Saturday, August 25, 2012

አገር ፀጉሩን ሲላጭ …

(ኤፍሬም እሸቴ/adebabay.com/ PDF)ይህንን ታሪክ ያካፈሉኝ ዕድሜ የጠገቡ ዘመዴ ናቸው። እርሳቸውም አርፈው በክብር ተቀብረዋል። ነፍሳቸውን በገነት ይኑርልኝ። ጨዋታው የዛሬ 50 ዓመት የሆነ ሲሆን ነገርን ነገር አንሥቶት፣ ዘመንን ዘመን ጠርቶት፣ ገጠመኝን ገጠመኝ አስተካክሎት ላካፍላችሁ ወደድኹ።
እቴጌ መነን የቀዳማዊ አጼ ኃ/ሥላሴ ባለቤት ናቸው። እናታቸው ከወሎው ንጉሥ ሚካኤል የሚወለዱ እጅግ መልከመልካም ሴት። እቴጌይቱ ለወጣቱ ተፈሪ መኮንን ጋር ከመጋባታቸው በፊት ከሌሎች ትዳሮች ልጆችን አፍርተዋል። በኋላ ግን በልጅ ኢያሱ አማካይነት ከራስ ተፈሪ መኮንን ጋር ተጋብተው ረዥም የትዳር ሕይወት አሳልፈዋል። ልጆችም አፍርተዋል።

ውሎ ውሎ ከቤት፣ ኖሮ ኖሮ ከሞት አይቀርምና በየካቲት 8 ቀን 1954 ዓ.ም እቴጌ መነን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ኃዘኑም ከባድ ነበር። አገር ምድሩ አለቀሰላቸው። በትውልድ አገራቸው በወሎም እንዲሁ ሕዝቡ አዘነላቸው፣ አለቀሰላቸው። በመካከሉ ግን ሌላ ትዕዛዝ ወጣ። ከላይ ከቤተ መንግሥት የመጣ ይሁን ወይም በዚያም በመንደር ሹመኛ የተፈጠረ አላወቅኹም።
ነገሩ እንዲህ ነው። እቴጌ መነን ካረፉ በኋላ ሐዘናቸውን ለማስታወስ ሴቶች በሙሉ “ጸጉራቸውን እንዲላጩ” ትዕዛዝ ወጣች። በየገበያው እና በሕዝብ መገናኛ ቦታዎች ሁሉ ጸጉር የተላጨውና ያልተላጨው ይመረመር ጀመር። በተለይም በገበያ ቦታ ዋነኛው ፍተሻ ይካሔድ ጀመር። ትዕዛዙን ቀለል አድርገው ተመልክተው ጸጉራቸውን ሳይላጩ ገበያ የወጡ ሴቶች ብርቱ ችግር ገጠማቸው። ሹመኛው እና ትዕዛዝ አስፈጻሚው ሴቶቹን በደረቁ ላጯቸው። ያለ ምንም ውኃ።
ታሪኩን ያወጉን ዘመዳችን ጸጉራቸውን ላለመላጨት ከመፈለጋቸው የተነሣ ጭንቅላታቸውን በሻሽ ግጥም አድርገው አስረው (መቸም በቅቤ አልመውት ይሆናል) የተላጩ መስለው ያንን ጊዜ አሳለፉት። ቢያዙ ኖሮ “በደረቁ መላጨታቸው” አይቀርም ነበር።
ይህንን ትዕዛዝ በኃዘን ላይ የነበሩት አጼ ኃ/ሥላሴ አዝዘውት ነው ለማለት ይከብዳል። ስንት እበላ ባይ፣ እከብር ባይ፣ እታይ ባይ … ያደረገው ይመስለኛል። በየጊዜው እንዲህ “ሕዝቡን በደረቅ እያስላጩ” እንጀራቸውን የጋገሩ ሰዎች አይተናል። አዛኝ ቅቤ አንጓቾች። ለሞተው ሳያዝኑ ነገር ግን ልባቸው በኃዘን የተሰበረ አስመስለው በሕዝቡ ላይ መከራ የሚያውጁ። የባለሥልጣን ሞት ለእነርሱ ሰርግና ምላሽ የሚሆንላቸው። ከቤተ መንግሥት ችግርም ደስታም ሲመጣ ደኃው ሕዝብ የሚሰቃይበት ምክንያት ያሳዝነኛል። እቴጌይቱ ለሞቱ የአንድ ጠቅላይ ግዛት ሕዝብ ያለውዴታው ጸጉሩን ሲላጭ።
እናንተ ጸጉራችንን በደረቅ በማስላጨት እንጀራችሁን የምትጋግሩ ሰዎች፣ ለሕዝቡ እዘኑለት።

31 comments:

Anonymous said...

echi kine betam temechitagnalech.thanks

Anonymous said...

Wonderful analogy for what is going on in the aftermath of The PM's death.

Anonymous said...

That is what is happening in Ethiopia now! Yigermal eko yihe diha hizb zarem Tikur libs asefa, alkis, dinkuan tekleh tekemet eyetebale beyeseferu, beyesira botaw, eytegedede new!

Zeleke Desta said...

Ahune degmo begna zemen deret yemeiyasemestu denkuane yemiyaseTlu nachew .21 amet hiziben seyasleqesu norew ahune embaw yaleqen zihib aleqes yemilu lehode adariwoch.

Ephrem ewentun bemetsafe enamesegnehalen

HaileMariam said...

This is just a precise analysis of what is happening right now. Dictatorship does not take a break or lets an opportunity to pass by they use it in all means to entrench their oppressive rule by all means possible.

Thank you again

Anonymous said...

Ephrem ante tenagerelen egnma ben afachen enenageralen tsugachehun telachu becha seqerachew bemeserabet bekebele bemuya be tsota eyalu yasechenqunal. yeEthiopia amlak yefaredachew.

Anonymous said...

Great jobe Efrem this is waht is happpening now in Ethiopia

Anonymous said...

Professor Mesfin once said "Hageren yekade lehager helewena ayeqomem". Ethiopia ende hager yeqomelate yelem yeande gosan yebelayenet lemaskeber yemeruruatu enji yehager fiqer yaleachew aydelem. le 37 amet yetagele ena yatagen meri enkuane ende tera lewerat aseqmetuT. yehen hulu lesew sayhone leseleTan kalechew temate new.

Anonymous said...

"Meles fooled those who wanted to be fooled."
Ana Gomez

Anonymous said...

ዛሬማ በየከተማው በየዞኑ የለቅሶ ወረፋ ህዝቡን እያስያዙ በየአደባባዩ ፕሮግራም ማዘጋጀቱን ቀጥለዋል የሚገርምነው

Anonymous said...

You put exactly what is going on Ethiopian at this time. Beged Alqsu;Beged tikur lebesu;Beged leqso dresu yegermal!!! Thank you
Demissie

Anonymous said...

Who ever wants to learn from history, will not repeat similar stupid mistakes again and again. It is specially annoying when that mistake is at the expense of a country as we see in Ethiopia.

Anonymous said...

ሕዝብ ሲያዝን፣ ሲያለቅስ፣ ሲሠለፍ፣ ሲጓዝ የሚታየው ቤተሰብና ዘመድ ስለሆነ አይደለም፡፡ የአገር መሪ ስላረፉ ነው፡፡ ለአገር ጥሩ ሠርተዋል ብሎ ስላመነ ነው፡፡ የቤተሰብና የዘመድ ወዳጅ አጀንዳ ሳይሆን የአገር አጀንዳ አድርጐ በመውሰዱ ነው ሕዝብ እንደዚህ ያዘነው፡፡ በፈቃደኝነትና በሙሉ ስሜት ለአገር አጀንዳ ይህን ያህል ክብርና ትኩረት በመስጠቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምስጋናና ክብር ይገባዋል፡፡

ይህ ብቻም አይደለም፡፡ እንደዚህ ሲያዝንና ሲያለቅስ የነበረ ሕዝብ በመንግሥት በኩል ምንም ጉዳት ያልደረሰበት ሕዝብ ነው አይባልም፡፡ ተጠቃሚ ስለሆነ ነው ያለቀሰው አይባልም፡፡ የተበደለም አለ፤ እስር ቤት የነበረና ያለ አለ፡፡ መሬትና ንብረት የተወሰደበትም አለ፤ የተሰቃየ፣ የተሰደበና የተወቀሰም አለ፡፡ ሆኖም ግን የግል አጀንዳንና የአገር አጀንዳን ለያይቶ በማየት እኔ የሚለውን ትቶ እኛ ኢትዮጵያውያንና አገራችን ኢትዮጵያ ብሎ በማዘን ነው የወጣው፤ የተሰለፈው፤ ቦሌ ሄዶ ያለቀሰው፤ ቤተ መንግሥት ገብቶ በእንባ የተራጨው፡፡ የአገርን ጉዳይ ከግል ጉዳይ በላይ አድርጐ ያየ ሕዝብ ነው፡፡

ይህ ብቻም አይደለም፡፡ ቅስቀሳ ስላልተደረገለትም አይደለም፡፡ በየሚዲያው፣ በየኢንተርኔቱ፣ በየፌስቡኩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመሞታቸው ዕልል በሉ፣ ተነሱ፣ መንግሥትን ገልብጣችሁ ያዙ የሚል ቅስቀሳ ስላልደረሰውም አይደለም፡፡ ወጣቱ ያውቃል፤ ምሁሩ አውቋል ሰምቷል፤ እንደዚያ የሚሉትን አሳፋሪዎች ናችሁ፤ ከሃዲዎችና የጠላት ተላላኪዎች ናችሁ፤ ገደል ግቡ በማለት አገርን ያስቀደመ ሕዝብ ነው፡፡

በችግር ጊዜ በአንድነት የሚሰባሰብ፣ ከግል ችግር በላይ የአገር ጉዳይን የሚያስቀድም ወርቅ፣ አኩሪና አስመኪ ሕዝብ ነውና ክብርና ምስጋና ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Anonymous said...

Efrem wendimachin,

Qine teqegniteh motehal.
Lezare atesakalihim, lela mokir!!

Anonymous said...

"ታሪክ እራሱን ይደግማል"እንደሚባለዉ ድሮ በመላጨት አዉን ደግሞ በትሽርት ሁኖል የሀዘን ማስመሰያ መገለጫዉ::
እዩኝ ባይ ባዳ አልቃሽ ማህል ይገባል እንደሚባለዉ ሀዘኑን የግላቸዉ አስመስለዉታል አንዳንድ አስመሳዬች::

Anonymous said...

ክብርሽን ሊያኮስስ ሊያዋርድሽ የዳዳ
የእናት ጡት ነካሽ ዉሉደ ይሁዳ
ከጥላቻ በቀር ፍቅር ከማይበቅልበት በርሃ ሕሊናዉ
ተንኮል የሚያበቅል ግፍን የሚዘራዉ
ደክሞ ተንጠራርቶ አልሳካ ብሎት
ሊያወርድሽ ሊያዋርድሽ ቋምጦ ለቀረበት
ሊያጠፋሽ ፎክሮ ተፀፍቶ ተከፍቶ የመሰከረልሽ
ሳይወድ ሳይፈልገዉ ክብርሽን ያወጀ ያ ክፉ ባላንጣሽ
ግፉ ለከት አጥቶ የድሆችሽ አምላክ ላይምረዉ ቢቀስፈዉ
ደፋር ጀሌዎቹ ስዉር ዓይናቸዉን በጨዉ ቀብተዉ አጥበዉ
ዝቅ በይ ይሉሻል አለማፈራቸዉ
እመቢ በይ ሰንደቋ ከፍ በይ ክበሪ
አሳዳጅሽ ወድቋል ድመቂልን አብሪ

Anonymous said...

Nice View!!!!

Anonymous said...

በዚህ ዘመንም አሉ በሆነ መንገድ ጥቅም ያገኙ የመሰላቸው አድርባይ ሁሉ ይህን ምስኪን ህዝብ የተሸከመው ችግር፣ የደረሰበት ግፍ ሳያንሰው ሃዘን ካልደረስክ ካላስመሰልክ እያሉ ለምን ስቃዩን እንደሚያበዙበት አይገባኝም። ይህ ህዝብ የመከራ ቀንን ተመሳስሎ ማለፍ ስለሚችልበት አብሮዓቸው መነዳቱ አይገርምም፡ ባለጊዜዎችና ደጋፊዎች ነን የሚሉ ሰዎች ግን በዚህ ሰው ትእዛዝ ስንት ንጹሃን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዳለፍ፣ ብዙዎቹስ በእሰር፣ በስደት፣ በአድሎ፣ በአሰቃቂ የአካል ድብደባ፣ ፍትህ በማጣት ኧረ በስንቱ እንደተጎዳ ውስጡስ እንደሚቃጠል አይገባቸውም። ለሁሉም ይህ ቀን ይለፍና አስላጭውም ተላጭውም የሚተዛዘቡበት ቀን ይመጣ ይሆናል።

Anonymous said...

የበሰለ አስተያየትህን ስላካፈልከን በጣም እናመሰግንሃለን፡፡ እንደ እነ ኤፍሬም እሸቴ አስተሳሰብ ሕዝቡ ተገዶ አይደለም እንባውን ያዘራው፣ እርር ድብን ያለው መጻኢ ሕይወቱ አሳስቦት እንጂ፡፡ ደግሞስ ለጀግና ይህም ሲያንሰው ነው፡፡ የአገራችንን መሪ ጣዕሙን ፍቅሩን የምናውቀው እኛው በአገራችን ኢትዮጵያ የምንኖር እንጂ የፈረንጅ አሽከር ለሆኑቱ አይደለም፡፡

Anonymous said...

ለኒህም እኮ እየተደረገ ነው፤ ግንባር ላይ በምላጭ መበጣትና ግንባርን በእሳት ማቃጠልም ልዩ የሃዘን ምልክት ሆኗል። ምናልባት በአጭር ቀን ውስጥ ከቢሄራዊ አልፎ አገርአቀፍ ይሆናል።

ውቤ said...

ይኸን ያህክልስ አስከሬኑ መቀመጥ አለበት ወይ? እግዚአብሔረ ሰጠ፤እርሱ ወሰደ በቃ!
ኀዘን ሲበዛ እኮ ደግም አይደል ፈጣሪ ይሰማል እኮ!

Anonymous said...

I am disappointed in the story telling of your relative for he has not mentioned how much the Empress is respected and loved by the people of Ethiopia not just the people of her birth place ( Wollo ).

Although the above mentioned story can be related to the current situation back home, I however disagree with the relation it has with the passing of PM and the well respected and loved Empress.

I beg to deffer with the assumption your relative had and the story you've shared believing that the same was done when Etege-Mennen passed away.

Let has revisit history for the sake of gaining knowledge about what had happen in the past and to help us understand what's going on now.

Thanks for sharing!!!

Anonymous said...

Ephrem, well done bro!..let's speak for our people! as every rational minded man knows they can not speak their mind for they are under "Democratic Dictatorial" regime - how else I can describe them, for them Democracy = Dictatorial...the "they are always right".

God bless Ethiopia!

Anonymous said...

ለኢትዮጵያውያን ከዚህ የሚበልጥ መራራ ሀዘን የለም
ፀሎትና አስማት የልሰበረውን የሺ ዘመናት ጣዕርና ሲቃ በፀዳና ታጋይ ብረት የሰበረ፤ ከብርቱ ርሐብና ከድንግል ምድር በቀር አንዳች ባልነበረበት አገር ላይ ስፍር ቁጥር የሌለው ፈጣንና ሰፊ የእድገትና ልማት ግስጋሴ እውን ለማድረግ ያስቻለውን ሕዝባዊ ንቅናቄ የመራ ነበር መለስ፡፡ የታላቅ ሕዝቦቹ ታላቅ መሪ፤ ስለ ራሱ የግል ሕይወት ለማሰብ ሰከንድ ታህል እንኳ ጊዜ ያልነበረው መላ ሕይወቱን፣ እውቀቱንና ጉልበቱን ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ክብርና ጥቅም የሰጠ የተሰጠ የታመነ . . . በዚህች ዓለም የሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ከፊተኞችም ከኋለኞችም ታላላቅ መሪዎች ከሚባሉት ሁሉ ታላቁ መሪ ነበር፡፡
በተባ ጥበብ የላቀ እውቀት ባለቤት፣ ታላቅ አእምሮ፣ ትሁት ፣ ከፍተኛ የንግግር ችሎታ ያለው ጥኡመ ልሳን፣ መልከ ቀና፣ ሕዝቡን እንዲመራ በልዩ ፀጋና ስጦታና ችሎታ ሁሉን በሚችል አምላክ የተቀባ አገልጋይም ነበር፡፡ መለስ የኢትዮጵያ አገሩና የአህጉረ አፍሪቃ የብርሃን ጌጥ፤ ለዚህች ዓለም እጅግ አስፈላጊው ታላቅ ሰው እጅግ የተከበረው እጅግ የተወደደው ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ገበሬዎች የልብ ወዳጅ ምስጢረኛም ነበር፡፡ ኢትዮጵያ በሺ ዘመናት ታሪኳ ውስጥ እንደዚህ ዘመን የማይርድ የማይርገደገድ ጽኑእ ሕዝባዊ መሠረት ያለው ሥልጡንና ጠንካራ የመንግሥት መዋቅር ተክላና አጽንታ አታውቅም፡፡ በግልጽ እንደሚታየው ኢትዮጵያ ማንም ሊገታው ሆነ ሊያዘገየው በማይቻለው የሁለንተናዊ የብርሃን ጐዳና ውስጥ ገብታለች፡፡
በኢትዮጵየ ለሺ ዘመናት ሥር የሰደዱ ችግሮችን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን እለት እለት ሕዝቡን የሀብቱና የመብቱ ተጠቃሚ የማድረግ ሥራ ተሠርቷል፡፡ ወገንን በሚያኮራና በሚያስደንቅ ፤ ባላጋራን በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ አኳኋን ሰላም የሰፈነባት ሥልጡንና ጠንካራ ዴሞክራቲክ አገር በመገንባት ወደ ማህበራዊ ብልጽግና መገስገስ ችለናል፡፡ ይህ ግስጋሴ በላቀ ብቃት ይቀጥላል፤ የሚያቆመንም የለም፡፡ በመላው ኢትዮጵያውያን የልብ ጽላት ውስጥ በፍቅርና በክብር ህያው ሆኖ ይኖራል፡፡
መለስን ከማንም ከማን ጋር ማነጻጸር አይገባም፡፡

Anonymous said...

What you wrote is what you expect to be happened; but to know the reality (if you are not currently in Ethiopia)ask your relatives and friends. Try to accept facts give respect to your people. This great leader is in the heart of every true Ethiopian.

Anonymous said...

I like the comment you gave us!

Anonymous said...

By the way, It is not a big deal to cry (deep sorrow) to our leader Meles Zenawi. You didn't heard about the south Korean president, pls read it.

Anonymous said...

@AnonymousAugust 28, 2012 12:13 AM የጻፍከው የምርህን ነው
ነው ሌላ ኢትዮጵያ ሌላ መለስ ይመራት የነበረ አለች ጐበዝ ከአንድ ወገን ብቻ አንይ እንጅ ወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ፣የሀገር ፍቅር የሌለው ትውልድ፣ዲግሪው ለኮብልስቶን የተሰጠበት፣ዘረኝነት የሞላበት ትውልድ……… ለማንኛውም ነፍሳቸውን ይማር ለሀገራችን መልካም መሪ ይስጥልን አሜን

Anonymous said...

Nonesense!

Anonymous said...

ስለ ጠቅ/ ሚ/ር ሞት የሀዘን መግለጫ
ሞት ሁሉንም እኩል ያደርጋል ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ያስደነግጣል ቢባል ማጋነን አይሆንም
በገድለ ጊዮርጊስ ላይ እንደሚነበበው ዘንዶ ይገዛ በነበረበት ዘመን ህዝብ ልጆችን ለዘንዶ ቀለብ በመገበር ተማርሮ በነበረበት ሰዓት እንኳ ፈረሰኛው ጊዮርጊስ ገድሎት ለተረኛዋ ተበይ ለነበረችው ብሩታይት አስረክቧት በህዝብ ፊት ስታቀርብ ያ ይፈሩት የነበረ ፍጡር በመሞቱ ደንግጠዋል ለተወሰነ ጊዜም አላመኑም ነበር
አሁን እኔ በደረስሁበት ዘመንም የመለስ ሞት ይህን ያስታውሰኛል ኧረ ከዚህም በላይ ሌላ የቅርብ ታሪክ አለ
ዶክተር መራራ ጉዴና በአንድ ወቅት እንዳሉት አቶ መለስ የደርግን አስከፊ ስራዎች በቪዲዮ እያዩ እየደገሙ እየደጋገሙ አቅርበው ሲሰለቻቸው በታሪክ ወደ ኋላ ሂደው ሌላ አስከፊ ታሪክ ፈልው ደገሙ
ይህም ቅድመ አያታቸው አጼ ዮሃንስ ያደረጉት ትዝ አላቸው ይህ ሁኔታም በራሳቸው ሞትና ሀዘን ላይም እነሆ ተደገመ
ሀዲስ አለማየሁ በየእልም ዣት በሚለው ልቦለድ መጻፋቸና ሌሎች ታሪክ ጸሀፊዎችም እንደዘገቡት በአጼ ዮሀንስ ዘመነ መንግስት የሸዋው ንጉስ ምኒልክና የጎጃሙ ንጉስ ተክለሀይማኖት አጼ ዮሀንስን በመቃወም አጼው በሸዋ የዘመቱ እንደሆነ ተክለሀይማኖት ለምኒልክ ርዳታ ሊደርሱ በጎጃም የዘመቱ እንደሆነ ምኒልክ ለተክለሀማኖት ርዳታ ሊደርሱ ተስማምተው ነበር
አጼውም አድማውን ሰምተው ምንም እንኳ ደርቡሽን ለመውጋት ወደመተማ መዝመት ቢያስቡም የአገር ውስጥ ጠላቴን ሳልቀጣና ሳላስገብር አልሄድም ብለው ወደጎጃም ዘመቱ
ንጉስ ተክለሀይማኖት ንጉስ ምኒልክ በተስማሙት መሰረት ለእርዳታ ስላልደረሱላቸውና የመጣውን ሀይል መመከት እንደማይችሉ ገምተው ጅበላ አምባ በተባለ ምሽግ ገብተው መሸጉ
አጼ ዮሀንስም የጅበላን ምሽግ መስበር ስላቃታቸው በቁጭት ተነሳስተው /ቁጭት የጠ/ ሚኒስትሩ ምርጥ ቃል እንደሆነች ያስታውሷል/ ጎጃምን አጥፍተው አስዘርፈው ህዝቡንም ክፉኛ በድለው ወደ መተማይሄዳሉ
ያኔ በጥቅምት ወር ነበር ወደ ጎጃም የዘመቱት እህሉ እሸት እንዳለ የፊቱ ባልደረሰበት የኋላው ባለቀበት ደርሰው እህሉን በከብት አስጠፍተው ከብቱን የሚችሉትን በልተው ቀረዉን አስነዱት ቤቶችን አቃጠሉ ሰዎችንም ገድለው ሄዱ ይታያችሁ ይህ ሁሉ ግፍ የሚደረገው ምንም በማያቀው ምንም ባላጠፋው ባላገር ላይ ነበር
አንድ ሰኔ የነቀለውን ሰባት ሰኔ አይተክለውም እንደሚባለው እህልም ሆነ ከብት ለዘር እንዳይቀር አድርገው አጥፍተውት ስለሄዱ በህይወት የተረፉ የጎጃም ሰዎች ከጫካ ፍሬ በመልቀም እየኖሩ የሰው ህይወትና ዘር አተረፉ ይህ በጎጃም ህዝብ የማይጠፋ የምን ጊዜም የታሪክ ጠባሳ ነው
አጼ ዮሀንስ መተማ ከመሄዳቸው በፊት ምኒልክንም ለመቅጣት አስበው ነበር ነገር ግን አነድ ባህታዊ የክርስቲያኑን የጎጃምን ህዝብ አጥፍተህ ደግመህ ሸዋ ብትሄድ መንግስትህ እድሜህ ይረዝማል አንተ ግን ትኮነናለህ ወደ መተማ ብትሄድ ግን ትሞታለህ ነገር ግን ትጸድቃለህ ብሎ ይነግራቸዋልለነገራቸው እሳቸውም ከምኮነንስ ጽድቅ ይሻለኛል ብለው መተማ መዝመትን መረጡ ይባላል
እዚህ ላይ አንዳንድ ሰዎች ባህታዊ መስሎ ይህን ትንቢት የነገራቸው የምኒልክ ሰላይ / መልክተኛ ነው ብለው ይላሉ ምክንያቱም ወደ ሸዋ ዘምተው እንዳይወጉዋቸው
በመንፈሳዊ አባት መልክ ማስነገራቸው እውነት ከሆነ ምኒልክ ብልህ ግን መሰሪ መሆናቸውን ያሳያል ምክንያቱም ሁለቱም ማለትም ተክለሀይማኖትም አጼ ዮሃንስም እንዲዳከሙላቸው ከተቻለም እንዲወገዱላቸው ይፈልጉ ነበርና ለዚሁ ነው ለተክለሀይማኖትም ርዳታ ያልመጡላቸው
አጼ ዮሀንስም ወደ መተማ ሲገሰግሱ ንጉስ ተክለሀይማኖትአጼው ርቀው እንደሄዱ አይተው ከጅበላ ወርደው መልክተኛ ልከው ተራርቀው አብረው መተማ ይዘምታሉ
አጼ ዩሀንስም በጦርነቱ ሞተው ንጉስ ተክለሀይማኖትም ከጦርነቱ ከተመለሱ በኋላ የጎጃምን ህዝብ እንዲህ እንደዛሬው ለአቶ መለስ እንደተደረገው ክተት አስወጥተው የንጉሰነገስቱን ምስል አስቀምጠው የጎጃምን ህዝብ እንዲያለቅስ ያዛሉ አንድ አስለቃሽ ተፈልጋ እንደሚከተለው እየገጠመት ለቅሶውን መራች
ሲገዙ እንዳልኖሩ እነዳልበሉ ሁላ
ለተባይ ሰጥተውን ዳርገውን ለተኩላ
ወጥተው ሲቀመጡ ንጉሱ ጅበላ
በጃችን ሳይጠጣ በጃችን ሳይበላ
ደም መላሽ ሆነልን መሀመድ አብደላ
ዘሩን ይባርክለት የሚያምንበት አላ
በዚህ ጊዜ ንጉሱ ተቆጥተው አስለቃሽዋ እንድትያዝ ያደርጉና ለቅሶው በሌላ ሰው እንዲቀጥልለ ያደርጋሉ ሁለተኛዋ አስለቃሽም ተነስታ
ደህና ተሰናድቷል ተጠርጓል መንገዱ
አጼ በሄዱበት ንጉሱም ይሂዱ

ስትል ለለቅሶ የተሰበሰበው ህዝብ የልቡን ስላንጸባረቁለት በማልቀስ ፋንታ ተደስቶ በሳቅ ሲያወካ ንጉሱ የሚያደርጉትን አጥተው የተያዘችውን አስለቃሽ ልቀቁ ብለው ለቅሶውን ፈቱ ይባላል
በዚያን ጊዜ እንኳ ለአዝማሪዎች የነበረ መፈራት ዛሬ የለም
የጠ/ ሚ/ሩ ሞታቸውን አስመልክቶ ዜና አቅራቢዎችን ሲያስሩ ሲፈቱ አሁንም ያሉት የሚደግሙት የያኔውን ነው
ቅድመ አያታቸው እንዳደረጉት በ97 ምርጫ አልመረጠኝም በሚል ቂም የጎጃምን ህዝብ /የሳቸውን አጫፋሪዎችና ሆዳሞችን አይጨምርም/ ባገሩ ላይ ብቻ ሳይሆን ተሰዶ በሄደበት በደቡብ ኢትዮጵያ ለይተው ቁም ስቅሉን ያሳዩት እነደነበረ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች ሁሉ የዘገቡት ነው
ከሳቸው ፈቃድ ያፈነገጠ ማንኛውም ብሄር ብሄረሰብ ወይም ግለሰብ በምን ሁኔታ ሲሰቃይና ሲንገላታ እንደነበር ብዙ ተብሏል እሳቸው የጨፈጨፉትንና ያስጨፈጨፉትን ወይም የሰሩትን ያሰሩትን አረመኔያዊ ስራ በቪዲዮ እያስቀረጹ ይህ እገሌ የተባለው ጠላትህ እንዲህ እያደረገህ ነው ብለው የሚያሳዩ ናቸው
ዲሞክራሲ አለ ብለው አናግረውና አስለፍልፈው የሚወነጅሉ የሚያስሩ የሚያስገድሉ ናቸው በኢትዮጵና ታሪክም ሆነ በአለም በአንዴ ቁጥሩ ብዙ የሆነ ህዝብ ያሰረ የለም እሳቸውን የሚበልጥ ለነገሩ አገሪቱ በሙሉ በእስር ቤት ውስጥ ነው ያለችው
የሳቸው አምባገነናዊ የግዛት ዘመን የሰው ልጅ ጭቆናና ስቃይ እጅግ የከፋና የተራቀቀ ደረጃ ወይም የመጨረሻው ጥግ የደረሰበት ነበር
በሀይማኖት በብሄር ብሄረሰብና በሌላም እየገቡ ህዝቡ እርስ በርስ እንዲጋጭ ሰላም እነዳያገኝ ስለሀገሩ እንዳያስብ ሲያደርጉ የነበረ ገጽታቸው ጥሩ የሚመልስ ውስጣቸው ተንኮልና ሸር የተሞላ ነበሩ
አገሪቱን በፍርሃት በረሃብ በኑሮ ውድነት ጠፍረው ይዘው ሲያሰቃዩዋት የነበሩ በመሆናቸው ህዝሁ ብሶቱን የሚገልጥበት አጋጣሚ ቢያገኝ የአያታቸውን ሙሾ ነበር የሚደግምላቸው እሳቸው እንዳደረጉት
አሁንም
አምባው ተሰበረ አምባው ተሰበረ
እንደነሙተራ እንደነ ጅበላ ይፈራ የነበረ
እንደተባለው ሞት ይህችን ምስኪን ሀገር ከአስከፊውና ከአስፈሪው ጠላቷ ገላገላት እንጂ ብዙ ጥፋት ያደርሱ ነበር ተከታዮቻቸውም ፈለጋቸውን ተከትለው የበለጠ ይህችን ሀገር እንዳያጎሳቁሏት
ደህና ተሰናድቷል ተጠርጓል መንገዱ
አጼ በሄዱበት ንጉሱም ይሂዱ

የሚለውን ሙሾ እንጋበዛቸዋለን መለስን ተከትለው እነሱም እንዲሄዱ

Blog Archive