Tuesday, August 21, 2012

የአገር መሪ ሲሞት


(ኤፍሬም እሸቴ/www.adebabay.com/ READ IN PDF)በሕይወቴ ኢትዮጵያ መሪ ሲሞትባት አላየኹም። ቀዳማዊ አጼ ኃ/ሥላሴ ሲወርዱ የሕልም ያህል ትዝ ይለኛል። ሞታቸውም እንደ ሕልም አለፈ። ከዚያ በኋላ የወታደራዊው መንግሥት ዘመን ብዙ ባለሥልጣናት ሲሞቱ መሪው ግን ምንም ሳይነኩ ቆዩ። ከዚያም የእርስበርስ ጦርነቱ መንግሥታቸውን ጠራርጎ ሲገነድሰው እሳቸው ወደ ዚምባብዌ ገቡ። አልሞቱም ዛሬም ድረስ። ከዚያ በኋላ ኢትዮጵያን የመሩት አቶ መለስ ዜናዊ፣ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እና ፕሬዚደንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ናቸው። ከእነርሱ መካከል በሞት በመለየት አቶ መለስ ቀደሙ ማለት ነው። ነፍሳቸውን ይማር።

ሞታቸውን የሰማኹት ልተኛ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩኝ ነበር። ኢቲቪ ኦንላይን ብከፍተው እምቢ አለ። ትዊተር ውስጥ ስገባ መሞታቸውን ብዙዎች ከአዲስ አበባ እየዘገቡ ነው። ከዚያ ኢቲቪውም ሠራ። ከዚያ ቢቢሲ ረዥም ዝግጅቱን ማቅረብ ቀጠለ። በእርግጥም አቶ መለስ ሞተዋል።

ስለ ኢትዮጵያውያን ስሜት በጥቂቱ የምረዳው ከማኅበራዊ ድረ ገጾች ነውና ሁሉንም ጓዳ ጎድጓዳ መፈተሽ ያዝኩ። ብዙው ሰው “ዕረፍተ ነፍስ ይስጥዎት” የምትለዋን የእንግሊዝኛ አሕጽሮት “R.I.P/ Rest in Peace” ደርድሮታል። በተለምዶ ስለ እርሳቸው ጠንካራ ትችቶች የሚያቀርቡ ሰዎች ሳይቀሩ “ዕረፍተ ነፍስ” እንዲሰጣቸው በመመኘቱ በኩል የተለየ ስሜት አላሳዩም። ባህሉም ከዚህ ውጪ አይፈቅድም። “ሙት አይወቀስ” እንዲል።
ከዚህ አልፎ ግን በቅርብ ዘመናት የአገር መሪ ሲሞት በቅጡ አስተናግዳ የማታውቀው ኢትዮጵያ አሁን እንዴት ባለ ስሜት እንደምትቀበለው ማወቁ በራሱ አንድ ታሪክ ነው። አገር የሚፈርስ ስሜት ግን መሰማቱ አይቀርም። መሪ ማለት አባትም፣ የሁሉ ጠባቂ ነው የሚለው ገሚስ ታሪካዊ ገሚስ ሃይማኖት መሰል ሚቶሎጂያዊ ሐሳብ ሥር የሰደደ ነው። የአገሪቱ እስትንፋስ በአንድ ሰው መዳፍ ውስጥ “እንደ ኒኩሊየር ቁልፍ” እንደሌለች እየተረዳን እንኳን ነገር ግን “ሞቱ” ሲባል ክው፣ ድንግጥ፣ ርብሽ እንላለን።
     አጼ ምኒሊክ ከሞቱም በኋላ ስንት ዘመን ነበር ሞታቸው የተደበቀው? ስድስት ዓመት? ንግሥት ዘውዲቱ ከሞቱ በኋላ ከሕዝቡ ሙሉ ፍቅር እና አክብሮት በክብር ተቀብረዋል። ልጅ ኢያሱ ያንን ዕድል አላገኙም። ተፈሪ መኮንን አስረዋቸው በዚያው እንዳረፉ ይታወቃል። ራሳቸው ተፈሪ መኮንን (አጼ ኃ/ሥላሴ) አረጋዊነታቸው እና ሽበታቸው ሳይከበር ከተራ ሰው ሞትም ያነሰ ሞት ሞቱ። አስከሬናቸው በድብቅ ተቀመጠ። መንግሥቱ ኃ/ማርያም አሉ።
እንግዲህ ኢትዮጵያ መንግሥታዊ የቀብር ሥርዓት ያደረገችለት የቅርብ ዘመን መሪ የላትም ማለት ነው። መለስ በዚህ በኩል ዕድለኛ ናቸው። በጦርነት ሥልጣን ቢይዙም በሰላም ከመንበራቸው ያውም በማይቀረው ጥሪ በሞት መውረዳቸው ሌሎቹ መሪዎች “ያዩትን” እንዳያዩ ያደርጋቸዋል። መንግሥታቸው ሳይነቃነቅ፣ ጦራቸው ሳይፈታ፣ ዙፋናቸው እንደተከበረ፣ ከደጃፍ ቆሞ የሚያንኳኳ ተቀናቃኝ ሳይገጥማቸው ወደላዩ ቤት ሔደዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕረፍት ከቅዱስነታቸው ጋር “ኋላና ፊት” መሆኑም በራሱ “የተለየ” ያደርገዋል። ከፖለቲከኛው እስከ ሃይማኖት ሰዉ ድረስ ሁሉም የየራሱን ትርጉም ይሰጠዋል። ይህንን ጽሑፍ የምጽፈው ዕረፍታቸው ከተሰማ ከጥቂት ጊዜ በኋላ አስተያየቶቹን በሙሉ ለመገምገም ጊዜ ባላገኝም ከሁለት ወር ላላነሰ ጊዜ “አርፈዋል” ሲል ከነበረው ተቀናቃኛቸው ጀምሮ በተለይም በዋልድባ እና በሙስሊሞች ጉዳይ እስከማይቀበላቸው ድረስ አንድምታው ሰፊ ሐተታ የሚፈልግ ይሆናል። ለሐተታው ደግሞ እንደርስበታለን።
ለጊዜው እንደ ባህላችን ለቤተሰባቸው፣ ወዳጅ ዘመዳቸው በሙሉ መጽናናትን ይስጥልን ማለት ይገባል።

30 comments:

mesay said...

“ዕረፍተ ነፍስ ይስጥዎት”
“R.I.P/ Rest in Peace”
ለቤተሰባቸው፣ ወዳጅ ዘመዳቸው በሙሉ መጽናናትን ይስጥልን !!!!!

mesay said...

ለቤተሰባቸው፣ ወዳጅ ዘመዳቸው በሙሉ መጽናናትን ይስጥልን !!!!!

Neway Abera said...

ለቤተሰባቸው፣ ወዳጅ ዘመዳቸው በሙሉ መጽናናትን ይስጥልን

Anonymous said...

"በሕይወቴ ኢትዮጵያ መሪ ሲሞትባት አላየኹም።" ታዲያ እንኳን ደስ ያለሀ።

Lala said...

If tears could build a stairway, and memories a lane, I’d walk right up to Heaven and bring you home again....

Anonymous said...

“ዕረፍተ ነፍስ ይስጥዎት”

Anonymous said...

You are good my friend. A cool Ethiopian eulogy.

abraham said...

ለቤተሰባቸው፣ ወዳጅ ዘመዳቸው በሙሉ መጽናናትን ይስጥልን
አብርሃም

Anonymous said...

“ዕረፍተ ነፍስ ይስጥዎት”

Negusies brother said...

ሁሉም ተራ አልው ዋጋውን ያግኛል በ1997 ዓ.ም ምርጫ ማግስት ሶሰት ልጆችህን ጥለሀ በግፍ ለተገደልክወ ያለስምሀ የባንክ ዘራፊ የሚል ስም ለተሰጣህ ወንደም ንጉሰ እና ለተስጣቹ ወገኖቺ ጸሎተ ፍትሕት እንኳን ለተነፈጋቸው ኢትዮጽያውያን ፍርዱን አምላክ እጅ ታግኙታላችህ
አምላክ ሆይ የሁሉንም ነፍስ ማርልን።

Anonymous said...

ስለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜና እረፍት ስሰማ በጣም ደነገጥሁ ስለ እርሳቸው እንዲህ ያለ ስሜት ይሰማኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ እግዚአብሐ,ሔር ነፍሳቸውን ይማር ለቤተሰቦቻቸው እና ለመዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይስጣቸው፡፡ ከስህተቶቻቸው እየተማሩ ህይወታቸውን ሙሉ ለህዝብ የኖሩ ታላቅ ሰው ነበሩ፡፡

ephrem amente said...

መልካም የእረፍት ጊዜ ባንልም (አር አይ ፒ)rest in peace

Anonymous said...

እንኳን አብሮ ደስ አለህ።

Anonymous said...

I fell sorry for his family,however,I wish he died making peace with opposition figures.In my view,he has done lots of bad things but let us GORGIVE him but we shouldn't FORGET it.RIP.

Anonymous said...

My friend, you just said "ፍርዱን አምላክ እጅ ታግኙታላችህ" then you said "አምላክ ሆይ የሁሉንም ነፍስ ማርልን", I am confused. Which one is yours and which one is your friend's idea? Just say RIP. I wont hurt you. Because there is nothing you can do at this time. We all will die if we do good or bad.

Anonymous said...

Girum new.

Anonymous said...

የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ የተደበላለቀ ሰሜት መፈጠሩ እውነት ነው። መለስ ዓለም አቀፍ አድናቆትን ያተረፉ መሪ ስለመሆናቸውም ክርክር ያለ አይመስለኝም። መለስ ከአንዲት ኋላ ቀር አገር የገጠር ከተማ ተገኘው፣ ለ17 ዓመታት ላመኑበት ዓላማ ታግለው ፣ በጣም አነጋጋሪ በሆነ መንገድ ሀገራቸውን ለ21 ዓመታት መርተው በድንገት በማይቀረው ሞት ተወስደዋል። በፖለቲካ አመለካከታቸው በአብዛኛው ባልሰማማም በሞታቸው አዝኛለሁ።እንደ አንድ ተራ ሰው ስናስባቸው ሊታዘነላቸው ይገባል። በእኔ አመላካከት መለስ በጭቅላነት ዕድሜአቸው የተቀበሉት ርእዮተ ዓለም ከፍተኛ ተጽእኖ ያሳደረባቸው ቢሆንም ለሀገራቸው የሚችሉትን ለማድረግ የሞከሩ መሪ ናቸው ማለት እችላለሁ። ምንም እንኳ ብዙዎቻችን የምናውቃቸው በፖለቲካ አቋማቸው ቢሆንም እንደማናችንም ለቤተሰቦቻቸው ልጅ፣ ወንድም፣ አባት እና ባል ናቸው። ስለሆነም ቤተሰቦቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲያጽናናቸው እመኛለሁ። የምህረቱ መጠን ወሰን የሌለው አምላክ በቸርነቱ እንዲያስባቸውም እመኛለሁ።

Anonymous said...

ለነፍሰ ገብሩ------------------ ነፍስ ይማር

selam said...

ጠ/ሚንስትራችን የነበሩትን ክቡር መለስ ዜናዊን በጣም አደንቃቸዋለሁ ፤ ያላቸው ዕውቀት እና ይህን ዕውቀታቸውን ለቆሙለት አላማ እንዴት እና መቼ መጠቀም እንደሚችሉ ያውቁበታል፡፡ በዚህም አካሄዳቸው አብረዋቸው የታገሉትን ሳይቀር እንዴት እና እስከ መቼ መጠቀም እንዳለባቸው ያውቃሉ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ስነልቦና በደንብ ተገንዝበውታል፡፡ እኔን የሚቆጨኝ ይህን ያላቸውን ዕውቀት ለፍቅር፣ለሰላም፣ለአንድነት፣ በአጠቃላይ ለሀገር ጥቅም ቢያውሉት ኖሮ በኢትዮጵያ መንግስታት ታሪክ ቅድሚያ ቦታውን ለመያዝ አጋጣሚውን አግኝተው ያልተጠቀሙበት ሰው ናቸው፡፡ ግን እሳቸው ያገኙትን በጣም ጥሩ አጋጣሚ ለሀገራቸው ትንሽ ጥሩ ነገር ሰርተው ግን በጣም አደገኛ የሆነ ብሄርተኝነት፣ጎጠኝነት፣ጥላቻ፣ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የነበራት የሀገር ፍቅር እና የአንድነት መንፈስ ሊያበላሽ የሚችል በጣም አደገኛ የሆነ ነገር ሊፈነዳ የሚችል መንፈስ ቀብረውልን አለፉ፡፡ ሆኖም የንስሀ ዕድሜ ሳያገኙ በመሄዳቸው አዝናለሁ ፣ እግዚአብሄርም ቸር ነው እና በምህረቱ እንዲምራቸው እመኛለሁ፡፡

Anonymous said...

ፈጣሪ መሆን የሚገባዉን ስራ ሰራ እኛም በባህላችን ነፍስ ይማር ብለናል

Anonymous said...

Well Said. In fact, unused opportunities were surplus but didn't care to utlize them.

Anonymous said...

Efrem chewa sew neh

Anonymous said...

Prime Minister is a human being and mortal. We will follow him when our turn come to us.He will not come back to us. He did many good things and bad things also. We can't find absolute person in this world.Any ways "I wish rest for him in Heaven"

Anonymous said...

ነፍስ ይማር/RIP/

Anonymous said...

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዜና ዕረፍትን ስሰማ እጅግ በጣም አዝኛለሁ፣ እኚህ የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ታላቅ ሰው ለዚህች አገር የተቻላቸውን ሁሉ አድርገዋል፣ አፍሪካንም ወክለው በታላላቅ መድረኮች ችግሯን ለዓለም አሰምተዋል፣ ጥቅሟንም ለማስከበር ተከራክረዋል።
እኝህ ታላቅ ሰው በሀገራቸውም ምናልባትም እስከሁን በታሪክ ያላየናቸውን ብዙ ታላላቅ ጅማሮዎችንም ጀምረዋል፣ ምንም እንኳን በስካሁኑ ስራቸው ኢትዮጵያን በተሻለ መልኩ ማራመድ እና መለወጥ ቢችሉም ሀገሪቱ ካለባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች አንጻር ከሳቸው ገና ብዙ ትጠብቅ ነበር፣ ተስፋም አድርጋ ነበር። ምንም እንኳን የሀገሪቱ ተስፋ ይጨልማል የሚል እምነት ባይኖረኝም፣ ከኛ ከኢትዮጵያውያን እጅግ ብዙ እንደሚጠበቅ ግን ይሰማኛል።
ነፍሳቸውን ይማር!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፣ ኢትዮጵያን ያረጋጋ!!! አሜን

Anonymous said...

R. I. P
HE SHOULD NOT HAVE DIED BEFORE COMING BEFORE THE COURT OF LAW FOR ALL THE BLOOD SHADE HE CAUSED. HOW MANY OF OUR FRIENDS WERE IMPRISONED, TORCHED AND KILLED JUST FOR TELLING THE TRUTH, DEMANDING THEIR RIGHT. WHY WE SPEAK ONLY THE GOOD. HE BUILT HIS INTERNATIONAL LEGASSY AT THE COST OF DOMESTIC HUMAN RIGHT.
COME ON GUYS
LE MIN YIWASHAL

Anonymous said...

ነፍስ ይማር።

Anonymous said...

የ ገብረ እግዚአብሔርን ነፍስ ይማርልን.... ከበሮ በሰው እጅ ሲያምር ....የሰውን ስራ መንቀፍ ሳይሆን መልካም የምንለውን ሰርተን እናሳይ...
እግዚአብሄር ህገራችንን ይጠብቅልን

Anonymous said...

enquane ke amba genne beselam awten lemin 2 gizie aymotim??????????
lebba hager korso shachi!!!!

Abeaselom Kebede said...

Ayi wodaje Ephrem,

minalibat yiheanin erkuset yebahiriwu yehone Gangrine Egzearu endigelagilih endenea sint ken Dawitun gelibiteh endedegemikewu balebeatu yiwok.

Blog Archive