Saturday, October 25, 2014

በአገር ላይ የሚመጣ አደጋን አቅልሎ የማየት ያልሰለጠነ አስተሳሰብ

ታዳጊ አገሮችን በሙሉ የሚያመሳስላቸው አንድ ግርም የሚለኝ ነገር ከገደል አፋፍ ቆሞ ገደሉን መናቅ፣ ከአደጋ ጫፍ ቆሞ አደጋን ማቃለል፤ ከዚያም ከገደሉ ወድቆ መሰበር፣ በአደጋው ተጠራርጎ መወሰድ። ይህ ሐሳብ በርግጥ ፍንትው ብሎ የታየኝ የማሌዢያ አውሮፕላን በዩክሬይን ሰማይ ላይ በሚሳኤል በጋየበት ጊዜ ነበር። ሁላችሁም እንደምታስታውሱት የሰው አካል ቁርጥራጭ ከሰማይ ይዘንብ እንደነበር እማኞች ሲናገሩ መልክተናል።
ታላላቆቹ የዜና አውታሮች ራሺያ ላይ አተኩረው ነገሩን በዚያ ፈፀሙት አንጂ “አውሮፕላኑ በጦርነት ሰማይ ላይ ለምን ሄደ?” የሚለውን የሚያነሱ ሰዎችም ተደምጠዋል። ብዙ አየር መንገዶች አቅጣጫቸውን ቀይረው በሌላ መስመር መሔድ ከጀመሩ ቆይተው ነበር። የሳንቲም ስባሪ ለማትረፍ አንድም በማሌዢያኛ “አቦ አታካብዱ” ብለው ሳይሆን አይቀርም በዚያ በታዳጊ አገር አስተሳሰብ መንገዳቸው ሳይቀይሩ ቀሩ።

“የእባብ ጉድጓድ በጅል ክንድ ይለካል” እንደሚባለው የዩክሬይን አየር በማሌዢያ አውሮፕላን ክንድ ሲለካ ጅልም እጁ አይተርፍ፣ አውሮፕላኑም አልተረፈ። ተመሳሳይ ነገር እነሆ ሊከሰት ነው። ኢትዮጵያ በበኩሏ 200 ነርሶች ወደ ኢቦላ ዞን (Ebola ZOne) ልትልክ ጀብደኛ ውሳኔ ወስናለች። የማሌዢያ ውሳኔ።
ኢቦላ ምዕራብ አፍሪካን ምን እያደረገ ነው? ከበሽተኛው በሚወጣ ፈሳሽ በሚተላለፈው በዚህ በሽታ የአገራች ኢኮኖሚ እንዴት እንዴት እየሆነ ነው? የዚያ አገር ዜጋ የሆኑ በማለው ዓለም የሚኖሩ ሰዎች እንዴት እየታዩ ነው? ምን ዓይነት ችግር እየገጠማቸው ነው? አይበለውና በሽታው አገራችን ቢገባ ዘመዶቹን በማስታመም የሚታወቅ የአገራችን ሰው እንዴት ባለ አደጋ ላይ ይወድቃል? የትኛው ሆስፒታል በርግጥ ብቁ ነው? መቸም በፌዴራል ፖሊስ ዱላ አታስቆሙት ነገር።“የሕዳር በሽታን” በአገራችን በ21ኛው ክ/ዘመን ልታመጡብን ካልሆነ በእውነቱ ምን ሌላ ምክንያት ይኖራችኋል?
በዓለም ላይ በሕክምና አያያዛቸው ጥራት የተመሰገነላቸው ብዙ አገሮች አሉ። ኢቦላን በረዓድ እያዩት ነው። ሕዝቡ ገና ስሙን ሲሰማ ሽብር ይይዘዋል። አንድ ሰው ቴክሳስ ግዛት በበሽታው በመሞቱ መላው አሜሪካ ከሥሩ ነው የተነቃነቀው። በርግጥ እነርሱ ፈሪዎች ስለሆኑ እኛ ጀግንነት ይዞን ይሆን? የሚመጣውን ጉድ ስለሚረዱት ነው።

ይህንን ያልሰለጠነ አስተሳብ እንዴት ማስለቀቅ ይቻል ይሆን? አለመሰልጠን ወንጀል አይደለም ነገር ግን አገር ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አደጋ እያወቁ ለጋ ወጣቶችን ወደ እሳት መላክ ግን ሌላ ዓላማ እንዳለው ነው የሚረዳኝ። ምናልባት በበሽታው የሚገኝ ትርፍ እንዳለ እንጃ። ፈጣሪ ሕዝቡን ይታደገዋል። ለእናንተ ግን እንጃ!!! 

3 comments:

Anonymous said...

That is a very sad truth. What an irresponsibility!

Anonymous said...

I do not expect this kind of analysis from a religious person . The fate of a mankind or the world determine by the almighty God. Ebola is not a new virus, it was in our neighbour country (Sudan ) in 1976. Instead of buying all western media exaggeration , try to think the God's words and do not give your back when your brother ask for help before he die. When was Ethiopian Airlines stop flying from these countries area. It was late compare to others but nothing happened to Ethiopia unless you want to bring tabloid news from facebook. Even i do not like the ruling party ideology, but i like this kind of humanity service that will have God blessing to the people and the whole country . This mission is not as dangerous as sending peace keeper. for Politician, i do not mind if the split and interpreted in various ways to gain their mission for you it is different...

Anonymous said...

What a crazy Government!