Saturday, January 19, 2013

የ“ዝም በል ዳያስጶራ” - አዋጅ፦ ከቤተ መንግሥት እስከ ቤተ እምነት (ኤፍሬም እሸቴ/ READ IN PDF)፦ በዚህ ሰሞን መቼም ከእግር ኳስ ውጪ ማውራት በሕማማት ስለ ቁርጥና ጥብስ እንደማውራት ሳይቆጠር አይቀርም። እኔም ብሆን ስለ እግር ኳሱ ማውራቱን መች ጠልቼው። በርግጥ ይኼ ሁሉ ወፈ ሰማይ የስፖርት ተንታኝ በየኤፍ.ኤሙ ሲተችበት በሚውለው የተጫዋቾቻችን ብቃት፣ ጥራት፣ የኳስ ጥበብ፣ የሽልማት ዓይነት፤ የተጋጣሚዎቻችን ሁኔታ፣ የተጫዋቾቻቸው ዝና፣ ማን ከየትና ከየትኛው ክለብ እንደመጣ፣ አሰላለፋቸው እና ከኢትዮጵያ ጋር ሲገጥሙ ሊኖራቸው ስለሚችለው አያያዝ ለመተንተን ሙያውም መረጃውም የለኝም። (“ችሎታ የለኝም” አለማለቴ ይሰመርበት። ማን ይሞታል። መቸም “አልችልም” ማለት ጎጂ ባህል ሆኗል።) ቢያንስ የእንጀራ አገሮቻችን አሜሪካ እና ስዊዲን ስላፈሯቸው እና ለእናት አገራችን ኢትዮጵያ ስላበረከቷቸው ተጫዋቾቻችን መወያየት ይቻላል።

 

ኢትዮጵያውያን እንደ ጨው በመላው ዓለም ተበትነዋል። በብዙ ቦታዎች አንድ ትውልድ አልፎ ሁለተኛ ትውልድ ላይ ደርሷል። በቅርብ ከሚገኙት ኬንያና ሱዳን እስከ አረብ አገሮች፣ ከምዕራብ አውሮፓና ስካንዲኔቪያን አገሮች እስከ አሜሪካና አውስትራሊያ ድረስ ብዙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ። ከእነርሱ መካከል የአሜሪካ ሜኔሶታው ፉአድ ኢብራሒም እና የስዊዲኑ ዩሱፍ ሳላህ ተገኝተዋል። ፉአድ ኢትዮጵያ ተወልዶ አሜሪካ ያደገ፤ ዩሱፍ ደግሞ እዛው ስዊዲን ተወልዶ እዛው ያደገ እግር ኳስ ተጫዋች ነው። የብዙ ኢትዮጵያውያን የኋላ ማንነት ማሳይ ሊሆኑ የሚችሉ ልጆች ናቸው። አድገውና ለቁም ነገር ደርሰው አገራቸውን ለመወከል መብቃታቸው ደስ ይላል። “አለ ገና፣ ገና፣ አለ ገና” እንላለን።

 

ጣዕመ-ኢትዮጵያ፣ ባህለ-ኢትዮጵያ በቀዘቀዘባቸው ባህሎች መካከል አድገው በመጨረሻ አገራቸውን ለመወከል መቻላቸው ትልቅ ነገር ነው። ስለ ፉአድ ያነበብኩት አንድ ጽሑፍ ይህ ወጣት ለአሜሪካ እግር ኳስ ቡድን (ከ17 ዓመት በታች እንዲሁም ከ21 ዓመት ላሉት) ቢጫወትም የማታ ማታ ግን አገሩን ለመወከልና የአገሩን ማሊያ ለመልበስ መወሰኑን ያትታል። ስዊዲን እነ ኢብራሒሞቪችን (በአባቱ ቦስንያዊ) እና ታዋቂው ሔንሪክ ላርሰንን (አባቱ ከኬፕቬርዴ ናቸው) የመሳሰሉ ተጫዋቾችን በማሰለፏ እናውቃታለን። ዩሱፍም ተመሳሳይ በሆነ መልክ ተመሳሳይ ዕድል ሊያገኝ እንደሚችል እገምታለኹ። ነገር ግን ያንን ትቶ የአገሩን መለያ ለብሷል።

 

ዳያስጶራው ለረዥም ዓመታት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወደ አገሩ በመላክ አገሩን በቀጥታም በተዘዋዋሪም ሲደግፍ ቆይቷል። በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከዳያስጶራው የሚገኘው ገቢ አገሪቱ ከወጪ ንግድ ከምታገኘው በእጅጉ እንደሚበልጥ የዓለም ባንክ ጥናቶች በተደጋጋሚ አሳይተውናል። ከዚህ የቀጥታ ገንዘብ ርዳታ ባሻገር ትውልደ-ኢትዮጵያዊው በአገሪቱ አጠቃላይ ሕይወት ላይ በጎ ሱታፌ ማሳየቱ አገሩን ለሚወድ ወገን ሁሉ ትልቅ ተስፋ ነው። ዩሱፍና ፉአድ ለዚህ መልካም አብነቶች ይሆናሉ።

 

ዩሱፍና ፉአድ ወደ አገራቸው ሲመለሱ በዚያው መጠን ብዙ ኢትዮጵያውያን ወደ ዳያስጶራነት ጎራ እየተቀላቀሉ ነው። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በዋሺንግተን ዲሲ የተደረገ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ሐኪሞች ማኅበር ስብሰባ ተገልጿል እንደተባለው በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ዶክተሮች ይልቅ በውጪ የሚገኙት ቁጥር ይበልጣል። አዝማሚያውን ስንመለከተው ይኸው የዕውቀትና የአዕምሮ ስደት እንደሚቀጥል እርግጥ ነው። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ዋስትና ማጣት እና ፖለቲካዊ ነጻነት አለመኖር ነው። ከኢኮኖሚው በበለጠ ፖለቲካዊ ጫናው ለብዙው ወገናችን መሰደድ ምክንያት ነው የሚለው የብዙዎች እምነት ነው። በፖለቲካዊ ምክንያቶች የተሰደዱት ደግሞ በየወጡበት አገር ባላቸው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን መንግሥት ዘወትር መክሰስ ቀጥለዋል። በቅርቡም ይቆማል ተብሎ አይጠበቅም። ይህም ፉአድንና ዩሱፍን የመሳሰሉ ትልውደ ኢትዮጵያውያን በየሙያቸው ትውልድ አገራቸውን እንዳያገለግሉ እንቅፋት ይሆናል። በአገሪቱ ያለው የሰብዓዊ መብት ገፈፋ ሲሻሻል ዳያስጶራውም ተጠቃሚ ይሆናል። ዳያስጶራውን በጥቅማጥቅም ማባበል መጠነኛ ደጋፊ ያስገኛል፤ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት መጠበቅና ሕገ መንግሥቱን ማክበር ግን ሙሉ ድጋፍ ያስገኛል።

 

ዳያስጶራው በየሚኖርበት አገር የሚተነፍሰው ፖለቲካዊ፣ ኅሊናዊ፣ አካላዊ እና ሰብዓዊ ነጻነት ይኸው ነጻነት በአገሩ እንዲኖር በጎ ምኞት ይቀሰቅስበታል። ስለዚህ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በአገሩ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ይኮንናል፤ ተጽዕኖ ለመፍጠርም የማይወጣው ዳገት የማይወርደው ቁልቁለት የለም። ይህም የተለያየ አመለካከት መፍጠሩ አይቀርም። ዳጳስጶራው “አክራሪ ነው” ከሚለው ጀምሮ “የአገሩን ነባራዊ ሁኔታ የማያውቅ” እንዲሁም “50 ዶላር ልኮ አገር ውስጥ ያለው ወጣት እንዲማገድ ይፈልጋል” ወዘተ ተብሎ ይቀርባል።

 

ሐሳቡ ቀደም ብሎ በመንግሥት ብቻ ተደጋግሞ ሲገለጽ የቆየ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ተርታ ዜጎችም በማኅበራዊ ድረ ገጾቻቸው ሲያስተጋቡት ይስተዋላል። በአጭር አባባል ለማቅረብ “ዳያስጶራ ዝም በል” ወይም “ዝም እንዲል አድርጉት” የሚል አዋጅ የተነገረ ይመስላል።

 

በመጀመሪያ ደረጃ አንድን ዜጋ ከአገሩ ርቆ በመኖሩ ስለ አገሩ ያለውን ሐሳብ፣ በመንግሥቱ ላይ የሚኖረውን ቅዋሜ እና ለችግሮች የሚኖረውን መፍትሔ ከማቅረብ ሊከለክለው የሚችል ሕግ የለም። ስለ አገርህ ለመናገር በአገርህ መሬት መኖር አለብህ የሚል “የቀበሌ ትእዛዝ” የመሰለ ሐሳብ ውኃ አያነሣም። ነቢዩ ዳዊት ስለ ኢየሩሳሌም ሲናገር “ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ” እንዳለው “እመሰ ረሳዕኩኪ ኢትዮጵያ  ለትርስዐኒ  የማንየ፣ ኢትዮጵያ ሆይ ብረሳኝ ቀኜ ትርሳኝ የሚሉ ኢትዮጵያውያንን ‘እኮ ምን አግብቷችሁ’ ማለት ከስድብ ይልቅ ያማል።

 

ዛሬ ባንኖርባት ተወልደንባት አድገንባታል፤ ዘር ማንዘሮቻችን ኖረው አልፈውባታል። ክቡር አጥንታቸው ረግፎባታል። በየወቅቱ በሚመጣና በሚሄድ ሥልጣን የአንድ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱ አይገመገምም። ኢትዮጵያዊነትን ማንም ባለሥልጣን አልሰጠንም፣ ማንምም አይነፍገንም። ከደርቡሽና ቱርክ፣ ጣሊያንና ግብጽ፣ ከሌሎችም ድንበር ገፊዎች ሲታገሉ በወደቁ ወገኖቻችን የቆመ ዜግነት እንጂ እንጀራ ፍለጋ፣ ነጻነት ፍለጋ እንደምንኖርባቸው አገሮች በወረቀት ብቻ የሚረጋገጥ አይደለም። ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከወረቀት እና ከፖለቲካ ወገንተኝነት እንዲሁም ከየብሔረሰባዊ ማንነታችን በላይ ነው።

 

በሌላም በኩል ካየነው ስለ ሰብዓዊ መብት ለመናገር የግድ የዚያ አገር ዜጋ መሆን፣ በዚያ አገር መኖርም አይጠይቅም። ሰብዓዊ መብቱ እንዲጠበቅለት የሚፈልግ ማንም ሰው የሌላው ሰው መብት ሲጣስ አይደሰትም። ሌላው ሁሉ ታሪካዊ ሐተታ እንኳን ቢቀር በቅርቡ ዘመን የኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ከኛ ሚሊሻ ጋር አብረው የተዋደቁልንን ኩባውያንን  መስዋዕትነት እንደምናከብረው፣ ዕድሜ ዘመናቸውን በሴቶች (ፊስቱላ) ሕክምና ረገድ አገራችንን የጠቀሙትን ሐኪሞች እንደምናመሰግነው ሁሉ ለዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት የሚከራከሩትንም በዚሁ መነጽር ልንመለከታቸው ይገባል።

 

በተጨማሪም የመንግሥትን አሠራር ማሔስ አገርን መተቸት አይደለም። መንግሥት የአገር መሪ እንጂ አገር አይደለም። ፓርቲና መንግሥትነት ከዘር ጋር በመቆራኘታቸው ፓርቲውን መተቸት የመጣበትን ዘር እንደመውቀስ ተደርጎ መቆጠሩም ትልቅ ስሕተት ነው። ፓርቲዎች በዓላማቸውና በአሠራራቸው መነቀስና መተቸት ግዴታቸው ስለሆነና በዘር ላይ የተመሠረተ የፓርቲ አወቃቀር እስካለ ድረስ ከፓርቲው ጀርባ ያለው ዘር ወቀሳው ለርሱ የተወረወረ አለመሆኑን ለመረዳት ብዙ ጥበብ አያስፈልገውም።

 

እንኳን የኢትዮጵያ መንግሥት በዲሞክራሲያዊነታቸው ወደር የማይገኝላቸው አገሮች የየጊዜው መንግሥታት ሳይቀሩ ከትችት አያመልጡም። ትችት መንግሥታቱን ከዓምባገነንነት የሚያተርፋቸው ፍቱን መድኃኒት ነው። ተቃዋሚዎችን፣ ፕሬሶችን፣ ጥቃቅን ስብስቦችን ሁሉ በመዋጥና በዓይነ ቁራኛ በመመልከት፣ ትችትን ሳይሆን ተቺውን በማፈን ጥሩ መንግሥት መሆን አይቻልም። “ልማት ላይ ነን አትንኩን” የሚል ፈሊጥ ወንዝ አያሻግርም። ጥያቄው ግድቡና ሕንጻው ላይ አይደለም። የዜጎችን ሰብዓዊ ሕንጻ እያፈረሱ የድንጋይ ሕንጻ እንሠራለን ማለት አይቻልም። ከግዑዝ ሕንጻ ሰብዓዊ ዜጋ ይቀድማል፤ከግድብ ግንባታም መብት ይቀድማል።

 

በውጪ የሚገኘው ዜጋ የአገሩን ሁኔታ በትኩረት ለመከታተል ቴክኖሎጂው ትልቅ ዕድል ይሰጠዋል። አራት ኪሎ የተፈጠረው አቃቂ፣ አንዱ ክፍለ ሀገር የተሠራው ሌላው ሳይረዳው ሳይሰማ፤ እረኛና አዝማሪ እንኳን ለዘፈኑና እንጉርጉሮው በራሱ ላይ ግላዊ-ሴንሰርሺፕ በጣለበት ዘመን፣ ከአንድ አፍ በሚወጣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚና ቁጥጥር የተደረገበት ወሬ አገር በሚተዳደርበት ጊዜ፣ አለመስማትን እና አለማወቅን (መንግሥታዊ የመረጃ ግርዶሽን) መታገል ሲገባ የሰማውንና ያወቀውን “እኮ ማን ስማ አለህ” ማለት አያዋጣም። ይህንን የሚለው አካል ነገሩ እንዳይሰማበት የፈለገው እንጂ ተጎጂው አለመሆኑም በቅጡ ይታወቃል።

 

ዳያስጶራውን አምርሮ የመጥላት እና በጅምላ ክፉ ስም የመስጠት ተደጋጋሚ ሙከራ ፍሬ ማፍራቱን ለማወቅ ተርታ ግለሰቦች እና ቤተ እምነቶች ሳይቀር ማንጸባረቅ የጀመሩትን ተመሳሳይ አመለካከት መመልከት ይገባል። የግለሰቦቹን እንኳን ለጊዜው ብናቆየው የአንዳንድ ቤተ እምነት አስተዳደሮችና መሪዎች ከውጪ የሚመጣላቸውን የአማኛቸውን ሐሳብ፣ ልክ እንደ መንግሥት፣ “አፍራሽ፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ጥያቄ” አድርገው ሲመለከቱት ማየት እየተለመደ መጥቷል። ‘አጋጣሚ ነው ወይስ የተላለፈ አዋጅ አለ?’ የሚያሰኝ ነው። የቤተ እምነት መሪዎች ሰማያዊውን መንግሥት መጠበቅ ትተው ምድራዊውን መንግሥት ለመጠበቅ ደፋ ቀና ሲሉ እነርሱን የሚከተላቸው ምእመን እንደሚመለከታቸው እንኳን ይዘነጉታል። እነርሱም ከምድራዊው ባለ ጉልበት ጋር ተደርበው “ውጪ ያላችሁት ዝም በሉልን፣ እንደፈቀድን እንሁን” ሲሉ አዋጃቸውንም በደህና ጊዜ የሚናገሩትንም ሰማያዊ ቃል የሚሰማቸው ጆሮ ያጣሉ። በርግጠኝነት ግን ማንም ዝም አይልም።

 

መልካም ዕድል ለብሔራዊ ቡድናችን!!!!

 

ይቆየን - ያቆየን      

 


© ይህ ጽሑፍ ተቀንጭቦ በሮዝ አሳታሚ ኃ.የተወሰነ የግ.ማ በሚታተመው “አዲስ ጉዳይ መጽሔት” ላይ ያወጣኹት ነው። ጽሑፎቹን በድጋሚ በመጽሔት፣ በጋዜጣ ወይም በተመሳሳይ የሕትመት ውጤት ማተም አይገባም::


 

 

 

 

 

15 comments:

Anonymous said...

ሰላም ፥ በእውነቱ ፡ ጥሩ ፡ ኃሳብ ፡ ነው ፤ ወዲህም ፡ ግን ፡እግዚአብሔርን ፡ እና ፡ ሰውንም ፡ ማፈር ፥ እንዲሁ ፡ አክብሮት ፥ የመናገርም ፣ የገንዘብም ፡ ነፃነት ፡ የተሻለ ካለው ፡ ዲያስጶራም ፡ ይጠበቃል ፤ አንዳንዴ ፡ ዲያስጶራ መሆን ፡ በእራሱ ፡ እንደፈለጉ ፡ የማድረግ ፡ ነፃነት ፡ ሆኖ ፡ ይታያል ፤ ይኸውም ፡ ኃላፊነት ፡ እና/ወይም ፡ ዕውቀት ፡ እና/ወይም ፡ ጨዋነት ፡ የጎደለው ፡ ሆኖ ፡ በቤተክርስቲያንም ሆነ ፡ በፖለቲካው ፡ ጉዳይ ፡ ላይ ፡ ይታያል ፤ ይህንን ፡ በሂደት ፡ ማረቅ ፡ ሲገባ ፤ ስለተሻለች ፥ እንዲያ ... እንድትሆን ፡ ስለምንናፍቃት ፡ ሃገራችን ፡ ኢትዮጵያም ፡ ሁኔታ ፡ ሆነ ፡ ስለቤተክርስቲያን ፡ ሰላም ፡ ግን ፡ እንደ ሁሌው ፡ ሁሉ ፡ ዝም ፡ አንልም ፤ ልንልም አንችልም ፤ እንናገራለን ፤ እንሠራለንም ።

Anonymous said...

Thank you man
we should do something about our church and let as stop double agent preachers and bishops from destroying the foundation of the orthodox church. enough is enough!!!

Anonymous said...

wounderful comment , it touches my heart ...in other words u said what was bugging my head for long time ,but u should allow this article to be distributed freely.Since this article meant to teach our ppl let it go around teach ppl freely

Anonymous said...

Unite and Fight woyane!

Anonymous said...

Unite and Fight woyane!

Anonymous said...

Let`s Unite and Fight woyane!

Anonymous said...

Wel-Said Anjete Kibe Teta , I wish this could be on media(radio and talk shows )

Dil leEthiopia Behereaw budin!!!!

Anonymous said...

dear efrem eshete if you really honest..visit websites and tubes like(nitroethiopian,ethiopian review) their message is always...tigrayans are not ethiopians,tigray become wealthy in the expense of other ethiopians, tigray ትገንጠል!!!!!!not one time but many times1

Anonymous said...

now finally Dawit Kebede of awrambatimes.com is under attack by some extremists in the diaspora for being tigrian!!!!

Anonymous said...

ወይ ጀግና ሁን አልያ ስምህን ቀይር

ወይ በደንብ ጻፍ ወይ ተወው
ይገባኛል አባ አብርሃምን መውቀስ ይከብድሃል
ምን ይደረግ ላም እሳት ወለደች ነው ነገሩ
ለማንኛውም ተባረክ ከዳንኤል ክስረት ተሻላለህ

Anonymous said...

በእውነቱ ጊዜው በጣም አስጨናቂ ነው፡፡ የህወሃት ጉጅሌ ፍጹም እኩይ ሥውር ዓላማን በቅጡ ለኢትዮጵያውያን ለማስረዳት፤ሕዝቡንም ለማንቃት ሕዝብን የመምራትና የማሳወቅ የማስተባበርም ተፈጥሮአዊ ተሰጥኦ ያላቸው ኢትዮጵያውያን መነሳት የግድ ነው፡፡ ነገ የምንፈራው ጥፋት ዛሬ እያሳሳቀንና በእኔ ምን አገባኝነት ውስጣችን እየመረዘው ከኢትዮጵያዊ ኃላፊነት እያራቀን ነው፡፡ ማዶና ማዶ እየተያዩ የሚደረገው የእርስበርስ መጠላለፍም ሆነ ውይይት ሽምቅ አጥፊያችንን ከአገራችን ገለል እንዲል አያደርገውም፡፡

የሕዝቦችን መድልዎና የጭቆና ቀንበር ለመስበር የታገለው ድርጅት ዛሬ በአገሪቱና በሕዝቦቿ ውስጥ የመጠፋፋት መርዝ እየረጨ ነው፡፡ የጥፋት ስልቱ ብዙ ነው፡፡

1. የትግራይ ሕዝብ ብቸኛው ጠበቃ ነኝ በማለት ታላቅ ሕዝብ ውስጥ መሽጎ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን ማሸበር
ቀዳሚው ስልት ነው
2. ኦሮሞና አማራ ብሔራዊ ጠላቶችን እንዲሆኑ ሌት ተቀን መሥራት ወደር የለውም
3. በአገር ውስጥና በውጪ አገር ጉጅሌዎችንና ሆድ አደሮችን በመመልመል ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በመበጀት
በስለላ መዋቅሩ ዜጎችን ያሸማቅቃል፡፡
4. አሸዋና ሲሚንቶ እየጋገረ በሕንፃ ጋጋታና ግዴታው በሆነ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ስም ሕዝቡን ሥልጣኔንና
ዘመናዊነትን ህወሃት የፈጠረው አድርጎ እንዲቀበል ተፈጥሮአዊ ኀሊናውን ራሱ በሚፈልገው መጠን
በማጥበብ ይጠቀምበታል (brain molding)
5. የፈጠራ ፕሮፓጋንዳዎችን በስፋት በመፍጠር ሆን ብሎ በተለያዩ መንገዶች ያናፍሳል
6. ካድሬዎቹን ከተኩላ በረቀቀ መመሳሰል ከአገር ውስጥ አልፎ በዳያስፖራው በመሰግሰግ ሲፈልግ መረጃ
ይሰበስባል፣ ሐሰትን እንደመረጃ ያሰራጫል፡፡ (ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ፈለሰ ማለት እኮ ለዚሁ ሥራ
ወጣ ማለት መሆኑንም ግምት ውስጥ ማስገባት ያሻል)
7. ቤተክህነቱን ከማይናወጽ ተቋማዊ መሠረቱ በመናድ ድምጥማጡን ለማጥፋት 21ዓመት ሠራ፤ ይኸው ዛሬ
ለማይታረቅ ቅራኔ በማብቃት የኢ.ኦ.ተ.ቤ መጻኢ አቋም እንዲናጋ አድርጎታል፡፡
8. የተቃውሞ ኃይሎችን በማናቆርና መደባዊ ከሆነው አሰላለፍ ይልቅ ወገናዊ እንዲሆኑ በቀመረላቸው ማጥመጃ
በማስኬድ ስጋቱን ያረግበዋል፡፡ (ከ50 በላይ ፓርቲዎች ብሎ ቀልድ ዓይነትን ማለት ነው)
9. ዳያስፖራውን የማጠልሸትና በአገሬው ሕዝብ የልማት ጠላት አድርጎ የማቅረብ ሥራው አዲሱ ስልት ሲሆን
በአቀንቃኞቹ አማካይነት ፌስቡክና ሌሎችም ገጾች ወቀሳቸውን በማቅረብ ረገድ ጉዳዩ ከመንግሥታዊ እይታ
ወጥቶ ተከራካሪዎቹ ዜጎች እንዲመስሉ ለማድረግ እየተሞከረ ነው፡፡

የከፋፍለህ ጨቁነህ ግዛው ስልቱ ከዚህም በላይ በእጥፍና የሚቆጠር ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ግን በዚህ ጉዳይ ላይ በቂ ግንዛቤ ያገኙ አይመስሉም፡፡ ያገኙትም በተባበረ ኃይልና መደማመጥ ሕዝቡን ሲያነቁ፣ ለለውጥም ሲያዘጋጁ አይታይም፡፡ በጋራ ለመሥራት የተስማሙበት ሠነድ ቀለሙ ሳይደርክ ተፍረክርከው ከሚገኙ መሪ ነን ባይ ኃይሎች ደካማነት የተነሳ ሕዝብን የማንቃት ሥራው ቀዝቃዛ ቢሆንም ተዳፈነ እንጂ ፈጽሞ ጠፋ ማለት አይደለም፡፡ ለመሪነት የተመረጡ ጀግኖች ሲወለዱ የዜጎች መንፈስ መታደሱ አይቀርምና ያንን ተስፋ ማድረግ ለጊዜው የተሻለው አማራጭ ነው፡፡

ተፈጥሮአዊ የተሟላ ነጻነትን ያገኘ ብቻ አይደለ የቀመሰ እንኳን ከቶ ዝም ሊል በማይችልበት ምዕራባዊ የመንግሥት አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የሚኖረውን ሕዝብ ዝም በል ብሎ ነገርን ከቶ ምን አመጣው? ያው አምባገነንነት አይደለምን?

Anonymous said...

ዲያስጶራውን ቅዱስም እርኩስም አድርጎ ማቅረብ ተገቢ አይደለም። አንድ አንድ ወገኖች ምንም ዓይነት የተለየ ሃሳብ እንዳይንሸራሸርባት እግር ተወርች በታሠረችው ሃገራች ተቀምጠውና በኢቲቪ ዲስኩር እየደነቆሩረ የተሳለላቸውን ስዕል ብቻ እየተመለከቱ በሃገራቸው በመኖራቸው ብቻ ምሁር/አዋቂ ሊባሉ አይችልም። ከሀገር ውጭ የሚኖረውም ባለበት ሃገር ያለውን ሃሳብን የማንሸራሸር እና የሌላውን አመለካከት የማክበር ሥርዓት ካልተማረ 50 ዓመት በውጭ ሃገር ስለኖረ ብቻ በተነሳው ርዕስ ሁሉ ማብራሪያ መስጠት እንዳለበት የሚያስብ ከሆነ ከመሳቂያነት በላይ ለምንም አይጠቅሙም። ሁለቱም አይነት ስዎች መኖራቸው እሙን ስለሆን በጅምላ መፈረጁ ያስገምታል። በአጠቃላይ የማኅበረሰባችንን ማኅበራዊ ሕይወት በተመለከት ብዙ ልንወያይባቸው የሚገቡ ርዕሶች አሉ። ቀስ በቀስ እያዋዛን መጫወቱ እንጂ ማዶ ለማዶ ሆኖ የነገር ውንጭፍ መወራወሩ ምንም አይጠቅመንም፤ እስቲ መቻቻሉን ይስጥን። በርታ ኤፍሬም።

Anonymous said...

አንድን ሃሳብ ኮት ስታደርግ ምንጩን መጥቀስ ይገባሃል፡፡ “50 ዶላር ልኮ አገር ውስጥ ያለው ወጣት እንዲማገድ ይፈልጋል” ይህን ቃል የተናገሩት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ናቸው፡፡

ብዙ ኢትዮጵያውያን አገር ቤት ያሉ ቤተሰቦቻቸውን መርዳታቸው፣ በተዘዋዋሪ አገሪቷ እንደምትረዳ የታወቀ ነገር ነው፡፡ ነጋሪ አያስፈልገውም፣ ምንም አዲስ ነገር የለውም፡፡

በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን ጥለው በብዛት የተሰደዱት በደርጉ ጊዜ መሆኑ አይካድም፡፡ ኢህአዴግ ኢትዮጵያን በተቆጣጠረበት ጊዜ ብዙ ምሁራን ወደ አገራቸው ተመልሰው እያገለገሉ ያሉ አሉ፡፡ ይሄም አዲስ ነገር የለውም ምክንያቱም አገራቸው ነውና፡፡ ኢትዮጵያም ምርጥ ምርጡን ለዲያስፖራ እስከማለት ደርሳም ነበር፡፡ በስማቸውም አደባባይ ተሰይሞላቸውም ነበር (ዲያስፖራ አደባባይ) መገናኛ አካባቢ፡፡ በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል እንዲሉ እዚህ ማጣፊያው ያጠራቸው ሰካራም ተቃዋሚዎች በፖለቲካ ሲከስሩ ስደታቸውን ወደ ውጭ አገራት አደረጉ ሄደውም አልቀሩ የተቀሩትን ጥሩዎቹን ዲያስፖራዎች በከሉዋቸው፡፡ እስኪ ማን ይሙት አማራ፣ ትግሬ፣ ወላይታ፣ ኦሮሞ ወዘተ በሚል ከዓለማዊው እስከ መንፈሳዊው ያለውን ሁሉ የከፋፈሉት አገር ቤት ያለነው ነን ወይስ በውጭ የሚኖረው ዲያስፖራ? መልስልኝ አደራ? ቢያንስ እዚህ እኛ አገር የትግሬ ቤ/ክ፣ የአማራ ፊልም ቤት፣ ለመናገር የሚቀፍ ክፍፍል የለም አራት ነጥብ

መልካም የሆኑትን፣ ክፉ የማይወጣቸውን ሰዎች፣ እንደ እርጎ ዝንብ እዛም እዛም ድርግም የማይሉትን ጨዋ ኢትዮጵያዊያን ምን እንደሚሏቸውስ ታውቃለህ? የወያኔ ካድሬ፣ ባንዳ፣ አገር አስገንጣይ አጋሜ . . . ወዘተ፡፡ ብቻ ስንቱ ይወራ፡፡ የአባይን ግድብ መዋጮ የሚሰጥ ከተገኘ ወያኔ፣ መልካም ነገር ስለኢትዮጵያ እድገት ስታወራ ከተገኘህ የማርያም ጠላት ነህ ወይም ትግሬ ነህ አልያም ባንዳ ነህ፡፡ ስለዚህ ኤፍሬሜ እስቲ በብሎግህ አንድ ቀን እንኳን ሀቅ፣ እውነት ጻፍና እነዚህን ጉዶች ታዘባቸው፡፡ ኤፍሬም የሚለው ቆንጆ ስምህ ተቀይሮ የወያኔ አሽከር፣ ተላላኪ፣ ጥቅመኛ፣ ባንዳ፣ አጐብዳጅ፣ ካድሬ እንደሚባል አትጠራጠር፡፡

Ewnet said...

I concur with you on the fact that there is a huge political problem in our country nevertheless i strongly disagree with your assertion that ''ከኢኮኖሚው በበለጠ ፖለቲካዊ ጫናው ለብዙው ወገናችን መሰደድ ምክንያት ነው የሚለው የብዙዎች እምነት ነው።''

Anonymous said...

ድያስፖራ ታሟል መድሃኒትm ያስፈልገዋል። የድያስፖራ ሙሁራን ይፅፋሉ ይናገራሉ
ሳቢና መሳጢ የሆኑ ስብሰባዎች ያደርጋሉ። ተናግሮው ፅፎው በመጨረሻ ግን በዘር፤ በሃይማኖት፤ በባህር በር ወዘተ ተውጦው ማውጫ
ቀዳዳ ያጣሉ። በአመለካከት ልዩነት መቻቻል አለበት ለሚባል ነገር ግን ደንታ አይሰጥቱም። ሁሉም ወደ ጥላቻ ይለውጡታል። ፀረ አቶ ልደቱ ያደረጉት *ሰላማዊ* ሰልፍ
እንደምሳሌ ሊጠቀስ ይችላል።በውጭ ያሉት ዌብ ሳይቶች፤ ቻቶች፤ ስብሰባዎች፤ ሰላማዊ ሰልፎች ወዘተ
ከፋፋይ፤ ዘራዊ፤ አጥንት ቆጣሪ ፕሮፖጋንዳዎች የሚያደርጉ ናቸው። በዘር ስድብ ፅህፎች በጠባብና በትምክህት ባጠቃላይ ፀረ ህዝብ
ፕሮፖጋንዳዎች የተሞሉ የበሰበሱ መእከኖች ናቸው።ለምሳሌ ከኤርትራ ከኤርትራ ህዝብ ህዝብ ምን ምን ምንምን ዓይነት ዓይነት ግኑኝነት ግኑኝነት ያስፈልገናል። ያስፈልገናል። ኢትዮጵያዊው ኢትዮጵያዊው ዲያስፖራ ዲያስፖራ እንዴት እንዴት ያየዋል?
የኤርትራ ናሽናሊዝም የፈጠርነው እኛ ነን። ንጉሱና ከንጉሱ የነበሩ መሳፍንት ሙሁራን የኤርትራ ህዝብ በሃይል ይዘው
ሃገሬ ኢትዮጵያ ሲል የነበረው ኤርትራዊው ሳይቀር ደበደቡት ረገጡት ። ራሱ እንዳያስተዳድር በተላኩ ነፍጠኞች እንዲተዳደር
አደረጉት። ንጉሱና ደርጎች እንኳን መገንጠል ለፈለጉ፤ ኤርትራውያን ሆነው ኢትዮጵያ ሀገሬ ሲሉ ለነበሩትም አብረው ገደሉ፤ አንጠለጠሉት፤
አነቁት፤ሰቀሉት። ገጠሮች በእሳት አጋዮት፤ በአውሮፕላን በታንክ በጀብደኝነት ወደ አፈር ለወጡት። ሴቶች ህፃናት ሽመግሌዎች ደካሞች ሳይቀሩ
ገደሉ ፈጁ ረሽኑ። መንግስቱ ሃይለማርያምም በከፋ መልኩ በመቶ እጥፍ ጨምሮ ኤርትራን በእሳት በዳፍኔ አጋያት።
በሰላማዊ ፖሎቲካዊ መንገድ ለመፍታት ፈልገው የነበሩ በደርግ ላይ የነበሩት እንደነ ጀነራል አማን አንዶም ሌሎች ኤርትራውያን
መኮንኖች ረሸን። እሳት በእሳት በመጨመር በራሽያዎች፤ በየመኖች፤ በኩባዎች፤ በምስራቅ ጀርመኖች፤ በሰሜን ኮርያዎች እየተደገፈ 20 ዓመት
በሙሉ ጦርነት አድረጎ የኤርትራ ህዝብ ትግል ልያሸንፍ አልቻለም። ደርግ ተሸነፈ። ደርግ ኤርትራ ብቻ አልተሸነፈም በሰበቡ በባህርዩም ሃገር
ውስጥም ተሰባበረ። ይሀ ሁሉ የደርግ ሠራዊት ተንኮታኮተ። ለምን? ፖሎቲካ የሌለው በጀብደኝነት የተነፋ መንግሥት ስለነበረ ነው።
ከሚገርመው ነገር ግን አሁንም ከ 20 ዓመት በሗላ የኤርትራ ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ፓርቲዎች አሉ? ምን ማለታቸው ነው? ሌላ ቀረቶ
የባህር ፖርት ያስፈልገናል ዽንበራችን ወደዚህ ነው ወደዛ ነው ወዘተ የሚባሉ ጥያቀዎች እየተነሱ ነበሩ አሁንም አሉ። ጥያቄው ለምን
እንደዚህ ዓይነት ጥያቀዎች ተነሱ አደለም? የኤርትራ ህዝብ በደርግና በንጉሱ የእብዶች መጫወቻ ሆኖ በሰበቡ በደሙ ሊሸከመው
የማይችል ናሽናሊዝም ሃገራዊነት አለበት። እኛን አይፈልጉንም። ሊፈልጉን የትውልድ ጊዜ ያስፈልገዋል። ከፖሎቲካ መሪዎቹ ጀምረህ እስከ
ተራ ህዝቡ አመለካከቱ እንደዚህ ነው። በራሳችን ውስጥ መምጣት ያለበትም በኤርትራ በንጉሱና በደርግ በተደረገው ጦርነት የሞተው ኢትዮጵያዊ
ቁጥር ነው። ለምን ይህ ሁሉ ደም ፈሰሰ? ሌላ መፍትሄ ታጥቶ ስለነበረ ነው? አደለም። የፖሎቲካ ስህተት ተደርጎ ወታደራዊነትና ጀብደኝነት ብቻ
ስላሸነፈን ነው።ብዙዎቹም
ሃገራችን እየተመላለሱ ናቸው። ለምን? ሃገራችንን እየወደዱት ነው። ለምን ቢባል ምክንያት አለው። በታሪክ በባህል በደም ከኛ የበለጠ የቅርብ
ዘመድ ሌላ እንደሌላቸው እየተረዳቸው ስለመጣ ነው። እኛም ይህ አጋጣሚ ለስተራተጂ ዝምድናና ለወንድማማኝነት አሰተውለን መጠቀም አለብን። ሃገራችን ለምን ይመላለሳሉ የሚሉ ጠባቦችና ትምክህተኞች ሙሁራንም እኛ ውስጥ አሉን። ስህተትና ጠባብነት ነው። ኤርትራውያንን
እንደወዳጅ ህዝብ ማየት አለብን። ትናንት አብረን የነበርን ህዝብ ነን።
መቀራረቡና መዋደዱ የመወሃሃድ ሂደት መንገድ ነው። ሁሉም ነገር በሃይል አይፈታም። ጀብደኝነት ነው.....