Sunday, April 19, 2015

ኢትዮጵያዊ መሆኑን ጠላቶቹ አውቀዋል የራሱ ወገን ግን አላወቀውም

ኢትዮጵያዊ መሆኑን ጠላቶቹ አውቀዋል የራሱ ወገን ግን አላወቀውም። የአሜሪካ መንግሥት አውቆ መግለጫ አውጥቶለታል፣ የራሱ ወገን ግን አላወቀውም። ሚዲያዎች በሙሉ አውቀውት በስሙ ጠርተውታል፤ የራሱ ወገን ግን አላወቀውም። የሊቢያ ምድር እንኳን 40 ቀኑ ተጠምቆ የሥላሴ ልጅነትን ባገኘው፣ የክርስቶስን ሥጋ በበላው፣ ክቡር ደሙንም በጠጣው በዚህ ኢትዮጵያዊ ደም ታጥባ "ፋሲካን ስታደርግ" ኢትዮጵያዊ መሆኑን አውቃለች፣ የራሱ ወገን የራሱ መንግሥት ግን አላወቀውም።

አንገታቸውን የሚቀላቸው፣ በጥይት የሚገድላቸው ጠላት አይሲስ ማንነታቸውን ጠንቅቆ ሲያውቅ መንግሥት ተብዬው መንደርተኛ ቡድን ግን ማን መሆናቸውን አላረጋገጥኩም እያለ ማፌዙ የዘመኑ ገራሚ ትዕንግርት መሆን አለበት። ምንም እንኳን የዚህን መንደርተኛና ጠባብ ቡድን ተፈጥሮ፣ ዓላማና ግብ ጠንቅቀን ብናውቀውምና በዚህ ዓይነቱ ጠባይ መደነቅ ባይገባንም በየዕለቱ ማስገረሙን እንደቀጠለ ነው።
ወገኖች፤ ምርር ያለውን እውነት ለመቀበል ባልደፈርን መጠን ኢትዮጵያም በውርደት ቁልቁለት መሽንቀንጠሯ አይቆምም። ይህ መሪር እውነት ደግሞ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያንን አለማወቋ፤ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድራት ኢትዮጵያውያንን የማያውቅ ልበ-ቀኝ-ገዢ ባዕድ ቡድን መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ የምታውቀው በመንደራችን ስንጠራ ብቻ ነው። አማራ ስንባል ኦሮሞ ስንባል፣ ትግሬ ስንባል ወዘተ ታውቀናለች። ከዚያ ውጪ ሁላችን አንድ ላይ ሆነን ያለ ወንዛችን መጠራት ስንፈልግገና ላጣራችሁ፣ ማንነታችሁን ልለይትላለች።
ይህ በሽታ ከአገራችን መነቀል አለበት። መሪሩ እውነት ይህ ነው። ያን ጊዜ አገራችንን የያዛት ልጆቿን የመርሳት አልዛይመር ይለቃታል።

3 comments:

Anonymous said...

ወገኖች፤ ምርር ያለውን እውነት ለመቀበል ባልደፈርን መጠን ኢትዮጵያም በውርደት ቁልቁለት መሽንቀንጠሯ አይቆምም። ይህ መሪር እውነት ደግሞ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያውያንን አለማወቋ፤ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድራት ኢትዮጵያውያንን የማያውቅ ልበ-ቀኝ-ገዢ ባዕድ ቡድን መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ የምታውቀው በመንደራችን ስንጠራ ብቻ ነው። አማራ ስንባል ኦሮሞ ስንባል፣ ትግሬ ስንባል ወዘተ ታውቀናለች። ከዚያ ውጪ ሁላችን አንድ ላይ ሆነን ያለ ወንዛችን መጠራት ስንፈልግ “ገና ላጣራችሁ፣ ማንነታችሁን ልለይ” ትላለች።
ይህ በሽታ ከአገራችን መነቀል አለበት። መሪሩ እውነት ይህ ነው። ያን ጊዜ አገራችንን የያዛት ልጆቿን የመርሳት አልዛይመር ይለቃታል።

Anonymous said...

ንገታቸውን የሚቀላቸው፣ በጥይት የሚገድላቸው ጠላት አይሲስ ማንነታቸውን ጠንቅቆ ሲያውቅ መንግሥት ተብዬው መንደርተኛ ቡድን ግን ማን መሆናቸውን አላረጋገጥኩም እያለ ማፌዙ የዘመኑ ገራሚ ትዕንግርት መሆን አለበት። ምንም እንኳን የዚህን መንደርተኛና ጠባብ ቡድን ተፈጥሮ፣ ዓላማና ግብ ጠንቅቀን ብናውቀውምና በዚህ ዓይነቱ ጠባይ መደነቅ ባይገባንም በየዕለቱ ማስገረሙን እንደቀጠለ ነው።

Anonymous said...

ንገታቸውን የሚቀላቸው፣ በጥይት የሚገድላቸው ጠላት አይሲስ ማንነታቸውን ጠንቅቆ ሲያውቅ መንግሥት ተብዬው መንደርተኛ ቡድን ግን ማን መሆናቸውን አላረጋገጥኩም እያለ ማፌዙ የዘመኑ ገራሚ ትዕንግርት መሆን አለበት።

Blog Archive