጄ።

ወዳጅህን ምን እንዳጋጠመው ባላውቅም ይሄ ተከስቷል ብለህ ወደ መደምደሚያ የሚያደርስ አይመስለኝም:: ለምሳሌ ባጠገቤ ያሉ ልጆች እንክዋን ሊቅሙ ሲጋራ እንክዋን አያጨሱም:: ከዚህ ተነስቼ ማንም አያደርግም ልል አልችልም:: እንክዋን ወንዱ ቀርቶ ሴቱ ሲያቦነው ስለማይ:: (ይህንንም አይቼ ደሞ ሴቱ አጫሽ ነው ማለትም ከባድ ነው::) ስለ አገሬው ሰው እና ፖሊሱም ከሌላው ስቴት ምንም የተለየ የለውም:: STEREOTYPE is everywhere, even in our country.

መኪናውን እንዴት እንደሚነዱ ብታይ ይዘገንንሃል። ላለው
ሾፌሮች ሁሉ ተቀጣሪ እና መኪኖቹም ሁሉ የተያዙት በ፱ ካምፓኒዎች ሲሆን በስራቸው በ16 የተለያዩ ካምፓኒዎች አገልግሎት ይሰጣል:: እነዚህ ኩባንያዎች ጥረታቸው ወጪያቸውን ቀንሰው ለባለቤቱ የሚገባውን ገቢ መጨመር ነው:: ይሄን ለማድረግ ደሞ ሌላ ወጭም ያወጣሉ:: ለምሳሌ ሁሉም መኪኖች ካሜራ ሲኖራቸው እንኩዋን ተጋጭተህ በጣም ፍሬን ከያዝክ እንኩዋን መቅረፅ ይጅምራሉ:: ይህንን ያደረጉትበት አንድኛው ምክንያት
በአደጋ የሚያወጡትን ገንዘብ ለመቀነስ ነው:: you have to be a safe driver; to have a job the next day.
በዛ ላይ አንዳንዶቹ self insurance ነው ያላቸው:: ስለዚህም እነዚህ ነገሮች አልተዋጡልኝም:: እንደ አንድ ወጣት ላስ ቬጋስ ውስጥህይወቱን ለማሸነፍ እንደሚሮጥ ሰው ሳየው ስህተቱ የጎላ ነው:: በአናናሩ ላር ብዙ ማለት እችል ነበር:: ከእድሜ ልዩነቶች ጀምሮ ግን ይሄው ይብቃን::
ከ ቬጋስ

belete engida ከቬጋስ

Anonymous said...

......ለምሳሌ ባጠገቤ ያሉ ልጆች እንክዋን ሊቅሙ ሲጋራ እንክዋን አያጨሱም..............ሲጋራ የተሻለ ሱስ መሆኑ ነው, the lesser evil? ሱስ እንደሆን ያዉ ሱስ ነው፡፡ እንግዲህ ላንተ አልታየህ ይሆናል፡፡

Anonymous said...

Please, I'm eager to know about Vegas. I appreciate Efriem. Let me know from you too about the state.

Anonymous said...

ወዳጄ እየተባለ እንኩዋን የነበረው ጫት ቅሞ ስለመንዳት እንጂ ስለ ሱስ ማወዳደር አልነበረም::

Anonymous said...

What a wonderful piece. No matter what you write about, you have that skill to make it lovely and attractive to anyone. That is a noble gift. Not many people have that. Thank God we have you!!!

Anonymous said...

Thanks for your information. God bless you
from Sweden