Monday, November 26, 2012

ከአብዮት ፍንዳታ እስከ ዘመነ “ፍንዳታ”(ኤፍሬም እሸቴ/adebabay.com/ PDF)፦ በንጉሠ ነገሥት የምትመራዋ ኢትዮጵያ ዘውዷን አፍርሳ፣ አልጋ አስገልብጣ፣ ንጉሥ አስገድላ፣ ሚኒስትር አስረሽና፣ ወጣት አሰድዳ ከምሥራቁ ካምፕ ከገባች እነሆ 40 ‘ዘበን’ ሆናት። የአንድ ጎልማሳ ሰው ዕድሜ ማለት ነው። በነዚህ 40 ዓመታት ውስጥ ያለፉ፣ ያሉ ኢትዮጵያውያን እንደየማንነታቸው አንዱን ዘመን ከአንዱ እያነጻጸሩ እንደሚያመሰግኑትና እንደሚረግሙት ሁሉ አንዱን ትውልድም ከአንዱ እያነጻጸሩና እያወዳደሩ አንዱን ያሞግሳሉ ሌላውን ያኮስሳሉ። አንዱን በትጋቱ፣ ሌላውን በሥራ-ፈትነቱ፤ አንዱን ለአገር በመሞቱ፣ ሌላውን በራስ-ወዳድነቱ ያነሱታል። እንዲህ መነጻጸሩ ካልቀረ መጠነኛ ሐሳብ ብናክልበትስ?

“ትውልድ” ምንድነው? በምንስ ይለካል?

 “ትውልድ”/generation የሚለው ሐሳብ ብዙ አንድምታ አለው። የማኅበረሰብ-ሊቃውንት (ሶሻል ሳይንቲስቶች) ቢያንስ አምስት ትርጉም ሊኖረው እንደሚችል ጽፈዋል። በመጀመሪያ ደረጃ በትውልድ ሐረግ ያሉ ዘር-ማንዘሮች በትውልድ ይቆጠራሉ። አባት፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ወዘተ እንዲል። እንደየመነሻው ወደታች አንደኛ ትውልድ፣ ሁለተኛ ትውልድ እያሉ መቀጠል ነው። ከአያቴ ብጀምር እኔ የሳቸው ሦስተኛ ትውልድ ነኝ፤ አባቴ ሁለተኛ፣ እርሳቸው አንደኛ።

ሁለተኛው ትርጓሜ በአንድ ዘመን ያሉ እና ተመሳሳይ “የሕይወት ዑደት” (life-course) የሚካፈሉ ሰዎችና ቡድኖች “አንድ ትውልድ” ሊባሉ ይችላሉ። ለምሳሌ በ2005 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የሚጨርሱ ተማሪዎች “አንድ ትውልድ ናቸው” እንደማለት ነው።

ሦስተኛው ደግሞ በአንድ የታሪክ ዘመን ያሉ እና በአንድ የታሪክ አጋጣሚ ላይ የነበሩ ሰዎችም አንድ ትውልድ ተብለው ይለያሉ። ለምሳሌ በአገራችን “በተማሪው ንቅናቄ እና ለውጥ” የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ የነበሩ ሰዎች አንድ ትውልድ ናቸው።

አራተኛው ትርጉም ደግሞ በአንድ የታሪክ ወቅት ያሉ ነገር ግን በዚያው የታሪክ ወቅት ውስጥ ከሌላው በተለየ ለብቻቸው የሚጋሩትና አንድ የሚሆኑበት ፖለቲካዊ ወይም ባህላዊ ማንነት ካለ ያ የተለየ ማንነታቸው “አንድ ትውልድ” ያረጋቸዋል። ለምሳሌ ከፍ ብዬ በጠቀስኩት የኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ውስጥ የተለያዩ ቡድኖች ነበሩ። አንዱ ውሎ አድሮ ኢሕአፓ ቢሆን፣ አንዱ ውሎ አድሮ ኢሕአዴግ ቢሆን፣ ሁለቱም በየራሳቸው የተለያየ ፖለቲካዊ አመለካከት እና ልምድ ስላላቸው የየራሳቸው ትውልድ ፈጥረዋል። ኢሕአፓዎቹ ክፍሉ ታደሰ በአጭር አባባል “ያ ትውልድ” ያላቸው ናቸው። ኢሕአዲግ በበኩሉ የራሱን ቡድን “ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ” ሊለው ይችላል። ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ሁለት የፖለቲካ ትውልዶች ናቸው ማለት ነው።

አምስተኛው የትውልድ ትርጉም “በዕድሜ አቻነት” የሚገኝ የትውልድ አንድነት ነው። ለምሳሌ “ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረራ በያዘችባቸው አምስት ዓመታት የተወለዱ ልጆች” ብንል በዘመን አንድነት “አንድ ትውልድ፡ እናደርጋቸዋለን። ይህም “ጄኔሬሽን” ከሚለው ቃል ይልቅ “cohort” በሚለው የበለጠ ይታወቃል። (የነዚህ ትርጓሜዎች ምንጭ Dictionary of Sociology፤ ስለ “Generalization” ያተተው ነው)።

. . . ያንቀጠቀጠው . . . “ያ” ትውልድ . . .

“ትውልድ” የሚለው ሐሳብ እንዲህ የተለያየ አንድምታ ቢኖረውም በዚህ ጽሑፍ ለመመልከት የምንሞክረው በሦስተኛና በአራተኛ ደረጃ የተጠቀሰውን ትርጉም ነው። ይህም የኢትዮጵያን ሶሺዮ-ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የሚመለከት ይሆናል። ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ “ምሁራንና መንግሥት በ20ኛ ክ/ዘመን ኢትዮጵያ” በተሰኘው ጽሑፋቸው ምሁራኑን በሦስት ዐበይት ትውልዶች ከፍለዋቸዋል። የገ/ሕይወት ባይከዳኝ ትውልድ፣ የገርማሜ ንዋይ ትውልድና ጥላሁን ግዛው ትውልድ። ገ/ሕይወት ከአጼ ምኒልክ ዘመን እስከ ጣሊያን መግባት ድረስ ያለውን፣ ገርማሜ ከጣሊያን መውጣት እስከ 1960ዎቹ ያለውን፣ ጥላሁን ደግሞ ከ1960ዎቹ እስከ አሁን ያለውን ዘመን ፖለቲካዊ አመለካከት እንደቀየሱ ተጠቅሷል።

የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ብንተውና የጥላሁንን ብንመለከት፣ በተማሪ እንቅስቃሴ ዘመኑ “የመገንጠል መብትን፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን፣ መሬት ላራሹን” በዋና ጉዳይነት በማቀንቀኑ ብቻ ሳይሆን ከዚያ ወዲህ ያሉት ግራ ዘመም ኢትዮጵያውያን ቃሉን እንደ አምላክ ቃል በመከተላቸውና በዘመነ ኢሕአዴግም ይኸው አስተምህሮ ቃል-በቃል በመተግበሩ ዘመኑን “የጥላሁን”፣ ትውልዱንም “የጥላሁን ትውልድ” እንዳሉት ከፍ ብዬ የጠቀስኹት ጽሑፍ ያትታል።

ይህንን “የጥላሁንን ትውልድ” ዘለግ ብለን ገብተን መጋረጃውን ብንገልጠው ደግሞ በውስጡ ብዙ “ፖለቲካዊ ትውልዶች” እናገኛለን። የጥላሁን የዕድሜ፣ የትምህርትና የዘመን አቻዎች ከሆኑት እንኳን ብንጀምር ኢትዮጵያ በአንድ የግራ አመለካከት ውስጥ የማይታረቁና አብረው የማይቆሙ ብዙ አመለካከቶችን እንደያዘች እንረዳለን። እርበርሳቸው የተላለቁት የዘመኑ ወጣቶች እነዚሁ ግራ ዘመሞች እና ሌኒናዊ-ስታሊናዊ አመለካከት አራማጆች እንጂ የምዕራብ አገሮች ፍልስፍና አድናቂዎች አልነበሩም።

ይህ ግራ ዘመም ሌኒናዊ-ስታሊናዊ ትውልድ በዘመን ብዛት ቢያረጅና አመለካከቱ ወንዝ እንዳላሻገረው ቢገነዘብም ቂሙን፣ አልታረቅ ባይነቱን፣ ሁሉን አዋቂ-ነኝ ባይነቱን፣ ቂመኛነቱንና በጎጥና በጎሳ ላይ የተመሠረተ ቡድነኛ አመለካከቱን የሙጥኝ እንዳለ ቀርቷል። በዘመኑ ከነበሩት የተለያዩ ግራ-አክራሪ ቡድኖች መካከል የሥልጣን ኮርቻውን የተቆናጠጠው ኢሕአዴግ የዘመነ-ተማሪነት ፍልስፍናዎቹን ቃል በቃል በመተግበር ላይ ይገኛል።

ከ “ያ. . .ንቀጠቀጠው” የቀጠለው ትውልድ፤ የቱ?

ከዚህ ግራ-አክራሪ ትውልድ ቀጥለው የተነሱ ቢያንስ ሁለት ትውልዶች ያሉ ይመስለኛል። የዘመነ ኢሰፓ እና የዘመነ-ኢሕአዴግ ትውልዶች። ሁለቱም የየራሳቸው መገለጫ አላቸው። የመጀመሪያው ቀይ/ነጭ ሽብር ጭንቀት፣ ከእርስበርስ ጦርነት፣ ከብሔራዊ ውትድርና ሽሽት የተረፈ እንደመሆኑ “መንግሥትን መሸሽ ወይም ደግሞ አንገትን ደፍቶና ተመሳስሎ አብሮ መኖር” የሚለውን የጎመን-በጤና መርሕ ተለማምዷል። አሁንም ድረስ ገፍቶበታል።

በዘመነ ኢሕአዴግ የመጣው የ“አዲሲቷ ኢትዮጵያ” ትውልድ ከግንዱ እንደተመለመለ ቅርንጫፍ መሠረታዊ የኢትዮጵያዊነት ዕውቀቶችን ሳይገነዘብ ያደገ ነው። ጎሳዊና ብሑረሰባዊ ማንነቱን እንጂ በዚህ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ እንደ አንድ አገር ያኖረውን የጋራ ማንነቱን እንዲገነዘብ ዕድል አልተሰጠውም። ዕውቀትና ችሎታ ሳይሆን ፖለቲካዊ ወገንተኝነት (በግምገማ ቋንቋ “አመለካከት” የሚባለው) ዋጋ ሲሰጠው ካየ “ወንዝ ከማያሻግረው” ትምህርት ይልቅ “ለፖለቲካ ጥናት” የተሻለ ሥፍራ ይሰጣል። ዘረኛ ቢሆን፣ ኢትዮጵያዊነት ባይሰማው፣ ማንነቱን ባያስታውስ፣ ከአገር ይልቅ ለፓርቲው ቅድሚያ ቢሰጥ ተጠያቂው እንዲያ እንዲሆን ያደረገው ሥርዓተ ማኅበር ነው።

ነገር ግን ይህ ነው የሚባል “ትውልዳዊ አሻራ” መተው የቻሉ አይደሉም። አንድም ወታደራዊውን መንግሥት አልያም በምትኩ የተተካውን ኢሕአዴግን በማገልገል የተጠመዱ ገባሮች ናቸው። ውድድሩ “ምን ያህል ታማኝ አገልጋይ ነኝ” ለማለት ካልሆነ በስተቀር የአገሪቱን ሁለንተናዊ ሕይወት ሊለውጥ የሚችል እንቅስቃሴ ለማድረግ ዕድል ያገኙ ትውልዶች አይደሉም።

አሁንም የዚያ ያለፈው “ትውልድ” ጥላውን በእጅጉ አጥልቶባቸዋል። በዘመነ ደርግ የነበሩትን በማስፈራራትና በማስገበር፤ በዘመነ ኢሕአዴግ ያደጉትን ደግሞ አንድ መልክና ቅርጽ ያላቸው፣ ለመጠየቅ የማይደፍሩ፣ “ሳይጠሯቸው አቤት፣ ሳይልኳቸው ወዴት” የሚሉ እንዲሆኑ “ሕጽበተ አእምሮ” (ብሬይንዎሺንግ) በመፈጸም አምክኗቸዋል። ከዚህ አንጻር ከዚያ ግራ-አክራሪ ትውልድ በኋላ የተፈጠሩ ትውልዶች እንደሚባለው “ለአገር የማያስቡ፣ ፍሬ ቢሶች” ሆነው ከሆነ በዋነኝነት ተጠያቂው ተራሮችን አንቀጠቀጠጥኩ የሚለው “ያ” ትውልድ ይሆናል።

ራሱን የቻለ ትውልድ

የትኛውም ትውልድ ለአገሩ ታላቅ አስተዋጽዖ ለማበርከት የበቃ ከነበረ፣ ለዚያ ታላቅ ሥፍራ እንዲበቃ ያደረገው የቀደመ ትውልድ መኖር አለበት። ፕ/ር ባሕሩ ዘውዴ የጠቀሷቸው የግርማሜ ንዋይ እና ኋላም የተነሣው የጥላሁን ግዛው ትውልዶች ለአገራቸው የሚቆረቆሩ፣ የአውሮፓውን ዕውቀት በመሸመት ለአገራቸው ጥቅም ለማዋል ከተጉ፣ የአገራቸው ወደ ኋላ መቅረት ካንገበገባቸውና ለመለወጥ ተግተው ከሠሩ አብሮ መመስገን ያለበት እነርሱ ያንን ዕድል እንዲያገኙ ያደረጋቸው ትውልድም ነው።

ለራሱ ብቻ የሚያስብ ገበሬ ሁል ጊዜ ቶሎ የሚደርስ ብቻ እህል እየዘራ፣ እሸት እሸቱን ብቻ እየበላ፣ ምድር ያፈራችውን ለራሱ ዘመን ብቻ እየተጠቀመ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ይላል። ለልጅ፣ ለልጅ-ልጅ-ልጅ የሚያስብ ሲኖር ደግሞ ቶሎ የሚደርስ ዘር መሥራት ብቻ ሳይሆን በትውልድ የሚደርስ ተክል ሲተክል ይገኛል። ያ ተክል በደረሰበት ዘመን የሚነሣ ትውልድ የቀደመውን ማመስገን እንዳለበት ይረዳል።

በዚህ የ40 ዓመት የተነሣ የኢትዮጵያ ትውልድ በራሱ እንዲያስብና “ራሱን የቻለ ትውልድ” እንዲሆን ዕድል አልተሰጠውም። ከዚህ በፊት የተፈጸሙ ስህተቶች አሁንም በሌላ ዘመን እንደ አዲስ ሲደገሙ ማየት የተለመደ ነው። አብዮቱ “በግብታዊነት ከፈነዳ” ለ40 አንድ ፈሪ ዓመት ቢሆንም አሁንም የፈነዳው አልሰከነም። አሁንም በዚያው የአብዮት መንፈስ ውስጥ ነን። ያልሰከነ ማኅበረሰብ የሰከነ ትውልድ ሊፈጥር አይችልም። የቃላት ለውጥ ካልሆነ በስተቀር የይዘት ለውጥ የለም። ስልቻ ቀንቀሎ፣ ቀንቀሎ ስልቻ ነው። ስለዚህ ያለፉትን ትውልዶች ከዚህኛው ጋር ማነጻጸር ፈረንጆቹ “comparing apples and oranges” ያሉት ነገር ነው። ሁሉም እንደየዘመኑ፣ እንደየአቅሙ፣ እንደየተሞክሮው ቢመዘን ይሻላል።

  

ይቆየን - ያቆየን።

 

10 comments:

ንጋቱ said...

I agree with most of your thoughtful analysis; but your characterization of the Dergue and EPRDF generation as not fortunate enough to shape its identity and leave its mark simply because of the repressive nature of the respective governments seems an attempt to relieve your generation(perhaps)off its responsibility. While I share the idea that both governments have crushed independent minds,which have contributed to creating the two subservient generations, these generations can't escape from the blame of selfishness and need to correct this.

Anonymous said...

Dear D/n Efrem, it is excellent and in depth article that defines and compares various generations and give in sight where we are what is expected from who, etc. We really need to change the generation to be responsible for his country, know his culture, history and identity, so that one day we could again create a unified Ethiopians and Ethiopia, the symbol of Africa, all black nations, which is the land of Lucy, the cradle of human being. Thank you so much, keep on writing

Anonymous said...

I am really worried about my Kids when I think about the Future generation. No body told them the past, they do no think about the future they care only for today. We are bringing up them in a confined area(small compound 70m2), no true history lessons at school,the church concentrates only on literal bible teachings...

Anonymous said...

Wede wendemachen Diakon or Guade[I don't know which name you like]any way yes yehe zemen yalesegate yemenenorebet,selezemecha[belate]sayehone seletemehert,edeget...yemenasebebet honoal!!ante endemetelew brain wash tedergen sayhone...selam men malet endehone, hager men malet endehone..DEHENA HUNU SAYHONE LENEGE QETERO TEYEZO YEMITEGNABET,[ANDEM...ENDELU ...[ABEYOTACHEN] HOYE SAYEHONE ..[ABATACHEN] HOYE YEMIBALEBET..ZEMEN DERSEN TAEMUN SELAYENEW NEW!!IN MY OPINION BRAIN WASH YETEDEREGUT YEMELACHEW ,EWENETUN EYAWEKU YEMAYAMENU,NACHEW!!WITH ALL RESPECT I KNOW U KNOW THE TRUTH!!ANTE BE AMERARENET YEMETAWEKW MK ZARE EZIH DERSO ...TALAQ SERA EYESERA YALEW BEZIH ZEMEN NEEW!!BEBEZU NEGER I RESEPECT U ASTEMEREHNGAL ENA...BUT BEZIH GEEN ALSEMAMAM [YE QEY SHEBER ZEMENEN ALFEN ARENGUDE ZEMEN LAYE DERSENALENA!!!PLEASE DON'T TELL ME THAT I HAVE BEEN BRAIN WASH?!

Anonymous said...

WENDEM DIAKON OR GUADE EPHREM [I DON'T KNOW WHICH ONE YOU LIKE BETTER] BUT ANY WAY ..YE AHUN ZEMEN TEWELEDOCH ..ANTE ENDE METELEN HAGER YEMANEWEDE WEYEM ZERGONCH SANHONE..YE HAGER FIKER SEMET BEDENB YEGEBAN , BESEMET SAYHON BETEGEBAR ,BE WESHET SAYHON BE EWENET ,BEZU BEZU....LEMEHONU WHAT DO U MEAN WHEN U SAID BRAIN WASH??YEH ZEMEN EKO YESELAM ZEMEN,YEH ZEMEN EKO NEEW YA LESEGAT YADEGNEBET ZEMEN,LE SELTENA WEDE BELATE ..MENEW TERESA ENDE YA QUMESATEN LAY TEDEBEKO MADEG?YE TEYAZUT DEGEMO WE DE BELATE!ENE YEMELEW D.EPHREM ENDET ENDET BETENQEN NEEW YEHENEN TEWELDE ENDEH YEMETAFERTEW??ENATOCHACHEN SELELEJOCH SAYCHENEKU ,BESELAM YETNGUBET ZEMEN, YEKEY SHIBER[RED TERRIOR]ZEMEN ABEQETO YE ARENGUADE ZEMWN...ANDEM....[ABEYOTACHEN HOYE SAYHON[ABATACHEN HOY YEMENELEBET ZEMEN ...WENDEM EPHREM EWENET EWENET NEEW 'EWNETE TEKETELUAT BELEH EKO ASTEMEREHENGAL..MENEW TADIYA NEEW WEYES HAGER BET BECHA NEEW YEMESERAW??HOO PLEASE DON'T TELL ME THAT I HAVE BEEN BRAIN WASHED?!SELEHAYMANOTE BEZU ASTEMEREHENGALENA AKEBREHALEHU!!

Anonymous said...

የማላውቅህ ወንድሜ AnonymousDecember 3, 2012 3:54 AM የምንኖረው ኑሮ በርግጥ አንተ እንዳልከው ነው ወይስ ‹ ሰውየው እንዳሉት› እያልከን ነው (ሴትየዋ ኑሮ እንዴት ነው ሲሏት ጠቅላይ ሚንስቴሩን ጠይቋቸው አለች ምን ታርገው እሷ የምትኖረው ኑሮ እና ሰውየው የሚሉት የሁለት ዓለም ነገር ሆኖባት ነዋ) እና እኔ የምልህ ወንድሜ እራሴ ፣ጓደኞቼ ፣እንዲሀም ታናናሽ ወንድሞቼ ሁልጊዜ የሚነግሩኝ እንተ የምትለውን አይደለም በአንጻሩ ለሚያደርገው ነገር ምንም ዓይነት ምክንያት የሌለው ፤ በቅኝ ግዛት ባለመያዙ የሚቆጭ ፤ instinctively ለሚደረጉ ነገሮች እንጂ ታስበው ለሚደረጉ ማናቸውም ጉዳዬች መንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ ጉዳይ ትግስትና ጥብዓት የሌለው (ለመዝናናትም እንዲሁ ነው ) እሺ እና እምቢ ለምን እንደሚል የማያውቅ ትውልድ መፈጠሩን እራሳችንን ስንመረምር በውስጣችን ቆሞ የምናገኘው አስደንጋጭ ደረቅ ሀቅ አይደል ፤ ደግነቱ ይሄን መጠየቅ የሚያስችል አቅም የለንም፡፡ እስቲ ፈጣሪ በጥበቡ ወደ እውቀት ዘመን ይምራን፡፡

Anonymous said...

Hey cadre dude, are you living in ETVopia? I believe you aren't talking about Ethiopia. ETVopia v Ethiopia!

Anonymous said...

my elementary school teacher always told us(his class students) you are very lazy since you have electric light,near by schools,..blah bla,on the contrary his generation was intellegent without these oppurtunity!but what about the challenges of this generation,there is a lot of movies,primier lig,internet...million .አዘናጊ problems!there is no internet,laliga,football,movies everywhere that divert their attention from their goal at that time!look for example who is more intellegent from the old american generation and the nearby generation?therefore the nearby generation is supported by many new thechnologies to compensate the አዘናጊ problems due to civilization!we need a support not ....!!!!!!!!!

Anonymous said...

my elementary school teacher always told us(his class students) you are very lazy since you have electric light,near by schools,..blah bla,on the contrary his generation was intellegent without these oppurtunity!but what about the challenges of this generation,there is a lot of movies,primier lig,internet...million .አዘናጊ problems!there is no internet,laliga,football,movies everywhere that divert their attention from their goal at that time!look for example who is more intellegent from the old american generation and the nearby generation?therefore the nearby generation is supported by many new thechnologies to compensate the አዘናጊ problems due to civilization!we need a support not ....!!!!!!!!!

Anonymous said...

my elementary school teacher always told us(his class students) you are very lazy since you have electric light,near by schools,..blah bla,on the contrary his generation was intellegent without these oppurtunity!but what about the challenges of this generation,there is a lot of movies,primier lig,internet...million .አዘናጊ problems!there is no internet,laliga,football,movies everywhere that divert their attention from their goal at that time!look for example who is more intellegent from the old american generation and the nearby generation?therefore the nearby generation is supported by many new thechnologies to compensate the አዘናጊ problems due to civilization!we need a support not ....!!!!!!!!!