Thursday, April 14, 2016

ኦርቶዶክሱ ራሱን ሁለተኛ ዜጋ ያደረገበት አካሔድ

(ኤፍሬም እሸቴ) 
 እንደ ዳራ
ሁለት የባፕቲስት ሚሲዮን እምነት ተከታዮች የሆኑ ፓስተሮች ባለፈው የጥምቀት ሰሞን አገራችንን መጎብኘታቸውን እንዲሁም ከአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋርም መነጋገራቸውን በፎቶግራፎች አስደገፈው ያወጡት ዜና ያትታል። ዜናውን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ከፍተኛ መነጋገሪያ እንዲሆን ያደረገው የሁለቱ ፓስተሮች ጉብኝት ሳይሆን እንገነባዋለን ያሉት የ50ሺህ አብያተ ጸሎት ጉዳይ እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው በተባሉት በአፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ላይ (ያውም በፓርላማው መንበራቸው ላይ እንደተሰየሙ) ከዳርና ከዳር ጠምደው ጸሎት ሲያደርጉላቸው የሚያሳየው ፎቶግራፍ ነው። http://www.bpnews.net/46636/layman-plans-for-50000-churches-in-ethiopia
ከዚህም ባሻገር የጉዞ ዘገባቸው ያነሣቸው አስገራሚ ነጥቦች አሉ።
1ኛ. የጉዞ ወጪያቸውን የሸፈነላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሆኑ፣
2ኛ. ከፕሬዚዳንቱ ጀምሮ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ከመከላከያ ሚኒስትሩ እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲሁም ከአየር መንገድ ኃላፊዎችና በአሜሪካ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ጋር መነጋገራቸው እና እነርሱም በሁሉም ነገር እንደሚተባበሯቸው ቃል መግባታቸው መገለጹ፣

3ኛ. የተገኙትና ተቃቅፈው ሲጸልዩ ፎቶ የተነሡት በጥምቀት በዓል ላይ ቢሆንም በሌላው ሰው በዓል የራሳቸውን ጸሎት ማድረጋቸው ሳያንስ ለፎቶው የሰጡት መግለጫ እንዲህ ይላል፡- ግርድፍ ትርጉም፡- “የኦርቶዶክስ ክርስትና የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ። ወደ 5 መቶ ሺህ ኢትዮጵያውያን ተካፍለውበታል ይህንን የኢየሱስን ጥምቀት ለማሰብ፤ ነገር ግን በተሳሳተ የነገረ መለኮት ትምህርት የተዘፈቀ … ” ነው። /“… the Christian Orthodox Epiphany festival in Addis Ababa, Ethiopia. About 500,000 Ethiopians attended the celebration marking Jesus’ baptism but steeped in false theology.”/ ስሕተቱ ምን ይሆን?
4ኛ. ከድሮ የትምህርት ቤት ጓደኛቸው ከነበሩት ከአምባሳደር ግርማ ብሩ ጋር በመነጋገር ይህንን ጉብኝት አስፈቅደዋል የተባሉት ኢትዮጵያዊ አቶ ኃይለየሱስ አባተ የተናገሩት አንድ አስገራሚ ንግግር ወዘተ። አቶ ኃይለየሱስ የማጀቱን ባደባባይ እንደተባለው ሁልጊዜው የሚታወቀውን አንድ እውነታ እንዲህ ሲሉ መግለጻቸው ተጠቅሷል።
"For the first time in 3,000 years, it is the first time an evangelical, a Protestant person is the ruler of the country," Haileyesus said. "This is the best opportunity to get [the Gospel] there. It is up to us to use this opportunity as quickly as possible." በግርድፉ ሲተረጎም፣- «በ3ሺህ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው አንድ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የአገሪቱ መሪ የሆነው። ይህ ወንጌልን ለማድረስ ትልቅ አጋጣሚ ነው። ይህንን አጋጣሚ በፍጥነት መጠቀም የእኛ ፈንታ ነው።»
ስለዚሁ ጉዳይ ጥናት ያደረጉ የፕሮቴስታንት እምነት አጥኚዎችም ይህንን እውነታ በተለያየ ጊዜ መግለጻቸው ይታወቃል። የጠ/ሚኒስትርነቱን ሥልጣን ከአቶ መለስ ዜናዊ «የተረከቡት» ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በእምነታቸው ጴንጤቆስጤ መሆናቸው የሰጠው ትርጉም እጅግ ሰፊ ነው።
“In particular the relationship between the government and Pentecostalism has taken on a new dimension with the leader of the country, Prime Minister Hailemariam Desalegn, for the first time being not an Orthodox Christian, but a Pentecostal himself.” (Guest Editorial: The Ethiopian Pentecostal Movement – History, Identity and Current Socio-Political Dynamics, PentecoStudies 12.2/2013, page 151)
ቀጥሎ የሚመጣው ጥያቄ ባለሥልጣናት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ መሆናቸው በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ምንድር ነው? የሚለው መሆኑ ግልጽ ነው። ምንም እንኳን ፖለቲካው ከእምነት ነጻ መሆኑ በአደባባይ ቢነገርም በተግባር ደረጃ ግን የፖለቲካውና በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቤተእምነቶች ጋብቻ ስር የሰደደ፣ ፖለቲካው በእምነቶቹ ላይ ያለው ተጽዕኖም እጅግ የጠነከረ መሆኑ የአደባባይ ሐቅ ነው። አብዛኞቹ ይህንን “ያላቻጋብቻ” ተቀብለው አብረው ሲኖሩ ጥቂቶቹ ደግሞ ተቃውሟቸውን በግልጽ ከመግለጽ ወደኋላ አላሉም። ለአብነት ያህል ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ላለፉት ዓመታት ያካሔደው ሰላማዊና እልህ አስጨራሽ ትግል ምስክር ነው።

ፕሮቴስታንትን በተመለከተ ግን “መንግሥት እየተጠቀመባቸው ነው ወይስ በመንግሥት እየተጠቀሙ ነው? ወይስ ሁለቱም የሚያገኙትን ጥቅም በማሰብ አብረው እየተመጋገቡ እየሠሩ ነው?” የሚለው የብዙ ኦርቶዶክሶች በይፋ ያልተነገረ ጥያቄ ነው። ጴንጤኮጥናት/PentecoStudies መጽሔት እንዳተተው “While estimated to account for less than 1 per cent of the population in the early 1960s,1 Protestants were recorded at 5.5 per cent by the 1984 Census and 10.2 per cent by the 1994 Census.2 The 2007 Population and Housing Census counts almost 14 million Protestants, namely 18.6 per cent of the population, next to 43.5 per cent of Christians Orthodox and 33.9 per cent of Muslims.” (page 150-151) የእምነቱ ተከታዮች ቁጥር በዚህ ደረጃ ዕድገት ማሳየቱ ላይ የእምነቱና የፖለቲካው ጋብቻ ድርሻ አለው ወይንስ በእምነቱ ተከታዮች ትጋት ብቻ የመጣ ነው?

ከእምነት አንድነት በፊት የብሔረሰብ አንድነት
ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በነገሥታቱ ዘመን የነበራቸውን ሥፍራ አሁን ድረስ በስሜት ሲያነሱት መስማት የተለመደ ነው። የ66ቱ አብዮት መፈንዳት ይህንን ሕልም የሚመስል ዘመን በማሳለፉ የኦርቶዶክሶች ፀሐይ እንደጠለቀች የሚገምቱ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ቀላል አይደለም። የወታደራዊውን መንግሥት ዘመን «ፀረ ሃይማኖት» ከመሆኑ አንጻር ብቻ ሳይሆን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የኢኮኖሚና ማሕበረሰባዊ የበላይነት ያሰናከለ በመሆኑ ክርስቲያኖች ምንም ድርሻ ሊኖራቸው እንደማይገባ ያሳሰቡ አያሌ ነበሩ። ኮሚኒስታዊ ዘመንም ቢሆን የእንቅስቃሴው ሞተር ክርስቲያኖች መሆናቸው ሳይዘነጋ ፀረ ሃይማኖት በሆነው መንግሥት ዘመንም ቢሆን ክርስቲያኑ ከፖለቲካው መገለልን እንደ አማራጭ አልወሰደም። በዘመኑ የነበሩ ጥቂት ሰባኪዎች የመንግሥትን አካሔድ ባገኙት አጋጣሚ በመንቀፍ አካሄዱ ለአገር መአት የሚያመጣ ኃጢአት መሆኑን በድፍረት በመናገር ሕዝቡን ለመታደግ ከመሞከራቸው በስተቀር።
በዘመነ ኢሕአዴግ ግን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለፖለቲካቸው ያላት አመለካከት “በጠላትነት እና በተቃራኒነት” በመፈረጁ ግልጽም ሆነ ሕቡዕ ተጽዕኖዎች እንዲጣልባት ምክንያት ሆኗል። ኦርቶዶክስን በተቀናቃኝነት የሚፈርጀው ይኸው የፖለቲካ አስተሳሰብ ዘውጋዊነት /ብሔረሰባዊ ማንነት/ ላይ የሚያተኩረው ሌላው ፍልስፍናው ኦርቶዶክሱ አማኝ በእምነቱ አንድነት ብቻ ተሰባስቦ ሃይማኖታዊ ሥፍራውን ለመያዝ ሊያደርግ የሚችለውን እንቅስቃሴ ሁነኛ በሆነ ሁኔታ አምክኖታል። አንድ እምነት ካላቸው ሁለት ግለሰቦች ይልቅ አንድ ዓይነት ብሔረሰብ ያላቸው ሁለት ግለሰቦች በእምነታቸው ሳይሆን በብሔረሰባቸው እንዲተማመኑ እና እንዲተባበሩ በማድረጉ የአንድ እምነት ሰዎች በተለያየ መስመሮች እንዲሰለፉ አድርጓቸዋል። የእምነት አንድነት ሳይሆን የብሔረሰብ አንድነት አሸናፊ ሆኗል። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም መንግሥት በሚፈልገው መሠረት እንድትተዳደር በብሔረሰብ ተኮር ቤተ ክህነት ተቀርቅባለች።
የዚህ የብሔረሰባዊ ቤተ ክህነት ጉዳይ የአደባባይ ምሥጢር ቢሆንም ብዙ ክርስቲያኖች ግን ጉዳዩ ሲነሣ አይስማማቸውም። ዘረኛ የሆኑ ወይም የተዘረጋው የዘረኝነት ወጥመድ ሰለባ የሆኑ ስለሚመስላቸው አለማንሣቱን ይመርጣሉ። (ማሳሰቢያ፡- ይህንን ጉዳይ ሣነሣ ፀረ ትግራዋይ ተብዬ ልፈረጅ እንደምችል ጠፍቶኝ አይደለም። በዚህ ማስፈራሪያ ዝም የሚባልበት ዘመን ማለፍ አለበት። ለአገራችንና ለቤተ ክርስቲያናችን ስንል ብዬ ስለማስብ እንጂ፡፡) በሌላ አነጋገር በትግራዋዮች የተገነባው ሕወሐት ታማኝ በሆኑ ትግራዋዮች የተገነባ ቤተ ክህነት መሥርቷል። የእርሱን በእምነት ላይ ሳይሆን በብሔረሰብ ላይ ያተኮረ ፍልስፍና የማይቀበሉ አያሌ የትግራይ ሊቃውንት ወደዳር ተገፍተዋል፡፡ የቤተ ክህነትን ሥልጣን ለመቆናጠጥ እምነት ሳይሆን ብሔረሰባዊ ማንነት ዋነኛ መስፈርት በመሆኑ ከመንበረ ፕትርክና እስከ አቃቢትና ዘበኛ ድረስ ያለው ሥፍራ በዚህ መስፈርት ተለክቶ ለሰዎች ተሰጥቷል።
    
የቅድስት አገር ፍልስፍና ሲፈርስ
ኦርቶዶክስ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን “አገር ብቻ” አድርገው አይመለከቱም። አገራቸውን ከሃይማኖታቸው ለይተውም አያዩም።። ለሃይማኖታቸው የሚሰጡትን ቅድስና ለአገራቸው ሰጥተዋል። ቅድስት አገር ኢትዮጵያ የሚለው አባባል (ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም እንዲል) አገር ማለት ተራራና ሸንተረር፣ ወንዝና ተረተር ብቻ እንዳልሆነ ማሳያቸው ነው። ሊቃውንቱ “ሰብእ ይቄድሶ ለመካን፥ ወመካን ይቄድሶ ለሰብእ፤ ሰው ቦታን ይቀድሳል፥ ቦታም ሰውን ይቀድሳል" በሚለው ትምህርታቸው መሠረት ቅዱሳን በኪደተ እግራቸው የቀደሷት ናትና (ስለኖሩባት፣ ዞረው ስላስተማሩባት፡ ገድል ትሩፋት ስለሠሩባት፡ በጸሎታቸው ሁልጊዜም ስለማይለዩዋት፣ የተቀደሰ አጽማቸው ስለረገፈባት) ኢትዮጵያ የተቀደሰች መሆኗን ያምናሉ ያስተምራሉ። ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የሚለው የቅዱስ ዳዊት ንግግር አገሪቱ ከሃይማኖቱ እንዳትለይ ሆና የተዋሐደች ያደርጋታል። ለአገር መሥራትም ሆነ ለአገር መሞት እንደ ተራ ግዳጅ ብቻ ሳይሆን እንደ ሰማዕትነት እና እንደ ሃይማኖታዊ ትሩፋት ተደርጎ የሚቆጠረው በዚህ ምክንያት ነው። “ሀገሪቱ ሀገረ እግዚአብሔር፣ ሕዝቡም ሕዝበ እግዚአብሔር” እንዲል።
ታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ ኢትዮጵያን በጌታችን መድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልብስ፤ መርፌ ባልነካውና ባደገ መጠን አብሮት በሚያድገው የጌታ ልብስ (ኋላም አይሁድ ዕጣ የተጣጣሉበት ልብስ) ይመስሏታል። ሊቃውንት “አልባሲሁሰ ለክርስቶስ መሐይምናን፤ የክርስቶስ ልብሶቹ መሐይምናን/ምእመናን ናቸው” ያሉትን ጠቅሰው ኢትዮጵያም ለእርሱ የተዘጋጀች፣ የተስተካከለች፣ ወጥ-ልብሱ መሆኗን ያስተምራሉ። በክርስቶስ ልብስ ላይ ዕጣ እንደተጣጣሉበትም በዚህ ዘመን የክርስቶስ ልብስ በሆነችው አገር ላይ /ሊቃደዷት/ ዕጣ የሚጣጣሉ  መኖራቸውን አስተምረው አልፈዋል።

በኦርቶዶክሳዊ እምነት ላይ የኮሎኒያሊስቶች ትምህርት
“When the Missionaries arrived, the Africans had the land and the Missionaries had the Bible. They taught how to pray with our eyes closed. When we opened them, they had the land and we had the Bible.” (Jomo Kenyatta)
ኦርቶዶክሳውያን ለአገራቸው ያላቸው አመለካከት ሃይማኖታዊነትን የተላበሰ ሆኖ ለብዙ ዘመን የቆየ ቢሆንም አሁን በተግባር የሚታየው ግን ከዚያ የተለየ ነው። እንዲያውም የአውሮፓ ኮሎኒያሊስቶች በእምነት ስም ሲያስተላልፉ የቆዩት “ስለ ጸሎቱ እንጂ ስለ መሬቱ አትጨነቁ” የሚለው ጊዜ ያለፈበት ትምህርት አሁን በኦርቶዶክሱ ዘንድ መሠረት እየያዘ ነው። አፍሪካውያን ወገኖቻችን ክርስትናን ሲቀበሉ አገራቸውን እንዳጡት ሁሉ ኦርቶዶክሱም ሃይማኖቱን ለመያዝ አገሩን እያጣ በራሱ አገር ወደ ሁለተኛ ዜጋነት እየወረደ ነው። በአገሩ ፖለቲካዊ እና ማሕበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ያለውን ድርሻ ቀስበቀስ እያጣ የዳር ተመልካች ሆኗል። “የአገሪቱን ፖለቲካ በዋነኝነት የሚዘውሩት ሰዎች ከክርስቲያን ቤተሰብ የተገኙ ክርስቲያኖች አይደሉምን” ቢባል “አዎ ናቸው። ነገር ግን ብሔረሰባዊ እምነት እንጂ ኦርቶዶክሳዊ እምነት የሚያራምዱ” አይደሉም። ኦርቶዶክሳዊ እምነት ግን ከብሔረሰባዊነት የላቀ ነው። በቋንቋና ዘር ማንነት የማይቀረቀብ የእምነት ቤተሰብነት ላይ የተመሠረተ ትምህርት ነው። በእምነት አንድነት ብቻ ለይቶ መውደድን የሚቃወም በሥላሴ አርአያ የተፈጠረ ማንኛውንም የሰው ልጅ በእኩልነት እንድንመለከት የሚያስገድድ ሰማያዊ ትምህርት ነው።
ወደ ርዕሰ ጉዳያችን ስንመለስ፣ ኦርቶዶክሳውያን ቀደምት አባቶቻቸው ያቆዩትን ባለአገርነት ቀስ በቀስ እያጡ፣ ከፖለቲካው አደባባይ እየሸሹ የሄዱበት ጉዳይ የኮሎኒያሊስቶች ትምህርት ሰለባ በመሆን እንጂ በሌላ ምክንያት አይመስልም። በምንኖርበት በአሜሪካን አገር ያሉ አፍሪካዊ ዝርያ ያላቸው አሜሪካውያን በፖለቲካ ለመሳተፍ ለዘመናት የቆየ እልህ አስጨራሽ ትግል አካሂደው የመብት ባለቤት ከሆኑ ገና 50 ዓመታቸው ነው። እኛ ኦርቶዶክሶች ግን አባቶቻችን ያቆዩልንን ነጻነት በሰላም አገር እያስረከብን የአፍሪካውያን ወገኖቻችንን ዕጣ ለመቀበል እያጎበደድን ነው። እነርሱ እንኳን ያንን ቀንበር አሽቀንጥረው ከጣሉ ብዙ ዘመን ሆናቸው። ሆነም ቀረም በአገራቸው ፖለቲካ እንዳይሳተፉ ማንም አይከለክላቸውም። “የፖለቲካ ነጻነት ማጣትን/በአገር ጉዳይ አለመሳተፍን፣ ምንቸገረኝነትን፣ ምንግዴነትን፣” ኦርቶዶክሱ ታዲያ ምነው መንፈሳዊነት አድርጎ ቆጠረው?

ሃይማኖተኝነት እና ፖለቲካዊ አቋም
ችግሩ ስር የሰደደ ነው። የማንንም ምርምር ሳልሻ በራሴ የታዘብኩትን እንደ ማሳያ ላቅርብ። በአገራችን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የግሌን ሐሳብ ለማካፈል ከመወሰኔ በፊት ብዙ የራስ-ከራስ-ጋር-ውይይቶች አድርጌያለኹ። ለፖለቲካዊ ጉዳዮች ባዳ የሆንኩበትን ዘመን ባላስታውስም በይፋ ሐሳብ ለመስጠት ግን ግራና ቀኙን ማየት ጠይቆኛል። ሐሳቤን መስጠት ከጀመርኩ በኋላም ብዙ ወንድሞቼ እና እህቶቼ አካሔዴ ትክክል አለመሆኑን ነግረውኛል። ፤አሁን ያንተ የፌስቡክ ጽሑፍ ምን ሊፈይድ ነው? መንግሥት በጽሑፍ ይወድቃል?፤ ብለውኛል። ምክራቸው ከቅንነት እና እኔን ከመጠበቅ አንጻር የተደረገ ነው። ዛሬም ድረስ ይኼንኑ የሚመክሩኝ አሉ።
በሌላኛው ወገን ያሉት ደግሞ “አንተን ብሎ ዲያቆን፤ ፖለቲካህን ከምታወራ ዝም ብለህ መጽሐፍ ቅዱስህን አታስተምርም?” ከሚሉኝ ጀምሮ “ፓለቲካውን ለእኛ ተዉልን፣ እናንተ ቸርቹ ላይ አተኩሩ” እስከሚሉት ድረስ ብዙ ሐሳብ ማስተናገድ የግድ ነው። ይህ ፖለቲካ የሚሉት ነገር በእኔና እኔን በሚመስሉ ዜጎች ላይ ያለውን መዘዝም የዘነጉት ይመስላል። ኢትዮጵያዊነት የእነርሱ ብቻ ነው እንዴ? ዜግነት መብቴን በሃይማኖተኝነቴ ምክንያት ሊገፉት ሲሞክሩ ወንጀል እየፈጸሙ እንደሆነ እንኳን አይገነዘቡም። አንድን ሰው ፖለቲካዊ ሐሳብ አይኑርህ ማለት የዜግነት መብትን መግፈፍ፣ ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ (second-class citizen) ሁን ማለት መሆኑን ልብ የሚሉ አልመሰለኝም።
እንዲህ ያለው ገጠመኝ የእኔ ብቻ ሳይሆን ሃይማኖታቸውን ከምር የሚወዱና የአቅማቸውን ለማገልገል ደፋ ቀና የሚሉ ብዙ ወንድሞችና እህቶችም ዕጣ መሆኑን አሁን አሁን ተረድቻለኹ። በዚሁ ነገር የተሰላቹ አንዳንዶችም የጀመሩትን አገልግሎት ለመስጠት እንቅፋት እንደሆነባቸው አወያይተውኛል። የሚገርመው ነፍሰ ገዳዮችንና ዘራፊዎችን የሚደግፉት ደረታቸውን ነፍተው በሚሄዱበት ዘመን አትግደሉ፣ አትዝረፉ የሚሉት ተሸማቀው መሔዳቸው ነው።
መፍትሔው ወደኋላ ማለት ሳይሆን ሌሎች ሰዎች ከገቡበት ሰመመን እንዲነቁ ማድረግ ብቻ ነው። የአገራችን ጉዳይ የሃይማኖታችንም ጉዳይ ነው። ሃይማኖታችንን በአገራችን ማኖር ስላለብን። የአገራችን ፀር የሃይማኖታችንም ፀር ነው። ሃይማኖቴን አይንካ ምእመናንን ግን እንደፈቀደ ያድርጋቸው ማለት ምን ዓይነት እምነት ነው? “ፍርድ አይጓደል፣ ድሃ አይበደል” ማለት ነው ሃይማኖተኝነት።
ቱርካዊው ፀሐፊ ኤሊፍ ዣፋቅ/ Elif Shafak/ ያለውን እዚህ መጥቀስ ይገባናል። "I don’t have the luxury of being apolitical"። ይህንን በአማርኛ ተርጉሙት ብንባል፡- 1. "ፖለቲካ የማይመለከተው ሰው ለመሆን መቼ ታደልኩና" ወይም 2. "የደላው ፖለቲካ አይንካኝ ይላል።" ወይም "ችግር ፖለቲካ ያናግራል (የቸገረው በቅቤ ይበላል - እንዲል)። ወይም 3. "የቸገረው ፖለቲካዊ ጉዳይ ያገባኛል ይላል" ወይም 4. "ቢደላኝ ፖለቲካ ባላናገረኝ" .... ወዘተ ብለን ልንፈታው እንችላለን። ለአገሩ፣ ለሃይማኖቱ፣ ለማንነቱ ግድ የሚሰጠው ሰው ዝምታን ሊመርጥ እንዴት ይችላል?

የሚኖረን መንግሥት ለእኛ የሚመጥነን መንግሥት ነው
"Every nation gets the government it deserves." (Joseph-Marie, comte de Maistre)
“እያንዳንዱ አገር የሚኖረው ለእርሱ የሚገባው/የሚመጥነው መንግሥት ነው።” /ባ ጠብቆ ይነበብ/
ይህ ፈረንሳዊ እንዳለው ክርስቲያኖች በአገራቸው ጉዳይ ሊኖራቸው የሚገባቸውን ድርሻ አሳልፈው በሰጡ መጠን እምነታቸውንና ታሪካቸውን፣ ሰብዓዊነታቸውንና ማንነታቸውን የሚያጎድፍ መሪ ይጫንባቸዋል። በሥላሴ አርአያ የተፈጠርን እንጂ በእንስሳት አርአያ የተፈጠርን እስካልሆንን ድረስ ክቡር ለሆነው ተፈጥሯችን የሚስማማ ኑሮ ይገባናል። በጥምቀት የከበረች ሕይወታችንን በኑሮም ልናስከብራት ይገባናል። ክርስቶስ የሞተለት የሰው ልጅ ከእንስሳት ያነሰ ሊኖር አይገባውም። ቅዱስ አምላክ ለቅድስና ፈጥሮናል፣ ክቡር አምላክ ለክብረት እንጂ ለውርደት አልፈጠረንም። የተፈጠርንለት ዓላማ ራሳችንን ማክበርን ያስተምረናል። በዘር የተከፋፈለ፣ በድህነት የደቀቀ፣ ተስፋ ያጣ ኑሮ ይመጥነናል?
ይህ ተረት እንዳይተረትብን እሰጋለኹ። በጣሊያን ፋሺስቶች ዘመን ነው አሉ። መሬቱን እያረሱ፣ ድንጋዩን እየፈረከሱ፣ ተራራውን እየበሱ፣ መንገድ ይሠራሉ። በአድዋ ዘመን በከብት ጀርባ መሣሪያ ጭነው የመጡ ሰዎች፤ ከ40 ዘመን በኋላ በታንክና በአውሮፕላን እንዲሁም በመርዝ ጋዝ ታግዘው ስለመጡ፣ አገሩን ለመቆጣጠር መንገድ መሥራት የግድ ነበር። እና .... በዚያ ዘመን ... ድንጋዩን ሲፈነቅሉ፣ ... ሲሰባብሩ፣... ያዩ አንድ ሰው፣ ድንጋይ ድንጋዩን እያዩ እንዲህ አሉ ይባላል፦ "ይበልህ!!! አንተም መጎለቱን አብዝተኸው ነበር።"

መንግሥት በፕሮቴስታንቶች ወይስ ፕሮቴስታንቶች በመንግሥት ተጠቀሙ?
የዚህ ጽሑፅ ምክንያት የሆነው የባፕቲስት አምነት አራማጅ ፓስተሮች ደረጉት ጉብኝትና ዘገባቸው እንደመሆኑ በዚያው ሐሳብ ጽሑፌን ላጠቃልል። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እምነቱን ማስፋፋት መብቱ ነው። 50ሺህ ቤተ እምነት ለመሥራት ማቀዳቸው መብታቸው ነው። ተቃውሞ የለኝም በግሌ። የሁሉም ዜጋ መጠቀሚያ በሆነው ፓርላማ የግል እምነታቸውን ማራመዳቸው ግን ስሕተት ነው። አሁን ከዘገዩና ሁለት ፀጉር ካበቀሉ እምነቱን የተቀላቀሉት አባ ዱላ በያዙት ሥልጣን እና ወንበር ያሳዩት ድርጊት የበታቾቻቸው በየጊዜው ሲያደርጉት ያየነው ነው። ጥያቄው የመንግሥት ሥልጣን የያዙት ፕሮቴስታንት ኢትዮጵያውያን በመንግሥት እየተጠቀሙ ነው ወይንስ መንግሥት በእነርሱ ተጠቅሞ ዓላማውን እያከናወነ ነው? የሚለው ነው። በእኔ አመለካከት ሁለቱም ይመጋገባሉ ባይ ነኝ።
መንግሥት የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ቀዝቀዝ እንዲል “ሪፎርምድ” የሆነ ኦርቶዶክስነትን ይፈልጋል። ከዘመኑ ጋር የሚሔድ ለብ ያለ፣ በራድም ትኩስም ያልሆነ ኦርቶዶክስ። ለዚህ ደግሞ በፕሮቴስታንቶች ፊትአውራሪነት የተጀመረው “የሪፎርሜሽን”/የተሐድሶ/ እንቅስቃሴ መልካም አጋጣሚ ነው። ይህንንም ራሳቸው በይፋ የሚናገሩት ሐቅ ነው። የሚከተሉትን ሁለት ጥቅሶች አዲስ ተስፋዬ ከጻፈው ጽሁፍ ላይ ማግኘቴን አስታውሼ ላስነብባችሁ።
1.      “The evangelist is hopeful that the seeds of revival are being planted and nurtured in the estimated 34,000 Orthodox churches in Ethiopia and abroad. So far more than 600 people have successfully completed the two-week course.” /Revival and Persecution in ETHIOPIA፤/http://www.charismamag.com/blogs/189-j15/features/africa/530-revival-and-persecution-in-ethiopia/
2.     “Today, many underground movements are operating within Ethiopian Orthodox Church, some with evangelical and others with Pentecostal convictions. … Some of these movements exemplify attempts at religious innovation, though it is hard to plot their trajectories because of their hidden nature and complex character. Such developments are affecting wide ranging areas of the established structure of the Orthodox institutions, such as Sunday Schools, the mahibers, the monastic centers, and even the local churches in major cities.” /Tibebe Eshete The Evangelical Movement in Ethiopia: Resistance and Resilience 2009፡ ገጽ 61. Bayor University press/
ይህ በሰው ቤት ገብቶ ማንጎዳጎድ በኦርቶዶክሱና በፕሮቴስታንቱ ኢትዮጵያዊ መካከል የሚፈጥረው አለመተማመን፣ መቃቃርና ጥላቻ ለአገራችን የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። ፈረንጆች ባላቸው ንቀት በትምቀት በዓል ላይ እንኳን ተገኝተው ከክርስትና ውጪ የሆነ ነገር እንደተፈፀመ ለመናገር መድፈራቸውን ለጥቁሮች ካላቸው ንቀት ወይም ከገቡበት ድንቁርና አለመንቃታቸውን መመዘን ሲገባን በገዛ ራሳችን ሕዝቦች መካከል አለመተማመንን መፍጠር አይገባም ነበር። አሁንም በአስተሳሰባቸው እና በኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነታቸው የነቁት የፕሮቴስታንት እምነት ሊቃውንት ቁስሉ እንዲጠግግ ማድረግ መቻል እንዳለባቸው ይሰማኛል። ተሐድሶው ላይሳካ ጥላቻ መዝራቱ አይረባንም።

ይቆየን፤ ያቆየን
(ኤፍሬም እሸቴ) (ephremeshete@gmail.com/ www.adebabay.com) 


30 comments:

semaw said...


It is a well thought and articulated piece. It is time to makeup for the lost time now. Rejim Edime yadililen
wondimalem!!

Anonymous said...

እንደ ሁልጊዜው "አባባ" የሚያሰኝ እይታ ነው። የሰዉ ልጅ ጠያቂ ካልሆነ አዛኝም ሆነ ሰሚ የለውም። መልካምን ነገር ከእጅ ካመለጠ በኋላ መቆጨቱ ዋጋቢስ ከንቱ ልፋት ነው። ዛሬ ግብረ ሰዶማዊው ያለ ሐፍረት "መብቱን" በሚጠይቅበት ዓለም፡ ብሔርተኝነት ዐይኑን አፍጦ ጥርሱን አግጦ በሚታይበት ዘመን አጉል ይሉኝታ የመልካም ምግባር መገለጫ ሊሆን አይችልም። ኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት አልተገዛችም ሲባል ወራሪን "ገድላ" ነው። መግደል በሌላ ዕይታ ያልተፈቀደ ነው ሊባል በቻለ ነበር። "ነጻነት ነጻ አይደለም" የሚለው ብሒል እንዲሁ የተነገረ ሳይሆን መነቀፍን፡ መገለልን፡ ሲያልፍም መገደልን ሊያስከትል እንደሚችል እየታወቀ እሚታገሉለት እንደሆነ የሚያሳይ ነው እንጂ።
መልካሙን ይግጠምህ

Tewodros Tesfaye said...

ene begle haymanot yelegnm neger gin betselot amnalew yetegnawm emnet teketay le ethiopia ketseleye tru negere new inj kifat aytayegnm. neger gin ethiopia yehulachi nech ethiopian lezelalem simeru yeneberu ortodogsoch nachew yaworesun gin dihinetina yeandi zere yebelaynet nw. bezaq sat and yelela haymanot teketay kireta alkerebem gin zare gn zena sajemere gin menchachat jemerachu. begile le ethiopia yemimegnew tru sewn new enj ortodox haymanot teketa woym protestant aydelem...

Anonymous said...

Ayee,ityopia bezih huneta alekelat. Ortodoxin mekenaken ketejemere eneho 40 amet honotal. Bemekakelegnaw misrak ortodox lematfat bemuslimoch ena bem'eraboch eyeketele n'ew. Egna kezih netsa enihonalen blen yihew kuch bilenal. Ende antena tikit sewoch nachew yemitagelut

Anonymous said...

Thank you .

Anonymous said...

-አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በአንድ ወቅት በአንድ ጋዜጠኛ ኢንተርቪው እየተደረገላቸው እንደዚህ አይነት ጥያቄ ጠየቃቸው ‹‹በሂወቶ በጣም ያዘኑበት ሁኔታ ካለ ቢገልጹልኝ ክቡር ምኒስትር›› ብሎ ጠየቀ፡- አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም እንዲህ ሲል መለሰ ‹‹በሂወቴ በጣም ያዘንኩበት ድርጊት ወይም ገጠመኝ ‹አባቴ ጌታን ሳይቀበል መሞቱ!› እስከ አሁን በጣም የሚያሳዝነኝ የህይወቴ ገጠመኝ ነው›› ብለው መለሱ፡፡
-ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም (የቀድሞ የፌዴሬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የአሁኑ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር) የበቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ቀርቦ ቃል በቃል እንደዚህ አለ፡- ጉባኤውን ፍጹም በደፈረ ሁኔታ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ኦርቶዶክስ ትክክል ነው የሚል የለም!፤››
- ቀጥሎም እንዲህ ሲል አወጀ፤ ‹‹የአንገቱን መስቀል ጉዳይ ተውት፤ እሱም ቢሆን የጊዜ ጉዳይ ነው፣ ይወልቃል! ይበጠሳል!!›› ቃል በቃል ለመንግስት 500 ያህል መካከለኛ አመራሮች በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ ውስጥ በስልጠና ላይ የተናገረው ያወጀው ነው፡፡
እስከ ዛሬ በዚህች ቤተክርስቲያን ላይ … አቶ … እገሌ … ስንት ብለዋል ፣ ስንት ዝተዋል … ፤ በተግባርም አሁን አባዱላና መሰሎቻቸው ባገኙት ቅጽበት ሁሉ እየፈጸሙ ያሉት ተግባር የሩቅ ጊዜ እቅዳቸው እስከ አሁን የተጓዙባቸው ሂደቶች ናቸው …

Negussie said...

Yes, I also say it is no time to keep silent. If so will end up with great loss! We have to shout to God and tell the truth those shameless and violent intruders!

Mulugeta Ashango said...

እኔ ያልገባኝ ያንድ ሀገር መሪ ፕሮቴስታንት መሆኑ ምንድነው ችግሩ? ወይስ ኦርቶዶክስ ካልመራ አገርቱ ሰላም አታገኝም? ይሄን ህል እንባ ያስነባል እንዴ? ደግሞም ፀልየው ስለጀመሩ ነው የከነከነህ?

Eskindir Mesfin said...

ለመሆኑ ግለሰቦች ስልጣናቸውን አላግባብ የሚጠቀሙባት የግል ፍላጎት እና እምነታቸውን ምክር ቤት የሚያራምዱባት ዜጎች ግን በህግ ፊት እንኳን የተፈቀደላቸውን የሚያጡባት ይህች ሀገር የማን ናት?

Eskindir Mesfin said...

ለመሆኑ ግለሰቦች ስልጣናቸውን አላግባብ የሚጠቀሙባት የግል ፍላጎት እና እምነታቸውን ምክር ቤት የሚያራምዱባት ዜጎች ግን በህግ ፊት እንኳን የተፈቀደላቸውን የሚያጡባት ይህች ሀገር የማን ናት?

Anonymous said...

ኤፍሬም እንደተለመደው ለመሞዳሞድ ሳትሞክር የግለ አመለካከትህን በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ለማንሳት መድፈርህ ሀገራችን እና ማኅበረሰባችን የመታው “የአደባባይ ምሁራን “ ድርቅ ላይ እንዳካፋ ጠል ነው ያየሁት። ማንኛው ሰው የተሰማው እና በጎ የመሰለውን ሃሳብ ደፈር ብሎ ለአደባባይ ሲያቀርብ ባያስማማ እንኳ ለውጤታማ ውይይት ያነሳሳል። ያለበለዚያ የተደበቀ እና በሽኩሹክታ የሚደረግ ውይይት ለማኅበረሰቡ የተሳሳተ መረጃ ለመዝራት እና ለጽንፈኝነት በር ይከፈታል። ፊደል የመቁጠር ትርጉሙም እንዲህ ደፈር ብሎ ለመናገር ካላበቃ ምንም ጥቅም ያለው አይመስለኝም። ስለሆነም ምሥጋናዬን ላስቀደም።

ወደ አነሳሀው ጉዳይ ስንመጣ የዘመኑ ባለሥልጣናት በሥልጣን ለመቆየት (የፈረንጆቹን ትኩረት ላመሳብ) ማንኛውንም ነገር ከማድረግ እንደማይመለሱ ተደጋግሞ ታይቷል። ባይሆን ኑሮ በሀገራቸው የበጉ አድራጎት ሥራዎችን የሚፈጽሙ ሀገር በቀል ተቋማት በየአጋጣሚው ሥራቸውን በአግባቡ እዳይፈጽሙ በሚሰጉበት ሀገር፥ በሀገራቸው ሃይማኖትን እርግፍ አድረገው የጣሉና ስመ እግዚአብሔርንና ሃይማኖትን ለፖለቲካና ኢኮኖሚ ዓላማቸው ማስፈጸሚያ በመጠቀም ለሚመጡ ሁሉ ሀገራችንን ክፍት ባላደረጉ ነበር። ይህንን ከሃይማኖታዊ ወገንተኝነት ነጻ ሆነን ብናየው ፍጹም አግባብ ያልሆነ ተግባር ነው። ከ90% በመቶ በላይ ዜጎች ሃይማኖተኛ በሆኑባት ሀገር ቃለ መሐላ በእግዚአብሔር ስም እንዳይፈጸም በተከለከለበት እና “እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ” ሲባል ከዳር እስከ ዳር በሚስቅ ፓርላማ ውስጥ በፈረንጅ ጸሎት የሚደረግለት “ባለ ሥልጣን” (ምንም እንኳን መዶሻው ከመሸከም ያለፈ ነጻነት ባይኖራቸውም) መታየቱ ህገ ወጥነት እንዴት በሀገራችን እንደተንሠራፋ የሚያሳብቅ ነው። ይህ ሲባል ግን በፓርላማችን ውስጥ ስመ እግዚአብሔር አይጠራ ማለት ሳይሆን ጸሎትና ካህን በሞላባት ሀገር ለምን በፈረንጆቹ ፓርላማው ተደፈረ ለማለት ነው።((እኔ እዚህ ጋ የምንቃወመው ሰዎቹ ከጀርባቸው የያዙትን የአፍዝ አደንግዝ ትብታብ እንጂ የሚያምኑትን እምነት ብቻ አይደለም።ለነገሩ እነርሱ በዶላር እንጂ በሌላ በምንም እንደማያምኑ የታወቀ ነውና።)

ለኦርቶዶክስ አማኞች ከፖለቲካው ዓላም መገለል ብዙ ምክንያቶች ሊጠቀሱ ቢችሉም በዋነኛነት በሀገራችን ለተተከለው የዘውጌ ፖለቲካ ምእመናኑ በተለይም ወጣቱ ትውልድ ካለው ከፍተኛ ጥላቻ የተነሳ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። በገዥውም ሆነ በተቃዋሚ ፖርቲዎች ዘንድ የሚታየው በመርህ ላይ ያልተመሠረተ ፖለቲካ ድሮውንም ቢሆን “ፖለቲካና ኤሌክትሪክ ከሩቁ” ለሚለው ኢትዮጵያዊ ጥሩ የመሻሻ ምክንያት ሆኗል። የሚያሳዝነው እውነተኞቹ ክርስቲያኖች የተጠየፉትን ፖለቲካ እምነትን የምድራዊ ስኬት ማደላደያ አድርገው የሚያምኑ (በፈረንጆቹ የተቀረጹ) መናፍቃን፣ ለሆዳቸው ያደሩ “ምሁራን” እና በዘር ፍቅር የሰከሩ ጎጠኞች ተቆጣጥረውት ስለሀገር የሚናገርም ሆነ የሚጽፍ (የጻፈውንም like የሚያደርግ ሁሉ) “ፖለቲካኛ” ተብሎ ከእምነት ወገኖቹ እንዲገለል እና ሀገር አልባ እንዲሆን በየቤተ እምነቱ እየተሠራ ነው። ከሁሉም በላይ የሚገርመው እና ለመረዳት የሚያዳግተው ደግሞ “ጅቡ እየበላ ያለው የእኔን እግር ስለሆነ ዝም በሉ” በሚሉና ዝም የሚያሰኙ “ሰባኪያን” ጉዳይ ነው። በየቀኑ ብሄራዊ ማንነት እየጠፋ፣ እንደ ሀገር የሚያግባቡን እሴቶች ቀን በቀን እየተሸረሸሩና እየጠፉ፣ በየመድረኩ ሀገራቸውን እንደሚወዱ የሚናገሩ ነግር ግን "የሚወዷት" ሀገራቸው ዜጎች ጉስቁልና የማይሰማቸው፣ ለተገፋው ሳይሁን ለገፊው ጥብቅና የሚቆሙ በአጠቃላይ ምን እያደረጉ እንደሆነ የማይረዱ “ክርስቲያኖች” እየተበራከቱ መጥተዋል። ይህንን አዙሪት መስበር የሚቻለው ሁሉም ዜጋ ከወገንተኝነት በጸዳ ሁኔታ ለሰው ልጅ እኩልነት መቆም በተለይም ለሃይማኖት ሰዎች ግዴታ መሆኑን በአግባቡ መረዳት ሲቻል ብቻ ነው።

Demissie Brile said...

@Mulugeta Ashango,
Why you jump to negative criticism before you read the whole message carefully!!! If you have positive thought, you get the answer in the article.
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እምነቱን ማስፋፋት መብቱ ነው። 50ሺህ ቤተ እምነት ለመሥራት ማቀዳቸው መብታቸው ነው። ተቃውሞ የለኝም በግሌ። የሁሉም ዜጋ መጠቀሚያ በሆነው ፓርላማ የግል እምነታቸውን ማራመዳቸው ግን ስሕተት ነው።

Unknown said...

The issue is the govt is helping in building church. This mean the govt over stepped in religious affairs of the people. I smell corruption !!!

Mam Dad said...

OMG . . best perception

Tullu said...

No argument with flesh and blood, Jesus is the way, the truth, and the life. No other way, but only through him that man can get to heaven John 14:6. The kingdom of God operates only with love, no less. Tone down, no born again christian is willing to argue, but love. It is too late to stop gospel.

Anonymous said...

Before 40 years ago orthodox was attached with government. Nothing is changed in the country. after EPRDF came all religions are equal. Especially the protestant extremely grow up to 20 million. Most of government officials are protestants.

The main problem in orthodox

1. does not preach Bible
2. full of criticism
3. Division Among them
4. corruption
5. refusing to accept technology

so, i swear orthodox after 10 years will dominated by others.

Anonymous said...

አየ እንደ አንተ አይነቱ የእርጎ ዝንቦች በዝተው ነው። የተጻፈውንም እንኳን በውል አያነቡም ጻሐፊው ለማለት የፈለገውን ጽሑፉን ብታነበው ታገኘው ነበር። ችግር ቢኖረውማ ኖሮ እስካሁን ዝም ባልተባለ ነበር። ችግሩ የድፍረታቸው ብዛት ከልክ ማለፉ ነው፦ በጥምቀታችን ላይ ተገኝተው ትክክል አለመሆናችን በድፍረት ነገሩን፤ ቀጥለውም ወንጌል አልተሰበካባትም አሉ ሀገራችንን፤ ሲቀጥል ሁሉም ሐይማኖቶች ተቻችለው በሚኖርባት ሀገር ፓርላማ ተገኝተው ድፍረታቸውን በግልጽ አሳዩን። ይህ ነው ወዳጄ የጸሓፊውና የብዙዎቻችን ህመም። አሁንስ ችግሩ ገብቶ ይሁን????

Dawit Abrham said...

አንዳንድ ሰዎች ‹‹በምስሉ ሰውዬው የግል እምነታቸውን በሚፈለጉበት መንገድ መግለፃቸው ሊነቀፍ የሚገባው አይመስለኝም።›› የሚል አስቂኝ አስተያየት ሲሰነዝሩ አጋጥሞኛል፡፡ ወንበሩ እኮ የሃይማኖት ተቋሙ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የሀገሪቱ መንግሥት ወንበር ነው፡፡ በዚህ ወንበር ላይ ማንም ድንበር ተሻግሮ የመጣ ነጭ ሊጨፍርበት አይገባም፡፡ የተሠራው ስህተት ሃይማኖትን ከመንግሥት ጋር የሚያላጥፍ ወንጀል ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ሉዓላዊነቱ የሚጻረር ነው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ኹኔታውን ከመለስ መስቀል መሳለም ምስል ጋር ሊያመሳስሉት ሞክረዋል፡፡ መለስ መስቀል ቢሳለም ግላዊ መብቱ ነው፡፡ አባዱላም ቢሆን የፈለገው ቦታ ሔዶ እምነቱን የማራመድ ግላዊ መብት አለው፡፡ በፓርላማ ወንበር ላይ ማጸለይ ግን ሕገ መንግሥቱን መጣስ ነው፡፡

Anonymous said...

Never Accomplished such a hidden and satanic mission!! God will defend it!!

Anonymous said...

I Appreciate the sense of belongingness by the blogger to the Ethiopian Ortho Church. But sorry to say that you are still reflecting your hatred towards other religions. Claiming as if Orthodox is the only and only religion within Christianity. No no. There is no religion as such in the face of God. This is a false claim by people and the clergy. Orthodox has got a good culture inherited from Old Testament period (which is before Christ). But what does this old culture do for the people? Do we get into heaven following this crap? Does this church recognize Jesus after all? I have doubts...I cannot see Ethiopian orthodox church any different than the Jews. culture, culture,... tradition, tradition.... The church is not preaching the Gospel at all(you may argue here, but the reality is no) Do you think that this Ethiopian Orthodox church will survive another decades? No I do no think so. Its life is very short whether we/you like it or not.

Anonymous said...

US house of representatives and senators pray frequently in congress. They have a Chaplin or priest assigned to serve their spiritual need. There is also a group of congress members who regularly pray in special prayer room inside congress. White house have prayer breakfast and national day of prayer. Separation of Church and State does not mean separating the politician from his belief. Tolerance is the rule of the land. You have the right not to believe or believe in something else.

Anonymous said...

Thanks brother. We need to be honest to face the truth; only the truth. No less or no more. Woyane is the enemy of Orthodox. WoyNe has a clear plan to eliminate Orthodox and we need to accept this bare fact. The other actions of other anti Orthodox groups are supportive action for the fulfilment of Woyane mission.

Shenkut

Anonymous said...

This is well written. Thanks. I came across a post at the link below and thought an addition to the discussion.
http://ethiopianchurch.org/en/editorial2/205-%E1%8B%AD%E1%8B%B5%E1%88%A8%E1%88%B5-%E1%88%88%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8B%8D%E1%8B%AB%E1%8A%95.html

Anonymous said...

@Anonymous April 15, 2016 at 5:03 AM. What about you? What are all your baseless claims against the Orthodox church implying? Your fairness? Aren't you happy in what the speaker of the house did? Is this recognition for the co-existence of several religions in the country? The speaker is there for a political purpose entrusted by the Ethiopian people. What do you say about the breach of trust he committed? Could you have been happy had this same thing been done by other religions? While you are free to belong to any religion, being unfair and promoting illegal deeds is not the manifestation of Christianity. If you have the gut to speak the truth, why don't you say something on the agenda--does the speaker have the right and the legal ground to let the religious leaders of a foreign country pray on that place where all the Ethiopian people are represented?

Elias N. said...

Hi Tewodros,
What you said is your opinion so you're entitled to have one. The thing is our poverty didn't have direct relation with orthodox church. It's rather lack of modernization and long history of war against foreign aggressors and domestic power struggle and of course the feudalism. So reading isn't a bad thing to do, so read!
The orthodox isn't asking for someone orthodox to be appointed as ahead of state, it's a question of securalism here. Officials should be neutral enough when they seat at office and keep their religion privately. That's all.

Andinet said...

great idea Ephrem ...it is nice to see you back. where have you been ?...your blog was inactive for about 5 months. I love your blog ...keep the good work

gedamu gebreyesus said...

Q1. What is main Objective of Ur message? Q2. Do you believe this, as the right way of teaching the people to make a positive difference between US.

Anonymous said...

Wow spot on. Even though you may judge me as a Protestant and I do indeed believe in Christ, I don't like the idea of a segregated religious mentality. I have deep and profound respect to the Orthodox Church. I also admire a lot of things (mostly the nationalism) I see in the orthodox tradition.Whoever disrespects the orthodox church is foolish in my view. For she deserves nothing but appreciation for how she kept the country as a christian state throughout the ages and also how she affects the culture to the point we all now say during greetings "Egziabher Yimesgen". The only major setback for the orthodox faith is it's lack of progress as outlined so well above. At the same time the Protestant church as the opposite problem. We tend to be more western than Ethiopian if u know what I mean. Having said this, articles like this need to be presented with a little more objectiveness or at least respect to the other faiths as well. In other words the writer of this article should also respect the other faiths and refrain from judging every Protestant believer as part of some big conspiracy against Ethiopia and the Orthodox Church. Don't say "the Protestants". Just say "some missionaries". I clearly remember pictures of our former prime minister kissing an orthodox cross being sold everywhere about the time he died. No one said/accused all of the orthodox believers for conspiracy against the rest of the country. But now that a protestant is working as a head of state you start panicking. I dont like your tone of disrespect/disgust when u speak of the protestants. However still, I agree with what you said in that (if at all what you said happened and the pictures are real - coz am not sure) I think what Aba Dula did was wrong. Simply because his seat in the Parliament is a symbol of every Ethiopian represented there. As to the missionaries who made remarks saying "false theology", I can see why it may come off as offensive and disrespectful specially with them coming in this land and witnessing it themselves. They definitely could have been more "diplomatic" in their remarks. But I urge you to ask yourself, "if I was in their shoes and saw a strictly Baptist event that I didn't believe in, wouldnt I say that it was false as well?" Of course that is not to say that they are right in how they said it... Overall I am happy to have across this but for next time, please be a little more "diplomatic" yourself when writing such an article. Trust me you will still be understood and heard. No need to be rash.

sam said...

This bastards think they own this country, shameful things happens in this country everyday.
We have so many problems not one of them is not believing in Jesus, we where believing the messiah before he came to this world, before the country called Germany(the source of this shit called religion).

I am not trying to be anti any religion but this fuckers(pasters) they are playing us the old fashion way while we believe in their religion they rob us off of our heritage, history and all the knowledge that we posses through this beauty called orthodox church.

Do all u want to do fuckers this church ain't going any where.

Anonymous said...

በምእራቡ ክፍለዓለም የክርስትና እምነት ባዶና ከንቱ ሆኖባቸው፤ እምነቱ ቅጡን አጥቶ የጌይና የሌዝብያን አማኞችን እያፈራ ያለ ሲሆን። ጅብ በማያቁት ሃገር ቁርበት አንጥፉልኝ አለ እንደተባለው እምነት የጠፋባቸው ግለሰቦች በድፍረት ፓርላማ ገብተው ጸለዩ? ይገርማል።
በማንነታቸው ጥላቻ የተቃጠሉትን ምስኪን የዋሃንን ወገኖቻችን ወደዚህ "እምነተ ባዶ ማህበር" በሰፊው እያጠመዱት ወደገደል እየገፉት ማየትን የመሰለ አሳዛኝ ሁኔታ የለም። ግን ሰው የራሱን ማንነት ከጠላና የሌላን የሙጢኝ ብሎ ከያዘ ምን ታደርገዋለህ? እምነቱንም ቋንቋውንም በአስከፊ የፖለቲካ ስርአት ምክንያት ስለጠላሁት ከዚህኛው አዘቅት ገብቼ ብቻ ከራሴ እኔን ከሚመስሉኝ መላቀቅ አልብኝ ባዮች የበዙበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። እነኛም ጠፍተዋል እነኝህም ለመጥፋት ጥድፊያ ላይ ናቸው።