Sunday, August 28, 2016

ሊታይና ሊደመጥ የሚገባው መልእክት

ሊታይና ሊደመጥ የሚገባው መልእክት
+++++
ስለ እውነት የሚናገሩ ብዙ ሰዎች አሉ። አንዳንዶቹ «ለእውነት የሚቆሙት» ጥቅም የሚያገኙ ሆኖ ሲታያቸው ብቻ ነው። አንዳንዶች ግን ስለ እውነት የሚቆሙት ቀጥሎ የሚመጣው ውጤት የሚጠቅማቸውም ሆነ የማይጠቅማቸው መሆኑ ብዙም ሳይሰቅቃቸው ነው። በመጀመሪያው ዘርፍ ያሉ ብዙ አፈ ጮሌ ሰዎች እናውቃለን። ከነዚህ አፈጮሌዎች መካከል ደግሞ ብዙዎቹ በምንኩስና በቅስና ስም ስለ እውነት ሳይሆን እውነትን ረግጠው የቆሙ ናቸው። ይሁን እንጂ ስለ እውነት ከመናገር ወደኋላ ከማይሉት እና በሌላ የሕይወታቸውም መስመር በእውነትና በትህትና ሲመላለሱ ከማውቃቸው መካከል በቪዲዮው ላይ የምንመለከታቸው ቀሲስ አሸናፊ ዹጋ (Ashenafi Wake) አንዱ ናቸው። ከዚህ በፊት ያስተላለፏቸውን መልእክቶችም በጥሙና ተመልክቼ ሳበቃ ለርሳቸው የነበረኝ ሐሳብ ትክክል መሆኑን የበለጠ አረጋግጦልኛል። እንድትመለከቱም እጋብዛለኹ፡
በዚህኛው ቪዲዮ ለቤተ ክርስቲያናችን አባቶች (በአገርም በውጪም) ላሉት እጅግ በትልቅ ትህትና ጥሪ አቅርበዋል። በቪዲዮው ሁለተኛ ክፍል ለጠ/ሚ ኃ/ማርያምና ለባለስልጣኖቻቸው ጥሪ አቅርበዋል፤ ተግሳጽም አስተላልፈዋል። ይህንን በቃለ እግዚአብሔር የተመላ እና እውነቱን በግልጽ የሚያቀርብ መልእክት በጎ ኅሊና ላለው ሰው ማድረስ ተገቢ መሆኑ ስለተሰማኝ እነሆ «ሼር» አድርጌያለኹ።
ረዥም ዕድሜ ይስጥልን፤ ቀሲስ።


No comments:

Blog Archive