Friday, August 31, 2012

ስለ “ግለሰብ እና ሕዝብ፤ ታሪክ እና ያለፈ ጉዳይ”ከዚህ በታች ያለው ጽሑፍ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሰጥተውት በነበረ ቃለ ምልልስ ላይ ተመርኩዞ  Sunday, March 20, 2011 (Part 1) Saturday, March 26, 2011 (Part 2) ላይ በዚሁ የጡመራ መድረክ ላይ የወጣ ነበር። ያላነበቡ ወዳጆቼ እንዲያዩት በሚል በድጋሚ በአንድ ላይ ተዘጋጅቷል። (READ IN PDF)
(ኤፍሬም እሸቴ/adebabay.com Sunday, March 20, 2011 Saturday, March 26, 2011):- ሰሞኑን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሰፊ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ተመልከቼ ነበር። በተለይም በሊቢያ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ጉዳይ እንዲሁም በጅማ እና አካባቢው ያለውን የሃይማኖት ግጭት በተመለከተ ምን እንዳሉ በስፋት ለመስማት ፈልጌ ነበር። በዩ-ቲዩብ ተቆራረጦ ከተቀመጠው የጠ/ሚኒስትሩ ቃለ ምልልስ ጥያቄና መልስ መካከል ባሰብኩት መልኩ ባይሆንም የ“ቁምነገር” መጽሔት ጋዜጠኛ ያነሣቸው ጥያቄዎች እና አቶ መለስ የሰጧቸው መልሶች ይህንን ጽሑፍ እንዳዘጋጅ ምክንያት ሆኑኝ።

Wednesday, August 29, 2012

ከ“ዜግነታዊ ጋዜጠኝነት” አንዱ “ጡመራ”


(ኤፍሬም እሸቴ/ www.adebabay.com/ PDF)ባለፈው ስለ ዕውቀት ምንነት እና ስለመረጃ” በተለያዩ ዘመኖች የዕውቀት እና የመረጃ ማዕከል እና ምንጭ ተደርገው የሚቆጠሩ ግለሰቦች እና ተቋማት እንዲሁም ስለ መረጃና ዕውቀት ተቀባዩም ክፍል መጠነኛ ሐሳቦች ለማካፈል መሞከሬን፣ እያንዳንዳችን የዕውቀት እና የመረጃ ምንጮች መሆናችንን፣ ዜጎች ይህንን ችሎታቸውን ከተረዱ በእጃቸው ከሚይዙት ስልክ ጀምሮ ታሪክ ሊሠሩበት የሚችሉት ብዙ መሣሪያ እንዳላቸው እንደሚረዱ፣ ዘመኑ የመረጃ መሆኑን መጠቆሜን ለማሳየት መሞከሬን፣ ጋዜጠኝነትን ባልተማሩ ነገር ግን መረጃን በሚያሰራጩ ሰዎች ላይ የተመሠረተን ጋዜጠኝነት ብዙዎች citizen journalism”/ “ዜግነታዊ ጋዜጠኝነት” እንደሚሉት በማስታወስ ልጀምር።

Tuesday, August 28, 2012

አልሰማ ብለሃል


ሩቅ ሁኘ ብጠራህ አልሰማ ብለሃል
መልክተኛም ብልክ ከበር መልሰሃል
ታምራትም ባደርግ አልሰማ ብለሃል
አሻፈረኝ ስላልህ ይኸው መጣሁልህ
የፈርኦንን ፅዋ ሰፍሬ ልሰጠህ::
(በፍቅር ይሄይስ-fikir.yiheyis@gmail.com) 

Monday, August 27, 2012

እኔ ምናገባኝ

"እኔ ምናገባኝ - የምትሉት ሃረግ፤
እሱ ነው ያረዳት - ሃገሬን እንደ በግ፤
የምትሰኝ ግጥም - ልፅፍ አሰብኩና፤
ምናገባኝ ብዬ - ቁጭ አልኩ እንደገና!"
(ግጥም - ኑረዲን ኢሳ)

Saturday, August 25, 2012

አገር ፀጉሩን ሲላጭ …


(ኤፍሬም እሸቴ/adebabay.com/ PDF)ይህንን ታሪክ ያካፈሉኝ ዕድሜ የጠገቡ ዘመዴ ናቸው። እርሳቸውም አርፈው በክብር ተቀብረዋል። ነፍሳቸውን በገነት ይኑርልኝ። ጨዋታው የዛሬ 50 ዓመት የሆነ ሲሆን ነገርን ነገር አንሥቶት፣ ዘመንን ዘመን ጠርቶት፣ ገጠመኝን ገጠመኝ አስተካክሎት ላካፍላችሁ ወደድኹ።
እቴጌ መነን የቀዳማዊ አጼ ኃ/ሥላሴ ባለቤት ናቸው። እናታቸው ከወሎው ንጉሥ ሚካኤል የሚወለዱ እጅግ መልከመልካም ሴት። እቴጌይቱ ለወጣቱ ተፈሪ መኮንን ጋር ከመጋባታቸው በፊት ከሌሎች ትዳሮች ልጆችን አፍርተዋል። በኋላ ግን በልጅ ኢያሱ አማካይነት ከራስ ተፈሪ መኮንን ጋር ተጋብተው ረዥም የትዳር ሕይወት አሳልፈዋል። ልጆችም አፍርተዋል።

ያኛው ሕይወት

ያልተበለሻሸ ያልተቀላቀለ፣


ከተራሮች ዕድሜ ከዛፎች የላቀ፣

ከወንዞቹ ቀድሞ ከቋጥኙ በፊት

ከሜዳ አራዊት ከቤቱ እንስሳት

እዚያም አለ ሕይወት።

ቦተሊካ?

ከመ'ኤሌትሪክ በሩቅ እንሽሸው
በአንደበታችን አንነጋገረው
አታንሳው አታንሺው
ተዪው እንተወው
እንዳያዳምጠን ባለ ብዙ ጆሮው::


(23/3/1993 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ)

አንድ ነን …

አንድ ነን …

በቋንቋና በዘር፣
በተመሳስሏችን ባደግንበት አገር።

አንድ ነን …
በመልክ በሃይማኖት፣
በፉንጋ ውብነት።

Wednesday, August 22, 2012

እየኖርን መስሎን


(ጽዮን መኮንን፤ ቨርጂኒያ - አሜሪካ) 
እየኖርን መስሎን
መስሎን እየኖርን እየተነፈስን
ህይወትን ባግባቡ በልኩ እያጣጣምን

ግን ከበስተኋላ ስናየው ጅራቱን
የኑሮ ግሳንግስ ደስታ ፈተናውን

የእስከዛሬው ለካ ነበር እያስመሰልን

የኖርን መስሎናል እኛ መች አወቅን!!!!!!


Blog Archive