Thursday, April 4, 2013

ድሀ ከሆኑ አይቀርስ - ልክ እንደ አቶ መለስ(ኤፍሬም እሸቴ/PDF)፦ ሰሞኑን በተካሔደው የኢሕአዴግ ጉባዔ ላይ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ያደረጉትና በኢቲቪ የዜና ዕወጃ ላይ የቀረበው ንግግራቸው የማኅበራዊ ድረ ገጾች የመወያያም የመሳሳቂያም የመሳለቂያም ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ነበር። “#SomeoneTellAzebMesfin” በሚል “ሐሽ ታግ/ #Hashtag” (ቅምር-ቃል ልበለው?) በትዊተር ላይ ኢትዮጵያውያን የግል ሐሳባቸውን ሲሰጡበት የቆዩት የወይዘሮዋ ንግግር ያተኮረው በአቶ መለስ ደሞዝና ድህነት ላይ ነበር።

 

ያልሰማ ካለ ንግግራቸውን ቀልበጭ አድርጎ ለማቅረብ፦ “ለቤተሰቤ፣ ለግሌ ሳይል የሞተ፣ አራት ሺህ ይሁን ስድስት ሺህ ብር የወር ደሞዝ በፔይሮል የሚከፈል ብቸኛ የአገር መሪ መለስ ብቻ ነበር። የኢሕአዴግ መዋጮ ተቆርጦ በሚተርፈው ገንዘብ እንተዳደርበታለን” ወይም ተዳድረናል የሚል ነው። ወይዘሮዋ ስለ ድህነታቸው ሲናገሩ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያቸው አይደለም። ከዚህ ቀድሞም ተመሳሳይ ሐሳብ ሲናገሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በየኢንተርኔቱ ላይ ተለጥፎ ተመልክቻለኹ። ለኢትዮጵያውያን ሐሳብ መነሻ የሆነው እንግዲህ በእኔ አባባል “እኛ ድሆች ነን” የሚለው አነጋገራቸው ነው።

 

አቶ መለስ ራሳቸው ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ አበባ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ደሞዛቸው 6400 ብር (360 ዶላር አካባቢ) እንደሆነ ተናግረው ነበር። በርግጥ አቶ መለስ ድሃ ነበሩ ወይስ አልነበሩም ብሎ መከራከር ጉንጭ ማልፋት ካልሆነ በስተቀር ድሃ እንዳልነበሩ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነታ ነው። ምናልባት ድሃ መሆን ማለት የተለየ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር።

 

እንዲያውም አንድ የትዊተር ፀሐፊ የወ/ሮ አዜብን አባባል ከ18ኛው መቶ ክ/ዘመን የፈረንሳይ ልዕልት ቀበጥ አባባል ጋር አመሳስሎባቸዋል። ሜሬ አንቶውኔት (Marie Antoinette) የተሰኘችው ይህች ልዕልት በድህነት ይማቅቅ የነበረው የፈረንሳይ ሕዝብ “የሚበላው ዳቦ አጣ” ስትባል “ለምን ኬክ አይበላም” እንዳለች ይነገራል። የድህነት መመዘኛዋ የሚበላ በማጣትና ባለማጣት ላይ ሳይሆን በምርጫ እና በማማረጥ ላይ ነው። የወ/ሮ አዜብም ንግግር ይህንን ስላቅ እንድናስታውስ ግድ ብሎናል።

 

እውነቱን ለመናገር ድህነት እንዲህ ከሆነ፣ ድሃ መሆን እንደ አቶ መለስ ነበር። በቤተ መንግሥት እየኖሩ፣ አገር ምድሩን እያዘዙ እየናዘዙ፣ በስንትና ስንት ብረት አንጋች እየታጀቡ፣ መሬት እንዳይነካቸው በቀይ ምንጣፍ እየሄዱ፣ ጠዋት የበሉትን ማታ ሳይደግሙ፣ ልጆቻቸውን በእንግሊዝ ት/ቤት ብሎም በውጪ አገር እያስተማሩ፣ ምድራችን ያፈራችውን ምርጥ ልብስ እየለበሱ፣ ጠዋት ማት በቴሌቪዥን እየታዩ … ድህነት እንዲህ ነው።

 

ወይዘሮ አዜብም ድሆች ሆንን፣ ማቀቅን፣ በ6ሺህ ብር ደሞዝ ኖርን ሲሉ የሌላውም ሕዝብ ድህነት ልክ እንደርሳቸው የሆነ ከመሰላቸው ነው ችግር የሚገጥመን። ሌላው ሕዝብ በርግጥም በኑሮ ውድነትና በድህነት እየማቀቀ ነው። ነገር ግን ድህነቱ እርሳቸው ካለባቸው ድህነት ይለያል።

 

ሌላው ሕዝብ ከወር ወር በልቶ የሚደርስበትን ቀለብ መግዣ እያጣ፣ ለልጆቹ ልብስ፣ ለራሱ ነጠላ መግዣ እየተቸገረ፣ ከሰውነት ጎዳና ወጥቶ፣ በቀን ሦስት ጊዜ መብላት ስለማይችል በቀን አንድ ጊዜ (አንዳንዱም በፈረቃ) እየቀመሰ ነው የሚኖረው። በርግጥ ባለቤታቸው አቶ መለስ ስልጣን ላይ እንደወጡ ሕልማቸው (ራዕያቸው) ምን እንደሆነ ሲጠየቁ “የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ሦስት ጊዜ ሲበላ ማየት ነው” እንዳሉት አልሆነም። ይባስ ብሎ ድሮ የነበረችውንም አጥቷል።

 

ያለፈ ሥርዓት ናፋቂ እንዳይሉኝ እንጂ ባለፉት ጊዜያት “ጤፍ ተወደደ” ሲባል የሚገባን “ጤፍ የማይበሉ ሕዝቦች ጤፍ መብላት በመጀመራቸው” ሳይሆን በርግጥም የእህል ችግር ስለነበር ነው። ጤፍ ባይበላ ስንዴውና ገብሱ፣ ሲቸግርም የፉርኖ ዱቄት እንጀራ አይጠፋም። ጎመንንና ቆሎን የመሳሰሉም ቢሆኑ ያጣ የነጣውም ቢሆን የማያጣቸው ነገሮች ነበሩ። የአሁኑ ድህነት ግን ቤት ዘግቶ የሚያስለቅስ፣ ወደ አደባባይ ወጥቶ ለመለመን የሚያስቸግር የእግር ውስጥ እሳት ነው።

 

በፌስቡክ አጫጭር ጽሑፎቿ የማውቃት ሕይወት እምሻው የተባለች አንዲት ፌስቡከኛ/ጦማሪት ከሰሞኑ ታክሲ ላይ የገጠማትን አንድ ገጠመኝ አንጀት በሚበላ አካኋን አስፍራው አንብቤያለኹ። ገጠመኟ ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ ጋር ስለሚሔድ ልጥቀሰው። ነገሩ ሥራ ስለረፈደባት አንዲት የመንግሥት ሠራተኛ የሚያትት ነው። ልጅቱ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀች፣ በኤክስፐርትነት ተቀጥራ የምትሠራ፣ ደሞዟ ከምንም ከምንም ተቆራርጦ 865 ብር እጇ ላይ እንደሚገባ ትጠቅሳለች። እንደርሷ ዓይነት ብዙ ሰዎችን እንደምታውቅ ትነግረናለች - ሕይወት። አንጀት የሚበላው ነገር ደግሞ እንዲህ ይላል፦


“እጄ ላይ የሚገባው ደሞዝ 865 ብር ነው፡፡ ፡፡ የቤት ኪራዬ 300፡፡ ለዛውም ከከተማ የትናየት፡፡ አስፋልት ለመድረስ 30 ደቂቃ በእግሬ ኳትኜ፡፡ ክፍለ ሃገር ላሉት እናትና አባቴ ካለዚያ መኖር ስለማይችሉ በወር 150 ብር እልካለሁ፡፡ የሚተርፈኝ 400 ምናምን ብር፡፡ መብላት አለብኝ፡፡ መልበስ አለብኝ፡፡ ትራንስፖርቱ እንደምታይው ነው፡፡ በታክሲ መሄድ ከተውኩማ ቆይቼ ነበር ሰሞኑን ግን ብዙ ግዜ ስላረፈድኩ አውቶብስ ለመጠበቅ ፈራሁ፡፡ ከሁለት መት ወዲህ ምግብ እንኳን በቱ መብላት አልችልም፡፡ አይገርምሽም…? ምግብ መብላት አልችልም! ከዩኒቨርስቲ በዲግሪ ተመርቄ ሌላው ቢቀር መራብ አለብኝ?!” ድህነት እንዲህ ነው - ወ/ሮ አዜብ።

ድሮ የምናውቀው ድህነት ሥራ የሌለውን፣ ምንም ገቢ የማያገኘውን፣ ጉልበትና ዕውቀት ያጣውን የሚያጠቃ የአገር በሽታ ነበር። የዘመናችን ድህነት ግን ሰው ሥራ ኖረው አልኖረው፣ ዕውቀት ኖረው አልኖረው፣ ዲግሪ ተሸከመ አልተሸከም፣ ኮሌጅ በጠሰ አልበጠሰ የማይለቅ ነው። ኮሌጅ መግባትና መማር፣ ሥራ መያዝ በድሮው ጊዜ ራስን ለቻለ ኑሮ አስተማማኝ ነበር። ዛሬ ጊዜ ግን ከቤተሰብ አንድ ሰው ብቻ ሠርቶ ሳይሆን ባልም ሚስትም ደህና ገንዘብ እያገኙ የኑሮን ቀንበር ለመሸከም የሚንገታገቱበት ዘመን ላይ ነን። ድህነት ማለት ይኼ ነው ወ/ሮ አዜብ።

 

ምናልባት ይህንን ጽሑፍ የሚያነብ አንዳንድ ቅንጡ በቃ ይኼ ሁሉ ስለ ወ/ሮ አዜብ መናገር ምን ያስፈልጋል፣ እርሳቸው የተናገሩት ሦስት ደቂቃ፣ እናንተ የምታላዝኑት 30 ሰዓት ሊል ይችላል። እኔ ግን በርሳቸው አባባል ውስጥ የፓርቲያቸውን አካሔድ፣ አቋም፣ መሪ ተብለው ሥልጣኑን የተቆናጠጡት ሰዎች ከሕዝቡ የቀን ተቀን ኑሮ ምን ያህል የራቁ ሰዎች እንደሆኑ የምረዳበት ስለሆነ ብዙ ብዙ ሊባልበት እንደሚገባ ነው የሚሰማኝ። አገራችን “ለምን ኬክ አይበሉም” የሚሉ የቅርብ ጊዜ ቀዳማይት እመቤት ነው ያሏት ማለት ነው።

 

ምናልባትም ወ/ሮ አዜብን በተመለከተ ውይይቱ መቀጠል ያለበት የአዲስ አበባ ቀጣይ ከንቲባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ከግምት በላይ እርግጠኝነት በመስፈኑም ነው። እንደ ፓርቲው አሠራር የፈለገውን ሐሳብ በሕዝብ አስተያት ምክንያት የሚለውጥ እንዳለመሆኑ አዜብም ከንቲባነታቸው ሳይታለም የተፈታ ይመስላል። ድህነትን በዚህ ደረጃ የሚመለከት ሰው እንዴት የድሀው ሕዝብ ከንቲባ ሊሆን ይችላል? ከንቲባዎች የግድ ድሆች መሆን የለባቸውም። ነገር ግን ድህነትን እና ሀብታምነትን የሚለዩ መሆን ግን ይጠበቅባቸዋል። ሕዝባቸውን ካላወቁት ምኑን ሊያስተዳድሩት ይችላሉ?

 

ወደ ሕዝብ ባለመቅረብና በቤተ መንግሥት ቤተ መንግሥታዊ ኑሮን በመኖር መለስን የሚስተካከላቸው አልነበረም። በሞታቸው ጊዜ ከየቪዲዮ ካዝናው እየወጣ ለማስተባበል እንደተሞከረው አልነበረም። የቦሌ መንገዶች ይመሰክራሉ። አካላቸው ከሕዝቡ እንደመራቁ ስለ ሕዝቡ እና ስለ ድህነቱ ያላቸው አስተያየት እንደሚስታቸው እንዳልነበረ ግን ቢያንስ ከንግግራቸው እንረዳለን።

 

ከኢሕአዲጎቹ ወደ ሕዝቡ በመቅረብ አቶ አርከብ የተሻሉ እንደነበሩ ብዙዎች ይናገራሉ። ወደ ሕዝቡ የዕለት ተዕለት ኑሮ ለመዝለቅ የደፈሩ ነበሩ። ሕዝቡም ለዚህ ቀረቤታ የአክብሮት ምላሹን ሰጥቷቸዋል። ፓርቲው ወደ ሕዝቡ መቅረብ ከፈለገ እንዲህ ዓይነት ሰዎችን ወይም እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ ያላቸውን መጠቀሙ ይበጀው ነበር። ከንቲባነትን ከአርከበ ወደ አዜብ ማውረድ ግን በሕዝብ ዕንባ መቀለድ ነው። ምናልባትም ለዚህ ዓይነቱ መራራ ቀልድ ፓርቲውም ዋጋ የሚከፍልበት ይመስለኛል።

 

ድሆች ባትሆኑም ድህነታችንን ብትረዱልን እንዴት ግሩም ነበር።

 

ይቆየን - ያቆየን

 


(ይህ ጽሑፍ አዲስ አበባ በሚታተመው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው።)

14 comments:

Anonymous said...

ኤፍሬም እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡ የልጅቷን ታሪክ /የኤክስፐርቷን/ ታሪክ እኔም እንባየ እየፈሰሰ አንብቤዋለሁ፡፡ የራሴ ታሪክ ግልባጭ ነው የመሰለኝ፡፡ በእርግጥም ከሁለት አመት በኋላ ታሪክን የሚለውጥ ጌታ ታሪኬን ለወጠው እና ቢያንስ ለምበላው ነገር አልጨነቅም/አይርበኝም/፡፡ በጣም ብዙ ጊዜ እጄን ወደ ላይ ዘርግቸ ቤቴን ዘግቸ “ጌታ ሆይ ቢያንስ ለምን ይርበኛል? ራበኝ እኮ” እያልኩ ከፈጣሪ ጋር ሙግት ቀረሽ ልመና አቀርብ ነበር፡፡ የዚህ አይነት ታሪክ ያላቸው ሚሊዮኖች ናቸው፡፡
ታዲያ መሪዎቻችን በዚህ እንባ እና ምሬት ላይ ነው እየቀለዱ ያሉት፡፡ እውነት ግን እስከ መቸ ነው ? ምንም ማድረግ ባይችሉ/ባይፈልጉ እንኳን ለምን ችግራችን አይገባቸውም ?

Anonymous said...

Thank you Deacon Efrem for your wonderful view as usual. You are one in a million. Keep up your good work. May God bless you with more wisdom. Amen!

Anonymous said...

D/n Efrem:

From what I see from your recent articles, I think you are heading the right direction, as opposed to most of our contemporary EOTC church scholars, whose primary target is becoming to keep the status quo.

keep the good work!

Anonymous said...

gin 6000 birr demoz yalew sew deha aybalm :)

Anonymous said...

ኢትዮጵያ እኮ መሪ ካጣች ብዙ ዘመናት ተቆጠሩ!!! ችግሩ ግን ይህን ያወቀልን ማናም የለም!!! እንደአለመታደል ሆኖ የሚሾሙትም አላማቸዉ ህዝብን ለማገልገል ሳይሆን አጋጣሚዉን በመጠቀም የሀገርን ሀብት ለመዝረፍ ነዉ፡፡ የሚበሉትን ያክል እንኩዋ ቢዘርፉ ምን ነበረበት??? ሀገር ዉስጥስ ቢሰሩበት ምን ነበረበት??? የህዝብን ገንዘብ እየዘረፉ የሌላ ሀገር ማሳደጊያ ማድረግስ የጤነኛ ሰዉ ስራ ነዉን??? እኔ ግን መሪወቻችን ኢትዮጵያዉያን ስለመሆናቸዉ በጣም እጠራጠራለሁ!!! ይህ ካልሆነ ታዲያ ሰዉ እንዴት በዎገኑ ላይ የህንን ያክል ደባ ይሰራል??? ሌላዉ እንኩዋ ቢቀር ፈጣሪ እደሚያያቸዉ ልብ አለማለታቸዉ ምን ያህል ቢታወሩ ነዉ???

Anonymous said...

I THINK YE WEYZERO AZEB NEGEGER,MELES KE MUSENA YETSEDA ENDENEBER LEMENAGER YEMESELEGHAL,YEHENEN DEGEMO BEZUWOCH YEMESEKERALU!!DN EPHREM PLEASE BE FAIR!!

Anonymous said...

selam Ephrem what u saying is none sense ,you know what she is trying to say!let be honest !YE ZEWAYUNE ADERA TETEH WEDE BELATEW YETEMELESK TEMESELALEH!!!!!!!!

Anonymous said...

Ephrem Your article it doesn't seem fair or just.

God Bless !

አግናቲዎስ ዘጋስጫ said...

ካደጉበት ስፍራ ከወንዝ ከቀያቸው
ተሰደው.....ተባረው ግፍ የበዛባቸው
እኒህ አማራዎች የትነው ሀገራቸው?
በሰሜን በደቡብ በምስራቅ በምዕራብ
በሁሉም አቅጣጫ መኖር ያለገደብ
መብቱ መሆኑ የእያንዳንዱ ዜጋ
በታሪክ አፍራሾች ምነው ተዘነጋ
ኧረ ያገር ያለህ አረ በባንድራው
እንድ ይባል ወያኔ ምንአልባት ቢገባው

4/9/13
አግናቲዎስ ዘጋስጫ

Anonymous said...

Absolutely genuine and unbiased reflection! Please Keep it up.

Anonymous said...

Poor or Not

http://www.therichest.org/celebnetworth/category/politician/minister/

Anonymous said...

Dear 'Diakon' Efrem,
As a 'diakon' you should be fair enough and remember one of the 10 commandments, 'You shall not bear false witness against your neighbor'.
You do not know about the wealth of Meles, of course most of the people do not know. So how could you say that he is wealthy. One thing we should agree that is the measurement of wealthy differs from person to person. But as Christian, and 'diakon', be fair and trust full.

Anonymous said...

You know what our leaders are?really the main theft body within the country because they seems to be poor external but the are rich internal.
we do not hear you Azeb Mesfin Leba(ladies)kemagna.
you and your idiot parlamintary EPDDRF authorities,kebele leaders ,cadrie(Dog of Azeb)
teaches US your Hasband Melese has no money as civil person where is the money you take and theft from the Ethiopian peoples that collacted by your kebele leaders and your caderi.
Eprdf killing the youth generation you know what your bulshit rules do in ethiopia ok?
think of that not think for poverty and others rather than work.
you know websites that shows Melese and his status at swiss bank.
LOOK THIS Web Site Address and guess what Melse and his work was before____?
Look This Web site:
http://www.celebritynetworth.com/list/top-50-richest-politicians/

Anonymous said...

Thank you for your article. I read it carefully but I doubt if i'm reading the exact opposite end of what W/ro Azeb was talking about. For me your biased or immature response doesn't make w/ro Azeb's immature speech wrong both of you lack credible sources that we can judge on. Both of you only reflect what is in your mind without evidence. When i wasted my time reading your article I was looking for evidence, justification, analysis instead of just hatred to blame people. Sorry if i'm being impolite, but i thought its good if we criticize one another b.c that is how we can improve. For example from your text

አቶ መለስ ራሳቸው ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ አበባ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ደሞዛቸው 6400 ብር (360 ዶላር አካባቢ) እንደሆነ ተናግረው ነበር። በርግጥ አቶ መለስ ድሃ ነበሩ ወይስ አልነበሩም ብሎ መከራከር ጉንጭ ማልፋት ካልሆነ በስተቀር ድሃ እንዳልነበሩ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው እውነታ ነው። ምናልባት ድሃ መሆን ማለት የተለየ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር።

Here instead of concluding on your own, i would have expected the criteria what it means being poor. Level of poorness is very wide because it all depends on our needs. Someone who doesn't have a car, might consider this as a sign of poorness because its subjective.

Additionally, you mentioned some characteristics which are very weird for me to consider this as a sign of richness instead of a sign of role (as a prime minister) that you play in your work.

እውነቱን ለመናገር ድህነት እንዲህ ከሆነ፣ ድሃ መሆን እንደ አቶ መለስ ነበር። በቤተ መንግሥት እየኖሩ፣ አገር ምድሩን እያዘዙ እየናዘዙ፣ በስንትና ስንት ብረት አንጋች እየታጀቡ፣ መሬት እንዳይነካቸው በቀይ ምንጣፍ እየሄዱ፣ ጠዋት የበሉትን ማታ ሳይደግሙ፣ ልጆቻቸውን በእንግሊዝ ት/ቤት ብሎም በውጪ አገር እያስተማሩ፣ ምድራችን ያፈራችውን ምርጥ ልብስ እየለበሱ፣ ጠዋት ማት በቴሌቪዥን እየታዩ … ድህነት እንዲህ ነው።

In any country having a degree from university doesn't mean you can get a job and live happily, please try to learn from other countries how they are living. I can imagine you are reflecting our old tradition, but that time we didn't have many scholars from university that is why every one with degree had a better life. Yesterday may not be same as today and tomorrow, which is the reality of life. I personally advice you to support your ideas with justifications NOT what it seems okay for you only, otherwise you will loose your audience.

As a conclusion, your article might give sense if you could provide me information about their property or ownership of items that you can give as an evidence. Consider your articulation as if its presented to a court, where you will be fined for accusing someone without evidence.

Finally, I have respect to the church and I wished if you keep honesty as you mention about your cleric duty. You are ordained to serve the truth what the church teaches but not to spread your personal conclusions with no evidence.

Thank you for your article.