Thursday, June 28, 2012
Friday, June 22, 2012
አድራሻ
(ኤፍሬም እሸቴ/ PDF):- ድንገት በአጋጣሚ ቴሌቪዥናችሁን ወይም ሬዲዮናችሁን ስትከፍቱ የምታዩትን - የምትሰሙትን ማስታወቂያ እና የማስታወቂያ አስነጋሪውን አድራሻ ልብ ብላችሁ አድምጡ። ድርጅቱ ስለሚሠጠው አገልገሎት መልካምነት፣ ስለሚሸጠው ዕቃ ምርጥነት፣ ስለሚያቀርበው ምግብ ጥዑምነት ዘርዝሮ ሲያበቃ አድራሻውን ማስቀመጡ አይቀሬ ነው። በርግጠኝነት ግን በዚህ ቦታ ነው ድርጅታችን ያለው ከማለት ይልቅ … “ከእንትን ወረድ ብሎ፣ ከእንትን ከፍ ብሎ፣ እንትን እና እንትን ፊት ለፊት፣ እንትን አውቶቡስ ማዞሪያ፣ እንትን ኤምባሲ አካባቢ” …. ይለናል።
Monday, June 18, 2012
ምንድር ነኝ? ማነኝ?
(በኢትዮጵያዊው ፍቅረ መድኅን/ READ IN PDF):- አንድ ሰው እንዲህ ብሎ ጠየቀ:: ምንድር ነኝ? ማነኝ? መለሰም፡- አንደኛ - የሥላሴ ፍጡር ፣ ሰው ነኝ፡፡ ኹለተኛ - ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ ሦስተኛ፣አራተኛ… እያለ ወደላይም ወደታችም፣ወደፊትም ወደኋላም፣ወደግራም ወደቀኝም ሊሳብ እና ሊቀጥል ይችላል፡፡ ቁም ነገሩ ወደፊት ማራመዱ፣ ሰውን ኹሉ በሰውነት አንድነቱ መቀበሉ ነው፡፡ እኔ ደግሞ እንደ ሰውነቴ በአገሬ ሆኜ ምንድር ነኝ? ማነኝ? ስል ጠየቅኹ፡፡ ስለዛም ‘ኢትዮጵያዊ ነኝ’ አልኩ፡፡
Saturday, June 9, 2012
የኛ ሰው በላስ ቬጋስ … “ሑቨር ዳም - የሑቨር ግድብ” (ክፍል ሦስት)
(ክፍል ሦስት/ PDF)
እንደምን ከረማችሁ?
ይህ ጽሑፍ ወደ ላስ ቬጋስ ካደረግኹት የጉዞ ማስታወሻ ቅንጫቢውን እና ሦስተኛውን ክፍለ- ትረካ የያዘው የመጨረሻው ነው።
በገባኹት ቃል መሠረት ስለ ታዋቂው የሑቨር ግድብ አጫውታችኋለሁ። እንደምታስታውሱት፣ ባለፈው የ “ገዳመ እንጦንስ” ጉዞዬ
ማስታወሻ፣ በኔቫዳ በረሃ ውስጥ የተገነባውን ገዳም አነሣሥ እና የኢትዮጵያዊውን ቅዱስ የሙሴ ጸሊምን ቤተ ክርስቲያን ጅማሮ
ጽፌላችሁ ነበር። ዛሬ ደግሞ ከመሐል ላስ ቬጋስም፣ ከበረሃው ገዳምም ወጥተን፣ ወደ 20ኛው መቶ ድንቅ የአሜሪካ የኢኒጂነሪንግ ግኝት
ወደሆነው ወደ ሑቨር-ግድብ እንዘልቃለን።
Subscribe to:
Posts (Atom)


