Monday, September 26, 2016

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ? እኛስ ምን እንበል?

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በ2009 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ የደመራ በዓል ትምህርታቸው ታሪካዊ መልእክት አስተላልፈዋል። በትምህርታቸው የሚከተሉትን ዐበይት ነጥቦች ጠቅሰው ተግሳጽና ማጽናኛ መልእክት አስተላልፈዋል። ከጠቀሷቸው ኃይለ ቃሎች ከብዙው በጥቂቱ፡-
«እንደ ፖለቲካ ሳይሆን እንደ ሃይማኖት መናገር ያለብኝን ነገር መናገር አለብኝ ብዬ አምናለሁ፤ መንግሥትንም ቢሆን»፤ 
በቀይ ሽብር ዘመን የተፈፀመውን አስታውሰው ይኸው ታሪክ እንዳይደገም አስጠንቅቀዋል፣
ችግርን መፍታት የመንግሥት ኃላፊነት እንደሆነ፤ መልስ መስጠት እንዳለበት፣ ሰዉ ጩኸቱን እንዲያቆም መልስ መስጠት እንደሚያስፈልግ፤ ሕዝቡ «ለምን ጮኽክ?» መባል እንደሌለበት  በሕጻን ልጅ ለቅሶ መስለው አብራርተዋል፤
በቤተ ክህነቱም በቤተ መንግሥቱም ችግር ሁልጊዜም የመሪ እንጂ የተመሪ/የሕዝብ እንዳልሆነ ገልጸዋል፤
በተለይም የመንግሥት ሚዲያዎችን በጽኑዕ ወቅሰዋል። «የምንናገረውን በትክክል አታስተላልፉም፣ በዚህ ምክንያት ከሕዝቡ ጋር ተጋጭተናል፤ ሕዝቡ ምን አባት አለን ይላል» ብለዋል፤ «የምንናገረውን በትክክል አድርሱ» ሲሉም ገስጸዋል፤

ለአገር ነጻነት ቤተ ክርስቲያን የከፈለችውን ዋጋ አውስተዋል፤ አማናዊ ሰላም ይናፍቃታል፤ 
«የቤተ ክርስቲያን ድምጿ ሊሰማ ይገባል» ብለዋል፤ 
ለወታደሮች ባስተላለፉት መልእክት፡- የመሣሪያውን ምላጭ/ቃታ ከመሳባቸው በፊት እንዲጠነቀቁ፣ እንዲያስቡበት፣  ለአገር ዳር ድንበር ለቆሙት ሠራዊት የምትጸልየውንም («ዕቀብ ሕዝባ ወሠራዊታ ለአገሪትነ ኢትዮጵያ») ጠቅሰዋል፣

ከብፁዕነታቸው መልእክት ምን እንረዳለን፡-
አባቶቻችን የሕዝባቸው ኃዘንፀ ስደትና ሞት እንደሚያሳስባቸውና እንደሚያስጨንቃቸው፤
መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ እንደሚሹ፤
የአገሪቱ ቀውስ በመሪዎች ስሕተት የመጣ እንጂ የሕዝቡ ችግር ያመጣው አለመሆኑን፣
ወታደሩ እየወሰደ ያለውን ርምጃ መግታት እንዳለበት፤
ሚዲያዎች (በተለይም የመንግሥት ሚዲያዎች) የሚመቻቸውን ብቻ እየቆረጡ የሚያቀርቡት መረጃ አባቶችን ከሕዝባቸው ጋር እያጋጫቸው እንደሆነ ይህንንም አባቶች እንደተረዱት፤

እና እኛስ ምን እናድርግ?
ብፁዕነታቸው በተናገሩት ነገር ብዙ ሰው ደስታውን በመግለጽ ላይ ይገኛል። አብሮ መታሰብ ያለበት ነገር ግን ጭብጨባው ጋብ ሲል ቂመኛው መንግሥት ሊያደርስባቸው የሚችለውን ጉዳት ማሰብ እና ከአባቶች ጋር አብሮ ለመቆም መወሰን ያስፈልጋል። «ውረድ እንውረድ ተባባሉና አስደበደቡት አፋፍ ቆሙና» ማለት አይሠራም። የአገራችንን ችግር የሚናገር አባት ፈለግን፤ እነሆ አገኘን። ከዚያም አብረነው መቆምም አለብን። ሰውን ለአርበኝነት ጋብዞ፣ አርበኛውን ሜዳ ላይ ጥሎ መሸሽ አያስፈልግም።
ቡራኬዎ ይድረሰን ብፁዕ አባታችን፤
የትምህርቱን ሙሉ ቃል ከዚህ ላይ ማግኘት ይቻላል፡-

4 comments:

Anonymous said...

Thanks for sharing Efrem. I can see the truly spiritual mentality in the speech by Abune Abraham.

Anonymous said...

ፋሺስትን ለማሸነፍ ጸሎት ብቻ በቂ ነው ቢሉ ኖሮ ጣሊያን አቡነ ጴጥሮስን አና አቡነ ሚካኤልን ባልገደለ ነበር
አውሮፓያውያን ወራሪዎች አፍሪካን፤ሰሜን እና ደቡብ አሜሪካን ለመያዝ ሲመጡ ሚሲዮናውያንን( ወንጌል ሰባኪ ነን ባዮችን) ከፊታቸው በማስቀደም የህዝቡን ስነልቦና ለመስለብ፤ የሚደርስበት ሁሉ በሀጢአቱ ብቻ ስለሆነ፤ እርስበርሱ ያስተሳሰረን ባህሉን ልምዱን እንዲጠላ፤ዕድሉ በሰማያዊው እንጂ በዚህ ምድር እንዳልሆነ፤ ሁሉን አሜን ብሎ መቀበል እና መጸለይ ብቻ እንዳለበት በመስበክ ፍጹም ፀጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ አድርገውበታል።
እውቁ የነጻነት ታጋይ ጆሞ ኬንያታ፤ አውሮፓውያን አይናችሁን ጨፍናቹ ጸልዩ አሉን፤ ዓይናችንን ስንጨፍን መሬታችንን ወሰዱት ማለቱ፤ ላቲን አሜሪካውያን፤ የጦር መሳሪያ ካደረሰብን ጉዳት፤ መጽሐፍ ቅዱስ ያደረሰብን ጉዳት ይበልጣል ማለታቸው ይህንኑ ሊያስረዳ ይኸው በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል። አንብቦ ለመረዳት ለሚፈልግ ሁሉ።
ታዲያ ይህች ዘዴያቸው፤ አልሰራ ያለችው ኢትዮጵያ ሲመጡ ነበር። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች፤ ክርስትና ራስን፤ሀገርን፤ ዕርስትን ለመከላከል የሚደረግን ብሎም ነጻነትን የማስከበር የሚደረግን ትግል ትደግፋለች በማለት ህዝቡን አንድ አደረጉ፤ እና አርበኛውን እያበረታቱ፤ አብረው ዱር በገደል እየዞሩ ጸሎት በማድረግ፤ ሁሉም ለሀይማኖቱ ለሀገሩ እንዲቆም፤እንኳን ሰው እና ምድሪቷም ለአረመኔዎች እንዳትገዛ በማለት የጠላትን ፍጻሜ እና የሀገርን ነጻነት ትንሳኤ አፋጠኑት።
ለዚህም ነው አቡነ ጴጥሮስ አና አቡነ ሚካኤልን በሰማዕትነት ያረፉት እንጂ…እንደ ሌሎች ዓለም ወንጌላውያን ነን ባዮች ጸሎት እና ዝምታ ይበቃል ቢሉ ጣልያን እነሱንንም አይገድል፤እኝም አሁን የምንናገርበትን የነጻነት አንደበት ባልነበረን።
ታዲያ ዛሬ ዛሬ እንሰብካለን የሚሉ፤ ሳይገባቸው በአባቶች መንበር የተቀመጡ ፍርሃትን፤ዝምታን፡ ፀሎትን ብቻ በማለማመድ፤የ ጨቃኞችን ዕድሜ እና የህዝቡን መከራ ዘመን ያራዝማሉ።
ደግነቱ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መቼ ምን መደርግ እንደሚገባው የሚፈቅደው ሥርዓቷ በጽሁፍም፤ በመላው ህዝበ ክርስቲያን ልቡና ውስጥ ተቀምጧል። ለዚህ አስታዋሽ ባንፈልግም፤ ህዝቡን በወንጌል እንመራለን እያሉ ሳይገባቸው የቤተክርስቲያንን አንደበት ይዘው ዝምታን የመረጡ ሁሉ ግን ወየሁላቸው። ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዳግም ታበራለች፤ እነሱ ገን ተዋርደው ያልፋሉ።
እግዚአብሐር አምላክ ሁሉም በክብር በእኩልነት እንዲኖር እንጂ አንዱ ወገን አሳዳጅ ሌላ ደግሞ ደም እየገበረ እንዲኖር አይፈቅድም። ስለሆነም ሰዎች እግዚአብሔር በተፈጥሮ ላደላቸው ነጻነት እኩልነት የሚያደርጉትን ትግል የፈቅዳል፤ይባርካልም። ቅዱስ ዳዊትን ጨምሮ እሥራኤላውያን እግዚአብሐርን አጋዥ በማድረግ በየዘመኑ ያደረጉት ተጋድሎዎች፤ በሀገራችንም የእግዚአብሐርን ታቦት ተሸክመው አድዋ ላይ አባቶቻችን ያደረጉት ተጋድሎ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው።
ታዲያ ዛሬ ከመካከላችን ከመብቀላቸው በስተቀር ከፋሽስት የበለጠ ግፍ በመስራት በቤተክርስቲያን ላይ፤ በምዕመናኖቿ ላይ አስቃቂ ጥቃት ለሚያደርሱም ጠላቶች ዛሬም ታሪካዊው የተዋህዶ ጥሪ ያስተጋባል። በያለህበት፤ በዱር በገደል፤ ለሀይማኖትህ ለሀገርህ፤ለክብርህ የምታደርገው መዋደቅ ከቡር ነው ይላል።
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዘረኝነትን አጥብቃ ትቃወማለች። በፋሺስት ጊዜ አማራውን፤ኦሮሞውን፤ትግሬውን፤ ጉራጌውን ወላይታውን… ሁሉንም አንድ አድርጋ ሀገርን ባለድል፤እኛንም ነጻ ህዝቦች አሰኝታናለች። ዛሬም ለሚያስተውል ሁሉ ይህ ጥሪዋ ያስተጋባል።
ይህች የህዝቦችን የነጻነት ትግል የምትደግፈው ፡ፀት ለጥ ብሎ ከመገዛት ይልቅ ብረት አንስቶ ፤የሌለውም በጦር በጎራዴ ለነጻነቱ የሚሰዋውን የምታከብረው እውነተኛዋ ተዋህዶ ናት፡ ፋና ወጊነቷ ከአፍሪካ እስከ ደቡብ አሜሪካ ያስተጋባው፡ አውሮፓውያኖችን ያሸማቀቀው፡ ግብጾችን፤ሱዳኖችን ፤ሶማልያን አደብ ያስገዛው። ታዲያ ከፋሺስት የበለጠ ዘረኝነትን የሚያስፋፋ፡ ልጇን ገድሎ በሬሳው ላይ የወለደች እናቱን አስቀምጦ የሚደበድብ ፡ ጳጳሳትን ባዕታቸውን ሰብሮ የሚደበድብ፡ ምንም ያማያውቁ ህጻናትን በአልሞ ተኳሽ ደማቸውን ለሚያፈስ፡ ለጭካኔው ልክ ለሌለው ወያኔ ተዋህዶ ዝም ትበል? በፍጹም ዛሬ መንበሯን የቀበሮ ባህታውያን አባ ጵውሎስ፤አባ ማትያስ ፤ እና የዘመናችን አፈ ጮሌ ቃላት አሳማሪ ሰባኪያን መሳዮችተቆጣጥረውት ልሳን አልባ ብትመስልም የተዋህዶ ጥሪ ግን በዝምታም በትውልዱ ያስተጋባል።

I definitely agree with your concern. In fact I mentioned the exact same point yesterday to a friend before reading your article. When the situation culms dowmn, the government will definitely start to root out anybody who displayed any form of dissent. Now, the government looked extremly torelant while working behind the scenes on the list of individuals and organizations to hit hard when the time comes. Then, it will again take years before another generation of protesters to stand up. This cycle will continue for many years, by that time the generation don't even know WOLQAYIT used to be GONDERE.

Blog Archive