Friday, June 22, 2012

አድራሻ


 (ኤፍሬም እሸቴ/ PDF):- ድንገት በአጋጣሚ ቴሌቪዥናችሁን ወይም ሬዲዮናችሁን ስትከፍቱ የምታዩትን - የምትሰሙትን ማስታወቂያ እና የማስታወቂያ አስነጋሪውን አድራሻ ልብ ብላችሁ አድምጡ። ድርጅቱ ስለሚሠጠው አገልገሎት መልካምነት፣ ስለሚሸጠው ዕቃ ምርጥነት፣ ስለሚያቀርበው ምግብ ጥዑምነት ዘርዝሮ ሲያበቃ አድራሻውን ማስቀመጡ አይቀሬ ነው። በርግጠኝነት ግን በዚህ ቦታ ነው ድርጅታችን ያለው ከማለት ይልቅ … “ከእንትን ወረድ ብሎ፣ ከእንትን ከፍ ብሎ፣ እንትን እና እንትን ፊት ለፊት፣ እንትን አውቶቡስ ማዞሪያ፣ እንትን ኤምባሲ አካባቢ” …. ይለናል።

 አንዱ የካዛንችዝ ልጅ ስለ ራሱ ሲናገር ከሚለው ግምት እንውሰድ። “ራስ መስፍን ሜዳ አጠገብ፣ ግንፍሌ ወንዝ ከፍ ብሎ፣ ከሸዋ ፖሊስ ወረድ ሲል ባለው መንገድ ገባ ብሎ ከሚገኝ አንዲት ቤት ውስጥ ተወለድኩ” ቢል ወይም ገጠር የተወለደው ደግሞ “እኔ እገሌ እገሌ፣ በእንትን ክፍለ ሀገር፣ እንትን አውራጃ፣ ልዩ ስሙ እንትን በሚባል ቀበሌ ተወለድኩ” ቢባልለት እንደማለት ነው።

ይህንን በሜትሮሎጂኛ ብንመነዝረው “በሚቀጥሉት ሦስት ቀናት የሰሜን እና ምዕራብ አማራ፣ መካከለኛው ኦሮሚያ፣ የደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች መጠነኛ ዝናብ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል” እንደሚለው ዓይነት ትክክለኛው አድራሻ ያልታወቀ ጥቆማ ነገር ነው። በርግጥም አድራሻን በግልጽ መናገር፣ አቅጣጫን በአጭሩ መግለጥ እንዲህ ከባድ ኖሯል?

የየትኛውም ያደገ ሥርዓት ያለው አገር ዋነኛ መገለጫው በዚያች አገር ውስጥ ያለን ማንኛውንም ሥፍራ፣ ማንኛውንም ሰው በትክክለኛ ማንነቱ እና አድራሻው መግለጥ መቻሉ ነው። አንድ እንግዳ ሰው አዲስ አበባ ከተማ ላይ ቢጠፋ እና ኒውዮርክ ላይ ቢጠፋ ከወጣበት ለመመለስ ቀላሉ ሥፍራ አዲስ አበባ ሳይሆን ኒውዮርክ ይመስለኛል። በንጽጽር ካየነው አዲስ አበባ ከኒውዮርክ በስፋት በግማሽ ያህል ያንሣል። በሕዝብ ብዛትም ብናየው ኒውዮርክ ከአዲስ አበባ በእጥፍ ይበልጣል። ኒውዮርክ 8.2 ሚሊዮን ነዋሪ አላት። ነገር ግን ያለማንም ረዳት ኒውዮርክ ውስጥ ወደየትኛውም ሥፍራ ለመሔድ እና ከወጡበት ዞሮ ለመመለስ ምንም አያዳግትም። ለእኛ ለአዲስ አበቤዎች ካልሆነ በስተቀር “አዲሳባ” ለእንግዳ ሰው መያዣና መጨበጫ የሌላት ከተማ ናት።

ጀርመን አገር ያገኘኹት አንድ ካሜሩናዊ ተማሪ ያለኝን አስታወሰኝ። ካሜሩናዊ ወዳጄ አንድ ሳምንት አዲስ አበባ የመቆየት አጋጣሚ ነበረው። ለካስ ከተማ ውስጥ ሲዘዋወር ከወጣበት በቀላሉ ለመግባት መከራውን ሲያይ ቆይቷል። በካሜሩን “ስታንዳርድ”ም ቢሆን አዲስ አበባ አቅጣጫ እና አድራሻዋ ውጥንቅጡን የወጣ ሆኖበት መቸገሩን እንዳጫወተኝ፣ “ከአየር መንገዳችሁ ውጪ ከተማችሁ አይረባም፤ አቅጣጫም አድራሻም የሌለባት ናት” እንዳለኝ አስታውሳለኹ።

ልብ ብለን ካስተዋልነው አድራሻ አገላለጻችን ፍፁም “ኢትዮጵያዊ” እና ለራሳችን ብቻ ካልሆነ ለሌላ ሰው ለማስረዳት ግራ የሆነ ነገር ነው። ወደ 6 ኪሎ የሚሄዱ ሚኒባሶች “ተፈሪ መኮንን፣ 6 ኪሎ” ሲሉ እኛ ነዋሪዎች በቀላሉ የት እንደሚሔዱ እንረዳለን። “ተፈሪ መኮንን” የሚለው አድራሻ ግን በሰው ልብ ካልሆነ በስተቀር በመንግሥት ልብ ስማቸው ከተቀየረ 30 ዓመታት አለፈ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ “ጀሞ ሠፈር፣ የሺ ደበሌ” ወይም ደግሞ ሰዉ በራሱ የሚግባባበት “ወርልድ ባንክ” የሚባል አድራሻ መስማት የተለመደ ነው።

እንዲህ ዓይነቱን አገላለጽ በደፈናው “ባህላዊ አድራሻ” ብንለው፣ ከተማይቱ ትክክለኛ ዓለማቀፋዊ ይዘቷን እንድትጠብቅ የሚያደርጋትን “ደረጃውን የጠበቀ አድራሻ” እንደሌላት እንረዳለን። በሌሎች ከተሞች እና ገጠራማ አካባቢዎች ያለው ሁኔታ በዚህ መልክ ቢኖር የማይገድ ቢሆንም የአፍሪካ መዲና የተባለች ከተማ፣ ቤቶች እና ነዋሪዎች በታወቀና በተረዳ አድራሻ የማይታወቁ መሆናቸው ከተማይቱን አይመጥናትም።

ይህንን ጽሑፍ በማዘጋጅበት ወቅት ልመለከተው የሞከርኩት አንድ “የቱሪስት መምሪያ” ወይም “Tourist Guide” ከተማይቱ ካሏት መንገዶች የተወሰኑት ስሞች እንደተለጠፉላቸው ከጠቀሰ በኋላ የተለጠፉት ስሞች ካርታ ላይ ካሉት ጋር ላይመሳሰሉ ስለሚችሉ ቱሪስቱ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያስገነዝባል። ያ በዘመቻ የተተከለው መንገዶችን ሁሉ በአፍሪካ አገሮች ስም የመሰየም ዘመቻ ፋሺኑ አልፎ ብረቶቹ ወዳድቀዋል ማለት ነው። መንገዶቹ አግኝተዋት የነበረችው ትንሽ ዕድል ተመልሳ ከስማለች ማለት ነው።

ይሁን እንጂ አድራሻ ማበጀትና ከተማይቱን መልክ መስጠት እንዲህ ከባድ ሆኖ አይደለም። ክፍለ ከተማው፣ ወረዳው፣ ቀበሌው እና የቤት ቁጥሩ ለሚታወቅ ሰው ‘አድራሻ’ ማበጀት እና ያንንም “ስታንዳርድ” ማድረግ ይቻላል። ለክፍለ ከተማዎቹና ወረዳዎቹ ቁጥር ቢሰጥ፣ ቀጥሎ የሚመጡት ቀበሌ እና ቤት ካለ ቁጥር መለያ ስለማይኖራቸው ያንን በማስከተል የአንድን ሥፍራ ቋሚ አድራሻ ማመልከት ይቻላል።

በፈረንጆቹ፣ ለምሳሌ በምንኖርበት በአሜሪካ ያለውን የአንድ ቤት አድራሻ አሰያየም እንመልከት። መጀመሪያ ክፍለ ከተማ ሊባል የሚችል “ሲቲ” የሚሉት አላቸው። ቀጥሎ የመንገዱ ስም፣ ከዚያም የቤቱ ቁጥር ይከተላል። በመጨረሻም የፖስታ አገልግሎት ድርጅቱ የሚጠቀምበት “ZIP code” የሚሉትና አገሪቱን የከፋፈሉበት ቁጥር አለ። የአንድ ቦታ አድራሻ በነዚህ ይታወቃል።

ለምሳሌ የፕሬዚዳንት ኦባማን መኖሪያ አድራሻ “ዋይት ሐውስን” እንዲህ ላስቀምጠው እችላለኹ። ቤተ መንግሥቱ ያለበት ጎዳና Pennsylvania Avenue ሲሆን ቁጥሩ ደግሞ 1600 ነው። ከተማ Washington, DCሲሆን ፖስታ መሥሪያ ቤቱ የሰጠው የአካባቢው “ኮድ” 20500 ነው። ይህ ሁሉ አንድ ላይ ሲገጣጠም ነው እንግዲህ “1600 Pennsylvania Avenue NW Washington, DC 20500” የቤተ መንግሥቱ አድራሻ የሚሆነው።

እያንዳንዱ መንገዳቸው ስም ስላለው፣ ቤቶቹም ቁጥር ስለተሰየመላቸው በዚህ መልክ መጠቀሙ ለእነርሱ ቀላል ነው። መንገዶችና ስሞች ባልተሰናሰሉበት እንደ ኢትዮጵያ ባለው አገር ደግሞ ከፍ ብዬ በጠቀስኩት መልክ መጠቀም ይቻል ይመስለኛል። ለምሳሌ እኔ በ“አራዳ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 01፣ ቀበሌ 02፣ የቤት ቁጥር 03” ውስጥ ነዋሪ ብሆን አድራሻዬ በአጭሩ፦

ኤፍሬም እሸቴ

አራዳ 1-2-3፣

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ይሆናል ማለት ነው። “አራዳ” የሚለውን የክፍለ ከተማውን ስም ተከትሎ የሚመጣው እያንዳንዱ ቁጥር ምን እንደሚወክል ስለሚታወቅ አድራሻው እንደዚያው ግልጽ ይሆናል ማለት ነው። በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01፣ ቀበሌ 02፣ የቤት ቁጥር 03 ውስጥ የሚኖር ኤፍሬም የሚባል ሰው አለ ማለት ነው።

አድራሻን በታወቀና በተረዳ ስም እና በተረዳ ቁጥር ሰፍሮና ለክቶ ለማስቀመጥ “እርግጠኛ” የሆነ ነገርን መሻት ያስፈልጋል። እርግጡን ሳይሆን “አካባቢውን” በማወቅ ብቻ ለሚረካ ማኅበረሰብ “እርግጠኛ” አድራሻ መኖሩ ብዙም ትርጉም ላይሰጠው ይችላል። እኛ ደግሞ በአብዛኛው ነገራችን “እርግጠኛውን” በማወቅ፣ በማሳወቅ፣ በመናገር፣ በመስማት ላይ ያልተመሠረተ ስለሆነ “እቅጩን” የሆነ ነገር ብዙም ትርጉም አይሰጠንም።

ለምሳሌ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ስንት ነው ቢባል - ከ80 ሚሊዮን በላይ፤ የአገራችን ቋንቋ ብዛት ስንት ነው - ከ80 በላይ፣ እገሌ የተባለው ድርጅታችሁ ስንት ሠራተኞች አሉት - ከ10 በላይ፤ በቀበሌያችሁ ስንት ወጣቶች አሉ - ከ10 ሺህ በላይ … ዛሬ የት የት ይዘንባል - በአንዳንድ የኦሮሚያ ተራራማ አካባቢዎች … ።  እርግጠኛ የሚታወቅ እና የሚነገር ነገር የለም። “በላይ፣ አካባቢ፣ ተብሎ ይገመታል፣ ይጠበቃል፣ ይጠናል፣ ይሻሻላል፣ አንዳንድ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ አንዳንድ አሸባሪዎች፣ ጥቂት ግለሰቦች” … ይቀጥላል። ምንም እርግጠኛ ነገር የለም።

እርግጠኝነቱ የሚጎድለው አንድም ነገሮቹን ለማወቅ ካለው ውሱንንት፣ አንድም ነገሮችን ሰፍሮ ቆጥሮ ለማወቅ ካለ ዳተኝነት ነው። 20 ሠራተኛ ያለው ድርጅት ብዛታቸውን በቁርጥ ለመናገር ቸግሮት “20 አካባቢ፣ ወደ 20 ግድም፣ ከ19 በላይ” በሚሉ ንጽጽራዊ፣ አመላካች ነገር ግን እርግጠኝነት የጎደላቸው አገላለጾች መጠቀም አይገባውም። ችግሩ እቅጩን የመናገር ነገር ነው። “ዕድሜህ ስንት ነው? ከ30 በላይ፣ ሰላሳዎቹ አጋማሽ፣ ወደ አርባው እየተጠጋሁ ነው” ዓይነት።

ከተሞች ጎጆ እየወጡና እየተስፋፉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ሕዝብን እና አካባቢን በሥርዓት ለማስተዳደር ዘመኑ ከሚጠይቀው የተቆረጠ እርግጠኛ አድራሻ ጋር መተዋወቅ፣ ለዚያም ለከተሞች አድራሻ “ስታንዳርድ” ማውጣት እና ልጆችን ገና ከለጋነታቸው ከትምህርት ቤታቸው ጀምሮ ማስተማርና መቅረጽ ያስፈልጋል። የሥልጣኔ ምልክቱ ነገሮችን ሰፍሮ እና ቆጥሮ ማወቅ ነውና ከመንገዱና ከቤቱ ግንባታ ትይዩ ይህም ዓይነቱ ዘዴ ይገንባ። አድራሻ ያላቸው ከተሞች ይኑሩን።

 

 

 

 

   

© ይህ ጽሑፍ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስጉዳይ መጽሔት ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም::
    

11 comments:

Anonymous said...

Possible Reason why there is no tangible Information In Ethiopia

1st…Most Ethiopia Believe by God !!!People give there will to God 100% so No Body not wants specific adders Our Adders is God …kidsa Mahile …Seatate..Tosme… on Sunday Every one is in church !!
2nd….We learn from our Government..Ato Melse Never Speak Truth … Let Us say Our Prime Min Ato Melse z Said I am In Arada Subcity that Means He is In Duba or Gojme because Nobody Believe Him So ….Why We should worry About Adders …
3rd Thanks you So much Good Lesson OneDaY We will be !!!!

Anonymous said...

ታ እሻይ ነን ቱማ ምኖ:: ኑ ጎዲያ ማርያማ ነና አንጁ::

Anonymous said...

Good view!

Anonymous said...

wey ephrem ene erasu ke 12 belay wede 14 yemitegu ehet ena wendemoch alugen bergtgnegnet gen 1 enat alegn

Anonymous said...

EXCELLENTAE!!

Addis Bezuwork said...

Wow! Nice view as always! Keep it up!!!

Anonymous said...

Dear Ato Ephrem,nice to read your view as usual.But I was wondering if you are aware of the current progress under the The Integrated Land Management Information System Project Development Office of the Addis Ababa City Administration.
http://addisfortune.com/Vol_12_No_621_Archive/news_radar.htm
http://www.addisfortune.com/Vol_12_No_595_Archive/news_radar.htm
I hope by now they are done with the sample sub cities.

ዘመድ said...

ዲ/ኤፍሬም በእውነቱ የአዲስ አበባን አድራሻ አሰያየም ችግር በደንብ ተመልክተህዋል፡፡አዲስ አባባ በአራቱም አቅጣጫ እየሰፋችን እያደገች ብትመጣም የሰፈሮቹንና የመንደሮቹን የስም አሰያየም ዘመናዊ መልክን ያልተከተለ እንዲሁም አድራሻቸውን ለማወቅ አስቸጋሪ የሆነች ከተማ ሆናለች፡፡ስለሆነም ችግሩን ማውጣት በመቻልህ ልትመሰገን ይገባል፡፡

Anonymous said...

አንድ እውነተኛ አጋጣሚ አስታወስከኝ ልጁ የሮረው ያደገውም ውጭ ሃገርነው ታዲያ ለእረፍት ከብዙ ዓመታት በኋላ ወደ ሃገሩ ቤተሰቦቹ ይሃድና አንድ ቀን ፍል ውኃ ገቤተ ሰብ ጋር ይሃዳል ልጁም ለጤናው በጣም ስለተስማማው በሚቀጥለው ቀን ብቻውን ሰው ላለማሸገር ይሄዳል እበሩ ላይ ደርሶ በተንተባተበ አማርኛ ልታጠብ ነው አስገቡኝ ብሎ ሲጠይቅ አናስገባም ሳይሆን ተገፍትሮ ወደ አንድ ጥግ እንዲቀመጥ ተደረገ እርሱም ዱላ እደሚከተለው ስላወቀ ሌላ እሚያነግረው ሰው እስኪመጣ ጠብቅ ስለተባለ ተቀመጠ ያም ሰው መታወቂአውን እዲያሳየው ጠየቀው መታወቂያውን ሲመለከት
የውጭ ሃገር ሰው ነው የት እዳለ ነግሮ ወደ ሚሄድበት መራው። ለካስ ቤተመንግስት ነበር

Anonymous said...

Nice perspective. Keep writing please

Anonymous said...

They just left the city and gone to abay to build another dam which it's adress is not known.