Monday, June 18, 2012

ምንድር ነኝ? ማነኝ?


(በኢትዮጵያዊው ፍቅረ መድኅን/ READ IN PDF):- አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ጠየቀ:: ምንድር ነኝ? ማነኝ? መለሰም፡- አንደኛ  - የሥላሴ ፍጡር ፣ ሰው ነኝ፡፡ ኹለተኛ - ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ሦስተኛ፣አራተኛ… እያለ ወደላይም ወደታችም፣ወደፊትም ወደኋላም፣ወደግራም ወደቀኝም ሊሳብ እና ሊቀጥል ይችላል፡፡ ቁም ነገሩ ወደፊት ማራመዱ፣ ሰውን ኹሉ በሰውነት አንድነቱ መቀበሉ ነው፡፡ እኔ ደግሞ እንደ ሰውነቴ በአገሬ ሆኜ ምንድር ነኝ? ማነኝ? ስል ጠየቅኹ፡፡ ስለዛም ‘ኢትዮጵያዊ ነኝ’ አልኩ፡፡


ቋንቋ ያ ወይንም  ይሄ ሊኾን ይችላል፡፡ አባ እንደሚናገረው እናቱ - አባታቸው ኦሮሞ እናታቸው ደግሞ አማራ እንደኾኑ ይናገሩ ነበር፡፡ የአባቴ አባት (አያቴ) ደግሞ አባታቸው ትግሬ እናታቸው ሳሆ እንደነበሩ ሰምቷል፡፡ እናቴአባቷ በአባቱ ጉራጌ በእናቱ ደግሞ የሸዋ ኦሮሞ እንደኾነ ነግሯታል፡፡ እናቷ ደግሞ አባቷ አማራ እናቷ አገው እንደኾኑ ነግራታለች፡፡ ረ ለኛም ለልጅ ልጆቿ ነግራናለች፡፡ አዎ አስታውሳለሁ፡፡ ነፍሱን ይማርና ያባቴንም አባት እንዲሁ፡፡

እኔ እንግዲህ ምንድር ነኝ? ማነኝ? እኔ ከላይ እንደተጠቀሰው እንደ ወላጆቼ አባባል ብቻ ብሄድ እንኳ ከአያቶቼ ሳልዘል፡-ኦሮሞ፣ አማራ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ፣ አገው እና ሳሆ ነኝ ማለትም አይደል? ወደ ቅድመ አያቶቼ እና ከዚያም ባልፍማ እኔነቴ እየበዛ እየበዛ ዘመደ ብዙ መኾኔ አያጠያይቅም፡፡ተመስገን ነው ላወቀበት፡፡

አሁን ባለ ትዳር ነኝ፡፡አግብቻለሁ፡፡ ሚስቴ አባቷ አባታቸው ከንባታ እናታቸው ደግሞ ሃድያ እንደኾኑ እንደነሯት ነግራኛለች፡፡ እናቷ ደግሞ አባታቸው አማራ እናታቸው ደግሞ የሐረር ኦሮሞ እንደኾኑ እንደሚናገሩ ትናገራለች፡፡ ልብ በሉልኝለኹላችን ልብ ይስጠንና፡፡ በአካሌ፣ በሚስቴም በኩል እንዲሁ ስንቆጥር ከአያቶቿ አላለፍንም እንጂ ጨምረን እንበዛ ነበር፡፡ ነገሩ በዝተናል፡፡ በእውነትም ብዙ ነን፡፡ እንደው እንቁጠር ካልን እንጂ፡፡ ከምር እንቁጠር ብንልማ መች ተዘልቆ? ማሰቡም ያደክማል፡፡ የምድር አሸዋ ይቆጠራል? እንደው ብዙ ስንኾን አንድ ነን ማለቱ ይበጀናል፡፡ ይቀጥላል

ባለቤቴ እና እኔ ልጆች ወልደናል፡፡ ልጆቻችን ምንድር ናቸው? የማን ናቸው? ለምታነቡቱ ቀላል የቤት ሥራ ሰጥቻለሁ፡፡ ጥያቄው የወጣበትን ምንባብ እያነበቡ እንደመመለስ ዓይነት፡፡ በእንግልጣሩ “ኦፕን ቡክ ቴስት” (open book test) እንደሚሉት  መኾኑ ነው፡፡ ገና ይቀጥላል፡፡ እኔ ግን ላበቃ ነው፡፡

ባለቤቴፈጣሪ ይመስገን እና አራት እህቶች እና ወንድሞች አሏት፡፡ እኔ ደግሞ ስድስት፡፡ እኔ እና ባለቤቴ ስንጨመር ድምሩ 12 አልሆነም? ወንድሜ እቴ የምንባባለው፡፡ ኾኗል፡፡ ረ ከዚያም ይበልጣል፡፡ በጣም በጣም… ፡፡ ምክንያቱም ከእኔ እህቶች እና ወንድሞች አራቱ ከእርሷ ደግሞ ሦስቱ አግብተዋል፡፡ እነዚሁ ደግሞ ኢትዮጵያን በአራቱም አቅጣጫ ተሳልመዋታል፡፡ ረ በስምንቱም አቅጣጫ፡፡ ከዚያም ደግሞ ይልቃል፡፡

በሰሜን ፣ በደቡብ ፣ በምስራቅ ፣ በምዕራብ ፣
በባሕር ፣ በመስዕ ፣ በሊባ ፣ በአዜብ ፣
የቀራቸው የለም ፡፡

“ከኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የቀራቸው የለም፡፡ አዳርሰውታል፡፡ አዳርሰነዋል፡፡ ከኹሉ  ተጋብተናል፡፡ ተጋብተዋል፡፡” እያልኋችሁ እንደኾነ መቼም ለናንተ አይነገርም፡፡ “ሠርገኛ ጤፍ ማለት ነን እኮ” ነው ያሉት እኒያ ኢትዮጵያዊ የአምቦ ሰው?
ታዲያ እኔ ምንድር ነኝ? ማነኝ? ሲባል አንደኛ  - የሥላሴ ፍጡር ፣ ሰው ነኝ፡፡ ኹለተኛ - ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ኹሉንም ፡፡


(ኢትዮጵያዊው ፍቅረ መድኅን እንደጻፈው)

20 comments:

Anonymous said...

እኔ ማን ነኝ የሚል የድሮ ጫወታ የጀመርከው ኢህአዴግ ልክ አይደለም ለማለት ነው አይደል ፡፡ አጼ ሚኒሊክ እና ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ያታለሉን ይበቃል ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ሆይ ስማ እድሜ ለመንግስቱ ኃ/ማሪያም የሰለሞን ስርወ መንግስት ላይመለስ ሄዷል፡፡

Anonymous said...

it is correct i am humane binge and i am black in
Africa i am Ethiopian

afi said...

thank you very much, God bless you!
you/Ephrem Eshete/ and Daniel Kibret is my hero that the Facebook guaranteed me. in many articles of you i have witnessed your corner of understanding really wonderful. you cannot know how much important you are for Ethiopia. please press on!
in my opinion the fact to ''who i am '' is just the moral what he has been living in and what is doing!
thank you indeed!

Anonymous said...

yemejemeriyaw asteyaye sechi chelemtegna athun

Anonymous said...

1st Anonymous.why you jump to emperior Menilik & Haile selase. they did all the best on their golden time to unite & modernize their country. you may question their method. if you are willing to open ur eyes ,it is EPRDF who is fooling you to stay on power with telling u to hate ur brothers & glorify differences not Menlik not Haile selase...

Anonymous said...

lek belehal yemjemriyaw asteyayet sechi chelmtegna new zelo poletica weset megebat ere wediya

Anonymous said...

ዲ/ን ኤፍሬም፡ እኔም እንዳንተው ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ክርስቲያንም ጭምር፡፡ የዘር ግንዳቸው ከተለያዩ ብሔር ስላሆኑ ሰዎች ዘምረሃል- ክፋት የለውም፡፡ ብዙም እንደሆናችሁ ገናም እነደምትበዙም ጭምር፡፡ ጥሩ ነው ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት- ደስ ይላል፡፡
ግን ማወቅ ያለብህ እንደኔ ወይም እንደ ሌሎች ብዙዎች አይነት ንፁህ አንድ ብሔር (አማራ፤ ኦሮሞ፤ ወላይታ….ወዘተ) ብቻ የሆነ ብዙ አሉ፡፡ ይህም ክፋት እንደሌለው ማመን አለብህ፡፡ ለእናንተ ሰላም ብልፅግና እድገት በአጠቃላይ ለሰው ልጅ ያለው መልካም ነገር እንደምያስፈልጋችሁ ሁሉ ለእነዚህም ያስፈልጋጨዋል፤ ይገባቸዋልም፡፡
በዚህች ምድር (ኢትዮጵያም ሆነ ሙሉ ዓለም) ላይ አብሮ በሰላም ለመኖር የግድ እንደናንተ መሆን አያስፈልግም፡፡ የተለያየንም ሆነን አብረን በሰላም መኖር እንችላለን፡፡

Anonymous said...

MELKAM !ENA MAN NEGNE? ABATE ERITRA,ENATE,TIGRA,MISTA,AMARA,QANKUAYE YEHABESHA,HAYMANOTE TEWAHEDO,ENA MAN NEGN? BEARAYA SELASE YETEFETERKUN SEW!BEKA LELAW HULU YEMEYALEF NEW!!
THANKYOU D EPHREM

Anonymous said...

Yesterday I was going to comment about your idiosy. However, I decided you're not worth of my comment and time. But today I want to let you know you don't worth my comment.

Anonymous said...

The issue will not stop to the end of the world ......However.. To slove the problem it need

Simple Math
Expreance+Age+Gun+discusion+money+Marrage+child+Blood+God+Hager+++++=የሥላሴ ፍጡር ፣ ሰው ነኝ፡፡ ኹለተኛ - ኢትዮጵያዊ ነኝ!!!!!

Otherwise You will be Stone Head Like Our.....Pm.Melse ....

ኤፍሬም እሸቴ said...

This article is not mine, my friend. But what you said above (ንደኔ ወይም እንደ ሌሎች ብዙዎች አይነት ንፁህ አንድ ብሔር (አማራ፤ ኦሮሞ፤ ወላይታ….ወዘተ) ብቻ የሆነ ብዙ አሉ፡፡ ይህም ክፋት እንደሌለው ማመን አለብህ፡፡)is correct. And your othger idea (በዚህች ምድር (ኢትዮጵያም ሆነ ሙሉ ዓለም) ላይ አብሮ በሰላም ለመኖር የግድ እንደናንተ መሆን አያስፈልግም፡፡ የተለያየንም ሆነን አብረን በሰላም መኖር እንችላለን፡፡) is correct too. The writer did not oppose that either. did he?

አንተነህ said...

አንድ መምህር ሲሰብክ ዘረኛ ሰዉ ኃይማኖት የሌለዉ ወይም መናፍቅ ነዉ አለ። እኔ እስማማለሁ።

Anonymous said...

In approaching where you from in health we need to be aware of complex and contentious history of Man!!! I do agree Strong army Will Solve the problem

First Step …Kill All people who have Same Brain like Our Pm Melse in all direction of Ethiopia because this Virus Will not removed by Education or age or discussion it is Like Hiv …… Eg TPLF. Aba paulus….

Second step… submit Continues Education… diversity concept, tolerance ……. For those wants to Change

Finaly All Ethiopia including Muslim Must Work With Mahiber Kidusan Concept… Mk is more advanced in every Direction Long Live Mk …… Keep Walking ... Had It been it was In American Mk Will have chair in congress b/c People see things in different Direction …

Anonymous said...

you racist and banda, dedeb, Hodam who you do not like Ethiopian Welfare and Unity;
wether you believe or not one day we will see the down fall of Bandas ok.we are one Ethiopian.

Anonymous said...

me too

Anonymous said...

He my bro.i agree with most of ur ideas and to kill another is not Gods willing and you should respect our pop. "endayferdebeh ateferd ". if ur christian u should be like christians.

Addis Bezuwork said...

የሥላሴ ፍጡር ፣ ሰው and ኢትዮጵያዊ ነኝ is enough!!! We are related with our nation and nationality one way or another a long time ago. We don't need a remainder like Epdrf strategies nation and nationality day. Nice issue!

Anonymous said...

I think we all fall under ethnic politics. believe or not we lost some kind of human development.

Tsegi said...

is there such thing as nesthu person from one behreseb ..i doubt that?

Etsegenet said...

ethiopiawinet is being included in one country called Ethiopia...an ancient word that means 'burnt face' but all human beings are one race..that is the human race...'adam and eve'