Thursday, December 15, 2016

ዕንባና ጸሎት ያሳደጉት ልጅ (ልቦለድ)

(ከኤፍሬም እሸቴ/ PDF)
ይህንን አጭር ልቦለድ ከማንበባችሁ በፊት በቪዲዮ የተቀናበረውን የተመስገን ደሳለኝን ወንድም የታሪኩ ደሳለኝን ጽሑፍ (HERE) እንታዳምጡ ልጋብዛችሁ። በቪዲዮው ላይ የቀረበው የታሪኩ ጽሑፍ እውነተኛ ታሪክ ሲሆን የእኔይቱ መጣጥፍ ግን ልቦለድ መሆኗን እንድትረዱ በማስጠንቀቅ ወደ ንባቡ ልምራችሁ።   Published Originally on 10/28/14, 10:57 PM
Pacific Standard Time
+++
ከዕለታት አንድ ቀን …
እትዬ ሸዋዬ ቤት ውስጥ። ስኒው ተዘርግቶ ቡናው በአንድ ጎን ይቆላል። የተንተረከከው ፍህም ቅላቱ የአፋርን እሳተ ገሞራ የቀለጠ ዐለት ያስታውሳል። በአንድ ጥግ ዳንቴል ለብሳ የተንጠለጠለች ብርቄ ሬዲዮ የምሳ ሰዓት ዜና ታሰማለች። ሕጻናት ውጪ ደጃፉ ላይ ሲጫወቱ የሚያስነሱት አቧራ ገርበብ ብሎ በተከፈተው በር ዘልቆ ይገባል። እንደ ሌላው ጊዜ “እንደው እነዚህ ውጫጮች፤” ብሎ የሚያባርራቸው የለም። ሴቶቹ በሙሉ ጆሯቸውን ከራዲዮኑ ደቅነው በዓይኖቻቸው የልጆቻቸውን ሩጫ ይመለከታሉ። ባሎች ወደ ኦጋዴን ግንባር ከዘመቱ ቆይተዋል። በሰፈሩ ውስጥ ዕድሜያቸው ከገፋ አረጋውያን እና በተለያየ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ከሚሠሩ ሰዎች በስተቀር ደልደል ያለ ወንድ በሰፈሩ ብዙም አይታይም። ወንዱ ሁሉ የናት አገር ጥሪ ብሎ ሚሊሻ ሆኗል።
በርግጥ ሬዲዮኑ ይሸልላል፤ ይፎክራል። ቤት ያሞቃል። ሴቶቹ ግን በዚያ ሁሉ የጀግና ፉከራና ቀረርቶ፣ “ውረድ በለው ግፋ በለው፤ ግደል ተጋደል በአባትህ ወኔ …” መካከል የባሎቻቸው ሕይወት፣ በእነርሱ ላይ እንዳይደርስ የሚፈሩት ነገር ሥጋት …. ያለ አባት ልጅ የማሳደግ ጭንቀት … እየተገለባበጠ ይመጣባቸዋል። ልጆቹ አቧራቸውን ያቦናሉ።

Wednesday, November 30, 2016

Did Menelik ever claim to be "Caucasian?" As argued by Dr. Tsegaye Ararsa?

(By Fikru Gebrekidan (PhD)/ November 30, 2016):- In reading Dr. Tedla's most recent reflection on Oromo politics posted on Ethiomedia, I was led by one of his reference notes to a debate he had with Dr.Tsegaye Ararsa in May this year. The debate was over Menelik's self-perception. Dr. Tsegaye had read at face value the now much-discredited claim by Robert Skinner about Menelik's snobbish treatment of a Haitian visitor, Benito Sylvain, from which he concluded that Menelik saw himself as a "Caucasian" instead of a black African. Dr. Tsegaye was not the first one to be misled, knowingly or unknowingly, by Skinner. The Ohio-journalist turned diplomat, Skinner believed that most Ethiopians, including the Oromo, belonged to the Caucasian race. More important, what Dr. Tsegaye did not read was the version in Sylvain's firsthand account, which was the exact opposite of Skinner's make-believe. Sylvain's Ethiopian diaries were published in 1969 in a biographical work by Antoine Bervin, and are the basis of this essay.

Tuesday, November 22, 2016

Thanksgiving የምሥጋና በዓል፣ በዓለ አኮቴት

ዛሬ “Thanksgiving” ላይ ቆሜ ስለዚህ በዓል ለብዙ ጊዜ ልጽፈበት እየፎከርኩ አለማድረጌን እየወቀስኩ ጥቂትም ቢሆን ልልበት ወሰንኩ። ምናልባት የፈረንጅ በዓል ስለሆነና ገና ስላልተዋሐደኝ ባዕድ ሆኖብኝ ይሆን እንጃ በተከታታይ ሦስት ዓመታት ብዕሬን አንስቼ ሳልፈጽመው ቀርቻለኹ። ዘንድሮስ አይሆንም ብያለኹ። በተለይ ለረዥም ዘመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያን በሐላፊነት ሲመሩ የነበሩትና በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ “እኛ ልመና እንጂ ምስጋና አናውቅም፤ ማመስገን ያስፈልገናል” ይሉት የነበረው አባባላቸው የበለጠ አበረታቶኝ የግል ሐሳቤን ለመጠቆም ደፈርኩ።
“Thanksgiving” ወይም በአማርኛ “የምሥጋና በዓል” ወይም ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ “በዓለ አኮቴት” ያሉት በዓል ከእንግሊዝ አገር በ17ኛው መ/ክ/ዘመን በስደት ወደ አሜሪካ የመጡ መጻተኛ እንግሊዞች ማክበር የጀመሩት፣ በፕሬዚዳንት ጆርጅ ዋሺንግተን ብሔራዊ በዓል ተደርጎ የተደነገገ በኖቬምበር ወር በአራተኛው ሐሙስ ላይ የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ በተለያየ ዘመን በተለያዩ የአገሪቱ ፕሬዚዳንቶች ሲከበር ቆይቶ ከ1941 ጀምሮ የአሜሪካ ኮንግረስ የኖቬምበር  በአራተኛው ሐሙስ ብሔራዊ ክብረ በዓል ሆኖ እንዲከበር የወሰነበት በዓል ነው።

Friday, November 18, 2016

የአገሬ ልጆች ሆይ፡- ቁልፉ ያለው ከታሪክ ላይ ነው፤ It's the history, stupid.

ቢል ክሊንተን ለ1992 ፕሬዚዳንትነት ሲወዳደሩ የተጠቀሙበት የምርጫ መፈክር ሁሌም የሚጠቀስ ትልቅ ሐሳብ ነበር። በወቅቱ በአገረ አሜሪካ ስለ ነበረው ዋና ጉዳይ (የኢኮኖሚ ጉዳይ) በአጭር አገላለጽ ያስቀመጡበት መሪ-ቃላቸው ነው። «ዋናው ነገር የኢኮኖሚው ነገር ነው» ለማለት በአጭሩ «ኢት ኢዝ ዘኢኮኖሚ፣ ስቱፒድ» (It's the economy, stupid) ማለትን መርጠዋል።

በአገራችን ያለውን ዕለት ተዕለት የሐሳብ ፍጭት እና ጦርነት ስመለከት እና ይህንን ሁሉ ምስቅልቅ በአንድ ሐረግ መግለጽ ስፈልግ ከቢል ክሊንተን የምርጫ መፈክር አባባሉን መኮረጅ ያምረኛል። እናም እኮርጃለሁ። «ኢት ኢዝ ዘሂስትሪ፣ ስቱፒድ» (It's the history, stupid) እላለሁ። የሀገራችን ዋና መግባቢያም መለያያም የታሪክ እና የታሪካችን እንዲሁም ታሪኮቻችን የሚተረኩበት ሁኔታ የታሪክ ፀሐፊዎቻችን እና የተራኪዋቻችን ነገር ነው። ቁልፉ እዚያ ላይ ነው። «ዋናው ነገር የታሪክ ነገር ነው»።

Thursday, November 17, 2016

«የራእየ ማርያም ትርጉም ችግር» (ጥናታዊ ጽሑፍ)

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በግራ ዘመም እና መሠረተ-ጎሳ በሆኑ የአገራችን የፖለቲካ አስተሳሰቦች ዘንድ በጠላትነት እንደምትፈረጅ የአደባባይ ምሥጢር ነው። በዚህ ረገድ የሕወሐት የ40 ዓመት ፖለቲካ እና በኦነግ እና ከዚያም በኋላ በተነሡ የኦሮሞ ፖለቲካ አራማጆች ዘንድ ያለው አመለካከት ተጠቃሽ ነው። እነዚህ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ቤተ ክርስቲያኒቱን በጠላትነት የፈረጁበትን ዝርዝር ጉዳይ ለጊዜው ብናቆየው እና በኦሮሞ ልሒቃን አካባቢ የሚጠቀሰውን አንድ መጽሐፍ (ራእየ ማርያምን) ብቻ ብናነሣ፣ ጥላቻው መሠረት የሌለው ይልቁንም በግልሰቦች ስሕተት እና ተደጋጋሚ ስሕተት ላይ የሚያጠነጥን መሆኑን እንመለከታለን። ስለዚህም በራእየ ማርያም ላይ በግእዝ መጻሕፍት ላይ ጥናት በሚያደርጉት በዶ/ር አምሳሉ ተፈራ «የራእየ ማርያም ትርጉም ችግር» በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን መሠረታዊ ጥናት እንድታነቡ እንጋብዛለን። ጽሑፉን በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን  ሊንክ («የራእየ ማርያም ትርጉም ችግር») ይጫኑ።

«ራእየ ማርያም» በርግጥ ኦሮሞዎችን ይሳደባል? (ዳሰሳ በመጽሐፉ ላይ)

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በግራ ዘመም እና መሠረተ-ጎሳ በሆኑ የአገራችን የፖለቲካ አስተሳሰቦች ዘንድ በጠላትነት እንደምትፈረጅ የአደባባይ ምሥጢር ነው። በዚህ ረገድ የሕወሐት የ40 ዓመት ፖለቲካ እና በኦነግ እና ከዚያም በኋላ በተነሡ የኦሮሞ ፖለቲካ አራማጆች ዘንድ ያለው አመለካከት ተጠቃሽ ነው። እነዚህ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ቤተ ክርስቲያኒቱን በጠላትነት የረጁበትን ዝርዝር ጉዳይ ለጊዜው ብናቆየው እና በኦሮሞ ልሒቃን አካባቢ የሚጠቀሰውን አንድ መጽሐፍ (ራእየ ማርያምን) ብቻ ብናነሣ፣ ጥላቻው መሠረት የሌለው ይልቁንም በግልሰቦች ስሕተት እና ተደጋጋሚ ስሕተት ላይ የሚያጠነጥን መሆኑን እንመለከታለን። ስለዚህም በዚህ ዙረያ የተደረገ አንድ የመነሻ ውይይት እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።  

Tuesday, October 25, 2016

Some Salient Points on the Lack of Compliance with the Constitution of the Decree of State of Emergency in Ethiopia

(By Getahun S Gesso): I wanted to write this piece after hearing several discussions on different fora and media on what the decree of state of emergency in Ethiopia means? How it affects freedom of expression and of the press? How it interferes with opposition and political space? etc and how the decree should be understood from the stipulations in the constitution itself?

I recall trying to highlight some of the cardinal features of a decree for declaration of state of emergency in my recent article published on www.adebabay.com: What We Know and What We Don't About the Decree of State of Emergency in the Wake of the Ethiopian Protests and Irecha Massacre: What is the way forward? As it was written in the wake of the issuance of the state of emergency, it did not cover certain areas hoping that the actual decree would. However, the scanty Directive published by the government since left much to be desired. Thus, in this article I will further elaborate what can be covered by a decree of state of emergency and what cannot; the levels of authority for its issuance and administration; and a brief assessment of whether the constitution is complied with so far and the benefits of compliance.

Thursday, October 20, 2016

ከአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ምን ይጠበቃል? («ውይይት በአደባባይ»)

በዚህ የ«ውይይት በአደባባይ» ዝግጅታችን የሚከተሉትን ዋና ሐሳቦች እና ተያያዥ ጉዳዮች አንስተናል። ተከታተሉት።
  • አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ይህንን ያህል ሰፊ ውክልና ያለው አካል ቢሆንም ውክልናው በትክክል ምዕመናን፣ ካህናት፣ የሰንበት ት/ቤቶች የሚወከሉበት አካል ነው ብለን መናገር እንችላለን?
  • አብዛኛውን ጊዜ የስብሰባ ሂደት ቀደም ባሉት ዓመታት ሲካሔድ ምን ገጽታ ነበረው?
  • የዚህን ዓመት ጉባዔ እንደ አምናው እንደ ካቻምናው ብቻ አይተን ልናልፈው የምንችለው ጉባዔ ነው? (ዝግጅታችንን  ለመከታተል እንዲመች በሁለት ክፍል አድርገነዋል። በአንድ ጊዜ ማዳመጥ ከፈለጉ ደሞ ይህንን «ሊንክ» ይጫኑ)


Monday, October 17, 2016

ፍርሃት ምንን ይወልዳል?

(ኤፍሬም እሸቴ)፡- ኒቸ የተባለው የጀርመን ፈላስፋ ስለ ፍርሃት በተናገረበት ተጠቃሽ ጥቅሱ «ፍርሃት የሥነ ምግባር እናት ናት፤ Fear is the mother of morality.» ይላል። ምን ማለቱ እንደሆነ ለመተንተን የፍልስፍና ተማሪ መሆን ስለሚጠይቅ ለማብራራት ይከብደኛል። ሃይማኖትን የፍርሃት ልጅ አድርጎ ለማቅረብ የፈለገ ቢመስለኝም ለመደምደም ግን አልችልም። ይልቅ እርሱ «ፍርሃት ሥነ ምግባርን ትወልዳለች» ሲል እኔ ደግሞ በልቤ «ፍርሃት የጭካኔ እናት ናት፣» ወይም «ፍርሃት ጭካኔን ትወልዳለች» ብዬ አሰብኩ።

Friday, October 14, 2016

አንዲት ሚጢጢ ትልቅ ጥያቄ፡ በእንተ «ሐበሻ»

(ኤፍሬም እሸቴ)፡- ሚጢጢ ካሉ ትልቅ፤ ትልቅ ካሉ ሚጢጢነት የለም ይቺ ግን ሁለቱንም ናት። ሚጢጢ ስላት ትልቅ እየሆነች ብዙ አስቸግራኛለች። ይቺም «ሐበሻ» የምትባል ቃል/ስም ናት። ቀደም ያሉ የፈረንጅ ምሁራን «አቢሲኒያ» የሚሉት «አቢስ» ‘abyss’ ከሚል ደግ ትርጉም ከሌለው ቃል አመንጭተው ቢሆንም አረብኛውን ጨምሮ በግሪኮቹምና በሄሮግሊፊክስ ጽሑፎች ያለው ግና በቀይ ባሕር አካባቢ ያለ አካባቢንና ሕዝብን የሚመለከት ነው። የውጪ አገር አጥኚዎች እና ካርታ ሰሪዎች የዓለም ካርታ በሚሠሩበት ወቅት አሁን አገራችን የምትገኝበት አካባቢ እና አፍሪካን በገባቸው መንገድ ሲሰይሙ፣ ሲቀይሩ ኖረዋል። አገራችንን አቢሲኒያ ብለው በሰፊው ሲጽፉ መኖራቸው እሙን ነው። ይሁንና ኢትዮጵያውያን ግን ራሳቸውን «ኢትዮጵያውያን» በማለት ሲጠሩ ኖረዋል። ነገሥታቱም «ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ» ይሉ ነበር እንጂ «የሐበሻ ንጉሥ» ማለታቸውን አንብቤ አላውቅም።

What is the way forward?

What We Know and What We Don't Know About the Decree of State of Emergency in Ethiopia in the Wake of the Ethiopian Protests and Ireecha Massacre: What is the way forward?
(By Getahun S Gesso)

Background

The protests in Ethiopia in the current form started in November 2015. Since then, they have claimed the lives of hundreds of innocent citizens in Addis Ababa, Oromia, Amhara and Southern regions. No one knows the exact number but the government (in)consistently tried to admit a suppressed number; and opposition parties and human rights defenders gave numbers based on their respective sources. It is doubtful if the government really knows how many it has killed thus far.

Thursday, October 13, 2016

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፈቀደው «ነጻ ርምጃ»ና ጭካኔን ይወልዳል

በጎ ኅሊና ወዳላቸው በሙሉ እንጮኻለን

(ኤፍሬም እሸቴ)፡- የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል የተፈጠረ እንደመሆኑ ጭካኔ፣ ሰቆቃ መፈፀም እና በሰው ላይ ግፍ መዋል የባሕርይው አይደለም። የሰው ልጅ «ሰው» ነውና እግዚአብሔር በኅሊናው ውስጥ ክፉውንና ደጉን የሚለይበት መዳልው (ሚዛን) ፈጥሮለታል። ከማንም ባይማረው እንኳን በኅሊናው ክፉውን እና ደጉን የመለየት ሥጦታ አለው። ይህ ክፉንናደጉን የመለየት ሥጦታ በሥነ ምግባር እና በትምህርት የበለጠ ይዳብራል፤ ያድጋል፣ ይጎለምሳል።
ይሁን እንጂ የሰው ልጅ ኅሊናው ክፉና ደጉን በመለየት መካከል ፈራጅ ሆኖ የተቀመጠለት ቢሆንም ክፉውን እየተወ ደጉን እንዲከተል «ሥነ ምግባር» ብሎም «ሕግ» የሚባል አጥር ይበጅለታል። በነጻነት የተፈጠረ እና ነጻ ፈቃድ ያለው ቢሆንም በነጻ ፈቃዱ ተጠቅሞ ለሚሠራው ሥራ ደግሞ ተጠያቂነት አለበት። ተጠያቂነት ነጻ ፈቃዱን በአግባቡ እንዲጠቀም ያደርገዋል። ለሰው ልጅ ሰማያዊ ሕግ እንዳለው ሁሉ ምድራዊ መተዳደሪያ ሕግም አለው። ለሰማያዊው ሕግ ብሎ መልካም ባይሠራ ስንኳ ምድራዊውን ቅጣት ፈርቶ ከክፉው ይልቅ በጎውን ይመርጣል። በእርግጥ በምድራዊው ሕግ ጥሩ የተባለ ነገር ሁሉ በሰማያዊው ሕግ ጥሩ የማይባል ሊሆን ቢችልም በዚህ ዓለም ላይ አንዱ ከአንዱ ተከባብሮ ለመኖር ግን ይጠቅመዋል። ያ ባይሆን ኖሮ ለሃይማኖት ደንታ የሌላቸው ነገር ግን በሥርዓት የሚኖሩት ሕዝቦች እርስበርሳቸው በተበላሉ ነበር።

Wednesday, October 12, 2016

የካህናት ሚና - በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ ዙሪያ (ውይይት በአደባባይ ቃለ ምልልስ)

አገራችን ኢትዮጵያ በጥልቅ የለውጥ ማዕበል ውስጥ ትገኛለች። በብዙ የአገራችን ክፍሎች ሕዝባዊ እምቢተኝነት በማየሉ ሕዝቡ አልገዛም በማለት ላይ ይገኛል። መንግሥት በበኩሉ ለሰላማዊ ጥያቄ አደባባይ የሚወጡ ዜጎችን ያለ ርኅራኄ ይገድላል። ወጣቶችን እና በተቃውሞ ቆመዋል ያላቸውን በሙሉ በመደብደብ፣ በማሰቃየት እና በግዞት መልክ ወደ ሩቅ ቦታ ወስዶ በማጎር ላይ ይገኛል። መንግሥት ሕዝቡ በምንም መልኩ የተቃውሞ ድምጽ እንዲያሰማ ባለመፍቀዱ የእሬቻን በዓል ለማክበር በወጡ ዜጎች ላይ አስለቃሽ ጢስ በመተኮስና ሕዝቡን በማስደንበር ብዙ ወገኖች ባህር ውስጥ በመግባት፣ ከገደል ውስጥ በመውደቅና በመረጋገጥ ሕይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል። ለጠፋው የሰዎች ሕይወት ተጸጽቶ ሕዝቡን ከማረጋጋት ይልቅም «ይህንን ያደረጉት ፀረ ሰላም ኃይሎች ናቸው» በሚል ሌላ ዙር ዘመቻ ከፍቷል።

Wednesday, October 5, 2016

«የአገራችን ወቅታዊ ችግር እና የክርስቲያኖች ሚና» (ውይይት)

«ውይይት በአደባባይ» የተባለው ዝግጅት በ«አደባባይ የጡመራ መድረክ» እየተዘጋጀ የሚቀርብ ግልጽ የውይይት መድረካችን ነው። አሐዱ ብለን በምንጀምረው በዚህ የመጀመሪያ ዝግጅታችን የመርሐ ግብሩ አዘጋጅ ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ ከሁለት እንግዶች ጋር ይመካከራል። እንግዶቻችን ቀሲስ አሸናፊ ዹጋ እና ቀሲስ ንዋይ ካሳሁን ናቸው። የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሎጅ ምሩቃን የሆኑት ሁለቱ እንግዶች በተለያዩ እርከኖች ቤተ ክርስቲያናችንን ያገለገሉና በማገልገል ላይ የሚገኙ ናቸው። «የአገራችን ወቅታዊ ችግር እና የክርስቲያኖች ሚና» በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የተደረገው ውይይት እነሆ። (ቪዲዮውን በዩቲዩብ ማዳመጥ ካልፈለጉ፤ በድምጽ የተቀናበረውን ዝግጅት ለማዳመጥ ይህንን (ሊንክ) ይጫኑ።) 

Sunday, October 2, 2016

አይረሴው የኦሮሞ «የምሥጋና ቀን» አያና ኢሬቻ እልቂት

(ኤፍሬም እሸቴ)፡- ዛሬ በዕለተ ሰንበት የኦሮሞ ሕዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር በሚያከብረው የኢሬቻ በዓል ላይ እጅግ ብዙ ሕዝብ አልቋል። ቁጥሩ ከሰዓት ወደ ሰዓት እያሻቀበ በመሆኑ በእርግጠኝነት ይኼንን ያህል ነው ለማለት ጊዜው ገና ነው። እስካሁን ግን ከ175 ሰው በላይ (ከ360 በላይ ሚሉም አሉ) መሞቱ ታውቋል። የሞቱት አብዛኞቹ ወጣቶች ቢሆኑም ካገባች ገና አንድ ወር ያልሞላትን ሙሽራ (ወ/ሮ ሲፈን ለገሰን) ጨምሮ ወንዶችም ሴቶችም፣ ወጣቶችም፣ ገና ለጋ ልጆችም ተቀጥፈዋል። በሕይወት ቢተርፍም አደጋ የደረሰበት ብዙ ሺህ ሰው እንደሚኖር ይገመታል። 
በዓሉ የሚከበርበት «ሆራ አርሰዲ»
 ወዳጄ አዲስ ተስፋዬ ስለቦታው እንዲህ ይላል፡- «እሬቻ የሚከበረው ሆራ አርሰዲ በተባለው በተለምዶ ሆራ እየተባለ በሚጠራው የቮልካኖ ሐይቅ(crater lake) ውስጥ ነው:: ሆራ ሀይቅ ያለው ለጥ ያለ ሜዳ ላይ አይደለም:: ጉድጓዳ ነው:: ዙርያውን ገደል ሆኖ መሀሉ ላይ ሀይቁ አለ:: ወደ ሐይቁ ለመግባትም ሆነ ለመውጣት የሚያገለግሉ ሁለት በሮች አሉት:: አንዱ በራስ ሆቴል በኩል ሲሆን ሌላኘው በደብረዘይት እርሻ ምርምር በኩል ያለው ነው:: እሬቻ የሚከበረው ገደሉን በመውረድ ውሃው አጠገብ ነው:: ውሃው አካባቢ ያለው መሬት በቂ ስላልሆነ አብዛኛው ሰው የሚታደመው ገደሉ ላይ ነው:: ገደሉ ላይ ቆሞ ከታች ውሃው ዳር የሚካሄደውን ሂደት ይከታተላል::»

Wednesday, September 28, 2016

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፡- የአገራችንን ሁኔታ በተመለከተ ያስተላለፏቸውና ተገቢውን ሽፋን ያላገኙት መልእክቶቻቸው

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው። ወደዚህ የአበው ማዕረግ ከመምጣታቸው በፊት በዋሺንግተን ዲሲ የቅ/ሚካኤልን ቤተ ክርስቲያን አቋቁመው ሲያገለግሉ ነበር። ማዕረግ ጵጵስናን ካገኙ በኋላ ወደ አገር ቤት ተጠርተው በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግለዋል። ከዚያም የዲሲ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ወደ አገር ቤት ሲጠሩ ቦታውን ተረክበዋል። ርክክቡ በወቅቱ በፈጠራቸው የተለያዩ ችግሮች ምክንያት አለመግባባቶች ተፈጥረው ለረዥም ጊዜ አገልግሎቱ ተጎድቶ የቆየ ቢሆንም በስተመጨረሻ ችግሩ እልባት ሊያገኝ ችሏል። በወቅቱ በነበረው ጉዳይ ብዙዎቻችን በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አካሔድ ባለመደሰታችን ተቃውሟችንን ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ስንገልጽ ቆይተናል። ያን ጊዜ ተቃውሟችንን በግልጽ እንዳቀረበውነው ሁሉ አሁን ደግሞ በመፈጸም ላይ ባሉት ሕዝብን የማጽናናት፣ «አይዞህ፣ አለሁልህ» የማለት አባታዊ በጎ ተግባር ደስታችንን መግለጽ ይገባናል።

Monday, September 26, 2016

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ? እኛስ ምን እንበል?

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በ2009 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ የደመራ በዓል ትምህርታቸው ታሪካዊ መልእክት አስተላልፈዋል። በትምህርታቸው የሚከተሉትን ዐበይት ነጥቦች ጠቅሰው ተግሳጽና ማጽናኛ መልእክት አስተላልፈዋል። ከጠቀሷቸው ኃይለ ቃሎች ከብዙው በጥቂቱ፡-
«እንደ ፖለቲካ ሳይሆን እንደ ሃይማኖት መናገር ያለብኝን ነገር መናገር አለብኝ ብዬ አምናለሁ፤ መንግሥትንም ቢሆን»፤ 
በቀይ ሽብር ዘመን የተፈፀመውን አስታውሰው ይኸው ታሪክ እንዳይደገም አስጠንቅቀዋል፣
ችግርን መፍታት የመንግሥት ኃላፊነት እንደሆነ፤ መልስ መስጠት እንዳለበት፣ ሰዉ ጩኸቱን እንዲያቆም መልስ መስጠት እንደሚያስፈልግ፤ ሕዝቡ «ለምን ጮኽክ?» መባል እንደሌለበት  በሕጻን ልጅ ለቅሶ መስለው አብራርተዋል፤
በቤተ ክህነቱም በቤተ መንግሥቱም ችግር ሁልጊዜም የመሪ እንጂ የተመሪ/የሕዝብ እንዳልሆነ ገልጸዋል፤
በተለይም የመንግሥት ሚዲያዎችን በጽኑዕ ወቅሰዋል። «የምንናገረውን በትክክል አታስተላልፉም፣ በዚህ ምክንያት ከሕዝቡ ጋር ተጋጭተናል፤ ሕዝቡ ምን አባት አለን ይላል» ብለዋል፤ «የምንናገረውን በትክክል አድርሱ» ሲሉም ገስጸዋል፤

Saturday, September 24, 2016

ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ ለውጥ እና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

(ከኤፍሬም እሸቴ)
+++
ኢትዮጵያ የለውጥ ማዕበል ውስጥ ናት። በመላው አገሪቱ የተቀሰቀሰው እምቢተኝነት በመንግሥት በኩል የገጠመው ጠንካራ እጅ ብዙ ዜጎችን ለሞት፣ ለእስር፣ ለስደት እና ለንብረት ውድመት የዳረገ ሆኗል። በመሆንም ላይ ይገኛል። ይሁን እንጂ የመንግሥት የብረት ጡጫ (አይረን ፊስት) ነገሮችን ከማረጋጋት ውጪ የበለጠ ቀውሱን እያሰፋውና እያበረከተው በመሔድ ላይ ይገኛል። በመንግሥት የሚፈጸሙት መንግሥታዊ ሽብሮች ደግሞ እንደ ቀድሞው ዘመን ተደብቀው የሚቀሩ ሳይሆን በተለያዩ ዘዴዎች ለሕዝብ ዓይንና ጆሮ የሚደርሱ ሆነዋል። በአልሞ ተኳሾች የተገደሉ ወጣቶች፣ በፖሊሶች ድብደባ ሲፈፀም የሚያሳዩ አሰቃቂ ቪዲዮዎች፣ ቃለ ምልልሶች እና የተቃጠሉ ንብረቶች ዘመኑ በፈቀዳቸው ቴክኖሎጂዎች በመሰነድ ላይ ይገኛሉ። ሌላው ቀርቶ መንግሥት ራሱ በምስጢር የሚያደርጋቸው ስብሰባዎች የድምጽ ቅጂዎች የአደባባይ ሲሳይ በመሆን ላይ ናቸው። በዚህ ዘመን ተወርቶና ተፈጽሞ ተደብቆ የሚቀር ምንም ምሥጢር ምንም ወንጀል አይኖርም።

Sunday, September 11, 2016

በ“መስከረም ሁለት” ትዝ የሚለኝ

(Sep 12, 2011)፡- እንዲህ እንደ አሁኑ ዓመታት አልፈው፣ አገር ቤቱም እንደ ጨረቃ ርቆ፣ ትዝታም የሕልም ያህል ቀጥኖ፣ ልቡና ዛሬን ሳይሆን ትናንትን፣ የዛሬን አዋቂነት ሳይሆን የትናንትን ልጅነት ሲናፍቅ … መስከረም ሁለትም ከአዲስ ዘመን ተርታ በትዝታ መስኮት መምጣቱ አይቀርም። የኔ ትውልድ፣ የልጅነታችን ወራት ያለፈው፣ ከመስከረም አንድ ይልቅ መስከረም ሁለት “ርዕሰ ዐውደ ዓመት” ሆኖ ነው። እንቁጣጣሽ ከዘመን መለወጫነቱ ይልቅ የመስከረም ሁለት ዋዜማ መሆኑ የታወቀ እስኪመስል ድረስ በልጅነት አዕምሯችን የተሳለው ዐቢዩ በዓል የቅ/ዮሐንስ ማግስት ነበር ማለት ይቻላል።

JUSTICE FOR PROTESTERS BRUTALLY KILLED AND TORTURED IN ETHIOPIA: Some points on the need for prompt international action

Brief Background to the Protests and Extent of Human Rights Violations
It has been about 10 (ten) months since the protests in Ethiopia started. To be exact, protests started in November 2015 in the largest region of Oromia. Though the protests generally have compounded causes, they were triggered by the dispossession of land under the government’s Addis Ababa Integrated Development Master Plan. There were widespread claims that Oromo farmers around Addis Ababa city have been exposed to undue pressure as a result of inadequate compensation for the displacement. At the time, human rights defenders reported, though neither accepted nor effectively denied by the government, that over 400 protests had been killed by the security apparatus using excessive, illegal force. Tens of thousands are arbitrarily arrested, enforced to disappear and tortured.

Saturday, September 3, 2016

The AU’s Call for “Restraint” on the Protests in Ethiopia: Too Little, Too Late

(By Getahun S. Gesso): A Press Release issued by the Chairperson of the African Union (AU) Commission, Dr. Nkosazana Dlamini Zuma, on 1st September 2016 states that the Chairperson “is following the evolving socio-political situation over the last few months in the Federal Democratic Republic of Ethiopia with great concern.” It states that “[p]rotests have taken place in some regions following disputes over the allocation of farmland for development.” It acknowledges that “[t]he socio-political situation in Ethiopia has led to a number of reported deaths, temporary disruptions of public and private businesses, as well as occasional interruption of telecommunication services.”


The Press Release concludes with the Chairperson calling “for a high level of restraint as well as for calm to reign” and “encourages dialogue among all stakeholders in Ethiopia, in order to find peaceful and lasting solutions to the social, political and economic issues motivating the protests.”

Friday, September 2, 2016

አድሏዊ ሐዘኔታ (Selective Sympathy) ምንድነው?

አድሏዊ ሐዘኔታ (Selective Sympathy) ማለት ተመሳሳይ ችግር የገጠማቸው ሁለት ወገኖች ቢኖሩ፣ ለአንዱ አዝኖ ለሌላኛው አለማዘን፣ ወይም ለአንዱ የበለጠ አዝኖ ለሌላኛው የነካነካ ሐዘን፣ አላዘኑም ላለመባል፣ ዕንባ ሳይመጣ «ወይኔ ወይኔ» ብሎ እንደሚለቀሰው ወጉን ለማድረስ የሚደረግ ጥረት ዓይነት ነው።
ይብዛም ይነስም ሁሉም ሰው ለአንድ ጉዳይ እኩል አያዝንም። በተለይም ዓለማችን የመከራ መአት በሚወርድባት በዚህ ዘመን፣ በዓለም ላይ ያለው መከራ ሁሉ እኩል ዋጋ አያገኝም፣ ሞትም ሁሉ እኩል ትኩረት አይሰጠውም። ሁሉም ነገር አድሏዊነት ያለበት በሚመስል መልኩ በግልጽ የሚታይ ነገር ነው።
በሊባኖስ እና በሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ቦንቦች ይፈነዳሉ፤ ብዙ ሰዎችም ያልቃሉ። በምዕራቡ ዓለም በኩል ከዕለት ዜና ማጣፈጫነት የዘለለ ፋይዳ አያገኝም። ይሁን እንጂ በፈረንሳይና በቤልጂየም ተመሳሳይ ፍንዳታ እና የኣሸባሪዎች አደጋ ሲደርስ ግን ዓለም ትገለበጣለች። ይህ አድሏዊ ሐዘኔታ ብዙ ሰዎችን ያበሳጫቸዋል። «የነዛን ነፍስ ነፍስ አይደለም ወይ?» እያሉ ምርር ብለው ይጠይቃሉ።

Thursday, September 1, 2016

ከሚዲያዎች ትልቅ ጥበብንና ጥንቃቄን የምንፈልግበት ጊዜ ነው

በአጠቃላይ .......

ዘመኑ ሬዲዮና የቴሌሺዥን ከመሆን አልፏል። በሙያቸው ጋዜጠኝነት የተማሩ የተመራመሩ ሰዎች ብቻ በማንኪያ እየቆነጠሩ መረጃ የሚያቀብሉበት ዘመን አልፏል። ዘመኑ የማኅበራዊ ጋዜጠኝነት/ citizen journalism (ሁሉም እንዳቅሙ ዜና የሚዘግብበት) ዘመን ነው። ይህ ማለት ግን የሚዲያ ባለቤቶችና ባለሙያዎች አሁንም የመሪነቱን ሥፍራ እንደያዙ መሆናቸው ቀርቷል ማለት አይደለም። የተለያየ መረጃ ከሁሉም ቦታ የቃረመ ሰው እውነታውን ለማረጋገጥ ዞሮ ዞሮ ወደ መደበኛዎቹ ሚዲያዎች ብቅ ማለቱ የግድ ነው።
የኢትዮጵያውያን የመረጃ ግብይትም ከፍ ብለን የጠቀስነውን ነው የሚመስለው። አገራችን ባለችበት በዚህ ሁኔታ ዜጎች መረጃዎችን በገፍ ያቅርቡ እንጂ መረጃውን አበጥረውና አንጠርጥረው መልሰው በማቅረቡ በኩል አሁንም የሚዲያዎች ኃላፊነት እንደተጠበቀ ነው፡፡ ዘመኑ የጦር መሣሪያ ብቻ ሳይሆን የዜናና የመረጃ ጦርነትም ዘመን ነው። በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች እየተፈፀሙ ያሉትን እጅግ ዘግናኝ ወንጀሎች ሕዝቡ በመዘገብ ሚዲያዎቹ ደግሞ አቀናብሮ መልሶ ለሕዝቡ በማድረስ ትልቅ ውለታ በመዋል ላይ ናቸው። ኢሳት፣ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ወርክ እና መንግሥታዊዎቹ የአሜሪካና የጀርመን ድምጾች እንዲሁም ዋዜማ የኢንተርኔት ሬዲዮ በመረጃ ግብዓትነት የምከታተላቸው ባለውለታዎቼ ናቸው። በድረ ገጽ በኩልም ሊጠቀሱ የሚገባቸው እጅግ ብዙ ባለውለታዎች አሉን።
በግለሰብ ደረጃም ከሚዲያዎች ባልተናነሰ የዜና እና የመረጃ ምንጭ መሆን ብቻ ሳይሆን ማኅበራዊ የሐሳብ ግብይቱን (ዲስኮርሱን) ቅርጽ በመስጠት ትልቅ አገራዊ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ ያሉ ወገኖቻችን አያሌ ናቸው። ለጊዜው ስማቸውን ከመዘርዘር ልቆጠብ። ደግሞስ ማንን አንስቼ ማንን ልተው ነው?
ሥጋቴ ......
-----

Blog Archive