Friday, April 22, 2016

ልብሱን በወይን ያጥባል፥ መጎናጸፊያውንም በወይን ደም (ዘየሐጽብ በወይን ልብሶ)

የራስ-ከራስ-ጋር-ጨዋታ

እየደጋገምኩ ባነበብኩት እና ዜማውን ባስታወስኩ ቁጥር አንዳች ስሜት ልቤን ያናውጸዋል።
የሆሳዕና ሥርዓተ ማኅሌት ተፈጽሞ ሥርዓተ ቅዳሴው ከመጀመሩ በፊት ሥርዓተ ዑደት በሚፈጸምበት ወቅት አራቱም ወንጌላት ይነበባሉ። ይኸውም ሊቃውንቱ የዕለቱን ድጓ እየቃኙ ይመራሉ፣ ዲያቆናቱም ከመዝሙረ ዳዊት የዕለቱን በዓል የተመለከተ ምስባክ ይሰብካሉ፣ ካህናቱም በዓሉን የተመለከተ ወንጌል በዐራቱም መዓዘን እያነበቡ ቤተ መቅደሱን አንድ ጊዜ ይዞሩታል፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ከመነበቡ በፊት የሚዜመው ዜማ የክርስቶስን መከራ ሞቱን የሚያጠይቁ ኃይለ ቃሎች ይዟል። ሊቃውንት አባቶቻችን በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 49 ላይ የሚገኘውን ጻድቁ ያዕቆብ ልጆቹን የነገራቸውን ታሪክ በማንሣት፣ ለይሁዳ የተነገረውን እና ስለ ክርስቶስ የተተነበየውን በማመስጠር ያስቀመጡበት ድንቅ ምሥጢር ነው።

“ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል፤ እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው፤ የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ። … በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ … ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል፥ የአህያይቱንም ግልገል በወይን አረግ፤ ልብሱን በወይን ያጥባል፥ መጎናጸፊያውንም በወይን ደም።” (ዘፍጥረት 49: 8-11)

አቡን፡-

“ሃሌሉያ (6 ጊዜ)
ባረኮ ያዕቆብ ለይሁዳ ወልዱ፣
ወይቤሎ ሀሎ ንጉሥ ዘይወጽእ እምኔከ፤
ዘየሐጽብ በወይን ልብሶ፤
ወበደመ አስካል ሰንዱኖ፤
ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ፤
ይብሉ ሆሳዕና በአርያም።”

ምልጣን፡-

“ዘየሐጽብ በወይን ልብሶ፤
ወበደመ አስካል ሰንዱኖ፤
ንጉሦሙ ለእስራኤል ውእቱ፤
ይብሉ ሆሳዕና በአርያም።”

ሕዝቡ በመቀባበል እንዲህ ያላሉ፡-

“ይብሉ ሆሳዕና በአርያም።”


2 comments:

Andinet said...

good post Ephrem. I love your idea about Hosahna and your professional geze writings... check my blog as well ...at http://gonder.blog.com/

Tigist Mulugeta said...

የዲያቆን ዳንኤል ክብረትና ያንተ ፅሁፍ ይለያል ይሄ እንዴት ይሆናል እባክህ መልስልኝ