Wednesday, July 11, 2012

አንድ-ትልቅ ወይስ ብዙ-ትንንሾች? (ክፍል ሁለት)


(ኤፍሬም እሸቴ/ PDF):- ባለፈው እትም የመግቢያ ጽሑፌ በዚህ ርዕስ መነሻ የሚሆኑ ሐሳቦችን ለማቅረብ መሞከሬ ይታወሳል። የርዕሰ ጉዳያችን መሠረታዊ ጭብጥ በማንኛውም ነገር ዙሪያ የምንፈልገው እና የምንገነባው “አንድ ትልቅ ነገር ነው ወይስ ከዚያ ከትልቁ የሚያንሱ ብዙ ትንንሾችን?” የሚል ተጠየቃዊ ሐሳብ ማኼድ ነበር። ለአብነትም እንዲሆን አንድ ትልቅ ከተማ - አዲስ አበባ፣ አንድ ስቴዲየም፣ በየዘመኑ ስመጥር የሚሆኑ ‘አንዳንድ’ አትሌቶች ወዘተ ማለታችን ይታወሳል። በሌላ በኩል ባደጉትና እኔ ከማውቃቸው አገሮች ምሳሌነት በመነሣት የጉዟቸው ፍልስፍና ከዚህ ተቃራኒ ማለትም አንድ ግዙፍ ነገር ሳይሆን የተመጠኑ-ብዙ-ትንንሾችን በመገንባት ላይ ያተኩራል ማለቴን አስታውሱልኝ። በዚህ እትም ደግሞ በዚሁ ርዕሰ ጉዳይ በመግፋት ሌሎች አብነቶችን ለማንሣት እሞክራለኹ።

ከትምህርት እንጀምር። ማንኛውም አገር በትምህርት አቀራረጹ እና ግቡ ለአገሬ ይጠቅመኛል ብሎ የሚይዘው አካሔድ አለው። ትምህርት ቤት በነበርኩባቸው ዘመናት እንደማስታውሰው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገባው በጣት የሚቆጠረው ከመሆኑም በላይ ጨርሶ የሚወጣውና ወደ ሥራ የሚሠማራውም ከገባው ላይ ተቆንጥሮ፣ ተንጠርጥሮ፣ ነጥሮ፣ ተፈትኖ፣ ተምሮ ብቻ ሳይሆን ተማርሮ፣ ተባርሮ ነው።
ዩኒቨርሲቲዎቼ በጣት የሚቆጠሩ፣ መምህራኑ በጣት የሚቆጠሩ እና እንደ አምላክ የሚፈሩ። ፈተናዎቹ ዕውቀት የሚጠይቁ ብቻ ሳይሆኑ የመምህራኑን የመሸወድ ችሎታ የሚያመለክቱ። በርግጥ ይህንን ሁሉ አልፎ የወጣው ተማሪ ግን ሥራ ለማግኘቱ እርግጠኛ የሚሆን፣ በሌላው ዓለምም ሄዶ ተወዳዳሪ የሚሆን፣ ተምሮና ተማሮ የወጣባቸውን ተቋማት የማያስወቅስ ነበር። በርግጥም ኢትዮጵያውያኑ በሄዱበት አገር በትምህርት ብቃታቸው ሲታሙ አልሰማኹም።
አሁን እንደሚታየው ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገሪቱን አጥለቅልቀዋል። በችሎታው ማነሥ  ሳይሆን በተቋማት ማነሥ ከ12ኛ ክፍል መዝለቅ የማይችለው ተማሪ አሁን ሰፊ ዕድል ተከፍቶለታል። የዚያኑ ያህል፣ መምህራን ጓደኞቼ ሲያማርሩ እንደምሰማው፣ ተማሪው ብዛት እንጂ ጥራት የለውም፣ መመረቅ እንጂ በቂ ዕውቀት ለመጨበጥ አልታደለም፣ ተመርቆ ከወጣ በኋላም ሥራ ለማግኘቱ ምንም እርግጠኝነት የለውም።
ምንም ቢሆን ካለመማር መማር ቢሻልም የጥራቱ ጉዳይ ዋዛ ፈዛዛ የበዛበት ሲሆን ግን አለመማር የሚያስመርጥበት ጊዜ አለ። የተማረ የሚመስል ነገር ግን በቂ ዕውቀት ያልገበየ ሕዝብ በመጣ መጠን መማርን ከቁም ነገር የሚቆጥር ቀጣይ ትውልድ ማግኘት ከባድ ይሆናል። መማርም አለመማርም እኩል ይሆንበታል። “ብማር ምን ቁም ነገር አለኝ? ባልማርስ ምን ልጎዳ? አንዲት ዲግሪ ለመጨበጥ አራት ዓመት ዕድሜዬን ከማጠፋ ለምን ሌላ ነገር አልሞክርም?” ይላል ወይም በአቋራጭ የሚከብርበትን መንገድ ይፈልጋል፤ የባለሥልጣናትን ጫማ በመሳም፣ በማጭበርበርና በጨለማ ሥራ ገንዘብ ሊያገኝ የሚችልበትን መንገድ ይፈልጋል።
አጎብዳጅነት እና የውስጥ እግር በመሳም የሚያድሩ ሰዎች በበዙ መጠን እውነተኛነት፣ ቀጥተኛነት፣ ግልጽነት እና በላብ ማደር፣ በችሎታ ማደግ እየቀጨጩ ይመጣሉ። በሠራ ሳይሆን በተገዛ፣ ባወቀ ሳይሆን ባሳበቀ፣ በለፋ ሳይሆን ባጎበደደ መጠቀምና ማደግ የአገር ባሕል ይሆናል። ከየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚመረቁ ነገር ግን የሚገባውን ዕውቀት ለመጨበጥ ያልቻሉ ሰዎች መብዛት ዕውቀት ላላቸው እና በችሎታቸው ለሚያድሩ ሰዎች አደጋ ነው። እንደ ካምቦዲያ አምባገነን ጨፍጫፊዎች ያሉ ፀረ-ምሁራን ይሆናሉ።
የካምቦዲያ አምባገነን መንግሥት የነበረው የኬሜንሩዥ አገዛዝ ዕውቀትን የሚጠላ ስለነበር መምህራንና ምሁራንን አስጨፍጭፏል። ሕዝቡ ከመሠረታዊ የሒሳብ ዕውቀት የበለጠ እንዳያውቅ በማድረግ ሕዝቡን በአብዮታቸው ዲስኩር ቁም ስቅሉን ያሳዩት ነበር። የተማረ ሰው ለአገዛዛቸው እንደማይመች ስለሚረዱ ምሁራን፣ መምህራን እና ዕውቀት ያላቸው ሰዎች የአገዛዙ ሰለባዎች ለመሆን በቅተዋል። ከዚያም አልፎ ሕጻናትን በማሰማራት፣ አዋቂዎችን እንዲሰልሉ በማድረግ ጠላትነትን አንግሰዋል። በዕድሜ ሕጻናት እና የመከነ ትምህርት ያፈራቸው ትልልቅ ሰዎች በአስተሳባቸው አይለያዩም።
ከዕውቀት-ጠል መሪዎች ጀርባ የደነበሸ-ትምህርት ሊኖር እንደሚችል ለመገመት አይከብድም። ምሁራንን የሚጠላ አገር በማን ሊመራ ይችላል? ዕውቀት ሳይሆን ድፍረት፣ ብቃት ሳይሆን ፍጥነት፣ ማመዛዘን ሳይሆን በደመነፍስ በሚመላለሱ ሰዎች እጅ መውደቅ ይመጣል። 
ትምህርትን በዚህ ርዕሰ ጉዳይ እንዳነሳው ያደረገኝ ስለ ትምህርታችን ጥራት ለመወያየት ሳይሆን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸውን ወፈ ሰማይ ምሩቃን አፍርቶ ሥራ ከመቸገር ይልቅ ለራሳቸው በአጭር ጊዜ በቂ ዕውቀት ገብይተው መጠነኛ ሥራዎችን የሚሠሩ ብዙ ዜጎችን ማፍራቱ ላይ የሚያተኩሩትን አገራት አጭር ግላዊ ግምገማ ለማካፈል ነው። በዚህ በምንኖርበት በአሜሪካ አብዛኛው በመካከለኛ ሥራ ላይ የተሠማራው ዜጋ በወራት ብቻ ለሚቆጠሩ ጊዜያት አንድ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ሥልጠናዎችን የወሰደ እና ወደ ሥራ የገባ ነው።
ብዙዎቹ የመብራት ኃይል እና የስልክ ካምፓኒዎች፣ አረጋውያን መጦሪያዎች፣ ሆስፒታሎች፣ የኮምፒውተር ሥራዎች ወዘተ በአጭር ጊዜ ሥልጠና የአንድ ሙያ ባለቤት የሆኑ ሠራተኞች የተቆጣጠሩት ነው። አጫጭር ሥልጠናዎች ለአንድ ለሚፈለግ ሥራ ተገቢውን ሰው ለማግኘት ይረዳሉ። ለምሳሌ በየሆስፒታሉ መሠረታዊውን ትንንሽ ሥራ የሚሠሩት ሰዎች ስለ ሕክምና ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው ሰዎች አይደሉም። የሕክምና ትምህርት ቤት ደጃፍም አልደረሱም። ነገር ግን ዶክተሮቹና ነርሶቹ የማይሸፍኗቸውን ብዙ ተግባራት ያከናውናሉ። ብዙ ኢትዮጵያንም እነዚህን የአጭር ጊዜ ሥልጠናዎች በመውሰድ በየሱቁና ነዳጅ ማደያው ከመሥራት በተሻለ ቦታ እና በተሻለ ገቢ ለመኖር ችለዋል።
አረጋውያንን በመንከባከቡ ሙያ ላይ የተሠማሩት አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያን ሴቶቹ ናቸው። በሰዓት ከ12 ዶላር ጀምሮ እስከ 20ዎቹ ድረስ እንደሚያገኙ ሰምቻለኹ። እነዚሁ እህቶች በሱፐር ማርኬቶች እና ነዳጅ ማደያዎች ቢሠሩ ከ5 እና 6 ዶላር ጀምሮ ቢበዛ እስከ 7 እና 8 ዶላር ብቻ ሊያገኙ በቻሉ ነበር። ነገር ግን የሁለት እና የሦስት ወር ሥልጠናዎች በመውሰድ “ጸዳ ያለ  ሥራ” (የኛ ሰዎች ፈገግ ብለው እንደሚሉት) ለመሥራት አስችሏቸዋል።
አገራችን ተረት “ሁሉ ከሆነ ቃልቻ፣ ማን ይሸከማል ስልቻ” እንደሚለው ሁሉም ለዓመታት በመማር እና ባለ ነጭ ኮሌታውን  (white collar) ሥራ ለመሥራት የሚጠብቅ ከሆነ የተማሩ ሥራ ፈቶች፣ ዲግሪ “የጫኑ” - ኮሌጅ
“የበጠሱ” ጎዳና ተዳዳሪዎች ከመብዛታቸው በቀር ውጤት አይኖረውም። በመካከለኛ ደረጃ ያለውን ሥራ የሚሠሩ ባለ ጠይም ኮሌታ (blue collar) ሠራተኞች በብዛት በብዛት ያስፈልጉናል። ያንን ባደረግን መጠን መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ይበዛሉ፣ ኢኮኖሚ ይረጋጋል፣ ጥሩ ቤተሰብ ይመሠረታል፣ ስደት ይቀንሳል፣ የአገር አከርካሪ ይጠነክራል። ብዙ ትንንሽ ባለሙያዎች፣ አንዱ ትልቁ የማይሸፍነውን በመሸፈን አገርን አገር ያደርጋሉ። ቅዱስ መጽሐፍ ከጉንዳን ተማሩ እንዳለው ብዙ ጉንዳኖች አንድ ትልቅ ነገር እንደሚሸከሙት ማለት ነው።
ከትምህርቱ ጎን አብሮ ሊታይ የሚችለው የአነስተኛ ተቋማት ጉዳይ ነው። አንድ ትልቅ ድርጅት ወይስ ብዙ ትንንሽ ድርጅቶች የሚለው እሳቤ። በዚህ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዋዜማ ከሚሰሙት ድምጾች መካከል ዋነኛው የምረጡኝ መቀስቀሻው “አነስተኛ ድርጅቶች”፣ ማን ጠቀማቸው/ ሊጠቅማቸው ይችላል/አይችልም የሚለው ነው።
ይህንን በእኛ አገር አንድምታ ብናየው አንድ ግዙፍ የቢራ ፋብሪካ የሚያስፈልገውን ያህል በየመንደሩ መደብ ሰርተው የሚሸቅጡ ቸርቻሪዎች በአገር አጠቃላይ ሒደት ላይ ቦታ አላቸው እንደማለት ይመስለኛል። አንዲት ተርታ ነጋዴ ከመደቧ ስትፈናቀል “ሥራ አጥ” የሆነችው እርሷ ብትሆንም፣ ችግር ላይ የሚወድቀው ግን መላው ቤተሰቧ ነው። እናስፋፋውም ብንል ትልቁን ፋብሪካ እንደመገንባት ያለ ትኩረት፣ የታክስ ማቃለያ፣ ርዳታ እና ድጋፍ ለዚያች ለባለ መደቧ ኢትዮጵያዊት ነጋዴም ያስፈልጋታል። ከውጪ ለሚመጣ እርሻ አስፋፋለኹ ለሚል ባለ ትራክተር የውጪ አገር ሰው እንደሚደረገው ዓይነት ትኩረት እና ድጋፍ እርሷም ያስፈልጋታል። ምናልባትም ከትልቁ እነዚህ ትንንሾቹ ለአገር የተሻለ ይጠቅሙ ይሆናል ብዬ አስባለኹ። በደፈናው “አነስተኛ እና ጥቃቅን” ሲባሉ “እዚህ ግቡ የማይባሉ እና ኑሮ ፊቷን ያዞረችባቸው” ተብሎ ካልተተረጎመና ዕጣ ፈንታቸው ለቀበሌ ሹማምንት ብቻ ካልተተወ በስተቀር።         
ስለዚህ ግዙፍ ግዙፉ ላይ ብቻ ከማተኮር አነስተኞቹ ላይ፣ ትንንሾቹ ዕውቀቶች፣ ንግዶች፣ ተቋማት ላይም ማተኮር፣ እነርሱም ላይ ሥራ መሥራት፣ እነርሱን ማበረታታት፤ አነስተኛው የኅብረተሰብ ክፍል አለመዘንጋት፣ ትንንሾቹን እሴቶች ላለማጣት መበርታት ያስፈልገናል። ትልልቆቹ ከሥር ከሥር በሚመግቧቸው በትንንሾቹ ላይ ይመሠረታሉ። ዓባይን ዓባይ ያደረጉት ተፋሰሶቹ፣ መጋቢዎቹ ናቸው እንጂ በራሱ አንዲት ትንሽ ጅረት ነው። ስለዚህ ከትንንሾቹ እንጀምር።

  

    
                © ይህ ጽሑፍ ተቀንጭቦ በሮዝ አሳታሚ ኃ. የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው አዲስ ጉዳይ መጽሔት” ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ላይ ማተም አይገባም::
     


  

9 comments:

Anonymous said...

SELAM DN EPHREM! MELAM YE HONE ENA GENBI YEHONE IDEA NEW!EGZIABEHARE YEBARKIH!ENDEZI INET POSTIVE YEHONE HASAB YE MIMETAW ,HAGERNE KEMEWEDED ENA LAGER KEMASEB NEW!
MARY LAND

afi said...

Thank you dear!
You covered it well, really I do agreed on the issue you made point. Here in mother land the hospitality industry is booming yet Ethiopia is not free from complaint on subject, many more the county has become a defined destinations to the most complex conference venue. On top peoples are wish to mushroom the career. In fact a figure count schools are lined to train this lovely industry serving people! My objection is the empowered shares are not in shape to nourish the industry as much as important, example this year just 200 (even it is less) students are invited to the industry. Additionally 2006 was the first ever year to the hospitality professions to graduate however many of them not in charge for the industry just in absence of attentions from government and others concerned body, no development, no recognitions, no no no no no ……Masters degree program in the HOTEL/HOSPITALITY INDUSTRY in the country. Ethiopia, mother land you need more HOSPITABLE people. Amsalu H.

Anonymous said...

በሠራ ሳይሆን በተገዛ፣ ባወቀ ሳይሆን ባሳበቀ፣ በለፋ ሳይሆን ባጎበደደ መጠቀምና ማደግ የአገር ባሕል ይሆናል።

Anonymous said...

ትንንሽ መቃድስ ወይስ ታላላቅ ካቴድራሎች

ዲ/ን ኤፍሬም ፤ ለተለመደው መልካም ዕይታህ ምስጋና ይገባሃል። ብዙ ጊዜ የሚያሳስበኝን ጉዳይ በአንተ ጽሑፍ መነሻነት ለማካፈል ፈለግሁ፤ በኢትዮጵያ ቤተከርስቲያን ሦስት ዓይነት የቤተከርስቲያን ሥሪት እንዳለ ማንበቤን አስታውሳለኹ - ገዳም፣ ደብርና የገጠር ቤተከርስቲያን። አስተዳደራዊውን ጉዳይ እና የካህናቱን ደጋፊ ማጣት ሳንቆጥር በገጠር ያለችው ቤተከርስቲያን በጭቃም ትሠራ በጨፈቃ ያበረከተችው (በማበርከት ላይ ያለችው አገልግሎት) ከደመቀው የከተማው አገልግሎት የተሻለ ሳይሆን አይቀርም። ካህኑ ከምዕመናኑ ጋር በቅርበት የሚኖር በመሆኑ የልጆቹን መንፈሳዊና ሥጋዊ ህይወት ችግሮች በሚገባ ይረዳል። ቢሳሳቱ ቀርቦ ለመምከር ውይም ተግሳጽ የሚያስፈልጋቸው ለመገሰጽ አይከብደውም። ኑሮ ራሱ አቆራኝቷቸዋልና ካህኑና ምእመናን ይከባበራሉ እንጂ አይፈራሩም።
ከዚያም በላይ ካህኑ የሁሉም አባት በመሆኑ በግልና ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ የሚያጋጥሙ ችገሮችን ከምእመናኑ ጋር ለመካፈልና ሕገ እግዚአብሔርንም ለማስጠበቅ ሰፊ እድል ይኖረዋል። እንደከተሜዎቹ መርሐ ግብር ዘርግቶ ባያስተምርም በዕለት ተዕለት ኑሮው ያስተምራል። ከዚህም የተነሳ ነው ዛሬም ከከተሜው ይልቅ በገጠሬው ለመንፈሳዊነትና ለነገረ እግዚአብሔር ተገቢው ክብር እየተሰጠ ያለው። በአንጻሩ ደግሞ በከተሞች ያለው መንፈሳዊነት በአብዛኛው ታላላቅ አብያተክርስቲያናትን (ካቴድራሎችን - ቃሉም አሠራሩም ከካቶሊክ የተወሰደ ይመስለኛል) በማነጽና ‘ጸዳ’ ያለ ልብስ በመልበስ በብዛት በመሰባሰብ የሚፈጸም ነው። ጸዳ ያለ መልበሱም ሆነ ግርማ ሞገስ ያላቸውን አቢያተ ክርስቲያን ማሳነጽ የሚያስነቅፍ ባይሆንም (በእርግጥም ኢትዮጵያዊያን ታላላቅ አብያተ ክርስቲያን በማሳነጽ ታሪክ በዓለም ከሚታወቁት ሁሉ ቀደምት እንደነበርን ዛሬ በአርኪዎሎጂ ቁፈራ ጭምር የተረጋገጠ ነው) መሠረታዊውን የቤተክርስቲያን ዓላማ- ይኹውም የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል በመስበክ ምእመናንን ማሳመንና በንሰሓ ህይወት ተመላልስው ለመንግሥተ ሰማያት ክብር እንዲበቁ ማድረግ ላይ ያለውን ተጽእኖ ማገናዘብ የሚያስፈልግ ይመስለኛል።

በየከተሞቹ ያለውን አገልገሎት ስንመለከት ምእመናኑና ካህናቱ በቅርበት የማይገናኙበት ፥ ብዙዎች ካህናትም የነፍስ /የንሰሐ/ ልጆቻቸውን ህይወት ለመከታተል የሚቸገሩበት መሆኑ አሳሳቢ ነው። የምእመናኑ ውሎና ግንኙነት ካካህናት በራቀ ቁጥርና ከአገልግሎቱ ስፋት የተነሳ ካህኑ ቤተክርስቲያን የመጡትን ልጆቹን እንኳ /መጽሐፍ እንደሚል/ ‘በየስማቸው እየጠራ’ የማያናግራቸው ከሆነ እውነተኛ ኦርቶዶከሳዊያን ክርስቲያኖችን ማፍራት ያስቸግራል። የቤተክርስቲያኒቷ መሠረታዊ አስተምሮ እንደወንጌሉ ቃል የካህናትንና የምዕመናንን የቅርብ ግንኙነት ይጠይቃልና። ለዚህም አንዱ መፍትሔ በከተሞችም ጭምር ለምእመናን አቅራቢያ የሆኑ አብያተክርስቲያናትን በብዛት መትከልና ካህናትን በብዛት በማሰልጠን ከምእመናን ጋር የጠበቀና የቅርብ ግንኙነት እንዲኖራቸው ማድረግ ይመስለኛል። ያለበለዚያ በታላላቅ ካቴድራሎች ታላላቅ ‘ኮንፈረንሶችን’ በማድረግ ብቻ እውነተኛና ጽኑ ክርስቲያኖችን ማፍራት አይቻልም። በእርግጥም በ19ኛው እና በ20ኛው መቶ ክ/ዘመን በአውሮፓ የነበረው የፕሮቴስታንት እንቀስቃሴ የተስፋፋው ብዙ ‘አብያተ ክርስቲያናትን’ (ከመንግሥት በነጻ በሚሰጥ ቦታ) በማነጽ ነበር። የካቶሊኮቹንም ልምድ ስናይ ምንም እንኳ በትልልቅ ከተሞች ታላላቅ ካቴድራሎችና ገዳማት ቢኖራቸውም አብዛኛውን አገልግሎት የሚፈጽሙት በየአካባቢው በሚገኙት አነስተኛ አብያተክርስቲያናት (እንዲያውም በተለያዩ ማኅበራዊ ተቋማት በኩል) መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም አንተም እንዳነሳሀው ለቤተክርስቲያናችንም ዘላቂ ዕድገት የሚጠቅመውም የሚመስለኝ ብዙ ምእመናንን በቅርብ የሚያገለግሉ አብያተ ክርስቲያንን ማፍራት እንጂ አሁን አሁን እየተለመደ እንዳለው ትልልቅ ካቴድራሎችንና (በዘመናችን እንደፋሽን የተያዘውን የልማት ተቋማትን /ከማን አንሼ በሚል ስሜት የማስፋፋት ሥራ) ብቻ መሆን የለበትም፤

ቸር ያሰማን!

ኤፍሬም እሸቴ said...

Very Good point.

Getachew Bekele said...

Selam Dn. Ephrem,
The issue you mentioned is so interesting.But I think from development point of view it is an issue of micro and small enterprises activities.Ethiopia trade law states that Micro enterprises are all enterprises with working capital between 20,000 to 500,000 birr. But small enterprises are those enterpirses with 20,000 and less working capital.There is capital difference in different countries based on trade law.
In previous years Economists were undermining micro and small enterprises just by calling INFORMAL SECTORS. While these days countries like Brazil,Argentina even in Britain it is handled properly and creates a massive job opportunity to the mass.
When we come to our country the implementation is in different way. The mass media speaks a lot about micro and small bussineses.But the implementation has two basic problems:-
1. It is politisized and run by politicians and kebele cadres. There fore there is much stress and fear with in the actors of the business.Even the opretors(kebele and Kifle ketema) are fully baised and loyal for their party-EPRDF instead of the business implementation. That is why even if million birr is invested to the sector in the form of loan,etc the return is really funny. Here there are very few enterprises which could transfer them selves to good business. But when we compare the cost to the return (the return must be to decrease poverty by transfering the small enterprise to micro or macro enterprise)

2. The second failority is that the implementation it self missed the target of the stakeholders. According to the trade law. The supporting process need to be provideded for all micro and small enterprises which are between working capital 20,000 and 500,000 for micro enterprises and below 20,000 birr for small enterpises. But in Ethiopia kebele and Kifle ketema opraters which are under the cities trade and industry office have fully ignored the capital base rather they are organizing and providing loan for young people who are not interested for trade. The major target is not to transfer the micro and small enterprises to big enterprise but to solve temporary problem of young people not to complain on the government.
When we see the amount of money provided for young people in the form of loan and the amount of money payed back to the government is funny.Almost over half of the loan is not returned.No one is responsible for that.
But if these all money was provided for the business comunity as loan based on their capital randomly, they will able to hire much labour.So employpment will increase by defoult. Becouse the well experianced and interested business community (even GULIT NIGD) will expand their business authomatically and cound hire more labour for their expanded business.Countries like England,France have the same experiance.That is the perfect implementation of BIZU TININISHOCH rather than ANDI TILIQ.
Any way perfect policy is very vital to make BIZU TININISHOCH.
By the way I have worked in the above sectors activity under Addis Ababa trade and industry office. So I shared the ''poor'' problem. The problem who is dare to hear ''poor's'' day and night shout?
Getachew
Oslo

Anonymous said...

Selam Dn. Ephrem,
yemetsefew betame yemechgnale menfesawi hiwote dess yelegnale betame bizu bizu teyaqewoche alugne sele menfesawi hiwot ezihe laye lawetaw yemalechle teyaqewocheme aluge adrashahene endet magegnet echelalehu bezihe agatami balebethene lejochehene selame belelegne
hewane

Anonymous said...

This is good direction indication for Ethiopian leaders and youths including me.Thanks much.

Anonymous said...

Dear Dn. Ehrem, Thank you so much for the very critical issue you let us think about.

Keep it up!!!