ለምን ሞተ ቢሉ
ለምን ሞተ ቢሉ
ንገሩ ለሁሉ
ሳትደብቁ ከቶ ፤
“ከዘመን ተኳርፎ
ከዘመን ተጣልቶ።”
(ደበበ ሰይፉ 1968)
"አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣2004 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው ደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ባጋጠመው ህመም ምክንያት ሆስፒታል ገብቶ የነበረው ደራሲ ስብሃት ባለፈው ረቡዕ ከሆስፒታል በመውጣት ወደ ቤቱ ቢመለስም ዛሬ ንጋት ላይ ህይወቱ አልፏል። የደራሲ ስብሃት ገብረ እግዚአብሄር የቀብር ስነ ስርአት ዛሬ ከቀኑ በ10 ሰአት 4 ኪሎ በሚገኘው የቅድስት ስላሴ ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል።"

