Thursday, September 12, 2013

ኤርትራን በአቋራጭ

(PDF):- በሰሜን ምዕራቧ የአሜሪካ ከተማ በሲያትል ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን የሚርመሰመሱበት አንድ ሰፈር አለ። ንግድ ቤቶቹ፣ ጋራዦቹ፣ ሬስቶራንቶቹ እና እዚያ አካባቢ የሚቆሙት መኪናዎች አብዛኛው የኛ ሰዎች ንብረት ናቸው። ከመንገዱ አንዱ ኮርነር ላይ “ስታርባክስ” ቡናመጠጫ ደረቱን ሰጥቶ መንገዱን ቁልቁል ይመለከታል። ወደ ውስጥ ሲገባ አንዱ ጥግ “የኢትዮጵያውያን ጥግ” ነው፤ ሌላው ደግሞ “የኤርትራውያን ጥግ”። አንድ ኢትዮጵያዊ ሲገባ እግሩ የሚመራው ወደራሱ አገር ጥግ ነው። መቀመጫ ባይኖርና በኤርትራው ጥግ በኩል ባዶ ቦታ ቢገኝ፣ ወደዚያ ለመሔድ አይሞክርም። ድንበር አይሻገርም። አንድ ኤርትራዊም እንዲሁ ወንበር ቢሞላበት ወደ ኢትዮጵያው ጥግ ለመሔድ አይሞክርም። ይህንን የሚነግረኝ ወዳጄ እየሳቀ ነው። ስታርባክሱ የባድመ ግንባር (ጦርነት የሌለበት፣ ነገር ግን ወታደሮቹ የተፋጠጡበት) አሊያም የአሰብ ቡሬ ግንባር መሰለኝ። ለመግባት አልፈለግኹም።

ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን በየሄዱበት ድንበርተኛ ሆነው መኖር ይፈልጋሉ ልበል? የተለያየን አገሮች ነን ብለው እንደሚለፍፉት ሳይሆን ተለያይተውና ተቆራርጠው ለመኖር አይፈልጉም።  ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ። የሚገርመው ግን ድንበርተኛ መሆን ሲፈልጉ ባድመ ግንባርንም አብረው እየገነቡ ነው። ጦራቸውን ሰድረው። የአበባ መስክ ያለበት ድንበር አይመቻቸውም - ሁለቱም። “አብረው ለመኖር የማይችሉ፣ ተለያይተው ለመኖርም የማይችሉ” የተባለው ለእነርሱ ሳይሆን አይቀርም። ይህንን የሚያፈርስ ገጠመኝ ያገኘኹት ደግሞ ከሰሞኑ ወደ ሰሜን ካሊፎርኒያ ጠቅላይ ግዛት ሳን-ሖዜ ከተማ በሔድኩበት ወቅት ነውና ገጠመኙን በደስታ (ከልቤ ደስስስስ እያለኝ) ላጫውታችሁ።

በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ስብብሰቦች አሉ። ከሰፈር ልጅና ዕድር ጉባኤ እስከ ሃይማኖትና ፖለቲካ፣ ከብሔረሰብ ስብስብ እስከ ስፖርት ቡድኖች ድረስ። ከነዚህ ውስጥ በአሜሪካ የሚገኙ ወጣቶች ያቋቋሙትና ባለፈው ሳምንት 13ኛ ዓመቱን ያከበረው “የሰሜን አሜሪካ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ” አንዱ ነው። ከመላው አገሪቱ የሚሰባሰቡ ወጣቶች የሚካፈሉበት የሦስት ቀናት ኮንፈረንስ አካሂዷል።

ዝግጅቱን ያዘጋጁት በሳንሆዜ እና በአካባቢው የሚገኙ ወጣቶች እና እነርሱ የሚያገለግሉባቸው አብያተ ክርስቲያናት ናቸው። ኋላ ግን እንደሰማኹት ዝግጅቱን አብረው ያከናወኑት ከሳንሆዜ ወጣ ብለው ከሚገኙት ከተሞች (ለምሳሌ ከኦክላንድ) የመጡ ኤርትራውያን ወጣቶች ጭምር መሆናቸውን ተረዳኹ። ለካስ አለማወቄ ነው እንጂ እዚያው አብረውኝ ከሚውሉት መካከል አንዳንዶቹ ኤርትራውያን ነበሩ። አንዱ ወጣት መልከ መልካም ልጅ ራሱን አስተዋውቆ እስኪነግረኝ ድረስ አላወቅኹም ነበር።

አማርኛው ለክፉ አይሰጥም። በእጁ የያዘው መጽሐፍ የአማርኛ ነው።
“የት ለመድክ አማርኛ” አልኩት።
“እዚሁ ነው የለመድኩ”።
“ስንት ጊዜ ፈጀብህ?”
“አንድ ስድስቲ ምናምን ወር ይሆናል”።

ዲያቆን ነው። የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ይማር ነበረው ከአንድ ኢትዮጵያዊ መሪጌታ ኖሯል። እሳቸውን ሁል ጊዜ “ደህና ነሽ” ይላቸው እንደነበር “ነሽ ለሴት፣ ነህ ለወንድ” እያሉ እንደሚያርሙት እየሳቀ ነገረኝ። ገና ለጋ ወጣት። 19 ዓመቱ ነው። በዚህ ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ትምህርቱን ተከታትሏል። ወደ ሁለተኛው ተሸጋግሯል። በዕድሜ እኩያ ከሚሆኑት ኢትዮጵያውያኑ ጋር ቶሎ ተላምዷል። ወጣት አይደል?

ሌላው ወጣት ወደ ሃያዎቹ አጋማሽ ነው። እዚሁ አሜሪካ ያደገ ሳይሆን የስደትን መከራ ቀምሶ የመጣ ስክን ያለ ልጅ ነው። እንደ ሌሎቹ ስደተኛ ወገኖቹ በሱዳንና የመን አልተጓዘም። በከባዱ የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር አልፎ ኢትዮጵያ በሰላም ለመግባት የቻለ “ዕድለኛ ልጅ”። ቃሉን ተውሼ እንጂ “ዕድለኛ ልጅ” ያለው ራሱ ነው። አማርኛ ጥሩ አድርጎ ይናገራል። “መጻፍ ነው ችግሬ”  ብሎኛል። ታሪኩ ደግሞ ልብ ይነካል።

ወጣቱ ብሔራዊ ውትድርናውን ጨርሷል። ከአንዱ የጦር ግንባር ወደ ሌላው ጦር ግንባር ሲዟዟር አሳልፏል። ጦርነት ባይኖርም። “ዓይንህን ለአፍታ እንኳን ከምሽጉ እንድትነቅል አይፈቀድም” ብሎኛል። “አንድ ቦታ አያስቆዩንም። መቀያየር ነው። አንዴ ቡሬ፣ አንድ ባድመ፣ አንዴ ….”። ከዚያ ሲመርረው አገሩን ጥሎ ለመሰደድ ወሰነ።

“አገሩ ውስጥ ወጣት የሚባል የለም’ኮ። አንድ ልጅ 16፤ 17፣ 18 ዓመት ከሆነ የሚያስበው መጥፋት ነው። አባት ከሆንክ ግን የት ትሔዳለህ። መማረር ብቻ። ሰዉ አይናገርም። ዝ…..ም ብቻ”። (‘ም’ን ላላ አድርጎ እየጠራት።)

ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ሽሬ አካባቢ ወደሚገኝ የስደተኞች ካምፕ እንዲገባ ተደረገ። እርሱ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ብዙ የአገሩ ሰዎች ጋር። ለአራት ዓመታት ኖረ።

“ምን ታደርግ ነበር?” ጠየቁት።
“ለእኔ ስኮላርሺፕ ማለት ነበር። አማርኛ ተማርኩ። መጻሕፍት ማንበብ ቻልኩ። የሚገርምህ ወደ አሜሪካ ስመጣ ሻንጣዬ 50ኪሎ ይመዝናል። 48ቱ ኪሎ መጽሐፍ ነው።”
“ሌሎቹስ ጓደኞችህ ምን ይሠሩ ነበር?”
“ሌሎቹም ዝም ብለው አልተቀመጡም። ቅኔ፣ ዜማ፣ መጻሕፍት ለመማር ወደ ጎጃም፣ ወደ ጎንደር፣ ወደ ሸዋ ሄዱ።”
“ኢትዮጵያ መጥተህ አታውቅም አይደል ከዚያ በፊት?”
“አላውቅም። ናጽነት ከመጣ በኋላ ደግሞ ችግር ሆነ። ኢትዮጵያ ማለት ሰይጣን ማለት ነበር የሚመስለኝ።”

ገታ አደረገና አንገቱን ነቀነቀ። እኔም “ለምን እንደዛ አሰብክ ምናምን” ወደሚል ጥያቄ ውስጥ መግባት አልፈለግኹም። ከሚናገረው ይልቅ በአካላዊ እንቅስቃሴው የሚያሳየው ብዙ ይናገር ነበር።

ወጋችንን ሳናጠናቅቅ የራት ሰዓት ደረሰና ወደ ማዕዱ ታደምን። ቀስ በቀስ ጠረጴዛችን ሞላች። ሁሉም ኤርትራውያን ናቸው። ወንዶችም ሴቶችም። ገና ወጣቶች። ሁሉም አማርኛ ይሰማሉ፣ ይናገራሉ። የተማሩት ግን በቅርብ ነው። አንዲቱ ልጅ ብቻ ገና አማርኛ አልተማረችም። አንዱ ኢትዮጵያዊ እየሳቀ “ጆሮሽን ቢቆርጡሽ አትሰሚም ማለት ነው?” አላት። ሌሎቹ የአገሯ ልጆች ሳቁ። ትርጉሙ ሲነገራት እሷም ሳቀች። የዛሬ ዓመት እሷም አማርኛ የምትችል ይመስለኛል።

“አማርኛ መማር ይሄን ያህል ቀላል ነው ማለት ነው?” አልኳቸው። አዎንታዊ መልስ አገኘኹ። በውስጤ “ለምን ትግርኛ አልተማርኩም ነበር? የመማር ዕድል ነበረኝ? ልማረው የምችለው ሌላ የአገራችን ቋንቋ  ነበር?” እያልኩ አሰላሰልኩ።

“አስመራ፤ ቤት ሙዚቃ ውስጥ አማርኛ ዘፈን እኮ መክፈት አይቻልም” አለኝ ቅድም ታሪኩን ያጫወተኝ ልጅ። ለካስ ክልከላው ጠንከር ያለ ኖሯል። ግን አልሰራም። ወጣቶቹ የፖለቲካ ድንበርን በፍቅር እየተሻገሩት ነው። ለብዙ ዘመናት ሲዘራ የነበረው የጥላቻ ዘር በጥቂት ግንኙነቶች ሲመክን ማየት እጅግ ያስደስታል። ወጣቱ በትግራይ ስላጋጠመው መልካም ነገር ሁሉ ተናግሮ አይበቃውም።

“አዲስ አበባ የቆየኹት አንድ ሳምንት ብቻ ነው። አሜሪካ ልመጣ ስል።” . . . ትንሽ ቆየት ብሎ ቢያየው ተመኘኹ። አዲስ አበባ የብሔረሰቦች ሁሉ መናኸሪያ፣ የኢትዮጵያዊነት ናሙና ማሳያ። ክትፎውን ቢበላ፣ ጠጁን ቢጠጣ፣ ከወያላው ጋር ቢላከፍ፣ ቆጮውን ቢሞክር፣ ቡላውን፣ ጨጨብሳውን፣ ዶሮ ወጡን …። “አብሮ የበላን ቅዱስ ዮሐንስ አይሽረውም” ይሉ የለ አባቶቻችን?

የሄድንበት ኮንፍረንስ እሑድ ማታ ሲጠናቀቅ ከሲያትል በመጡ ወጣቶች እና በሳንሆዜ አካባቢ በሚገኙበት መካከል ትልቅ የጨረታ ፉክክር ተጀምሮ ነበር። የሳንሆዜዎቹ ቁጥራቸው አነስተኛ በመሆኑ ውድድሩ ሲከብዳቸው ኤርትራውያኑ ወጣቶች ያግዟቸው ጀመር። በዚያ ውስጥ የምመለከተው የተለያዩና ለጦርነት የሚፈላለጉ ድንበርተኛ አገሮች ሳይሆን ወጣትነትና ፍቅር ያስተሳሰራቸው ፍጡራንን ነበር። ጠቢቡ ሰሎሞን እንዳለው ሆነ፤ “የጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል።” (መጽሐፈ ምሳሌ 15፥17)

ይቆየን - ያቆየን

15 comments:

Anonymous said...

GERUME NEWE DN EPHERME
TSEHUFEHEN LERJEM GEZE SETBEKE NEBRE. ENKANE DEHENA NMETAHELENE.

Anonymous said...

Indeed. we have a great time Deacon.

Getnet Mesfin said...

Well Come!
Really Amazing Conference!

Anonymous said...

bakih ketayun atakoyew!!!!!!!

Addis Bezuwork said...

Betam girum tsihufe,Egziabher yestilen selakefelken.

yidnek said...

“የጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል።” (መጽሐፈ ምሳሌ 15፥17)

Anonymous said...

ሰላም ላንተ ይሁን ዲያቆን ኤፍሬም። በመጀመሪያ እግዚአብሔር እንደዚህ ጹሁፍ ለመጻፍ እኛንም ለማስተማር ጸጋ ስለሰጠህ ክብር ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን። እኔ ያንተን ብሎግ ከሚከታተሉ አንዱ ነኝ። ስለ ባለፈው ሳምንት የነበረው ጉባኤ ያወጣኸው ጽሑፍ መግብያው ላይ የጻፍከው እጅግ የሚያድስትና ፍቅርን የሚያጸና ሆኖ ሳለ .... ማህከል ላይ እና ወደ መጨረሻ ላይ የጻፍከው ከመንፈሳዊነት ወጣ ያለ ሆኖ ኣግኝቸዋለው። ስለዚህ በሚቀጥለው ጽሁፍህ መንፈሳዊነቱን ሳይለቅ ቢሆን የተሻለ ይመስለኛል።.. ይቆየን

Alem said...

ebakihin wendim gashe! . . . esti cherisew?

Anonymous said...

ERitrea beakorach weys Eritreawian beakorach

ኤርትራ ወይስ ኤርትራዊያን

Anonymous said...

Oh! after long time. Have you been in 'kerchele'?

Anonymous said...

ኤፍሬም ይሄn አጉል ...ርህራሄህን ተወው!.. ለመሆኑ ኤርትራውያን ኢትዮጵያውያን ላይ ምን እንዳደረጉ እና ምን ለማድረግ እንደሚስቡ ታውቅ ይሆን..አንድ ምሳሌ ልጥቅስልህ--ቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት በኤርትራ ምድር ለ30 ዓመታት የዘለቀ ጦርነት አካሂደዋል፡፡ በዚህም ከሁሉም ወገን እስከ 300 ሺሕ ሲቪልና ወታደሮች እንደሞቱ ይህንኑ ያህል እንደቆስሉ ይገመታል፡፡ አገር ከድህነት ሊያወጣ የሚችል ትልቅ ሀብትም በጦርነት አረር ወድሟል፡፡ በዚህ ውጊያ ጦርነት ነውና ስለገደላቸው ተዋጊዎች ሊወቀሱ አይችልም፡፡ ነገር ግን ከዓለም የጦር ሕግና የምርኮኛ አያያዝ ግዴታ ውጭ በሆነ አኳኋን በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው በደል ታሪክ የሚረሳው አይደለም፡፡

በምፅዋ፣ በከረንና በደቀመሐሪ አካባቢ የተማረኩ ወታደሮችን ጎዳና ላይ አስተኝቶ በታንክ ፈጭቷቸዋል፡፡ (‹‹የኤርትራ መዘዝ››፣ ‹‹የምሥራቅና ሰሜን የጦር ሜዳ ውሎ›› እና ‹‹ቅስም የሰበረ ዕርምጃ››)... በሱዳን ድንበር አካባቢ ትጥቅ ፈትተው በበረሃ ስደት ላይ የነበሩ ከአምስት ሺሕ የማያንሱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮችን በእሩምታ ተኩስ ረሽኗል፡፡ በእስር ቤት ይዞ ለዓመታት መንገድና ምሽግ ሲያስቆፍራቸው የነበሩ፣ ሀብታቸውን ወርሶ (የጥርስ ወርቅ ሳይቀር) አውጥቶታል...አሁንሳ ተቃዋሚዎቹሳ...የባሱ ናቼው...I too was a product of my upbringing who did not feign any qualms of expressing hatred towards the Amara. Like my generation, I hated everything Amara, and took pride in not being able to speak their language. I still don’t speak Amharic, but as I got older and hopefully wiser, I am neither proud nor ashamed of it— just neutral. The song encapsulates our burning desire to avenge the wrongs committed against our people by the Amara. In all honesty, I didn’t even know the Amara look like us till I came to Khartoum, Sudan; I thought they all looked like Menghistu Hailemariam....http://awate.com/in-support-of-ato-kidane-alemayehus-initiative/ ...

Anonymous said...

...እናንተ አጉል ቢደርስባችሁ ይቅር የማትሉትን ሃጥያት የፈጸሙብንን ሰዎች እንደ አኩራፊ ወንድማማቾች አይነት ጸብ አርገህ አታቅለው!ከላይ ለጻፍከው ይሄ በቂ መልስ ይመስለኛል http://awate.com/seyoum-haregots-new-book-a-critique/...in comment section Semere Habtemariam on May 25, 2013 at 12:29 pm said: i’m indeed intrigued (believe whatever you want) by the impact of Amharization. I know people some (amiches) who have been in the US for more than 20 years and still speak Amharic when they fully know most of the Eritreans with them don’t know or speak Amharic. I even know some Eritreans who have invested a great deal to learn Amharic in order to fit in with these group and their Ethiopian circles. As someone who grew up in the struggle and in the Sudan, this was totally a culture shock to me. I could not believe an Eritrean who didn’t have cultural and linguistic pride, the very things that ignited our revolution.
Eritreans were not immune to Amharization; some have purposefully and intentionally adopted everything Amara. Imagine the late Seyoum, who didn’t speak Amharic in 1957, acting more Amara than the Amara, more Ethiopian than the Ethiopians. Imagine a decade before, the likes of Wel Wel were saying, “iziom Amhara, ashunkuay kgez’ikas ktgez’om uka zeyebhugu.”Indeed, I’m very intrigued why Tigrinya speaking Eritreans in Ethiopia did not ethnically identify with their Tegaru brothers. I’m even puzzled why many Eritreans (let me qualify it by saying of the ones I know and on the discussions I’ve had with other Eritreans)prefer Amharas than Tigaru. You see I don’t see any difference between Tigrinya speaking Eritreans and Tigaru–we’re the same. I honestly don’t care about the prevailing politics that is unnecessarily creating divisions among us, but I cannt deny the fact that a Tigrinya speaking person from Seraye, Akeleguzay, Hamasein, Adwa, Agame, Tembien…are the same people, ethnically, culturally, religiously and historically. I’ve not had the honor of visiting Tigray but I can imagine that is one place outside Eritrea where I will completely feel at home. I’ve never met a Tigrayan I didn’t like or one I didn’t feel a sense of kinship with it. As I said before, when a Tigrinya speaking Eritrean sees him/herself in the mirror, s/he sees a Tigrayan and the opposite is true. The sooner we realize, appreciate and honor this truth, the better chance we will have for a better future.
If I would live in Ethiopia, I would proudly identify myself as Tigraway just as Eritreans of Tigrayan ancestry identify themselves as either Hamasenay, Seraye and Akeleguzay.My reading of history tells me we need to reflect on our past and prepare a better future for our kids. Towards that goal, I’m ready to do my part.@ አነበብከው ኤፍ እና ትክክል አልመስልህም ከአክብሮት ጋር...antiaskaris

I have read so many posts regarding the blogger lovers but this article
is in fact a nice post, keep it up.

Also visit my web page Easy Money Making Ideas

Anonymous said...

erget new telacha eskahun ale ertra weste mn endetesera gn yawek ayemeslegm.bzu beteseboch. Eske ne zerachew yetefu betachew weste bederg wetaderoch yetegedelu alu .betank techefeleku lalkew demo smetawyan wetaderoch yaderegut new enji sent mrkonoch wede agerachrw temelsewal. Yh tarik new ahun yalewn telacha be endezi weyeytoch enades.